ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች ብቸኛ ሀገር ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አምሀራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች። 
ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።
ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የአባይ ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ያንን ካሳለፈች በኋላ ሀገሪቱዋ አዲስ መንገድ በመፈለግ ላይ ትገኛለች።
“ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ትርጉሙንና አመጣጡን ለመመርመር በ፲፱፻፹፩ (1987 እ.ኤ.አ.) በወጣው ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት ፪ኛ ዓመት፣ ቁጥር ፬ አጥር ያለ ጽሑፍ አቅርበን፣ አንዳንድ ምሁራን፤ “ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፣ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ’ ማለት ነው ...” የሚሉት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት፤ ናይጀርያ የሚባል አገርና፣ (Nigeria) ኒጀር (Niger) የሚባሉ አገርና ወንዝ በአፍሪካ እንዳሉ ጠቅሰን፣ ኔግራ፣ ኔግሮ፣ ኒገር፣ ኔግሪትዩድ (Negra, Negro, Nigger, Negritude) ለሚሏቸው ቃላት ወደ ላቲን/እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመግባት ምክንያት ሆኑ እንጂ፣ ከላቲን ቋንቋ ተወስዶ ለአፍሪካ አገሮችና ወንዝ የተሰጠ ስም አይደለም በማለት፣ ኢትዮጵያ የሚለውም ቃል እንዲሁ ጥንታዊ ምንጩ ከግሪክ ሳይሆን ከአገራችን የወጣ ቃል መሆኑን ለመግለጽ ሞክረን ነበር።
አንድ-አንድ ቃላትን ስንመረምር በውስጣቸው የተደበቅ ምስጢር እናገኛለን። የተደበቀውን ምስጠር ለማግኘት ጥልቅ የታሪክና የቃላት ምርምርና ጥናት (Philology / Etimology) ማድረግ ያስፈልጋል። በብዙ ምርምርና ጥናትም ምስጢሩ የሚገለጥበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በግዕዝ፣ በትግርኛና፣ አማርኛ ‘አነ’፣ ‘እኔ’ የሚሉ ቃላት ስናገኝ፣ በላቲን/በእንግሊዝኛ ደግሞ ‘አይ’ (I - እንግሊዝኛ)፣ ‘ኢዮ’ (Io -ጣልያንኛ) አሏቸው። በግዕዝ፣ ትግርኛና፣ አማርኛ ‘ዓይን’ ‘ዓይኒ’ ለሚሉ ቃላት ደግሞ፣ በእንግሊዝኛ አይ (eye) እናገኛለን። በአማርኛና ትግርኛ፤ ‘ያለቀለት ጉዳይ’ ለማለት ‘ሙት፣ የሞተ ነገር’፣ ስንል በእንግሊዝኛ ‘ሙት ኢሹ’ (moot issue) ይላሉ። በግዕዝና፣ ትግርኛ፣ ‘መርዓ’ ስንል፣ በእንግሊዝኛ (marriage) ‘መረጅ’ ይላሉ። ፈርኦን (Pharaoh) ከሚባል ጥንታዊ የግብፅ ንጉሥም ወደ ግዕዝ፣ ትግርኛና አማርኛ፣ እንዲሁም ወደ እንግሊዝኛ ቃላት፤ ‘ፈሪሃ’ ‘ፍርሓት’ ‘fear’ (ፊር) ለሚሏቸው ቃላት ምንጭ የሆነ ይመስላል። ንጉሡ ታላቅና የሚፈራ የነበረ ነው የሚመስል። እነዚህን ለምሳሌ አቀረብን እንጂ እንደዚህ ብዙ የቃላት መቀራረብ እናገኛለን። “ማን ከማን ወሰደ? ታሪካዊ አመጣጡና አወራረዱስ እንዴት ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው የቃላት ጥናትና ምርምር የሚያስፈልግ።
አንድ-አንድ ቃላትም ከቋንቋችን ፈልቀው ይወጡና ዓለምን ዞረው ተመልሰው ሲመጡ ብርቅ አድርገን እንቀበላቸዋለን። ለምሳሌ በኃይለሥላሴ ዘመን ያኔ ልዕልት ፀሓይ ሲባል ከነበረው ሆስፒታል ጎን አዲስ የሕንፃ ኮሌጅ ተከፍቶ፣ ‘የመሃንድስ ኮሌጅ’ በመባል ይታወቅ ነበር። መሃንድስ ማለት ምን ማለት ነው? መሃንድስ ማለት መሃናስ/መሃንዳሰ ከሚል የዓረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ ሃነፀ፣ ይሃንፅ፣ ማነፅ፣ ማሕፀን (ሕፃን የሚታነፅበት ቦታ) ... ወዘተ ከሚሉ የግዕዝ፣ የትግርኛና፣ የአማርኛም ቃላት ይዛመዳል። እንግዲያውስ ማነፅ ከሚለው ቃል መሃንዳስ ሆኖ ተጣመመና፣ ከዚያም መሃንድስ ተብሎ፣ ዞሮ ተመልሶ ብርቅ ቃል ሆኖብን ለሕንፃ ኮሌጀ መጠሪያ ሆነ። አሁንም ቢሆን ኢንጂኔር ለማለት መሃንድስ ሲባል እንሰማለን።
ሌላም ቃል ፋጡማ/ፋጢማ የሚል ስም ስንመለከት፣ ከነብዩ ሙሓመድ ሴት ልጆች ለአንዷ የተሰጠ መጠሪያ ነበረ። በዓረብኛ አባባል ግን ጠ/ጸ የሚለው ሳይሆን ተ የሚለው ፊዴል ድምፅ ነው። ይህም ማለት፣ ቃሉ “ፈቲማ” ብለው ሲሉ፣ ትርጉሙም፡ ፍጽምት፣ (Perfect) ማለት ነው። ስለዚህ ፈቲማ ማለት፣ ፈጺማ (ትግረኛ) ፈጸመች (አማርኛ) ማለት ነው።
ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ሰምና ወርቅ በተባለው የምርምር መጽሔት (1987 እ.ኤ.አ.) ያቀረብነው፣ “ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምን ማለት ነው? ኢትዮጲስ የሚባለው ንጉሥስ ለምን ይህ ስም ተሰጠው ... ብለን በጠየቅንበት ጊዜ አጥጋቢ መልስ ባለማግኘታችን ቋንቋ ለሚመረምሩ (liniguists) እንዲያተኩሩበት በዚሁ እንተወዋለን” በማለት ምርምሩን ደመደምነው።በዚህም ይህን መልስ አግኝተናል ኢትዮጲስ በመጽሐፈ አክሱም ዘንድ ኑቢያን የመሠረተው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ ነበር። በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ የሚኖሩት ኩሺቲክ ብሔሮች አባት በመሆኑ አገሩ 'ኢትዮጵያ' መባሉ እንደሚገባው ይታመናል።

===፩ኛ የታሪክ ምርምር===
በተክለ ጻድቅ መኩሪያ የተጻፈው “የኢ'

'ዮጵያ ታሪክ፣ ኑብያ፣ (ናፓታ-መርዌ)” በተባለው መጽሐፍ በገጽ19-22 የካም ወገን የሆኑ 22 ነገሥታ
ን ስምጠቅሶ፣ 55 ዓመት ከገዛው ከአክናሁስ ወይም ሳባ ፪ኛ (1985-1930 BC) ከክርስቶስ ልደት በፊት አንስቶ የ29 ነገሥታትን ስም አስቅምጦ፤ “... ራማ የተባለ የህንድ ንጉሥ ወደ ኢትዮጵያ ዘምቶ ማሸነፉንና ሕዝቡን እንደ ባርያ ...” ይገዛው እንደ ጀመረ ያትታል። ከዚያ ግን ሦስት የዮቅጣን ልጆች ተባብረው ተነስተው እሸነፉት፥ ገድለውም፣ አግዓዝያን (ነፃ አውጭዎች) ተብለው መንግሥቱን እንደ ያዙ ገልጾ፣ ከዚያ ቀጥለው የነገሡትን የ52 የኢትዮጵያ ነገሥታት ስም ይዘረዝራል። ከፊተኞቹ 29 ነገሥታትም የመጀመሪያዎቹ 10 ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው:-
The meaning of the name Ethiopia
ከዚህም ዓምድ እንደሚታየው ኢትዮጲስ ፩ኛ ከ1856-1800 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ56 ዓመት መንገሡ፣ ኢትዮጲስ ፪ኛው ደግሞ ከ1730-1700 ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ለ30 ዓመት ያህል መንገሡ በታሪክ ተጽፏል። ይህንን ያላነበቡ ምሁራኖቻችን ግን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ ቃል፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ይሉናል።
ታላቁ የግሪክ ተራኪና ባለ ቅኔ፣ ሆመር የኖረው 800 - 700 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሲሆን፣ የግሪክ ስልጣኔ ዘመን ወይም የሄሌኒስቲክ ኤጅ (Hellenistic Age) ተብሎ የሚታወቀውም ከታላቁ እስክንድር ዘመን አንስቶ፣ ማለትም 300-30 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ ያለው ጊዜ ነው። ይህ ማለት ኢትዮጲስ ፩ኛ ከባለቅኔው ከሆመር በፊት አንድ ሺሕ ዓመት ቀድሞ የነገሠ ንጉሥ ነው።
እንግዲያውስ ምሁራኖቻችን ኢትዮጵያ ማለት ከግሪክ ቋንቋ የመጣ፤ ‘ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ነው’ ሲሉን፣ ሊመልሷችው የማይችሉ ሁለት ጥያቄዎች አሉን፣
1 - የጥንት የአገራችን ነገሥታት የግሪክን ቋንቋ ከሆመር መወለድ በፊት አንድ ሺሕ ዓመት አስቀድመው እንደምን ዐወቁት? ዘመኑ አቴናውያንና ስፓርታውያን የእርስ-በርስ ጦርነት (peloponnesian war 431-404 ከክርስቶስ ልደት በፊት) አንድ ሺሕ አራት መቶ ዓመት በፊት ነው። የግሪክ ቋንቋም በአካባቢው ከነበሩ መቄዶንያ፣ ማግያር፣ አናጦልያ ... ወዘተ ከመሳሰሉት ቋንቋዎች በምኑም ተለይቶ የሚታወቅ፣ ወይም የገነነ ልሳን አልነበረም። ስለዚህ እንዴት ተብሎ ይህንን ስም የአገራችን ነገሥታት ከግሪክ ቋንቋ ወሰዱት ማለት ይቻላል?
2 - ቋንቋውን ቢያውቁና ቃሉን ከግሪክ ወሰዱት ብንልም፣ እንዴት የአገራችን ነገሥታት ራሳቸውን፤ “ፊታችን በፀሓይ ያረረ፣ የተጠበሰ፣ የተቃጠለ ነውና ራሳችንን ኢትዮጲስ፤ ‘ፊታቸው በፀሓይ ያረረ፣ የተጠበሰ፣ የተቃጠለ’ ብለን እንጥራ ...” ብለው የራሳቸውን የንግሥ ስም አወጡ? ይህ ዓይነቱ አባባል ይታመናል? ፈጽሞ የማይመስል ወሬ ነው።
ምሁራኖቻችን እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች ሲጠየቁ፣ “አፋፍ-ላፋፍ ስትሄድ አግኝቸ ሚዳቋ፣ በጅራቷ ብይዛት ዓይኗ ፍጥጥ አለ ...” እንደሚሉት ዓይናቸውን ከማፍጠጠና ከመቅበዝበዝ በቀር ሌላ የሚያድርጉት ሆነ የሚሰጡት ምንም መልስ የላቸውም።
በግሪክ ቋንቋ Αιθιοπία (አይትዮፕያ) ማለት ፊቱ በፀሓይ የተቃጠለ፣ የተጠበሰ፣ ያረረ ማለት ለመሆኑ አያጠያይቅም። ጥያቄው፤ የትኛው ቃል ከየትኛው መጣ? ነው። ግሪኮች የአገራችን ጥቁር ሰው አይተው ነው ቃሉን ወደ ቋንቋቸው ያስገቡት፣ ወይስ የአገራችን ነገሥታት ናቸው ስማቸውን ከግሪክ ቋንቋ ወስደው ለራሳቸው መጠሪያ ያደረጉት? ጥያቄው ይህ ነው!
የዚህ ዓይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ የተላበሰ አንድ የሃይማኖት መሪ፤ “... ድንቅና ተአምር የሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገርም ነገር አለ፣ ዓይናችን፣ አፍንጫችንና፣ ጆሮአችን እንዴት ብሎ ለመነጽር እንደሚገጥም ሆኖ መፈጠሩ ዕጹብ አይደለም?” እያለ ሰብኳል ይባላል። ይህ ግን የትኛው ቀዳሚ፣ የትኛው ኋለኛ መሆኑን ባለማወቁ ነው። መነጽር ነው ለዓይን፣ ለአፍንጫና ለጆሮ እንዲገጥም ሆኖ የተሠራ እንጂ፣ ፊታችን ለመነጽር እንዲገጥም ሆኖ አልተፈጠረም። ጥልቀት የሌለው ዐውቃለሁ ባይነት ግን ለእንዲህ ዓይነቱ መዘላበድ ያጋልጣል።

፪ኛ የቃላትና የፊዴላት ምርምር
‘ፐ’ ‘ጰ’ ‘ጠ’ ‘ተ’
በመጀመሪያ (Αιθιοπία) ‘አይትዮፕያ’‘ኢትዮጵያ’ የሚሉ ቃላት ለመሆኑ የአገራችን ቃላት ናቸው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ለመሆኑ ከግዕዝ፣ ከአማርኛና፣ ከትግርኛ ቋንቋዎች “ጰ” ወይም “ፐ” የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት ብንፈልግ ምን እናገኛለን?
በግዕዝፅ በትግርኛና በአማርኛ ፖሊስ ከሚል ቃል ሌላ ‘ፐ’ ፊዴል ያለበት ምን ቃል አለ? ምንም ያለ አይመስለንም። የአገራችን ሰውም ፓሊስ ከማለት ‘ቦሊስ’ ማለት ነው የሚቀናው፥ ኢትዮጵያ ከማለትም ይጦብያ ማለት ይቀልለዋል። ‘ፐ’ እና ‘ጰ’ የሚባሉ ፊዴላትም ወደ አገራችን የፊዴል ሰነድ የገቡት በቅርብ ጊዜ ከመሆኑም በላይ፥ የውጭ ቃላትን ለመጻፍ እንዲያመቹ ተብሎ መሆኑ ግልጽ ነው። በፊደላት ሰንጠረጅም ከሁሉ በታች፣ ወይም ከመጨረሻ ቦታ መስፈራቸው ኋላ የመጡ ለመሆናቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው።
Trapezium‘ጰ’ የሚል ፊዴል ያላቸውን ቃላት የአገራችን ቋንቋዎች ብንፈልግም፤ ጴጥሮስ፣ ጳውሎስ፣ ቆጵሮስ፣ ጠረጴዛ ወዘተ... እናገኛለን። ይሁንና እነዚህ ሁሉ የውጭ ቃላት፣ ከመካከለኛው ምስራቅና ከኤውሮጳ የገቡ እንጂ የአገራችን ቃላት አይደሉም። ‘ጠረጴዛ’ የሚል ቃልም ትራፔዞይድ (trapezoid: a rectangular shaped object) ከሚለው የላቲን/የእንግሊዝኛ ቋንቋ የተገኘ እንጂ በመሰረቱ የአማርኛ ቃል አይደለም። በጥንታዊ ግዕዝ ጽሑፍም ስንመለከት፤ ‘ክሊዎፓትራ፣ የፕቶሎሚ ልጅ’ ለማለት፤ “አከልኡበጥራ፣ ወለተ በጥሊሞስ” ይላታል። ይህ የሚያሳየው “ፐ” የሚባል ፊዴል በጥንታዊ የአገራችን ቋንቋዎች ፈጽሞ እንዳልነበረ ነው። ክሊዎፓትራና አባቷ ፕቶሎሚ ግን ዘራቸው ግሪክ፣ ታላቁ እስክንድር ግብፅን አሸንፎ ከዚያው በኋላ ተክሏቸው የሄደ የግሪክ ገዢዎች ስለሆኑ፣ ስማቸው የግሪክ ስም ነው። ‘ፐ’ የሚል ፊዴልም አለበት።
ይህንን የፊዴላት ጥያቄ ያመጣነው ጥንታዊው የሁለቱ ነገሥታት ስም አጠራር ‘ኢትዮጲስ’ ወይም ‘ኢትዮፒስ’ ሊሆን እንደማይችል ለማስረዳት ነው። እንግዲያውስ ከዚህ የቃላት ምርምር የምናገኘው ነገር ካለ ይኽ ነው፤ በትክክለኛው ጥንታዊ አባባል ኢትዮጲስ፣ ኢይቶጲስ፣ ኢቶፒስ፣ አይቶፒስ... የሚሉ ስሞች ፈጽሞ የአገራችን ንገሥታት ስም ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው።
ስለ ‘ጠ’ ፊዴል ካነሳን ደግሞ በግሪክ ቋንቋና በሌሎችም የኤውሮጳ ቋንቋዎች ‘ጠ’ የሚል ድምፅ የላቸውምና ‘ጠ’ የሚለውን በ ‘ተ’ እና ‘ፐ’ በሚሉ ፊዴላት ይተኳቸዋል። እንግዲያው ትክክለኛው አባባል ‘ይቶፒስ’ ሳይሆን “ይጦብስ” መሆን ይገባዋል እንላለን። ግሪኮች ‘ጠ’ ማለት ስላልቻሉ ነው (Αιθιοπία) ‘አይትዮፕያ’ ያሉት። እኛም ይኸው እስከ ዛሬ ኤውሮ‘ፓ’ ከማለት ኤውሮ‘ጳ’ እንደሚቀናን ማለት ነው።
የውጭ ታሪክ ጸሓፊዎች እነ ዮሴፍ ሃለቪ (Josph Halevi)፣ እኖ ሊትማን (Enno Litman)፣ ኤድዋርድ ግላሴር (Edward Glaser)፣ ኮንቲ ሮሲኒ (Conti Rossini)፣ ጂ. ሪክማንስ (G. Rickmans) የመሳሰሉትና ሌሎችም የውጭ አገር ሰዎች ያቀረቡት ጽሑፍ ይጦብያ ለማለት ስላልቻሉ ይቶፕያ፣ ኢቶፕያ፣ ሆኖ ወደ ቋንቋችን ሲተረጐም ‘ኢትዮጵያ’ ተብሎ ሊጸና ቻለ እንጂ ይህ ስም ትክክለኛ የአገራችን ይሁን የንጉሦቻችን ስም እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
በአገራችን ታሪክ የምናገኘው ሓቅ ደግሞ፣ “ይጦብያ”፣ “ይጦብስ” የሚል ስም ለሕዝብና ለአገር ቀርቶ ለተራ ንጉሥም የማይሰጥ እንደ ነበረ ነው። ሕዝቡ ነገደ አግዓዝያን፣ አገሩ ብሔረ አግዓዚ፣ ቋንቋው ልሳነ ግዕዝ ነበር። ነገሥታቱም በየክፍለ-ሃገሩ ስም፤ የትግራይ ንጉሥ፣ የወሎ ንጉሥ፣ የጎጃም ንጉሥ፣ የሸዋ ንጉሥ... ወዘተ፣ ይባሉ ነበር። “ይጦብያ” ተብሎ የሚታወቀው ሁሉን የጠቀለለ ንጉሠ-ነገሥቱ ብቻ ነበር። ይህም የጥንቱን የይጦብስ ንጉሥን ጠቅላይ ስም ወራሽነት መያዙ ለማሳየት ሆን ብሎ የተደረገ ብልሓት ይመስላል።
ይጦብስ ማለትስ ምን ማለት ነው? በግዕዝ በትግርኛና በአማርኛም “መጥበስ” የሚል ቃል አለ። ቃሉም ሲራባ፤ ጠበሰ፣ ተጠበሰ፣ ይጠብስ፣ ትጠብስ፣ ጥቡስ፣... ወዘተ፣ እያለ ይራባል። እንግዲያውስ ይጦብስ ማለት ጥንታዊ ትርጉሙ፤ ይጠብሳል፣ ያቃጥላል፣ ኃይለኛ ንጉሥ ነው! ተብሎ ጠላቶችን ለማስፈራሪያ የወጣ ስም ይመስላል እንጂ ከግሪክ ቋንቋ ተወስዶ ለአገራችን ነገሥታት ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ ተብሎ የተሰጠ ስም ነው ማለት አይቻልም።
ይህንን የምንለው ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪኮች የመጣ ነው ለሚሉት አጉል ምሁራን ስሕተታቸውን ለማሳየት ነው እንጂ፣ በየዘመናቱ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደ ተሰጡት አይጠረጠርም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ማለት መልካም መዓዛ ያለው ዕጣን ነው የሚሉ አሉ። የለም፣ ታላቅና ጠቅላይ ማለት ነው የሚሉም አሉ። ከዘመናት ብዛትልዩ-ልዩ ትርጉሞች እንደተሰጡት አያጠራጥርም። የሚደንቀው ነገር ግን መሃነስ/መሃንደስ የሚል ቃል ዓለምን ዞሮ ወደኛ መሃንድስ ሆኖ ሲመለስ ህንፃ የሚለውን ትርጉሙን እንዳልሳተ፣ ‘ይጦብስ’ የሚለውም ቃል እንዲሁ የቃሉ አባባል ትንሽ ተወላግዶ በግሪኮች አነጋገር ‘ይቶፒስ’ ቢባልም የመቃጠልና የመጠበስ ትርጉሙን ሳይስት እንደ ተቀመጠ ለብዙ ዘመናት የቆየ ይመስላል።
እዚህ ላይ ‘ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?’ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ምናልባት በይጦብስ ዘመን የአገራችን ተጓዦች ወይም ነጋዴዎች ከግሪክ ሰዎች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ፤
“እናንተ እነማንናችሁ?”ብለዋቸው ይሆናል።
“የይጦብስ ሰዎች ነን”፣ብለው መልሰዋል።
“ይጦብስ ማለትስ ምን ማለት ነው?” ብለው ሳይጠይቋቸው አልቀሩም።
“የሚያሳርር፣ የሚያቃጥል፣ የሚጠብስ ኃይለኛ!” ማለት ነው ብለው አስረድተዋቸዋል።
ከዚያ ወድያ ግሪኮችጠቆር ያለውን ሰው ባዩ ቁጥር (Αιθιοπίs) “ይጦብስ” እያሉ መጥራት ጀምረው፣ ቃሉም ወደ ቋንቋቸው ከመግባቱም በላይ፣ “ይጠብስ” የሚለውን ጥንታዊውን ትርጉም ሳይስት ለጥቁር አፍሪካዊ ሁሉ ‘ፊቱ የተጠበሰ፣ በፀሓይ የተቃጠለ’ (Αιθιοπία) ‘ኢትዮጵያ’ የሚል መጠሪያ ለመሆን የበቃ ነው የሚመስል።

ምርምራችን በዚህ ያበቃል።
ምንጭ፡ https://ethiopiazare.com/amharic/history/history/4204-the-meaning-of-the-name-ethiopia-by-ge-gorfu

ታሪክ
ቅድመ ታሪክ
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ ከነበረባችው ቦታዎች አንዷ መሆኗ ትታወቃለች። የሰው ፍልሰት ጥናቶች ፣ የቅሪተ አካል ጥናቶችና ሌሎች የሳይንሳዊ ዘዴዎች ይህን ያረጋግጣሉ። ድንቅነሽ የምትባለው በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው አጽም በአለም በዕድሜ ሁለተኛ ጥንታዊ ናት። ከ 3.2 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ እንደኖረች ይገመታል። ሌሎችም ታዋቂ አጽሞች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ደሴት በመሆን የቆየች ታላቅ ሀገር ናት።

የመጀመሪያዎቹ መንግስታት
በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር።
የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ።
ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ።

ከአውሮፓ ጋር የታደሰ ግንኙነት
በ ፲ ፭ኛው ምዕተ-ዓመት መጀመሪያ ኢትዮጵያ ከአክሱም ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአውሮፓ ጋር ግንኙነት ጀመረች። ከእንግሊዝ ንጉሥ ሄነሪ አራተኛ (Henry IV) ወደ የአቢሲኒያ ንጉሠ-ነገሥት የተላከ ደብዳቤ እስከ ዛሬ ድረስ አለ። በ1428 እ.ኤ.አ. አፄ ይስሐቅ ወደ የአራጎን ንጉሥ አልፎንዞ አምስተኛ (Alfonso V) ሁለት መልክተኞች ልከው ነበር። ግን የመጀመራያው ያልተቋረጠ ግንኙነት በአፄ ልብነ ድንግል ስር ከፖርቱጋል ጋር ከ1508 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ነው የተካሄደው።
ኢትዮጵያ በአህመድ ግራኝ ስትጠቃ ፣ ፖርቱጋል አራት መቶ ወታደሮችና የጦር መሳሪያ በመላክ ኢትዮጵያን ረድታለች። አፄ ሱስንዮስ በፖርቱጋልና እስፓንያ ተጽዕኖ እና ተጨማሪ እርዳታ ከመፈለጋቸው የተነሳ ወደ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ተለወጡ ፤ የኢትዮጵያ ይፋ ሀይማኖትንም አደረገቱት። ይህ ውሳኔ ወደ ግዙፍ ተቃውሞና ጦርነት አመራ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ፣ የአፄ ሱስንዮስ ልጅ አፄ ፋሲለደስ በ 1632 እ.ኤ.አ. ኢትዮጵያ ወደ አርቶዶክስ ክርስትና መመለሷን አወጁ። አውሮፓውያኖቹንም ከኢትዮጵያ አስወጡ።

ዘመነ መሳፍንት
ከ ፲፯፻፶፭ (1755) እስከ ፲፰፻፶፭ (1855) እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያ እንደገና ከአለም ጉዳዮች ተገላ ነበር። ይህ ጊዜ «ዘመነ-መሳፍንት» ይባላል ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥቶች በራስ ሚካኬል ስሁል ፣ ራስ ወልደ ሥላሴ ፣ ራስ ጉግሳ እና በመሳሰሉት ቁጥጥር ስር ነበሩ። ራስ ጉግሳ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደርን በመምራታቸው የቤተ-መንግሥቱን ቋንቋ ከአማርኛ ወደ ኦሮምኛ ለውጠው ነበር።
የኢትዮጵያ ግለልኘነት ያበቃው ከእንግሊዝ ጋር ግንኙነት ስትጀምር ነው። ኢትዮጵያ እንደገና የተዋሀደችው እንዲሁም የዘውዱ ስልጣን የተጠናከረው በ ፲፰፻፶፭ (1855) እ. ኤ. አ. በአፄ ቴዎድሮስ ምክኒያት ነው። የሰሜን አሮሞዎችና ትግሬዎች አመፅና የግብፆች ተደጋጋሚ ድንበር መጣስ የአፄ ቴዎድሮስ ስልጣን እንዲዳከም አደረጉት። በመጨረሻም ከእንግሊዝ ጋር በነበረው ጦርነት እስረኛ አልሆንም ብለው አፄ ቴዎድሮስ እራሳቸውን አጠፉ። በ ፲፰፻፷፰ (1868) እ. ኤ. አ. ኢትዮጵያና ግብፅ ጉራ በሚባለው ቦታ ተዋጉ። በአፄ ዮሐንስ አራተኛ የተመሩት የሰሜን ኢትዮጵያ ኃይሎች ድል ተቀናጁ።
በ ፲፰፻፹፱ (1889) እና በ ፲፰፻፺ (1890) ዎቹ እ.ኤ.አ. መጀመሪያ ፣ የሸዋ ንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ከዚያም ዳግማዊ አፄምኒልክ በራስ ጎበና እርዳታ አማካኝነት ሀገሯን ወደ ደቡብና ምሥራቅ ማስፋፋት ጀመሩ። ከአህመድ ግራኝ ወረራ በኋላ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ፣ ሌሎች ደግሞ በማንኛው ጊዜ በኢትዮጵይ ቁጥጥር ስር ያልነበሩ ቦታዎች በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አገዛዝ ጊዜ በኢትዮጵያ ስር ሆኑ። ከዚህ ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ድንበር ብዙ አልተለወጠም። ከ ፲፰፻፹፰ (1888) እስከ ፲፰፻፺፪ (1892) እ. ኤ. አ. ድረስ የነበረው የሰፋ ድርቅ ከኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሶስተኛ የሚገመተውን ቀጥፎአል።

የአውሮፓ ሽሚያ ለአፍሪካ
በ ፲፰፻፹ (1880) ዎቹ እ. ኤ. አ. የአውሮፓ መንግሥቶች በበርሊን ጉባኤ ተስማምተው አፍሪካን በቅኝ ገዢነት መከፋፈል ጀመሩ። በኢትዮጵያ እና ጣልያን መካከል የነበሩ የዚያ ዘመን ውዝግቦች ወደ አድዋ ጦርነት በ ፲፰፻፹፰ (1888) ዓ. ም. አመሩ። በጦርነቱ የጣልያን ትልቅ ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያ ጦር ትልቅ ሽንፈት የደረሰበት መሆኑ ዓለምን አስደነቀ።

የግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን
በ ፳ኛው ምእት ሁለተኛው ሩብ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያን ከልጅ ኢያሱ በኋላ መምራት ጀመሩ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ ሕብረት መቋቋም ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።
የኢትዮጵያ ነጻነት በጣልያን ወረራ ከ ፲፱፻፴፮ (1936) እስከ ፲፱፻፵፩ (1941) እ. ኤ. አ. ድረስ ቢጠቃም በጀግኖችዋ መከታ ተጠብቋል። በአዚህ ጥቃት ጊዜ ዓፄ ኃይለሥላሴ በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ. ኤ. አ. በሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) ፊት የሚታወስ ንግግር በአማርኛ አደረጉ። ይህ ንግግር በዓለም ታዋቂ አደረጋቸው። እንዲሁም በ ፲፱፻፴፭ (1935) እ.ኤ.አ. በ ታይም (Time) መጽሄት «የዓመቱ ሰው» አስባላቸው። ጣልያን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውስጥ መሳተፍ ስትጀምር ፣ እንግሊዝ ከኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ጋር ኢትዮጵያን ነጻ አወጣች። ግን እስከ ፲፱፻፵፫ (1943) እ. ኤ. አ. ድረስ አንዳንድ ጣልያኖች በደፈጣ ያለ ስኬት ይዋጉ ነበር። በ ፲፱፻፵፪ (1942) እ. ኤ. አ. ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባርነት እንደ ተከለከለ አወጁ።
ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ጀግና ሆነው ቢታዩም ፣ የ ፲፱፻፸፫ (1973) እ.ኤ.አ. ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፣ የምግብ ዕጥረትና የድንበር ጦርነቶች ተቃውሞ አስነሱ። ከዚያም በ ፲፱፻፸፬ (1974) እ. ኤ. አ. በሶቪየት ሕብረት የተደገፈውና በመንግስቱ ኃይለ ማርያም የተመራው ደርግ (ደርግ ማለት ኮሚቴ ማለት ነው) ዓፄ ኃይለ ሥላሴን ከስልጣን አስወረደ።

ኮምዩኒዝም
የተለያዩ መፈንቅለ መንግሥቶች ፣ የሰፋ ድርቀትና ስደተኞች የደርግ ሥርዓት ትልቅ ችግሮች ነበሩ። በ ፲፱፻፸፯ (1977) እ. ኤ. አ. ሶማሊያ ኦጋዴንን በመውረሯ የኦጋዴን ጦርነት ተነሳ። በሶቪየት ሕብረት ፣ ኩባ ፣ ደቡብ የመን ፣ ምስራቅ ጀርመንና ሰሜን ኮሪያ የመሳሪያ እርዳታ እንዲሁም ወደ ፲፭ ሺህ በሚቆጠሩ የኩባ ወታደሮች ድጋፍ አማካኝነት ደርግ ኦጋዴንን እንደገና መቆጣጠር ቻለ።
በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በቀይ ሽብር ፣ የግዴታ ስደት ፣ ወይም ረሀብ ሞተዋል። መንግስቱ ቀይ ሽብር ያካሄደው በተቀዋሚዎች በተፈጸመው ነጭ ሽብር መልስ እንደሆነ ጠቅሷል። በ ፳፻፮ (2006) እ. ኤ. አ. መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሌሉበት የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።
በ ፲፱፻፹ (1980) ዎቹ መጀመሪያ የተከሰቱ ድርቀቶች ምክኒያት ስምንት ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ ሲራብ ፣ አንድ ሚሊዮን ደግሞ ሞተዋል። ተቃውሞ በትግራይና ኤርትራ ክልሎች ተስፋፋ። በ ፲፱፻፹፱ (1989) እ. ኤ. አ. ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባርን መሠረተ። የሶቪየት ሕብረትም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ መቀነስ ጀመረች። የኢኮኖሚ ችግሮች ተከሰቱ ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ተዳከመ። 
በሜይ ፲፱፻፺፩ (1991) እ. ኤ. አ. የኢ. ህ. አ. ዴ. ግ. ጦር ወደ አዲስ አበባ አመራ። የመንግስት ኃይሎች ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ስላላገኙ ፣ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ጥቃቶች መቋቋም አልቻሉም። መንግስቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባብዌ ሄደው እስከ ዛሬ ድረስ በዛችው ሀገር ይኖራሉ። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ፹ ፯ አባላት ያሉት የሽግግር መንግሥት መሠረተ። በጁን ፲፱፻፺፪ (1992) እ. ኤ. አ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፣ እንዲሁም በማርች ፲፱፻፺፫ (1993) እ. ኤ. አ. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት የሽግግር መንግሥቱን ለቀው ወጡ። በ ፲፱፻፺፬ (1994) እ. ኤ. አ. ሁለት የሕግ አውጪ ምክር ቤቶችንና የፍትሕ ስርዓትን የሚደነግግ አዲስ ሕገ መንግሥት ተፃፈ። የመጀመሪያው ምርጫ በሜይ ፲፱፻፺፭ (1995) እ.ኤ.አ. ተካሄደ። አቶ መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በቅርብ ጊዜ
በየተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌደሬሽን ተዋህደው ነበር። በ ፲፱፻፺፫ (1993) እ.ኤ.አ. በተካሄደውና የተባበሩት መንግሥታት በታዘበው ሕዝበ ድምፅ ፣ 
በወቅቱ ስልጣንን በጠመንጃ አፈሙዝ የያዙትና የኤርትራን መገንጠል በሚፈልጉት በህውአትና ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አማካይነት ለኤርትራ ህዝብ ‹ባርነት› ወይንስ ‹ነፃነት› ተብሎ እንዲመርጡ ተገደው ማንም ባርነትን የሚመርጥ የለምና ነፃነትን መረጡ ተባሎ  በረሃ ገብተው ሲታገሉለት የነበረውን አላማ ስልጣናቸውን በመጠቀም አስፈፅመው ከ ፺፱ ከመቶ በላይ የሚሆነው የኤርትራ ሕዝብና በውጭ ሀገር የነበሩ ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ መገንጠልን መርጠዋል። በሜይ ፳፬ ፣ ፲፱፻፺፫ (1993) እ. ኤ. አ. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች።
በሜይ ፲፱፻፺፰ (1998) እ. ኤ. አ. የድንበር ውዝግብ እስከ ጁን ፳፻ (2000) እ. ኤ. አ. ወደ ቀጠለው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አምርቶአል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን ጎድቶአል። በሜይ ፲፭ ፣  ፳፻፭ (2005) እ.ኤ.አ. አጠቃላይ ምርጫ ቢካሄድም ተቃዋሚዎች ማጭበርበር እንደነበረ ወንጅለዋል። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከ ፪፻ (200) በላይ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ግን አንዳንድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባሎች ከምርጫው በኋላ ከነበረው ረብሻ ጋር በተያያዘ ታስረው ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያለው የፖለቲካ ስርአት በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራላዊ ስርአት ነው፡፡

መልክዓ-ምድር
ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ከ 3-14 ዲግሪ ሰሜን እና ከ 33-48 ዲግሪ ምሥራቅ የምትገኝ አገር ስትሆን የቆዳ ስፋቱዋም 1,127,127 ካሬ ኪ.ሜ. ነው። በሰሜን ከኤርትራ ፣ በምዕራብ ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ፣ በደቡብ ከኬኒያ ፣ እንዲሁም በምሥራቅ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ ጋር ትዋሰናለች። የኢትዮጵያ አብዛኛው ግዛት በተራሮች እና አንባዎች የተሞላ ሲሆን ፣ ታላቁ የምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ እነዚህኑ ከፍተኛ ቦታዎች ከሰሜን ምሥራቅ ወደ ደቡብ ምዕራብ በመጋደም ለሁለት ይከፍላቸዋል። በስምጥ ሸለቆው ዙሪያም በረሃማ የሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛሉ። ይሄን መሰሉ የመልክዓ-ምድር ልዩነት አገሪቷ የተለያዩ የአየር ንብረት ፣ የአፈር ፣ የዕፅዋት እና የሕዝብ አሰፋፈር ገጽታዎች እንዲኖሯት አስችሏታል። በከፍታና በመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዓይነት የአየር-፡ ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም፦

ደጋ – ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግሪ ሴ. ግ. የማይበልጥ
ወይናደጋ – ከፍታቸው ከባሐር ጠለል ከ 1500 እስከ 2400 ሜትር ፣ ሙቀታቸውም ከ 16 ዲግሪ ሴ. ግ. እስከ 30 ዲግሪ ሴ. ግ. የሚደርስ ፣ እና
ቆላ – ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው ፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ 30 ዲግሪ ሴ. ግ. እስከ 50 ዲግሪ ሴ. ግ. የሚደርስ አካባቢዎች ናቸው።
ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን ፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

አስተዳደራዊ ክልሎችውጤት
ከ ፲፱፻፺፮ (1996) እ.ኤ.አ. በፊት ኢትዮጵያ በ ፲፬ ክልሎች ተከፍላ ነበር። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጽያ ውስጥ ፱ አስተዳደራዊ ክልሎች ይገኛሉ። አወቃቀራቸውም በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት «በህዝብ አሰፋፈር ፤ ቋንቋ ማንነት እና ፈቃድ ላይ» ተመስርቶ ሲሆን ክልሎቹም፦

የትግራይ ክልል
የአፋር ክልል
የአማራ ክልል
የኦሮሚያ ክልል
የሶማሌ ክልል
የቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል
የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
የሐረሪ ሕዝብ ክልል
የሲዳማ ሕዝቦች ክልል
ሲሆኑ በተጨማሪም

አዲስ አበባ እና
ድሬዳዋ እራሳቸውን የቻሉ የአስተዳደር አካባቢዎች ሆነው ተዋቅረዋል።
ዋና ሰሪ ምዕራፍ ሰሎሞን

ሕዝብ
የኢትዮጵያ ሕዘብ ቁጥር ከ ፼፼ (100000000) በላይ ሲሆን እንዲሁም ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ።
በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣  እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ።

ቋንቋዎች
ዋና መጣጥፍ፦ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች

በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ።
ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ ፣ቀቤንኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው። እንደ ወላይትኛ ፣ [[ጋሞኛ]፣
ጎፍኛ ፣ ከፋኛ ፣ ሃመርኛ የመሳሰሉት የኦሞአዊ ቋንቋ ዘሮች ሲሆኑ አማርኛ ፣ ትግርኛ ፣ ጉራጊኛ ፣ ስልጢኛ ፣ ሀደሪኛ፣ አርጎብኛ፣
ጎፍኛ እና መሰል ቋንቋዎች ከሴማዊ ቋንቋዎች ይመደባሉ። ዘጋቢ በአወል ሙሀመድ ደራ

ፊደል
የሴሚቲክ ምንጭ ያላቸው እንደ ትግርኛና አማርኛ ያሉት ቋንቋዎች የራሱ የሆነ የተለየ የፊደል ስርአት ያላቸው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን ከአፍሪቃ ብቸኛዋ ባለ ጥንት ፊደል ሀገር ያደርጋታል። እነኚህ የሴሚቲክ ምንጭ ያላችው ቋንቋዎች ግዕዝ የተባለ በአሁኑ ወቅት ከቤተክርስትያን ውጭ ለዕለት ተዕለት ግልጋሎት ላይ የማይውል ግንድ ዘር አላቸው።
በኣሁኑ ጊዜ ግዕዝ በዩኒኮድ ዕውቅና ያገኙትን የቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ሙርሲ፣ ሱሪ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኣውንጂ፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ዲዚ፣ ዳውሮ፣ ጉሙዝ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ጎፋ እና ግዕዝ ቋንቋዎች የሚጋሯቸውን ቀለሞችና ሌሎች ያጠቃልላል። በፊደሉ ከሚጠቀሙ ቋንቋዎች መካከል ሓረሪ ኣንዱ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ ሙሉዉን ወይም በከፊል ከ፲፭፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ በግዕዝ ቀለሞች በማተሚያ ቤቶች ከታተሙባቸው ቋንቋዎች መካከል ሃዲያ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ይገኙበታል። (ደግሞ ኣበራ ሞላ ይዩ።)
በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይቀርብ የነበረው የግዕዝ ፊደል በ፲፱፻፹ ገደማ ኮምፕዩተራይዝድ ስለሆነ ኣጠቃቀሙ ወደ ኮምፕዩተር ዞሯል። ከእዚያም ወዲህ ፊደሉ የዩኒኮድ የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ ስለገባ እያንዳንዱ ቀለም የእራሱ ስፍራ ኣለው። (en:Ethiopic_(Unicode_block)) ይህ የኣማርኛ ውክፔድያ ድረገጽም የቀረበው በእዚሁ ፊደል ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ፊደሉን በእጅ ስልክ መጠቀም ተችሏል። ለፊደሉ ኣጠቃቀም ኣስፈላጊ ሆነው የተፈጠሩ ኣዳዲስ የቴክኖሎጂ ዘዴዎችም የዩናይትድ እስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ ወይንም ፓተንት ማግኘት ጀምረዋል። [1] [2]

ሰብአዊ መብቶች
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ አሁንም ሕገ ወጥ ነው።

ባህል እና ሃይማኖት
ዋና መጣጥፍ፦ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር

የውጭ መያያዣዎች
[3] Ethiopic Character Entry
[4] Phonetic Keyboards
አዲስ አበባ (Addis Abeba) ፤ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት ። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት የፌደራል ከተማነትን ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በ1999 አ.ም በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ወደ 2,739,551 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ናት።
ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍልውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን ወደ አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል።
ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ነች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።

ታሪክ
ቅድመ ታሪክ
በዓለም ዙሪያ ካሉ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎች በዘረመል መረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናት የሰው ዘር ከአዲስ አበባ ቅርብ ከሆነ ቦታ ከ100,000 ዓመታት በፊት እንደተበተነ ያመለክታል።

መካከለኛው ዘመን
የመካከለኛው ዘመን ነገሥታት መዲና የነበረው በራራ ተብሎ ለሚጠራው ቦታ ከቀረቡት ጥቂት ቦታዎች መካከል ከአሁኑ አዲስ አበባ በስተሰሜን የሚገኘው እንጦጦ ተራራ ላይ ያለ ከፍ ያለ ጠፍጣፋ መሬት ነው። ይህ ቦታ እስከ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዐጼ ልብነ ድንግል አገዛዝ ድረስ የበርካታ ነገስታት ዋና መኖሪያ ሆኖ አገልግሏል።  
በ1442 ዓ.ም አካባቢ ጣሊያናዊው የካርታ ባለሙያ ፍራ ማውሮ ባሳለው ካርታ ላይ ከተማዋን በዝቋላ ተራራ እና በመንጋሻ መካከል አስቀምጧታል። ሆኖም ግን የመናዊው ጸሃፊ አረብ-ፋቂህ እንደዘገበው በ1521 ዓ.ም የንጉሠ ነገሥቱ ጦር ከአዋሽ ወንዝ በስተደቡብ ተይዞ ሳለ  በግራኝ አህመድ ተመትታለች። በራራ የሚገኘው በእንጦጦ ተራራ ላይ ነው የሚለው ሀሳብ የሚደግፈው በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የተመሰረተውና በዓለት በተፈለፈለው ዋሻ ሚካኤል እና በእንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስቲያን መካከል የሚገኝ ትልቅ የመካከለኛው ዘመን ከተማ በመገኘቱ ነው። በ30 ሄክታር ቦታ ለ ያረፈው ይህ ጥንታዊ ከተማ ከ 520 ሜትር የድንጋይ ግንብ እስከ 5 ሜትር ቁመት ያላቸው 12 ማማዎች ያሉት ቤተመንግስት ያካትታል።

ምስረታ
ከከተማዋ በፊት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነበረችው እንጦጦ የተመሰረተችው በዳግማዊ ዐጼ ምኒልክ  በ1871 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ንጉስ የነበሩት ምኒልክ የእንጦጦ ተራራን በደቡብ ወታደራዊ ዘመቻቸው ጠቃሚ መሰረት አድርገው አገኙት። በስፍራው የነበረውንም ፍርስራሽ እና ያልተጠናቀቀ የመካከለኛው ዘመን ውቅር ቤተክርስቲያን ጎበኙ። ሚስታቸው እቴጌ ጣይቱ ቤተክርስቲያን በእንጦጦ ላይ መስራት በጀመሩበት ወቅት፣ የምኒሊክ ዝንባሌ ወደእዚህ ስፍራ በተለይ ተሳበ፤ ሁለተኛም ቤተክርስቲያን ባቅራቢያው ሠሩ። ነገር ግን ማገዶም ሆነ ውኃ በማጣት ምክንያት አካባቢው መንደር ለመመሥረት አይመችም ነበር፤ ስለዚህ ሰፈራው የጀመረበት ከተራራው ትንሽ ወደ ደቡብ በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በ1878 ነበረ። 

እቴጌ ጣይቱ እርሳቸውና የሸዋ ቤተመንግስት ወገን መታጠብ ይወዱ የነበረበት ፍልወሃ ምንጭ አጠገብ ለራሳቸው ቤት ሠሩ።  አዲስ አበባ (ወይም ባጭሩ «አዲስ») ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልወሃ ምንጭ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። ከእዚያ በኋላ ሌሎች መኳንንቶች ከነቤተሰቦቻቸው አቅራቢያውን ሠፈሩ፤ ምኒልክም የሚስታቸውን ቤት ቤተመንግሥት እንዲሆን አስፋፉትና እስከ ዛሬ ድረስ ቤተ መንግሥት ሆኖ ቆይቷል። ምኒልክ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት በሆነበት ወቅት በ1881 ዓ.ም  አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆነች። ከእዚያ ጀምሮ  ከተማዋ ለመኳንንቶች ብቻ ሳይሆን የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ነጋዴዎችን እና የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን ጨምሮ በርካታ የስራ ክፍሎችን በመሳብ አደገች። 
ቀደምት የመኖሪያ ቤቶች ጎጆዎች ነበሩ። የአዲስ አበባ ዕድገት የጀመረው ያለቅድመ ዕቅድ በተከሰተ ፈጣን የከተማ መስፋፋት  ነው። ከአፄ ምኒልክ አስተዋፅዖዎች አንዱ ዛሬም በከተማው ጎዳናዎች የሚታዩት በርካታ የባሕር ዛፎች ተከላ ነው። እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት ገለጻ የከተማዋ የተፋጠነ የህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት በጊዜያዊ ገዥዎች እና በወታደሮቻቸው፣ በ1892 ረሃብ እና የአድዋ ጦርነት ምክንያት ነው። ሌላው የ1899 የመሬት ህግ፣ በ1901 የማዘጋጃ ቤት አስተዳደር  እና  ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረው የባቡር እና የዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት እድገት ነው።

20ኛው ክፍለ ዘመን
ቅድመ-ጣሊያን ወረራ (1908-1927)
በ1908 አቶ ገብረህይወት ባይከዳኝ  የዋና ዋና የአስተዳደር ክፍሎችና የኢትዮ– ጅቡቲ የባቡር መስመር አስተዳዳሪ ሆኑ። በ1909 ራስ ተፈሪ መኮንን፣ (በኋላም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ከተሾሙ በኋላ በከተማዋ ከፍተኛ ሰው ነበሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ራስ ተፈሪ በ1910 እንደ እንደራሴ ህጋዊ ስልጣን አግኝተዋል። የዘመናዊነትንና ከተሜነትን አስፈላጊነት በመገንዘብም ከተማዋን ወደ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ያበረከቱ ሲሆን  ሀብት ክፍፍልም አድርገዋል። በ1918 እና 1919 መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ አብዮት ተፈጠረ ፣ በካፒታል ክምችት ምክንያት የተትረፈረፈ የቡና ምርት ማደግ ጀመረ ።መካከለኛው የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ ሃብት በማትረፍ  ከውጪ የሚገቡ የአውሮፓ የቤት እቃዎች እና አዳዲስ አውቶሞቢሎችን በማስመጣት፤ ባንኮችን በማስፋፋትና አዳዲስና በድንጋይ የተገነቡ ቤቶችን በመስራት ከተማዋን ተጠቃሚ አድርገዋል። በ1918 የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ መዝገብ 76 ሲሆን በ1922 ወደ 578 ደርሷል። የመጀመሪያው የመንገድ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ እና በጅቡቲ መካከል  በደሴ አቅጣጫ የተከፈተው አውራ ጎዳና ነው። አውራ ጎዳናው ለጅቡቲው የፈረንሳይ የባቡር መስመር ጠቃሚ ነበር። በ 1922 ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ ጭነው  አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ቀጥለዋል ። ከእነዚህም መካከል የኤሌክትሪክ መስመሮችንና ስልክ እንዲሁም እንደ ሚያዚያ 27 አደባባይ ያሉ በርካታ ሐውልቶችን ይካተታሉ።

በጣሊያን ወረራ ጊዜ (1928-1933)
በ1928 ዓ.ም. በጦርነት ጊዜ የፋሺስቶች ሠራዊት ከተማዋን ወርረው ዋና ከተማቸው አደረጉዋት፤ እስከ 1931 ድረስ የኢጣልያ ምስራቅ አፍሪቃ አገረ ገዥ ነበረባት።ከተማዋ ከወረራ በኋላ እስከ 1933 ድረስ የጣሊያን ምስራቅ አፍሪካ ዋና ከተማ ሆና ነበረች። በ1933 ከተማይቱ በሜጀር ጄነራል ዊንጌት እና በአፄ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ጌዲዮን ሃይል እና የኢትዮጵያ ንቅናቄ ነፃ ወጣች። አፄ ኃይለ ሥላሴም ከሄዱ ከአምስት ዓመታት በኋላ ግንቦት 5 ቀን 1941 ዓ.ም. ተመለሱ።

የድህረ-ጣሊያን ወረራ (1933-1966)
በ1938 አጼ ኃይለ ሥላሴ ከተማዋን የአፍሪካ ዋና ከተማ እንድትሆን ንድፍና እና የማስዋብ ግቦችን ለማሰራት ታዋቂውን እንግሊዛዊ ማስተር ፕላን ሰሪ ፓትሪክ አበርክሮምቢን ጋበዙ። ማስተር ፕላኑ በ1935 ከነበረው የለንደን የትራፊክ ችግር ተሞክሮ በመውሰድ የዋና ዋና የትራፊክ መስመርና የሰፈር ክፍሎችን ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ በመለየት ተጠናቀቀ።
ኃይለ ሥላሴ በ1963 በኋላም በ1994 ፈርሶ በአፍሪካ ኅብረት የተተካውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰርትም ረድተው ነበር፣ ዋና መሥሪያ ቤቱም በከተማዋ ነው።  የተባበሩት መንግሥታት ምጣኔ ሀብት ጉባኤ ለአፍሪቃ ደግሞ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ባዲስ አበባ አለው። በ1957 ዓ.ም. አዲስ አበባ ለኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ስብሰባ ሥፍራው ነበረች። 
እ.ኤ.አ. በ1957 የተማሪዎች ሰልፍ “መሬት ላራሹ” በሚል መፈክር በማሰማት በኢትዮጵያ የማርክሲስት ሌኒኒስት እንቅስቃሴ ተካሂዷል። በተጨማሪም በ1955 የተከሰተው የነዳጅ ቀውስ በከተማይቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። በ1966 ዓ.ም ሃይለስላሴ ከስልጣናቸው በፖሊስ አባላት ወረዱ። በኋላም ቡድኑ በይፋ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ምክር ቤት” በማለት ራሱን ደርግ ብሎ ሰየመ። በወቅቱ ከተማዋ 10 ወረዳዎች ብቻ ነበሩት።

የደርግ አስተዳደር (1966-1983)
ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ በግምት ሁለት ሶስተኛው ቤቶች ወደ ኪራይ ቤት ተዛወሩ። የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከ6.5% ወደ 3.7% ቀነሰ። በ1975 ደርግ በግል ባለ አክሲዮኖች የተገነቡ “ተጨማሪ” የኪራይ ቤቶችን የአገር ንብረት አደረገ። በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 47/1975 የተዳከሙ ቤቶች(ከጭቃ የተገነቡ)  በቀበሌ ቤቶች ይተዳደራሉ፣ ጥራት ያላቸው የኪራይ ቤቶች ደግሞ በኪራይ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ (ARHA) ስር ይሆናሉ። እነዚያ የኪራይ ቤቶች ዋጋ ከ100 ብር (48.31 የአሜሪካ ዶላር) በታች ከሆነ በቀበሌ አስተዳደር ሥር ይሆናል። ይህን ተከትሎ የአስተዳደር ክፍፍሉ ወረዳዎች ወደ 25 እና 284 ቀበሌዎች አድጓል።
በደርግ ጊዜ የሃንጋሪው አርክቴክት ፖሎኒ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እገዛ የከተማውን ማስተር ፕላን የጀመረው የመጀመሪያው ሰው ነው ፖሎኒ በጊዜው አብዮት አደባባይ ተብሎ የተጠራውን የመስቀል አደባባይን በአዲስ መልክ በመንደፍ ሠርቷል።

ኢ.ፌ.ዲ.ሪ (1983-አሁን)
ደርግን ለመጣል እየታገለ የነበረው ጥምር ፓርቲ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ግንቦት 20 ቀን 1983  አዲስ አበባን ተቆጣጠረ። ተዋጊዎች 4ኪሎ ቤተመንግስት ታንክና ከባድ መሳርያ ታጥቀው ገቡ። ከአንድ ዓመት በኋላ አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት ወጣ። ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልል አስተዳደር ሲሆን፣ አዲስ አበባ (አዋጅ ቁጥር 87/1997) እና ድሬዳዋ (አዋጅ ቁጥር 416/2004) እራስን በራስ የማስተዳደር እና የልማታዊ ማዕከልነት ስልጣን ያላቸው ቻርተርድ ከተሞች ሆኑ።
በሚያዝያ 25/2007 ዓ.ም የአዲስ አበባን ድንበሮች በ1.1 ሚሊዮን ሄክታር ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተዘጋጀው አወዛጋቢ ማስተር ፕላን፣ የ2007ቱን የኦሮሞ ተቃውሞ አስነስቷል። መንግስት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በመተኮስና በድብደባ የሰጠው ምላሽ ወደ ለየለት አድማና ተቃውሞ አባባሰው። አወዛጋቢው ማስተር ፕላን በጥር 12 ቀን 2008 ተሰርዟል።በዚያን ጊዜ 140 ተቃዋሚዎች ተገድለዋል።
በአብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ጊዜ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ "ሸገርን ማስዋብ" የተሰኘ ስራ ተካሂዷል። ይህ ፕሮጀክት የከተማዋን አረንጓዴ ሽፋንና ውበት ለማሳደግ ያለመ ነው። 2010 ዶ/ር አብይ ከእንጦጦ ተራሮች እስከ አቃቂ ወንዝ ድረስ 56 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻዎችን ለማስፋፋት ያቀደውን "የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት" የተሰኘ ፕሮጀክት አስጀመሩ።

ሰፈሮች
የአዲስ አበባ ከተማ ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በተለያዩ ምክንያቶችና አጋጣሚዎች ነው። እነዚህንም በተለያዩ ዘርፎች ከፍሎ በቅደም ተከተል ማየት ይቻላል።
በርካታዎቹ የከተማዋ ቀደምት ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በቤተ-መንግሥቱ ዙሪያ መሬት በጉልት መልክ በተሠጣቸው መሣፍንቶችና መኳንንቶች ስም ነው። በዚህ መልክ ስያሜያቸውን ካገኙት ሠፈሮች መካከል ራስ መኮንን ሠፈር፣ ራስ ተሰማ ሠፈር፣ ራስ ብሩ ሠፈር፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሠፈር፣ ራስ ስዩም ሠፈር፣ ደጃዝማች ውቤ ሠፈር፣ ነጋድራስ ኃይለ ጊዮርጊስ ሠፈር ፣ ደጃዝማች ዘውዱ አባኮራን ሠፈር እና ሸጎሌ (የአሶሣ ገዢ በነበሩት በሼክ ሆጀሌ አል ሐሠን የተሠየመው) ሠፈር ይጠቀሳሉ።
ከእነዚህ ሠፈሮች መካከል ደጃዝማች ውቤ ሠፈር በተለይ ከጣሊያን ወረራ በፊት በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኙባቸው የከተማዋ ሠፈሮች አንዱ እንደነበረ ይነገራል። በዚህም ሳቢያ በስነ ቃል በርካታ ግጥሞች በዚህ ሠፈር ዙሪያ ተገጥመዋል። ከነዚህም መካከል፣

«ደጃች ውቤ ሠፈር ምን ሠፈር ሆነች፣
ያችም ልጅ አገባች ያችም ልጅ ታጨች።
ደጃች ውቤ ሠፈር ሲጣሉ እወዳለሁ፣
ገላጋይ መስዬ እገሊትን አያለሁ።

ደጃች ውቤ ሠፈር የሚሠራው ሥራ፣ጠይሟን በጥፊ ቀይዋን በከዘራ»
የሚሉት ይገኙበታል።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመላው የአገሪቱ ማዕዘናት መጥተው አዲስ አበባ በሠፈሩ ብሔረሰቦች የተመሠረቱ ሠፈሮች ይጠቀሳሉ። በዚህ መልክ ከተመሠረቱት ሠፈሮች መካከል ለአብነት አደሬ ሠፈር፣ ጎፋ ሠፈር፣ ወሎ ሠፈር፣ ወርጂ ሠፈር፣ መንዜ ሠፈርና ሱማሌ ተራ ይገኙበታል። የወርጂ ሠፈርን የመሠረቱት የወርጂ ብሔረሰብ አባላት በቆዳና በበርኖስ ንግድ የተሠማሩ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። በተመሣሣይ መልኩ የሱማሌ ተራ ነዋሪዎች ዋነኛ መተዳደሪያ የሻይ ቤት ሥራ እንደነበር ይታመናል።
በሶስተኛ ደረጃ በተለያዩ ሙያዎች ተሠማርተው በተለይም በቤተ መንግሥቱ የተለያዩ የሥራ ድርሻዎች በነበራቸው ባለሙያዎች የተቆረቆሩ ሠፈሮችን እናገኛለን። እነዚህም ከብዙ በጥቂቱ ሠራተኛ ሠፈር፣ ዘበኛ ሠፈር፣ ሥጋ ቤት ሠፈር፣ ኩባንያ ሠፈር፣ ጠመንጃ ያዥ ሠፈር፣ ካህን ሠፈር (በኋላ ገዳም ሠፈር) ፣ ገባር ሠፈር ፣ ሠረገላ ሳቢ ሠፈርና ውሃ ስንቁ ሠፈርን ያካትታሉ። ሠራተኛ ሠፈር በአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግሥት በዕደ ጥበባት ሙያ በተሠማሩ ነዋሪዎች የተመሠረተ ሠፈር ነው። የሠፈሩ መሥራቾች ዋነኛ ሙያ የብረታ ብረት ሥራ እንደነበረ ይነገራል። ይሄም የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን ለምሣሌ ማረሻ፣ የፈረስ እርካብን፣ የቤት እቃዎችን፣ የጋሻና ጦር እና የጠመንጃ ዕድሳትን ይጨምራል። በቤተ መንግሥቱ በአናጢነት የተሠማሩ ባለሙያዎችም የሚኖሩት በሠራተኛ ሠፈር እንደነበር ይነገራል።
በከተማዋ ከሚኖሩት የውጭ ተወላጆችም መካከል ጥቂቶቹ የሚኖሩት በዚሁ ሠፈር ነበር። ከነዚህም የውጭ ነዋሪዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አርመናዊው የግብረ ህንፃ ባለሙያ ሙሴ ሚናስ ሔርቤጊን ነበሩ። ዘበኛ ሠፈር የቤተ-መንግሥቱ ጠባቂዎች ወይም የዕልፍኝ ዘበኞች የሠፈሩበት ሠፈር ሲሆን፣ ገባር ሠፈር ደግሞ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍላተ ሀገር እንደ ማር፣ እህልና ከብት በመሣሠሉት ምርቶች ዓመታዊ ግብር ለመክፈል ወደ ከተማዋ በሚመጡ ግለሰቦች የተመሠረተ ሠፈር እንደሆነ ይነገራል። የውሃ ስንቁ ሠፈር መስራቾች ደግሞ መደበኛ ክፍያ የሌላቸው እና ስንቃቸው ውሃ ብቻ የሆነ የጦሩ አባላት የሠፈሩበት ሠፈር እንደነበረ ይነገራል።
በሌላ በኩል ጥቂት የማይባሉ የአዲስ አበባ ሠፈሮች ስያሜያቸውን ያገኙት በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ ክስተቶችና ታሪካዊ ክንዋኔዎች ነው። ሠባራ ባቡር ፣ እሪ በከንቱ ፣ ዶሮ ማነቂያ ፣ አፍንጮ በር ፣አራት ኪሎ ፣ ስድስት ኪሎ ፣ አምስት ኪሎ ፣ ጣሊያን ሠፈር፣ ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ ሽሮ ሜዳ እና ነፋስ ስልክ ተብለው የሚጠሩትን ሠፈሮች በዚሁ ዘርፍ መፈረጅ ይቻላል። ሰባራ ባቡር ሠፈር ስያሜውን ያገኘው ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን በሚባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ አገር መጥቶ አሁን ስያሜውን ባገኘበት ቦታ ተበላሽቶ በቀረው የመንገድ መሥሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ሠፈሩ ሰባራ ባቡር እንደተባለ ይነገራል። አገሬው “የሠርኪስ ባቡር” እያለ የሚጠራው መሣሪያ አዲስ አበባ በደረሰ ጊዜ የሚከተለው ግጥም ተገጥሞለት ነበር።

«ባቡሩ ሰገረ ስልኩም ተናገረ፣ምኒልክ መልአክ ነው ልቤ ጠረጠረ።»
በሌላ በኩል ከዐድዋ ጦርነት በኋላ በድል አድራጊው የኢትዮጵያ ሠራዊት የጦር ምርኮኞች የሆኑት የጣሊያን ተወላጆች በማረፊያነት የተመረጠው ቦታ ጣሊያን ሠፈር የሚለውን ስያሜ ማግኘቱ ይታወቃል። እንደዚሁም የስድስት ኪሎ ሠፈር ፣ አራት መንገዶች መገናኛ የሆነው አካባቢ አራት ኪሎ ሠፈር በሁለቱ ሠፈሮች መካከል ያለው አካባቢ ቆይቶ አምስት ኪሎ ሠፈር የሚለውን ስያሜ ማግኘቱም የሚታወቅ ነው።

ሌላው በከተማው ከሚገኙ ዋና ዋና ሠፈሮች መካከል በከተማዋ ቀደምት ነዋሪዎች በሆኑት የኦሮሞ ተወላጆችና የቦታ ስሞች የተሰየሙ ሠፈሮችን እናገኛለን። ከነዚህም መካከል ጉለሌ ፣ ጎርዶሜ ፣ ቀበና ፣ ኮተቤ ፣የካ ፣ እንዲሁም ገርጂ እና ላፍቶ የተባሉት ሠፈሮች ለአብነት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህም ሠፈሮች መካከል በቀበና ወንዝ ስም በተሰየመው ቀበና ሠፈር ከተገጠሙት ግጥሞች አንዱን እንመልከት።

«ቀበና ለዋለ አራዳ ብርቁ ነው፣

አራዳም ለዋለ ቀበና ብርቁ ነው፣እሱስ ላገናኘው ሴት ወይዘሮም ደግ ነው።»
በሌላ ዘርፍ ከ1928 የጣሊያን ወረራ እና የአምስት ዓመት ቆይታ ጊዜ አንዳንድ የአዲስ አበባ ቦታዎች እና ሠፈሮች የጣሊያንኛ ስያሜ አግኝተዋል። ከእነዚህም መካከል መርካቶ (የአገሬው ገበያ) ፣ ፒያሣ (የቀድሞው አራዳ) ፣ ካዛንቺስ፣ ካዛ ፖፖላሬ እና ካምቦሎጆ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ካዛንቺስ ስያሜውን ያገኘው አዲስ አበባ በጣሊያን ይዞታ ስር በነበረችበት ጊዜ ለከፍተኛ የጣሊያን ሹማምንት መኖሪያ ቤቶች በሠራው የጣሊያን ኩባንያ ምህፃረ ቃል ሲሆን ካዛ ፖፖላሬ ደግሞ በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ ጣሊያናዊያን ቤቶች በሠራው በካዛ ፖፖላሬ ኩባንያ ስም ነው ስያሜውን ያገኘው። በሌላ በኩል ካምቦሎጆ ሠፈር መጠሪያውን ያገኘው ካምፖ አሎጅዬ ኦፔራ (Campo Allogio Opera) ከሚለው ስም ሲሆን ይሄም ማለት የሠራተኞች ካምፕ ማለት ነው።

እንዲሁም በከተማዋ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያን እና አጥቢያዎች የተሰየሙ ሠፈሮች ሌላው ዋነኛ ዘርፍ ነው። በዚህ ዘርፍ ከሚገኙ ሠፈሮች መካከል ተቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዘው አራዳ ጊዮርጊስ ሠፈር ነው። አራዳ በተለይም ከጣሊያን ወረራ ቀደም ባለው ጊዜ የአዲስ አበባ የኢኮኖሚ ማዕከል ከመሆኑ አኳያና በርካታ ማሕበራዊ ክንዋኔዎችን ያስተናግድ የነበረ ሠፈር እንደመሆኑ በስነቃል ብዙ ተብሎለታል። ለአብነት

«ሱሪ ያለቀበት አይገዛም አዲስ፣
ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ጊዮርጊስ።
እስኪ አራዳ ልውጣ ብርቱካን ባገኝ፣
ትናንት ኮሶ ጠጣሁ ዛሬ መረረኝ።
ምነው በአደረገኝ ከአራዳ ልጅ መሣ፣
እንኳን ለገንዘቡ ለነፍሱ የማይሣሣ።

የአራዳ ዘበኛ ክብሬ ነው ሞገሴ፣በቸገረኝ ጊዜ የሚደርስ ለነፍሴ» የሚሉት ይገኙባቸዋል።
በዚህ ዘርፍ የሚመደቡ ሌሎች ሠፈሮች ደግሞ አማኑኤል ፣ ዮሴፍ ፣ ኪዳነ ምሕረት ፣ ቀራኒዮ መድኃኔ ዓለም ፣ እና ቀጨኔ መድኃኔ ዓለምን ያካትታሉ። እ.ኤ.አ. ከ 1888 ዓ.ም. የዐድዋ ጦርነት ድል እና ከአዲስ አበባው ስምምነት በኋላ ጣሊያን፣ ሌሎች የአውሮፓ መንግሥታት እና አሜሪካ የአገራችንን ሉዓላዊነት በመቀበል ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሥርተዋል። በዚህ ሂደት በርካታ አገሮች የነዚህን አገሮች ፈለግ በመከተል ኤምባሲዎቻቸውን በአዲስ አበባ ከፍተዋል። ከአዲስ አበባ በርካታ ሠፈሮች መካከል አንዳንዶቹ ስያሜያቸውን ያገኙት ከእነዚህ ኤምባሲዎችና ቀደም ሲል ደግሞ ከሌጋሲዮኖች ነው። ፈረንሣይ ሌጋሲዮንና ሩዋንዳ ሠፈሮች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። በመጨረሻም ከአዲስ አበባ ሠፈሮች መካከል አንዳንዶቹ በታዋቂ የውጭ አገር ዜጎች ስም የተሠየሙ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ቤኒን ሠፈር እና ተረት ሠፈር ይገኙበታል። ቤኒን ሠፈር ስያሜውን ያገኘው ከጣሊያን ወረራ በፊት ተዋቂ ነጋዴ በሆኑት የአይሁድ ተወላጅ ቤኑን ሲሆን ተረት ሠፈር ደግሞ ስያሜውን ያገኘው በአዲስ አበባ ከተከፈቱት ከመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች አንዱ በነበረው በሆቴል ዳፍራንስ ባለቤት በሆኑት ፈረንሣዊው ሙሤ ቴረስ ስም ነው። ተረት ሰፈር በጣም ታዋቂ የሆኑ አረብ እመቤት ይኖሩ ነበር ።የሰፈሩ ሰው እኚህን እመቤት <የተረት ሰፈር አድባር> ብሎ ይጠራቸው ነበር : ትክክለኛ ስማቸው ግን ወ/ሮ መርየም ቃሲም ሲሆን የሰፈሩ ሰው ያወጣላቸው የሁልግዜም መጠሪያ ስማቸው ግን "እሜት ማሪያም" ነበር ።የተረት ሰፈር ሰው ሆኖ እሜት ማሪያምን እና የመካሻ ማሞ ጋራጅን የማያውቅ የለም ።

ክፍለ ከተሞች
አዲስ አበባ በዐሥር ክፍለ ከተሞች እና በዘጠና ዘጠኝ ቀበሌዎች ትከፈላለች። ዐሥሩ ክፍለ ከተሞች ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩት ናቸው።

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ2012 አስራ አንደኛው የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ሆኖ ተጨምሯል።

የስነ ሕዝብ አወቃቀር
በ1999 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ስታስቲክስ ባለስልጣናት ባደረገው የህዝብ ቆጠራ አዲስ አበባ በአጠቃላይ 2,739,551 የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች አሏት። ለዋና ከተማው 662,728 አባወራዎች በ628,984 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደሚኖሩ ተቆጥሯል, ይህም በአማካይ 5.3 ሰዎች በአንድ ቤተሰብ ማለት ነው።. ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በአዲስ አበባ የሀገሪቱ ዋና ከተማ በመሆኗ የተወከሉ ቢሆንም፣ ትልቁ የአማራ (47.05%)፣ ተከትሎም ኦሮሞ (19.51%)፣ እንዲሁም ጉራጌ (16.34%)፣ ትግራዋይ (6.18%)፣ ስልጤ (2.94%)፣ እና ጋሞ (1.68%) ያጠቃልላል።
በአፍ መፍቻ ቋንቋነት የሚነገሩ ቋንቋዎች አማርኛ (70.99%)፣ አፋን ኦሮሞ (10.72%)፣ ጉራጌኛ (8.37%)፣ ትግርኛ (3.60%)፣ ስልጤ (1.82%) እና ጋሞ (1.03%) ይገኙበታል።

የኑሮ ደረጃ
በ1999 በተካሄደው ሀገር አቀፍ የህዝብ ቆጠራ መሰረት 98.64 በመቶው የአዲስ አበባ መኖሪያ ቤቶች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ 14.9% ንጹህ መጸዳጃ ቤት፣ 70.7% ጉድጓድ መጸዳጃ ቤቶች (አየር ማናፈሻም ያላቸውም ሆነ የሌላቸው) እና 14.3% የሚሆኑት የመጸዳጃ ቤት አገልግሎት አልነበራቸውም። የአዋቂዎች ማንበብና መጻፍ በሀገሪቱ በሁለቱም ፆታዎች ከፍተኛ ሲሆን ለወንዶች 93.6% እና ለሴቶች 79.95% ነው።

ኢኮኖሚ
ከፌዴራል መንግሥት በተገኘው ኦፊሴላዊ አኃዛዊ መረጃ መሠረት በከተማው ውስጥ 119,197 የሚያህሉ ሰዎች በንግድና ንግድ ላይ ተሰማርተዋል; 113,977 በማኑፋክቸሪንግ እና በኢንዱስትሪ; 80,391 የተለያዩ የቤት ሰሪዎች; 71,186 በሲቪል አስተዳደር; 50,538 በትራንስፖርት እና በመገናኛ; 42,514 በትምህርት, በጤና እና በማህበራዊ አገልግሎቶች; 32,685 በሆቴል እና በመመገቢያ አገልግሎቶች; እና 16,602 በግብርና። ከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዙ ቦታዎች ላይ በረጃጅም ሕንፃዎች ግንባታ ላይ ትገኛለች። የተለያዩ የቅንጦት አገልግሎቶችም እየታዩ ሲሆን የገበያ ማዕከላት ግንባታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

ቱሪዝም
ቱሪዝም በአዲስ አበባ እና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እያደገ ያለ ኢንዱስትሪ ነው። በ2007 የአውሮፓ የቱሪዝም እና ንግድ ምክር ቤት ኢትዮጵያን ለሀገር ውስጥ ቱሪዝም ምርጥ ሀገር ብሎ ሰይሟታል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና የትግራይ ጦርነት የቱሪዝም ቅነሳ አስከትሏል።

አስተዳደር
በ1987 በወጣው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የአዲስ አበባ ከተማ ተጠሪነታቸው ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ከሆኑ ሁለት የፌዴራል ከተሞች አንዷ ነች።  ቀደም ሲል በ1983ቱ በኢትዮጵያ የሽግግር ቻርተር መሰረት የፌደራል አወቃቀሩን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅቱ ከነበሩት 14 ክልላዊ መንግስታት አንዱ ነበር። ነገር ግን ያ መዋቅር በፌዴራል ሕገ መንግሥት በ1987 ተቀይሮ አዲስ አበባ የክልልነት ደረጃ የላትም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላቱን የሚመራ ከንቲባ እና የከተማውን ደንብ የሚያወጣ የከተማውን ምክር ቤት ያቀፈ ነው። ነገር ግን የፌዴራል መንግሥት አካል እንደመሆኑ መጠን የፌዴራል ሕግ አውጪው በአዲስ አበባ ውስጥ አስገዳጅ የሆኑ ሕጎችን ያወጣል። የከተማው ምክር ቤት አባላት በቀጥታ የሚመረጡት በከተማው ነዋሪዎች ሲሆን ምክር ቤቱ በተራው ደግሞ ከአባላቱ መካከል ከንቲባውን ይመርጣል። ለተመረጡት ባለስልጣናት የስራ ዘመን አምስት ዓመት ነው። ነገር ግን የፌደራሉ መንግስት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የከተማውን ምክር ቤት እና አጠቃላይ አስተዳደሩን አፍርሶ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደር ሊተካ ይችላል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌዴራል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወክለዋል። ነገር ግን ከተማዋ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አልተወከለችም። በከንቲባው ስር ያለው አስፈፃሚ አካል የከተማውን ስራ አስኪያጅ እና የተለያዩ የሲቪል ሰርቪስ መሥሪያ ቤቶችን ያካትታል።
ከ2012 ጀምሮ ከታከለ ኡማ በኋላ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው በማገልገል ላይ ሲሆኑ፣ በከንቲባነት በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው።ከታከለ በፊት የፌዴራል መንግስት ከግንቦት 9 ቀን 1998 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2000 ያገለገሉትን  ብርሃነ ደሬሳን በጊዜያዊ ባለአደራ ከንቲባነት እንዲመሩ ሾሟቸው ነበር። የዚህም ምክንያቱ በ1997 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ትልቅ ሽንፈት ቢያስተናግድም በአዲስ አበባ ያሸነፉት ተቃዋሚዎች በክልል እና በፌዴራል ደረጃ በመንግስት ውስጥ አልተሳተፉም። ይህ ሁኔታ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ በኢህአዴግ የሚመራው የፌደራል መንግስት ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመድብ አስገድዶታል።  
ከቀዳሚዎቹ የአዲስ አበባ ከንቲቦች ፦ አርከበ ዕቁባይ (1995-1997)፣ ዘውዴ ተክሉ (1977-81)፣ ዓለሙ አበበ (1969-77) እና ዘውዴ ገብረሕይወት (1952-61) ይገኙበታል።

ታሪካዊ ምስሎች
የውጭ መያያዣ
የአዲስ አበባ ካርታ

ማመዛገቢያ

የአዲስ አበባ ካርታ
አ.አ. ሚሌኒየም ጽ/ቤት አዲስ አበባ ባለፈውና በአዲሱ ሚሌኒየም ገጽ 20-23
አማርኛ ፡  የኢትዮጵያ ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነው ። ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ውስጥ ፡ የሚመደብ ፡ ሲሆን ፡ ካረቢኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ሁለተኛ ፡ ብዙ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ያሉት ፡ ቋንቋ ፡ ነው ። በአፍሪካ ፡ ከስዋሂሊ ፡ ቀጥሎ ፡ 3ኛውን ፡ ቦታ ፡ የያዘ ፡ ነው(በተናጋሪ ፡ ቁጥር)። እንዲያውም ፡ 85.6 ፡ ሚሊዮን ፡ ያህል ፡ ተናጋሪዎች ፡ እያሉት ፣ አማርኛ ፡ ከአረብኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ትልቁ ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የሚጻፈውም ፡ በአማርኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። አማርኛ ፡ ከዓረብኛና ፡ ከዕብራይስጥ ፡ ያለው ፡  መሰረታዊ ፡ ልዩነት ፡ እንደ ፡ ላቲን ፡ ከግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ መጻፉ ፡ ነው።
የዐምሐራ * ግዛት ፡ ተብሎ ፡ የሚታወቀው ፡ ቦታ ፡ በአሁኑ ፡ መካከለኛና ፡ ደቡብ ፡ ወሎ ፡ እና ፡ ሰሜን ፡ ሸዋ ፡ ይገኝ ፡ እንደነበር ፡ በታሪክ ፡ ይጠቀሳል። ከክርስቶስ ፡ ልደት ፡ በፊት ፡ ከ200 - 130 ዓ.ዓ. ፡ የነበረው ፡ አጋታርከስ ፡ ስለ ፡ ቀይ ፡ ባህር ፡ እና ፡ አካባቢው ፡ ሲጽፍ ፣ ትሮጎዶላይት ፡ ያላቸው ፡ ሕዝቦች – τής Kαμάρ λέξιςα (የካማራ Camàra ቋንቋ) ወይንም ፡ Kαμάρα λέξιςα (ካማራ Camàra ቋንቋ) ይናገሩ ፡ እንደነበር ፡ ዘግቧል። ከዚህ ተነስተው ፡ የተለያዩ ፡ ታሪክ ፡ አጥኝዎች ፡ የአጋታርከስ ፡ ካማራ ፡ ቋንቋ ፡ የአሁኑ ፡ አማርኛ በወር የቋንቋ አባሪና ፡ ወላጅ ፡ እንደሆነ ፡ ያስረዳሉ።
ትክክለኛው ፡ አማርኛ ፡ አንዳንዴ ፡ «የንጉሥ ፡ ቋንቋ» ፡ ወይም ፡ ደግሞ ፡ «ልሳነ-ንጉሥ» በመሰየም ፡ ታወቋል። አማርኛ ፡ ልሳነ-ንጉሥ ፡ የሆነው ፡ በ1272 ዓ.ም. ከዛጔ ሥርወ መንግሥት ፡ በኋላ ፡ አጼ ፡ ይኩኖ ፡ አምላክ ፡ ሰሎሞናዊውን ፡ ሥርወ-መንግሥት ፡ መልሶ ፡ ሲያቋቁም ፡ ነበር። አማርኛ ፡ ልሳነ-ጽሑፍ ፡ መሆን ፡ የጀመረው ፡ በ14ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ላይ ፡ ሲሆን ፡ ይህንንም ፡ ያደረገው ፡ ሁሉንም ፡ የግዕዝ ፡ ፈደላትን ፡ በመውሰድና ፡ 6 ፡ አዳዲስ ፡ የላንቃ ፡ ፊደላትን ፡ (ማለትም ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ዠ ፣ ጀ ፣ ጨ) እና ፡ ኸን ፡ በመጨመር ፡ ነበር። ነገር ፡ ግን ፡ በጽሑፍ ፡ ይበልጥ ፡ መስፋፋት ፡ የጀመረው ፡ ከአጼ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ጀምሮ ፡ ሲሆን ፡ ለእዚህም ፡ በተለይ ፡ አስተዋጽኦ ፡ ያደረገው ፡ ጸሐፊያቸው ፡ ደብተራ ፡ ዘነብ ፡ ነበር። አማርኛ ፡ በተለይ ፡ የተስፋፋው ፡ የዳግማዊ ፡ አጼ ፡ ምኒሊክን ፡ የግዛት ፡ ማስፋፋት ፡ ዘመቻ ፡ ተከትሎና ፡ እንዲሁም ፡ ዘመናዊ ፡ ትምህርት ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከተጀመረ ፡ በኋላ ፡ ነበር።
አማርኛ ለብዙ ዘመናት በእጅ ሲጻፍ ቆይቶ በ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ በማተሚያ መሣሪያ ሊከተብ ችሏል። የግዕዝን ፊደል በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፈጠራ ወደ ኮምፕዩተር ገብቶ ከ፲፱፻፹ ዓ. ም. ወዲህ በኮምፕዩተር መጠቀም ከመቻሉም ሌላ በዩኒኮድ ዕውቅና ኣግኝቷል። ይህ የተስፋፋ ገጽም የቀረበው በእዚሁ ሥርዓት ሲሆን በቋንቋው የተጻፉ መረጃዎች ቊጥሮች እያደጉ ነው። የዓማርኛ ፊደልና ቋንቋም ዕውቅና እያደገ ስለመጣ በእጅ ስልኮችም በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ኣፕል የቋንቋ ገበታዎቹን ሌሎችም እንዲጠቀሙበት በ፳፻፯ ዓ. ም. ስለከፈተ ዓማርኛን እንደሌሎች የዓለም ባለፊደል ቋንቋዎች መርጦ መጠቀም ተችሏል። በ፳፻፰ ዓ. ም. ግዕዝ የመጀመሪያን የኣሜሪካ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) ኣግኝቷል። [1]
ይህም የሆነው በየካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. አማርኛ ወደ ማናቸውም ሌላ ቋንቋ በኮምፒውተር በቀላሉ ወደሚተረጎሙት ቋንቋዎች ገብታለች። ሆኖም የትርጉሙ ጥራት ከፍ ያለ ሳይሆን ስኅተቶች የተሞላበት ሆኖ ቀርቷል።
ዘዬ
አማርኛ ቋንቋ ወስጥ አራት ዋና ዘዬዎች አሉ እነሱም የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ እና ዘመናዊ አማርኛ ናቸው። ዘየወቹ ብዙም ልዩነት የላቸውም ይህም ማለት ሁለት የተለያየ አማርኛ የሚያወሩ ሰዎች ይግባባሉ ማለት ነው። በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚነገረው ዘመናዊ አማርኛ ነው። ዘመናዊ አማርኛ በብዛት በሸዋ አማርኛ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የሚለይበት ብዙ ገጸ ባህሪያትም አሉ። ከነዚህ በሃሪያት ውስጥ የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸው።
ሸዋ አማርኛ                                    ዘመናዊ አማርኛ
'ቀ' እንደ 'ኧ' ሲባል                              'ቀ' እንደ 'ቀ' ነው የሚባለው
'ከ' በ'ተ' እና በ'ኸ' ሲባል                       'ከ' እንደ 'ከ' ይባላል
ከላይ ከተጠቀሱት ምሳሌያት ማየት እንደሚቻለው ከሸዋ አማርኛ በተቃራኒ ዘመናዊ አማርኛ እንደሚጻፈው ነው የሚባለው። በተጨማሪም ዘመናዊ አማርኛ ውስጥ ብዙ የተውሶ ቃላት ይገኛሉ።

ትንተና
በሷዴሽ ዝርዝር 207 ተራ ቃላት ውስጥ

28 ቃላት ወይም 13.5% ከግዕዙ በምንም አይለዩም (አንተ፣ እንስሳ፣ ዓሣ፣ ፍሬ፣ ሥጋ፣ ደም፣ ዐይን፣ አፍ፣ እግር፣ ክንፍ፣ ልብ፣ ነከሰ፣ ሞተ፣ ቆመ፣ ዞረ፣ አሠረ፣ ፀሐይ፣ ኮከብ፣ ባሕር፣ ደመና፣ ሰማይ፣ ነፋስ፣ ጢስ፣ እሳት፣ ሌሊት፣ ዓመት፣ ክብ፣ ስም።)
77 ወይም 37% ከግዕዙ ቃላት በቀጥታ የተደረጁ ናቸው (እኔ፣ እኛ፣ እናንተ፣ ማን፣ ምን፣ የት፣ መቼ፣ ሁሉ፣ ብዙ፣ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፣ አምስት፣ ረጅም፣ ከባድ፣ ትንሽ፣ አጭር፣ ጠባብ፣ ቀጭን፣ ሴት፣ ሰው፣ ልጅ፣ ሚስት፣ አባት፣ ወፍ፣ ቅማል፣ ዘር፣ ቅጠል፣ ሥር፣ ልጥ፣ ሣር፣ አጥንት፣ ስብ፣ እንቁላል፣ ቀንድ፣ ጸጉር፣ ራስ፣ ጥፍር፣ እጅ፣ ጉበት፣ ጠጣ፣ በላ፣ ጠባ፣ ነፋ፣ ተነፈሰ፣ ሳቀ፣ አየ፣ ሰማ፣ አሠበ፣ ፈራ፣ ገደለ፣ ቈረጠ፣ መጣ፣ ወደቀ፣ ያዘ፣ ጨመቀ፣ አጠበ፣ ሳበ፣ ገፋ፣ ጣለ፣ ሰፋ፣ አለ፣ አበጠ፣ ዝናብ፣ ጨው፣ ጉም፣ አመዳይ፣ አመድ፣ ቀይ፣ ሙቅ፣ ሙሉ፣ አዲስ፣ አሮጌ፣ እርጥብ፣ ቅርብ፣ ሩቅ።)
በዝርዝሩ ከተረፉት ግማሽ ቃላት፣ ብዙዎች ከሌሎች የግዕዝ ሥሮች በሌላ መንገድ መጡ፣ ለምሳሌ «እርሱ» በግዕዝ «ውእቱ» ፈንታ፣ ከ«ርዕሱ» (ራሱ) ይመስላል።
ከግዕዝ ጭምር ከሰው ልጆች ልሳናት የተበደሩ ሌሎች ቃላት እንደ ዘመኑ ይለያያሉ፦ ከግሪክኛ፣ ከአረብኛ፣ ከፖርቱጊዝኛ፣ ከቱርክኛ፣ ከፈረንሳይኛ፣ ከጣልኛና ከእንግሊዝኛ ቃላት የተቀበሉባቸው ዘመኖች ኑረዋል። ከ16ተኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ በኋላ ፡ አማርኛ ፡ ውስጥ ፡ ኦሮምኛ ፡ ቃላት ፡ መግባት ፡ ጀምረዋል ፡ ባሁኑ ፡ ሰዓትም ፡ እየገቡ ፡ ይገኛሉ። 
ምሳሌዎች፦

ከግሪክኛ፦ ጠረጴዛ
ከአረብኛ፦ ባሩድ፣ ሻይ፣ ብርቱካን
ከቱርክኛ፦ ሰንደቅ
ከፈረንሳይኛ፦ ባቡር
ከጣልኛ፦ ቡሎን፣ መኪና
ከእንግሊዝኛ፦ ኢንተርናሽናል፣ ሬዲዮ
ከኦሮሚኛ፦ ጨጨብሳ፣ ጉዲፈቻ

lpA
ደግሞ ፡ ይዩ
መዝገበ ፡ ቃላት
ቅድመ-ሴማዊ ፡ ጽሕፈት

የውጭ ፡ መያያዣዎች
አማርኛ-እንግሊዝኛ ፡ መዝገበ ፡ ቃላት
ኢትዮፒክ.ኮም በኣበራ ፡ ሞላ Archived ኦገስት 1, 2007 at the Wayback Machine
አዲስ ፡ ሳይንስ
ዋርካ - ውይይት ፡ በአማርኛ
ፌስቡክ ፡ በአማርኛ
ግዕዝኤዲት ፡ ነፃ ፡ የአማርኛ ፡ መክተቢያ ለዊንዶውስና ማክ Archived ዲሴምበር 4, 2020 at the Wayback Machine
ጉግል ፡ በአማርኛ Archived ጁላይ 10, 2011 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ፡ ፊደል
የiPhone አማርኛ ፡ ቋንቋ ፡ መማሪያ
ታይፕ፥ ኢሜል፥ እና ቴክስት በአማርኛ - iPhone
itunes.com/apps/amharic [2]
itunes.com/apps/ahaz [3]
[4] ግዕዝኤዲት ቴክስት በአማርኛ ለመጻፍ፣ ለመላክ፣ ለመፈለግ፣ በኣይፎን 6 እና ኣይፓድ GeezEdit Amharic Typing for iPhone 6 and iPad
[5] ግዕዝኤዲት ለዊንዶውስ
ስለ ፡ ነፃው ፡ ግዕዝኤዲት GeezEdit ቪድዮ ፡ በዶ/ር ፡ ኣበራ ፡ ሞላ ፡ እና ፡ የኣዲስ ፡ ኣበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ተማሪዎች
[6] ኣበራ ፡ ሞላ Aberra Molla, "Ethiopic character entry", published 2015-04-07, issued 2015-04-07
[7] ኣበራ ፡ ሞላ Aberra Molla, "Phonetic Keyboards", published 2017-08-15, issued 2017-08-15

ማጣቀሻ

nbsp;
|- style="font-size:2em"
!style="font-size:0.5em"|
|ደ||ዱ||ዲ||ዳ||ዴ||ድ||ዶ||colspan="2" style="background:#ccc;"|
nbsp;
|- style="font-size:2em"
!style="font-size:0.5em"|
|ቸ||ቹ||ቺ||ቻ||ቼ||ች||ቾ||colspan="2" style="background:#ccc;"|
ኦሮሞ' በኢትዮጵያ፣ በኬንያና፣ በሶማሊያ የሚኖር ማህበረሰብ ነው። ኦሮሞ ማለት በገዳ ሥርኣተ መንገሥት ስር ይተዳደር የነበረ ህዝብ ነው። በገዳ መንግሥት ስር የአገር መሪ በየ፰ቱ (ስምንት) ዓመት የሚቀይር ሲሆን በተለያዩ የኦሮሞ ክልሎች ንጉሣን እንደነበሩም ታሪክ ይነግረናል። በኦሮሚያ ክልሎች ከነበሩት ንጉሦች መካከል የታወቁት አባ ጂፋር ናቸው። የኦሮም ሕዝብ ከግራኝ ወረራ በኋላ ሰሜኑን ኢትዮጵያ ወሯል። በአንድ ሺ ስምንት መቶ ክፍለዘመን ማለቂያ ላይ በንጉሥ ዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ከአቢሲኒያ ጋር ተቀላቀሎ ኢትዮጵያ ስትመሰረት፣ የቀዳሚ ሃገሩ ሕዝብ ችግር አሳልፏል። 
እንደ ሌሎች ኩሺቲክ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች፣ ከጥንት ጀምሮ ትውልዳቸው ከጥንታዊው ኩሽ መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው። ሆኖም በሃይል ስጋት መገንጠልን ያሰቡ ወገኖች ጥቂት ናቸው።

ታዋቂ ሰዎች
እቴጌ መነን
ጀኔራል አብዲሳ አጋ፤ ኣትሌት አበበ ቢቂላ፣ ኣትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፤ ኣትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ ኣትሌት ቀነኒሳ በቀለ፤ ጀኔራል ከበደ ብዙነሽ፤ ኣጋሪ ቱሉ፣ መንግስቱ ኣበበ፣ አትሌት ኃይሌገ/ስላሴ፣ መሰረት ደፋር፣ እጅጋየሁ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ ጄ.አሊ በርኬ፣ ባልቻ፣ ፊ/አ ገበየሁ፣ ዶ.ር አብይ፣ አለማየሁ አቶምሳ..................ሌሎችም ይገኛሉ። 


== ማመዛገቢያ ==
ትግራይ (በተጨማሪም ትግሬ፣ ትግርኛ) ከ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ አማራ ክልላዊ መንግስት እና አፋር ክልላዊ መንግስት ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ መቐለ ሲሆን ከክልሉ ታዋቂ ከተሞች ውቅሮ፣ ዛላምበሳ፣ ዓብዪ ዓዲ፣ ዓድዋ፣ ሓውዜን፥ ሸራሮ፣ ሑመራ፣ ዓዲግራት፣ ኣላማጣ፥ ኮረም፥ አኽሱም፣ ሽረ እንዳስላሰ፣ ሑመራ፥ ማይፀብሪ፥ ዳንሻ፥ መኮኒ፣ ማይጨውና ሌሎችም ታዳጊ ከተሞች ይገኛሉ። በ1999 ዓ.ም በተደረገው  የቤትና ህዝብ ቆጠራ ግምት መሰረት የክልሉ ህዝብ ቁጥር ከ4.9 ሚልዮን በላይ ይሆናል። የክልሉ ዋነኛ ቋንቋ ትግርኛ  ሆኖ ኢሮብኛና ኩናምኛ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ህዝቦች ይኖሩበታል። እምባ ኣላጀ፣ ፅበት፣ ሶሎዳ እና ወርሐት በትግራይ ካሉ ከፍተኛ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። የትግራይ ክልል በበርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ሃብቶች የታደለ ክልል ነው። ከ1000 ዓመት ቅድመልደተ ክርስቶስ ጀምሮ የኣክሱም መንግስት እስኪወድቅ የዳኣማት እና ኣክሱም ስልጣኔዎች የታሪክ ኣሻራቸውን ጥለው ኣልፈዋል፡፡ የሓ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ፣ የ2500 ዓመት የአክሱም ጥንታዊ ሃውልቶች፣ ከ4ኛው እስከ 18ኛው ክ/ዘመን እንደተሰሩ የሚታወቀው ከ120 በላይ የሚሆኑ ከኣለት ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ውቅር ኣብያተክርስትያናትና ገዳማት እንዲሁም ሌሌች በርካታ ታሪካዊና ኣርኪኦሎጂካዊ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው። ትግራይን በባህልና በታሪካዊ ኣመጣጥ ከኤርትራ እንዲሁም በዛጉዬዎች ከተመራው የአገው ስልጣኔ ነጥሎ ማየት ኣይቻለም። 


== ምንጮች ==

ያሉአፄWikify}}
ጎጃም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝና በአባይ ወንዝ ተከቦ የሚገኝ ባህር ዳርን ፍኖተ ሰላምን አገው ምድርን መተከልን ፓዊ ቆላ-ደጋዳሞትን፣ አቸፈርን ደብረ ማርቆስን ሞጣና ብቸና አውርጃዎች እና በነዚ ውስጥም ከ 35 በላይ ወረዳዎችን ይዞ የሚገኝ የራሱ ስርዎ መንግሥት የነበረው ከፍለ-ሃገር ነው። ጎጃም ውስጥ ኣሉ ከሚባሉት ከተሞች እንደ ባሕር ዳር ፡ ደብረ ማርቆስ ፡ፍኖተ ሰላም ፡ቡሬ ፡ኮሶበር ፡ ዳንግላ ፡ቻግኒ ፡ ኣዴት ፡ መራዊ ፡ ሞጣ፡ ቢቸና፡ ደጀን ይገኙበታል ፡፡
ጎጃም እንደነ በላይ ዘለቀ:አፄ ሱስንዮስ የአፄ ፋሲል አባት: ንጉስ ተክለሀይማኖት በጣልያን ወረራ ጊዜ በአድዋ ድል ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበራቸው: ሀዲስ አለማየሁ አቤ ጉበኛና ሌሎችም ደራሲያን ጀግኖችን ያፈራ እንዲሁም የዓባይ እና የጣና መናገሻ ነው ፡፡
ጎጃም የቅኔ ትምህርት በስፋት የሚሰጥበት ፡እንዲሁም    እንደነ የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ (ዶ ር) (1902- 1996  )ኣ.ም  ኣቤ ጉበኛ (1925 - 1972 )ኣ.ም  ዮፍታሄ  ንጉሤ(1897-1937  ) ኣ.ም የመሳሰሉ  የጥበብ ሰወችን ኣፍርታለች ፡፡  ጎጃም በጤፍ አምራችነት ከታወቁት የኢትዮጵያ ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። በተለይ የአዴት ጤፍ በባህር ዳር ጎንደር ደሴ እና መቀሌ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት የታወቀ እና ተወዳጅም ነው። እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም  እነብሴ ሞጣ ዙሪያ ወይንውሀ  እና ጎንቻ  ሲሶ ግንደወይን ዙሪያ የሚመረተው ጤፍ የአዲስ አበባን ህዝብ ገትሮ እንደያዘ ይነገራል።[[ቡሬ]] ዙሪያ የሚበቅለው በርበሬ በቆሎ ደግሞ የመላው የኢቲዮጵያን ህዝብ ገትሮ እንደያዘም ይነገርለታል፡፡ በነገራችን ላይ ቡሬ ዙሪያ ይህንን ብቻ አይደለም የሚያበቅል እንደ ጤፍ፣ሽንብራ፣ቦለቄ፣ዳጉሳ፣መጥቀስ ሆነብን እንጂ የማይበቅል ነገር የለም፡፡በዋናነትም ከ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ [[ገዳም ልጃሞር]] ቀበሌ ይህንን በማምረት ይጠቀሳል፡፡ 
ጎጃም ሌሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ባቄላ አተር ወዘተ የሰብል አይነቶችን በማምረትም ይታወቃል።
ጎጃም የአባይ  እና ሌሎች የበርካታ ወንዞች መነሻ ነው ።ጮቄ ተራራ በዚሁ ክፍለ ሃገር ይገኛል።ጎጃም በኣሁኑ ጊዜ ማለትም ኣገራችን የፌደራሊዝም ስርኣት ከተከተለች ወዲህ ከኣራት ኣስተዳደር ዞን ተከፍሏል ።ሥወስቱ ማለትም አዊ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በአማራ ክልል ሲገኙ መተከል ቤሻንጉል ጉምዝ ክልል ተካቷል ።
ምዕራብ ጐጃም ዞን                §የዞኑ ዋና ከተማ፡- ፍኖተ ሰላም

                                            §የወረዳዎች ብዛት፡- 16

                                              §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 6

                                                 oባህር ዳር 
                                                   oፍኖተ ሰላም
                                                    oመርዓዊ
                                                   oቡሬ
                                                   oደንበ ጫ  
                                                        o   አዴት
                                                      

                                                           §የቀበሌዎች ብዛት፡- 370

                                                               oየገጠር፡-328

                                                                    oየከተማ፡-42

                                                     §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2714017

                                                              ወንድ 1 364 143

                                                                                 ሴት 1 349 874

የወረዳው ስም    የወረዳው ዋና ከተማ                                                                                                               
      
1 ሜጫ    መርዓዊ
2ደምበጫ    ደምበጫ
3ቡሬ ዙሪያ    ቡሬ
4ወንበርማ       ሺንዲ
5ጃቢ ጣህናን    ፍኖተ ሠላም
6ባህር ዳር ዙሪያ   ባህር ዳር
7ደጋ ዳሞት    ፈረስ ቤት
8ሰከላ     ግሽ ዓባይ
9ቋሪት   ገበዘ ማርያም
10ሰሜን አቸፈር    ቢን
11ደቡብ አቸፈር    ዱር ቤቴ
12ይልማና ዴንሳ      አዴት
13ጐንጅ ቆለላ     አዲስ አለም

አዊ  ዞን                §የዞኑ ዋና ከተማ፡- እንጅባራ 
                                                  §የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት-122 ኪ.ሜ
                                                                                                                              

                                                      §የወረዳዎች ብዛት፡- 7

                                                     §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት፡- 3

                                                            oዳንግላ

                                                           oእንጅባራ

                                                           oቻግኒ

                                                      §የቀበሌዎች ብዛት፡- 201

                                                             oየገጠር፡- 180

                                                        oየከተማ፡- 21

                                                 §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 1058 289

                                                     oወንድ916015

                                                    oሴት142274
      

የወረዳው ስም                                  የወረዳው ዋና ከተማ
1አንካሻ ጓጉሣ                                                                                            አገው ግምጃ ቤት
2ባንጃ ሽኩዳድ                                                                                          እንጅባራ
3ጓጉሣ ሽኩዳድ                                                                                       ቲሊሊ
4ፋግታ ለኮማ                                                                                       አዲስ ቅዳም
5ዳንግላ                                                                                                 ዳንግላ
6ጃዊ                                                                                                      ፈንድቃ
7ጓንጓ                                                                                                      ቻግኒ

ምስራቅ ጐጃም ዞን                  

 §የዞኑ ዋና ከተማ፡- ደብረ ማርቆስ

    §የዞኑ ዋና ከተማ ከክልሉ ዋና ከተማ ያለው ርቀት፡-

              249 ኪ.ሜ

       §የወረዳዎች ብዛት፡- 16

      §የከተማ አስተዳደሮች ብዛት ፡- 4

 oደብረ ማርቆ
oሞጣ

   oቢቸና

    oደጀን

 §የቀበሌዎች ብዛት፡- 424

   oየገጠር፡- 388

    oየከተማ፡- 36

  §በዞኑ ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ብዛት፡- 2 152 671

ወንድ1 066 09    ሴት1 086 577

የወረዳው ስም                                     የወረዳው ዋና ከተማ

1ባሶሊበን                                           የጁቤ
2ማቻከል                                    አማኑኤል
3እነማይ                                         ቢቸና
4ደባይጥላት ግን                                    ቁይ
5ደጀን ዙሪያ                                        ደጀን
6እናርጅና እናውጋ                             ደብረ ወርቅ
7ሁለት እጁ እነሴ                                   ሞጣ
8 ቢቡኝ

                                      ድጓፅዮን

9አዋበል                                             ሉማሜ
10እነብሴ ሳር ምድር                  መርጡ ለማሪያም
11ጐዛምን                                 ደብረ ማርቆስ
12 ስናን                                        ረቡዕ ገበያ
13አነደድ                                       አምበር
14ሸበል በረንታ                            የዕድ ውኃ
15ጐንቻሲሶ እነብሴ                    ግንደ ወይን
16ደብረ ኤልያስ                      ደብረ ኤልያስ
17  ሰዴ

                 ሰዴ 

1.  http://www.amhara.gov.et/web/communcation-affairs-office/information-desk?p_p_id=56_INSTANCE_o5RZ&p_p_lifecycle=0&p_p_state=normal&p_p_mode=view&p_p_col_id=column-2&p_p_col_count=1&page=8

2. «Bibliography of Ethiopian Writers» ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ - ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (pdf)

#ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 14:27, 23 ጁላይ 2019 (UTC)
ወሎ የሀይማኖት፣ የጥበብና የጀግንነት እንዲሁም  የዉበትና የብዝሃነት አምባ ነዉ ስንል እንዲሁ አይደለም።
ወሎ የኢትዮጵያ አራቱ የዜማ ቅኝቶች  አምባሰል፣ ባቲ፣ ትዝታና አንቺሆዬ ዜማዎች ፍለቂያ  የጥበብ ምድር ስለሆነች ነዉ። በተጨማሪም ወሎ  የበርካታ ከያንያንና ፃህፍት መፍለቂያ ፣ የጥበበኞች ምድር ናት።
ወሎ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ብዝነት እንዲሁም  የአንድነትና የመቻቻል  ማሳያ ድንቅና ቅድስት ምድር ናት። የወሎ ምድር የክርስትናና የእስልምና  ሃይማኖቶች የየራሳቸዉን የደመቀ ታሪክ ጠብቀዉ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነዉ የሚኖሩበት ቅድስት ምድር ነዉ።
የኦርቶዶክስ ክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች ከፍታን የሚገትፁ ድንቅዬና ብርቅዬ የአምልኮ ቦታዎችና የአስተምህሮ  ባለቤቶች  የሚገኙባት ቅድስት ምድር ናት ወሎ።
የአማራ ሳይንት ተደባበ ማሪያም መገኛ ወሎ ነዉ። የግማደ መስቀል መገኛ ግሸን ማሪያም መገኛ አምባሰል ወሎ ነዉ።
ከእስልምና እምነት አንፃርም የነብዩ መሀመድ የመጀመሪያዉ  መዉሊድ ከተበረበት የጀማ ንጉሰ ነገስት መስጊድ  መገኛ ወሎ ነዉ። 
ወሎ እስልምናና ክርስትና አንድ አምሳልና አንድ አካል ሆነዉ ለዘመናት አብነት የዘለቁበት ሰፊ ሚስጢር በውስጣቸው ይዘው  ሁለቱን ሀይማኖቶች  አቻችለዉ ትዉልድ ያዘለቁ   የእነ መምህር አካለ ወልድ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲያሰሩ ፣ መስጊዱን አብረዉ  የሚያሳንፁ  የእነ ባህታዊ  አባ ምስክርና  የእነ ሀጂ መሀመድ ገታ ቃል ኪዳን  ስላለበት ነዉ።
ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ የሚጋባበት፣ የስም አወጣጥ ባህሉ ድንበር የሌለዉ ፍቅርን  የሚያንፀባርቅ የወሎ ምድር ነዉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካባቢዉን ስነ ቃል ልዋስና
ልጅየዉ ሰለሞን አባቱ መሀመድ፣
ምንኛ ደስ ይላል ወሎ ላይ መወለድ፣  የተባለለት ምድር ነዉ ወሎ ።
በረጅምና  ዘመን ተሻጋሪ የኢትዮጵያና የአማራ ህዝብ  ታሪክ ዉስጥ ወሎ  የታሪክ ሀብትና ጉልህ አሻራዎች መገኛ ነዉ።
በኢትዮጵያ የመካከለኛዉ ዘመን ታሪክ ዉስጥ የብዙ ነገስታት  ዋና የአቅም ግንባታ ማዕከልና የሀይቅ እስጢፋኖስ ገዳም  መገኛዉ ወሎ ነዉ። 
በነፃነት ታሪካችን የአድዋ ፍልሚያ ምክንያት የሆነዉ  የዉጫሌ ስምምነት የታሰረበት  ይስማ ንጉስ  መገኛዉ ወሎ ነዉ። 
የዳግማዊ ሚኒሊክ የአድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ ነጋሪት  የተጎሰመበት  ወረኢሉ  መገኛዉ ወሎ ነዉ። የጣሊያን ወራሪ ሀይል በማይባር ሀይቅ ዙሪያ  ልኩን ያሳዩት  የእነ ደጃች መንገሻ አብዬ ምድር ነዉ ወሎ
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስና ፊትአዉራሪ ገብርዬ የመሰሉ ጀግኖች ለኢትዮጵያ አንድነት ሲዋደቁ በክብር ያረፉበት የመቅደላ  አምባ ታሪካዊ ስፍራ  መገኛዉ ወሎ ነዉ።
ወሎ  በኢትዮጵያ አማራ እና አርጎባ ህዝብ የስነ መንግስት  ታሪክ መሰረት የጣሉ  አርቆ አሳቢ ነገስታቶችን  ለአብነትም እነ ራስ አሊ እና ንጉስ ሚካኤል(ኢማም መሀመድ አሊ… …ወላስማ ካሶ  የተገኙበት ብርቅዬ ምድር ነዉ። ምስራቃዊው ክፍል በአብዛኛው የሚሸፍነው ሙስሊም ማህበረሰቦችን ሲሆን ምእራባዊው ክፍል ደግሞ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ ተሳስሮ የሚኖርበት ምድር ነው።
ይህ ሁሉ ማሳያዎችን ጠቅሱ ለማለፍ እንጂ የወሎ የታሪክ ሀብታምነት  በዚህ ብቻ የሚያልቅ አይሆንም። 
ወሎ የቆንጆዎችና የገራገሮች  ምድር ነዉ።ወሎ የአማራ አቃፊነትማሳያ፣ የብዝሃነት ተምሳሌት ነዉ
ወሎ የአማራዉ፣ የኦሮሞዉ፣ የአፋሩ፣ የአርጎባዉ እና ሌሎችም በፍቅርና በመዋደድ አብረዉ ለዘመናት የዘለቁበት ምድር ነዉ።
ብዝሃነት ለወሎ   ጌጥ እንጂ ስጋት ሆኖት አያዉቅም።
ቤተክርስቲያን ሦስት ትርጉም ያለው በዘርፍና በባለቤትነት የተጠቃለለ ስም ነው፡፡

አንደኛው ትርጉም ፡- የክርስቲያን ቤት የክርስቲያን መሰብሰቢያ የክርስቲያን መገኛ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ክርስቲያኖች የሚጸልዩበት ሥጋ እና ደሙን የሚቀበሉበት የሚሰግዱበት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት የጸሎት ቤት ማለት ነው፡፡ (ኢሳ. 56፡7፤ ኤር. 6፡10-16፤ ማቴ. 21፡13፤ ማር. 11፡17፤ ሉቃ. 19፡46 )
ሁለተኛ ትርጉም ፡- የክርስቲያን ወገን ክርስቲያን ሁሉ የሚጠራበት ስም ነው፡፡ ‹‹ ቤተ እስራኤል፣ ቤተ ያዕቆብ፣ ቤተ አሮን በማለት የሚጠሩት፡፡ (መዝ. 117፡3፤ ማቴ. 16፡18)
ሦስተኛ ትርጉም ፡- ቤተክርስቲያን ሲል ምዕመናን ነው፡፡ ይህም ማለት ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡ የክርስቲያን ወገኖች ቤተመቅደስ ማለት ነው፡፡ የእያንዳንዱ የክርስቲያኖችን ሰውነት የሚያመላክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ አታውቁምን›› 1ኛ ቆሮ. 3፡101
እስልምና (/ˈɪslɑːm/; አረብኛ: الإسلام, በላቲን: al-’Islām [ɪsˈlaːm] (listen),  "ለ [አምላክ]መገዛት ወይም መተናነስ  ") አሀዳዊ ኢብራሂማዊ እምነት ነው, በዋናነት ቁርአንን ማእከል ያደረገ እምነት ነው , ቁርአን ሀይማኖታዊ ፅሁፍ ሲሆን በሙስሊሞች ዘንድ ከአላህ ለመሐመድ(ሰ.አ.ወ) የተገለጠ ነው ተብሎ ይታሰባል, መሐመድም ዋነኛ እና የመጨረሻ እስላማዊ ነብይ ነው.ከክርስትና እምነት በመቀጠል በአለማችን በአማኝ ብዛት በሁለተኛ ረድፍ ይመደባል; ከሁለት ቢሊየን ተከታይ በላይ ; በአለም አቀፍ ደረጃ 25ፐርሰንት ይሸፍናል።እስልምና አምላክ(አላህ)(ምስጋና ይገባው) አዛኝ, አይነተኛ, ሀያል እና የሰው ልጆችን በተላያዩ ነብያት ,ሀይማኖታዊ መፅሀፍት እና ተአምራት አማካኝነት ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል። የመሀመድ አስተምህሮት እና ተግባራት(ሱና) ተሰብስቦ እና ተጠርዞ በሰነድ ይገኛል ይህም ሀዲስ ይባላል።ሀዲስ በሙስሊሞች ዘንድ ከቁርአን በመቀጠል ለህግ እና ለተዛማጅ አገልግሎት ይውላል። 
ሙስሊሙን አሊያም ሙስሊሚን ነው ፣ ሙስሊማ አንስታይ ሲሆን የርሱ ብዙ ቁጥር ሙስሊማት ነው። ኢስላም إِسْلَٰم ደግሞ ዲኑ ሲሆን 8 ጊዜ ተወስቷል። ወጅህ وَجَّهْ ሁለንተናን አሊያም ህላዌን የሚያሳይ ሲሆን የቃል ትርጉሙ *ፊት* ማለት ነው፣ አንድ ሰው ሁለንተናውን ለአላህ ሲሰጥ ታዛዥ፣ ተገዥ፣ አምላኪ ይባላል፣ ይህ በአረቢኛ *ሙስሊም* ማለት ነው፦

2:112 እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ የሰጠ أَسْلَمَ ሰው ለርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ በነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
4:125 እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ ከሠጠ أَسْلَمَ እና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን፣ ከተከተለ ሰው፣ ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ሰው ማነው?
3:20 ቢከራከሩህም:- ፊቴን وَجْهِيَ ለአላህ ሰጠሁ أَسْلَمْتُ ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸዉ፤
የኢስላም አስኳሉ ተህሊል تهليل‎,ነው፣ ተህሊል ማለትም “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ”لا اله الاّ الله ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ማለት *ከአንዱ አላህ በስተቀት ሌላ አምላክ የለም* ማለት ነው፣ “ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ” ሁለት ማዕዘናት አለው፣ አንዱ *ነፍይ* ሲሆን ሁለተኛው *ኢሥባት* ነው፣ ነፍይ ማለት ላ-ኢላሀ*ሌላ አምላክ የለም* ስንል ጣኦታትን ውድቅ ማድረግን ሲያመለክት ኢሥባት ደግሞ ኢልለሏህ*ከአንዱ አላህ በስተቀት* ስንል አንዱን አምላክ እያረጋገጥን ነው፣ ይህ ተህሊል *ጠንካራን ዘለበት* ይባላል፦
31:22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ወደ አላህ የሚሰጥም يُسْلِمْ ሰው፣ ጠንካራ ገመድ بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፤ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው።
2:256 በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት بِالْعُرْوَةِ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ሙስሊም ማለት እንግዲህ ይህ ነው፣ አንዱን አምላክ በብቸኝነት ከሌሎች ጣኦታት ለይቶ የሚያመልክ ማለት ነው፣ በዚህ ሂሳብ ሁሉም ነቢያት ሙስሊሞች ናቸው፣ ሙስሊሞች አልነበሩም ማለት አንዱ አምላክ አያመልኩም ማለት ነው፣ ነገር ግን ቁርአን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ የሚያመልኩ ነበሩ ይለናል፦
ነጥብ አንድ
ነቢያት
አላህ ጥንት ለነበሩት ነቢያት ወህይ (melekotawi raey) የሚያወርድላቸው የነበረው “ላ ኢላሃ ኢልላ አና” لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* የሚል ነው፦
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
16:2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፤ አስጠንቅቁ፤ እነሆ *ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም* لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا ፍሩኝም ማለትን አሳታውቁ በማለት ያወርዳል።
20:14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፣*ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም*لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا እና ተገዛኝ፤ ሶላትንም በርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ።
ወደ ሰዎች ሲልካቸውም *ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም* ብለው እንዲናገሩ ነው፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤
23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ለናንተ *ከእርሱ በቀር ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ *ከእርሱ ሌላ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤
ይህን መረዳት ይዘን ሁሉም ነቢያት አንዱን አምላክ አላህን የሚያመልኩ ነበሩ በአረቢኛ ሙስሊሞች ነበሩ ማለት ነው፣ ችግራችሁ ቋንቋ ከሆነ ሙስሊም የሚለውን አማርኛው ታዛዦች ብሎ ይፈታዋል፦
2:133 ያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለርሱ ፍፁም *ታዛዦች* مُسْلِمُونَ ኾነን እናመልካለን አሉ፡፡
10:83 ሙሳም አለ፡-«ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ *ታዛዦች* مُسْلِمِينَ እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ»
3:52 ዒሳ ከነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ ፡-ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ *ታዛዦች* مُسْلِمُونَ መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ።
5:44 እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት أَسْلَمُوا ነቢያት በነዚያ ይሁዳውያን በሆኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፤
አላህ የነቢያችንን ኡማ ሙስሊሞችን ነው ብሎ የተናገረው የጥንቶቹን በተናገረበት ስሌት ነው፦
29:46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ ነዚያን የበደሉትን ሲቀር በሉም፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን።
3:84 በአላህ አመንን፤ በኛ ላይ በተወረደዉም በቁርአን በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሐቅም በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደዉ፤ ለሙሳና ለዒሳም፣ ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸዉ በተሰጠዉ አመንን፤ ከነርሱ መካከል አንዱንም አንለይም፤ እኛ ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን፣ በል።
2:136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው ቁርኣን ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች مُسْلِمُونَ ነን» በሉ፡፡
21:108 ያ ወደኔ የሚወረደው፣ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች مُسْلِمُونَ ናችሁን? በላቸው።
22:34 አምላካችሁም አንድ አምላህ ብቻ ነው፤ ለርሱም ብቻ ታዘዙ أَسْلِمُوا፤ ለአላህ ተዋራጆቸንም አብስራቸው።
40:66 እኔ ከጌታዬ አስረጅዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን እንዳላመልክ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማት ጌታም እንድግገዛ أُسْلِمَ ታዝዣለሁ በላቸው።
6:71 «የአላህ መንገድ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ ነው፡፡ ለዓለማት ጌታ ልንገዛም لِنُسْلِمَ ታዘዝን» በላቸው፡፡
አላህ ነቢያትን ሲልክ በማህበረሰቡ ሊግባባበት በሚችል ቋንቋ ነው፣ በራሳቸው ቋንቋ ሁሉንም ያለው *ሙስሊም* ማለትም ታዛዢዎች፣ አምላኪዎች፣ ተገዢዎች ነው፣ ሙስሊሞች አይደሉም ብሎ መቃወም አንዱን አምላክ አያመልኩም፣ ጣኦታውያን ነበሩ እንደማለት ነው፣ ስለዚህ ኢስላም በነቢያችን የተጀመረ ሳይሆን የተጠናቀቀ የአላህ ዲን ነው፦
22:78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ; አርሱ መርጧችኃል በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ ከዚህ በፊት *ሙስሊሞች* الْمُسْلِمِينَ ብሎ ሰይሟችኋል፤
14:4 ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ *ቋንቋ* እንጂ በሌላ አልላክንም፤
30:22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፥ *የቋንቋዎቻችሁ* እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤
ነጥብ ሁለት
የነቢያት አምላክ
አላህ ጥንት ነቢያቶች የሚያመልኩት የነቢያት አምላክ መሆኑን የምናውቀው ከጥንቶቹ ነቢያት ጋር የነበረውን መስተጋብር ለመግለጽ ቁልና قُلْنَا *አልን* ፣ አርሰልና أَرْسَلْنَا*ላክን*፣ አውሃይና أَوْحَيْنَا *አወረድን* በማለት ጥንትም ነቢያትን ሲልክ የነበረው፣ ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲያወርድ የነበረውና በተለያየ መንገድ ሲያናግራቸው የነበረው እርሱ መሆኑን ይገልጻል፦
1. አልን፦
20:116 ለመላእክትም፣ ለአዳም ስገዱ፣ *ባልን* ጊዜ አስታውስ፤
2:35 «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» *አልንም*፡፡
11:40 ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ፣ በርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት፣ ወንድና ሴት ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን *አልነው*፤
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ *ባልነው* ጊዜ አስታውስ።
2:125 ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
2:60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡
17:2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፤ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፤ ከኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ *አልናቸውም*።
2. ላክን፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ *ልከናል*፤
57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ *ላክን*፤
23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት *ላክን*፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤
3. አወረድን፦
4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድን*፣ ወደ አንተም *አወረድን*፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው።
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ *የምናወርድለት* ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
12:109 ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደ እነርሱ ራዕይ *የምናወርድላቸው* የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤
21:7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ *የምናወርድላቸው* የኾኑ ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፤
16:43 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን *የምናወርድላቸውን* ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤
የኢስላም መሰረቶች
አርካኑል ኢስላም أركان الإسلام *የኢስላም መሰረቶች* አምስት ናቸው፣ እነዚህም፦ ሸሃዳ الشهادة‎፣ ሶላት صلاة‎ ፣ ሰውምصوم‎ ፣ ዘካزكاة እና ሃጅ حج ናቸው።
ሰሂህ ቡሃሪ ቅጽ 1, መጽሃፍ 2, ቁጥር 8: ይመልከቱ፦
حَدَّثَنَا عُبَيْدُ اللَّهِ بْنُ مُوسَى، قَالَ أَخْبَرَنَا حَنْظَلَةُ بْنُ أَبِي سُفْيَانَ، عَنْ عِكْرِمَةَ بْنِ خَالِدٍ، عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةِ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَإِقَامِ الصَّلاَةِ، وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ، وَالْحَجِّ، وَصَوْمِ رَمَضَانَ
ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ከሆነ ነቢያችን የመሰረቱት ሳይሆን ከጥንት ነቢያት የመጣ አስተምህሮት ነው፣ እነዚህን የኢስላም መሰረቶች የጥንቶቹ ነቢያት ድርጊት መሆኑን አንድ በአንድ እንመልከት፦
1.ሸሃዳ
ሸሃዳ الشهادةምስክርነት ሲሆን ከአላህ በቀር አምላክ አለመኖሩን በቀውል የሚደረግ የኢባዳ ክፍል ነው፣ ይህንን ምስክርነት ሰዎች በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን በዘመኑ የነበረውን ነብይ መልእክተኛ አድርገው ይቀበላሉ፦
23:32 በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡
7:59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፤ አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ለናንተ *ከእርሱ በቀር ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ *ከእርሱ ሌላ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ፤
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ *ከእርሱ በቀር ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም* مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ፤
7:61 አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፤ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ *መልክተኛ* ነኝ።
7:67 አላቸው፦ወገኖቼ ሆይ! እኔ ሞኝነት የለብኝም፤ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ *የተላክሁ* ነኝ፤
61:5 ሙሳም ለሕዝቦቹ ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ *የአላህ መልክተኛ* መሆኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትሆኡ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?
61:6 የመርየም ልጅ ዒሳም የ እስራኤል ልጆች ሆይ እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በሆነው የማበስር ስሆን ወደናንተ የተላክሁ *የአላህ መልክተኛ* ነኝ ባለ ጊዜ አስታውስ፤
በተመሳሳይ መልኩ አላህ ለነቢያችን *እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም* *የአላህ መልክተኛ* ነኝ በል ብሏቸዋል፦
9:129 ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው።
7:158 በላቸው፦እላንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደሁላችሁም *የአላህ መልክተኛ* ነኝ፤ ያ የሰማይና የምድር ንግስና ለርሱ ብቻ የሆነ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ሌላ አምላክ የለም لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ፤
በአላህና በመልክተኞቹም አምኖ ምስክርነት መስጠት የኢስላም ማዕዘን ነው፣ ለዛ ነው *ከአላህ በቀር አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው* لا إله إلا الله محمد رسول الله ብለን የምንመሰክረው፦
3:179 ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻዉን ይመርጣል፤ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ።
57:7 በአላህና በመልክተኛው እመኑ፤
63:1 መናፍቃን በመጡህ ጊዜ አንተ የአላህ መልክተኛው መሆንህን በእርግጥ *እንመሰክራለን* ይላሉ፤
2. ሶላት
ሶላት صلاة‎ *ጸሎት* ከኢስላም መሰረቶች አንዱ ነው፣ ሁሉም ነቢያት ሶላት ነበራቸው ምናልባት ይዘቱ ይለያይ ይሆናል፣ በቀን አምስት ጊዜ ላይሆን ይችል ይሆናል እንጂ ሶላት ከነቢያችን በፊት በነበሩት ነቢያት ነበር፦
21:73 በትእዛዛችንም፣ ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ፣ መሪዎች አደረግናቸው፤ ወደነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትን الصَّلَاةِ መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን፣ አወረድን፤ ለኛ ተገዢዎችም ነበሩ።
20:14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፣ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፤ ሶላትንም الصَّلَاةَ በርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ።
14:37 ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥሁ፤ ጌታችን ሆይ! ሶላትን الصَّلَاةَ ያቋቁሙ ዘንድ አስቀመጥኳቸው፤ ከሰዎችም ልቦችን ወደነሱ የሚናፍቁ አድርግ፤ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፤
14:40 ጌታዬ ሆይ! ሶላትን الصَّلَاةِ አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፤ ከዘሮቼም አድርግ፤ ጌታችን ሆይ ጸሎቴን ተቀበለኝ፤
20:132 ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፤ በርሷም ላይ ዘውትር፤ ሲሳይን አንጠይቅህም፤ እኛ እንሰጥሃለን መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት።
19:31 በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል፤ በሕይወትም እስከ አለዉ ሶላትን بِالصَّلَاةِ በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል።
19:55 ቤተሰቦቹንም በሶላት بِالصَّلَاةِ እና በዘካ ያዝ ነበር፤ እጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።
2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ አድርጉ፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም በምስኪኖችም በጎ ዋሉ፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም الصَّلَاةَ ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡
10:87 ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም الصَّلَاةَ በደንቡ ስገዱ፡፡ ለሙሳ ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡
3. ሰውም
ሰውምصوم‎ ጾም በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት በዘጠነኛው ወር በረመዳን አይሁን እንጂ ጾም ነበረ፦
2:183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት ሕዝቦች ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
4.ዘካ
ዘካزكاة ምጽዋት በቀድሞቹ ነቢያት የተሰጠ መመሪያ ነው፣ ምናልባት ከመቶ ሁለት ነጥብ አምስት አይሁን እንጂ ምጽዋት ነበረ፦
21:73 በትእዛዛችንም፣ ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ፣ መሪዎች አደረግናቸው፤ ወደነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትን መስገድን፣ ዘካንም الزَّكَاةِ መስጠትን፣ አወረድን፤ ለኛ ተገዢዎችም ነበሩ።
19:31 በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል፤ በሕይወትም እስከ አለዉ ሶላትን በመስገድ ዘካንም وَالزَّكَاةِ በመስጠት አዞኛል።
19:55 ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ وَالزَّكَاةِ ያዝ ነበር፤ እጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።
2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ አድርጉ፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም በምስኪኖችም በጎ ዋሉ፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም الزَّكَاةَ ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡
5. ሃጅ
ሚሽነሪዎች ስለራሳቸው ዲን በቅጡ ስላልተረዱ ሙስሊሞች ስነ-አመክኖአዊ ጥያቄዎች ስንጠይቃቸው እርርና ምርር ብለው ከመንጨርጨርና ከመንተክተክ ውጪ ምላሽ አይሰጡም፣ ከዚያም አልፎ ከኢስላም ድንቅና ብርቅ መሰረቶች አንዱ የሆነውን ሃጅ ከፓጋን የተቀዳ ነው ሲሉ በመሰለኝ ሲተቹ ይታያል፣ እግር እራስን ሊያክ አይችልም፣ ምን ከኢስላም የተሻለ ነገር ተይዞ ነው ኢስላምን ሊያኩ የተነሱት? እስቲ ይህንን ሃጅ እናስተንትን፣ ሃጅ حج የሚለው ቃል ሃጅጀ حَآجَّ *ጎበኘ* ከሚል የመጣ ሲሆህ *ጉብኝት*“pilgrimage” ማለት ነው፣ ሃጅ የተጀመረው በነቢያችን አሊያም በሙሽሪኮች ሳይሆን በጥንቱ ነብይ ኢብራሂም ዘመን ነው፣ ይህን አምላካችን አላህ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ #መመለሻ# ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ። አልነውም፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ بِالْحَجِّ ትዕዛዝ ጥራ፤
2:125 ቤቱንም ለሰዎች #መመለሻ# እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
አላህ ሰዎች እንዲጎበኙት ያዘዘው ቤት የራሱ ጥንታዊ ቤት ነው፦
22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ #ቤቴንም#፣ ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ።
2:125 #ቤቴን# ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
22:29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ #በጥንታዊው #ቤት# ይዙሩ ።
3:96-97 ለሰዎች #መጀመሪያ የተኖረዉ #ቤት# ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ #በበካህ ያለው ነው፡፡ በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ #ቤቱን# መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡
አላህ በነቢያችን ያዘዘው ጉብኝት የጥንቱን ትዕዛዝ ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፦
3:97ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጐብኘት حِجُّ ግዴታ አለባቸዉ፤ የካደም ሰዉ አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነዉ።
ሃጅ ምንጩ መለኮታዊ እንጂ ፓጋናዊ እንደሆነ የሚያሳይ የቁርአን፣ የሃዲስ፣ የታሪክ መረጃ የለም፣ ለመሆኑ የአረቦችስ ታሪክ ከኢስላማዊ ምንጭ ሌላ ኖሮስ ነው እንዴ ለመተቸት የተበቃው? ሙሽሪኮች የጥንቱን ነብይ የኢብራሂምን አምልኮ ከጣኦት ጋር ቀላቅለው ማምለክ መጀመራቸውን የሚተርከው ኢስላማዊ ምንጭ ነው፣ መመዘንም ያለበት በዚሁ ምንጭ ነው፣ እስቲ የሚተቹትን የሃጅ ስርዓቶች እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
ጠዋፍ
ጠዋፍ طواف, የሚለው ቃል ጣፈ طَافَ *ዞረ* ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን *መዞር* ማለት ነው፣ ይህንንም ያዘዘው አምላካችን አላህ ለጥንቱ ነብይ ለኢብራሂም ነው
22:26-27 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም፣ ለሚዞሩት لِلطَّائِفِينَ እና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ባልነው ጊዜ አስታውስ።
2:125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹ لِلطَّائِفِينَ እና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡
22:27-29 አልነውም፦ በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ፤ ……ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት ይዙሩوَلْيَطَّوَّفُوا ።
ነጥብ ሁለት
ኢህራም
ኢህራም إحرام ግላዊ ፍላጎትን በመተው በኢህክላስ ወደ አላህ የመቅረብ ውሳኔና ተግባር ነው፦
2:197 ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን እንዲሠራ ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡
አሲም አነስን ስለ ሶፋና መርዋ ሲጠይቀው አነስ ከመዲና የሆነ ሰሃቢይ ስለሆነ ግንዛቤው ስላልነበረውን እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡሃሪ ቅጽ2 መጽሃፍ 26 ቁጥር 710
حَدَّثَنَا مُحَمَّدُ بْنُ يُوسُفَ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، عَنْ عَاصِمِ بْنِ سُلَيْمَانَ، قَالَ سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ الصَّفَا، وَالْمَرْوَةِ،. فَقَالَ كُنَّا نَرَى أَنَّهُمَا مِنْ أَمْرِ الْجَاهِلِيَّةِ، فَلَمَّا كَانَ الإِسْلاَمُ أَمْسَكْنَا عَنْهُمَا، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى {إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ } إِلَى قَوْلِهِ {أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا}
አሲም ኢብኑ ሱለይማን እንደተረከው፦ እኔ አነስ ኢብኑ ማሊክን ስለ ሶፋና መርዋ ጠየኩት፣ እርሱም መለሰልኝ ኢስላም ከመምጣቱ በፊት በዘመነ መሃይማኑ ጊዜ የነበረ ስርአት አድርገን እናስብ ነበር፣ ግን ኢስላም በመጣ ጊዜ በዚያ መዞርን አቆምን፣ ከዚያም አላህ እንዲህ የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦
2:158 ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡
ሙሽሪኮች ሶፋና መርዋ መካከል ማናት የምትባለውን ጣኦት አስገብተው ያመልኩ ነበር፣ ይህን የተረዱት የመዲና ሰዎች ኢህራም የማናት ስም ይመስላቸው ነበር፣ ይህንን ጉዳይ እሜቴ አይሻ ሲናገሩ፦
ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 384
وَةُ قَالَتْ عَائِشَةُ نَزَلَتْ فِي الأَنْصَارِ كَانُوا هُمْ وَغَسَّانُ قَبْلَ أَنْ يُسْلِمُوا يُهِلُّونَ لِمَنَاةَ. مِثْلَهُ. وَقَالَ مَعْمَرٌ عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ عُرْوَةَ عَنْ عَائِشَةَ كَانَ رِجَالٌ مِنَ الأَنْصَارِ مِمَّنْ كَانَ يُهِلُّ لِمَنَاةَ ـ وَمَنَاةُ صَنَمٌ بَيْنَ مَكَّةَ وَالْمَدِينَةِ
አይሻ በመጨመር፦ ይህ አንቀጽ የወረደው ከአንሷር ጋር የሚገናኝ ነው፣ እነርሱ ወደ ኢስላም ከመግባታቸው በፊት ኢህራም የማናት ስም ነው ብለው ያስቡ ነበር።
ተቺዎች ይህንን ሃዲስ ይዘው ነው ሃጅ፣ ጠዋፍ፣ ኢህራም፣ ሶፋና መርዋ የፓጋን ነው የሚሉት፣ ጥቅሱ የሚያወራው ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፣ ለመተቸው ምንጩ ኢስላማዊ እስከሆነ ድረስ መልሱም ኢስላማዊ ምንጭ ነውና መቀበል አለባችሁ፣ ከሃጅ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚደረጉ ጠጉርና ጥፍር መቆረጥና ዕድፍን ማስወገድ ለኢብራሂም የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፦
22:29 *ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላችቸንንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ*፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት ይዙሩ።
ማጠቃለያ
ኢስላም የነቢያት ሃይማኖት ነው፣ ይህን የነቢያት አስተምሮት ሙሽሪኮች ከጊዜ በኋላ ከጣኦታት ጋር ደባልቀውታል፣ ያን ጊዜ የመሃይምነቱ ጊዜ ተጀመረ፣ የነቢያቱ አምላክ አላህ ነቢያችንን በማስነሳት የጥንቱን የኢብራሂምን አስተምህሮት አመጣ፣ ሙሽሪኮች የሚሰሩትን ነገር አላህ በቃሉ ሲናገር፦
6:136 ለአላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ድርሻን አደረጉ፡፡ በሐሳባቸውም «ይህ ለአላህ ነው፡፡ ይህም ለተጋሪዎቻችን ነው፡፡» ለተጋሪዎቻቸውም «ለጣዖታት የኾነው ነገር ወደ አላህ አይደርስም፡፡ ለአላህም የኾነው እርሱ ወደ ተጋሪዎቻቸው ይደርሳል» አሉ፡፡ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ።
አላህ የዓለማቱ ጌታ መሆኑን ቢረዱም አላህም ከፈጠረው ከአዝመራና ከግመል፣ ከከብት፣ ከፍየልም ለጣኦቶቻቸው ድርሻን አደረጉ፡፡ ይህን ያደረጉበት 360 ጣኦቶቻቸው ወደ አላህ ያቃርቡናል ብለው ነው፣ ይህን አድራጎታቸው የቂያማ ቀን ዋጋቸውን ያገኛሉ፦
39:3 እነዚያም ከርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች የያዙት ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን እንጅ ለሌላ አንግገዛቸውም፣ ይላሉ፤
19:81-82 ከአላህም ሌላ አማልክትን ለነሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲኾኑዋቸዉ ያዙ፤ ይከልከሉ መገዛታቸዉን በእርግጥ ይክዷቸዋል ፤ በነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል።
29:17 ከአላህ ሌላ የምትግገዙት ጣዖታትን ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዙዋችው ለናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፤ ተገዙትም፤ ለርሱም አመስግኑ፤ ወደርሱ ትመለሳላችሁ።
10:104 «እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
8:35 በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፤ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ ይባላሉ።
ኢማም ቡሃሪ ቅጽ 9 መጽሃፍ 83ቁጥር 21

حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي حُسَيْنٍ، حَدَّثَنَا نَافِعُ بْنُ جُبَيْرٍ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ “ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ ”

ወሰላሙ አለይኩም
✍️ ፀሐፊው ሑሴይን ከድር ሐፊዘሁላህ
ትምህርት ማለት ዕውቀትንም ሆነ ሙያን የማስተማርና የመማር ሂደት ነው።
ሥነ ንዋይ የምጣኔ ሀብት ጥናት ነው።

ትርጓሜዎች
በእንግሊዝኛ «economy» /ኢኮኖሚ/ ለ«ምጣኔ ሀብት» እራሱ ሲያመልከት፣ የምጣኔ ሀብት ጥናት ወይም «ሥነ ንዋይ» ትርጓሜ «economics» /ኤኮኖሚክስ/ ነው።

የጥናት ክፍሎች
ንግድ

ምጣኔ-ሃብታዊ መላ-ምቶች
ፍላጎትና አቅርቦት
ዋጋ
እጥረት
ከምጣኔ ሀብት አስተሳሰብ በስተጀርባ ያለው አበይት ምክኒያት 'እጥረት' ነው። የተፈጥሮ ሃብት አላቂነትና የሰው ልጅ ያልተገደበ ፈላጎት ተጣምረው ለምጣኔ ሀብት አስተሳሰብ አስፈላጊነት አስተዋጽኦ ምጣኔ ሀብት ባህሪ አበርክተዋል።
የዚህ አስተሳሰብ ፈልሳፊዎች፦

አዳም ስሚስ (ነጻ ገበያ)
ሪካርዶ (በ ሃራት መካከል ስላለው ትስስር)
ጆን ሎክ
ሚልተን ፍሪድማን ኬይንስ
ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የምጣኔ-ሃብታዊ አስተሳሰብ ዕድገት
ዘመናዊ
ስልጣኔ

ክላሲካዊ-ተሃድሶ
ድህረ-ኬንስ


=== ሌሎች አማራጮች ===
ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ ' («ዜጋ») ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣  ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ።  የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥር፣ የውሳኔ ላይ መድረስ፣ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄወች በሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰወች መካከል ሲነሱ ያንን ጥያቄ ለመፍታት በሚደረግ ሂደት፣ በዚያ ፖለቲካ አለ።  ከዚህ አንጻር በአንዳንዶች አስተሳሰብ አብዮት፣ ጦርነት፣ ማህበረሳባዊ ግጭት ፖለቲካ ሳይሆኑ የፖለቲካ  ሂደቱ ክሽፈት ናቸው። በሌሎች አስተያየት እኒህም የአጠቃላይ ሂደቱ አካል ስለሆኑ እንደ ፖለቲካ ይወሰዳሉ። 
ፖለቲካን የሚያጠናው የትምህርት አይነት የፖለቲካ ሳይንስ ወይም  የፖለቲካ ጥናት ይባላል።
ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል።  ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ-ታሪክ ይባላል። 
በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም «ቅድመ-ታሪክ» ነው። 
በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት  አጠያያቂ ተብለዋል።   ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል። 
ከግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የኩኔይፎርም ጽሑፍ መዝገቦች ከመስጴጦምያ ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የቻይና መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1200 ዓክልበ. በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1600 ዓክልበ. በፊት የነበረውንም የሥያ ሥርወ መንግስት የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ «አፈ ታሪክ» ሊባል ይችላል።

ደግሞ ይዩ
ድንጋይ ዘመን
ናስ ዘመን
የብረት ዘመን
መካከለኛ ዘመን
ዘመነ ህዳሴ
የብርሃናት ክፍለ ዘመን
የኢንዱስትሪ አብዮት
የመረጃ ኅብረተሠብ
የፈጠራዎች ታሪክ
ታሪካዊ አቆጣጠር በየክፍለዘመኑ
የታሪካዊ ዓመት በዓላት መቁጠርያ
የዓለም ታሪክ
የአፍሪቃ ታሪክ
የኢትዮጵያ ታሪክ
የአውሮጳ ታሪክ
የእስያ ታሪክ
ባሕል  ማለት የአንድ ኅብረተሰብ አኗኗር ነው።  
እንደ የሰው ልጅ ጥናት  «ባህል» የኅብረተሠቡ ቋንቋ፣ ሥነ ጥበብ፣ ሥነ ጽሑፍ፣ ሙዚቃ፣ ጭፈራ፣ ሃይማኖት፣ ቴክኖሎጂ፣ አበሳሰል፣ አለባበስ፣ ስነ ሕንጻ፣ ሕግ፣ አስተያየት፣ ፍልስፍና፣ አፈ ታሪክ እና ብዙ ሌሎች ረገዶች ያጠቅልላል። 
የባሕል ጥናት ደግሞ «ሥነ ኅብረተሰብ» ወይም «ሥነ ማኅበረሰብ» ሌላ ስሙም «ሶሲዮሎጂ» ነው።
ሙዚቃ ድምጸቱ ልዩ ዉበት ያለውና በስው ልቡና ውስጥ ሰርስሮ ሊገባ የሚችል ኃይል አለው። ሙዚቃን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዱስ ያሬድ እንደፈለሰፈው ይነገርለታል። ሙዚቃ እከሌ ፈጠረው የሚባል አይደልም በመሳሪያ ተደግፎ ወይንም በድምጥ ውስጣዊ ስሜትን መግልጫ አንጉርጉሮ ወይም ደምጥ ነው። ቅዱስ ያሬድ የቤተክርስቲያን ዜማን ይፈለሰፈ ታላቅ መንፈሳዊ አባት ነው። 

የኢትዮጵያ ሙዚቃ
የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች
ቴዲ አፍሮ
አርባ ልጆች
ሙሉቁን መለሠ ዘፈን ሠውነቷ ታሪክ
አዝማሪቤት ሙዚቃና በቪዲዮ www.AzmariBet.com Archived ማርች 8, 2009 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ሙዚቃና ቀልድ በቪዲዮ በያይነቱ እዚህ ይመልከቱ  Archived ሴፕቴምበር 28, 2006 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በያይነቱ Archived ኖቬምበር 1, 2008 at the Wayback Machine
ፊልም ተረት ለማሳየት በተንቀሳሳሽ ስዕልና በድምፅ የሚጠቀም ትርዒት ማለት ነው። ፊልሞች በተለመደ ሊታዩ የሚቻል በቴሌቪዥንም ሆነ በሲኒማ ውስጥ ነው።

ገብረ እምባየ
ሰማያዊ ፈረስ
ስፖርት ወይም አርትዖተ መሌሊት የተደራጀ እና ውድድራዊ መልክ ያለው አካላዊ ብቃትን እና ነጻ ጨዋታን (fair play) የሚጋብዝ እንቅስቃሴ ነው። የሚመራው ራሳቸውን ችለው በተቀመጡ ህጎች እና ደንቦች ነው። የተወዳዳሪው አካላዊ ጥንካሬ እና ብቃት የክንውኑን ውጠት (ማሸነፍ ወይም መሸነፍ) ይወስናሉ። አካላዊ እንቅስቃሴዎቹ የሰዎችን፣ የእንስሳቶቹን እና የመሳሪያዎቹን (መሳሪያ ስንል ኳስ፣ ጦር፣ ራኬት የመሳሰሉትን ያጠቃልላል) እንቅስቃሴ ናቸው። ነገር ግን የካርታ እና የመደብ ጨዋታዎችን የአካል ብቃት ስለማይጠይቁ የጭንቅላት ስፖርቶች ሽንላቸዋለን።
መለጠፊያ:መዋቅር-ባህል መፅሐፍት
ቴክኖሎጂ የመሳሪያዎች አጠቃቀም እውቀት ወይም ዘዴ እና ጥበብ ወይም መሳሪያዎችን (እቃዎች ወይም ልብሶች ሊሆኑ ይችላሉ) የማደራጀት እና የማምረት መንገድ ነው።

ደግሞ ይዩ
የፈጠራዎች ታሪክ
ሥልጣኔ