በባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር በውጭ አገር ሠራተኞች ላይ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለያየ ጊዜ ሪፖርቶች ይወጣሉ።
የዘንድሮውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅትን ተከትሎም በስታዲየሙ እና በሆቴሎች ግንባታ ስለተሳተፉ የውጭ አገር ሠራተኞች አያያዝ ብዙ ተጽፏል።
ይሁን እንጂ ለኳታር ገዢ ንጉሣውያን ቤተሰቦች ስለሚሰሩ የውጭ አገር የቤት ውስጥ ሠራተኞች እምብዛም አልተነገረም።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እነዚህ የቤት ውስጥ ሠራተኞች መብታቸው በወረቀት ላይ ቢሰፍርላቸውም ተግባር ላይ ግን የለም።
በኳታር ባለሥልጣን ቤት ውስጥ ተቀጥራ የምትሰራው ግላዲስ [ስሟ የተለወጠ] በቀን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5፡00 እንደምትሰራ ትናገራለች።
ቤት ታጸዳለች፤ ምግብ ታዘጋጃለች፤ ልጆችን ትጠብቃለች።
የምትመገበው የእነርሱን ትራፊ ነው። ግላዲስ እንደምትለው በእነርሱ ቤት ውስጥ መሥራት ከጀመረችበት ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር ገደማ በፊት አንስቶ የእረፍት ቀን ኖሯት አያውቅም።
በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኘው ፊሊፒናዊቷ ግላዲስ ‘ማዳም’ ስትል የምትጠራትን አሰሪዋን “እብድ ናት” ስትል ነው የምትገልጻት።
ኳታር የ2022 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን ለማዘጋጀት የተካሄደውን ውድድር ከማሸነፏ በፊት የውጭ አገር ሠራተኞች ያለ አሰሪያቸው ፈቃድ ሥራቸውን መቀየር አሊያም አገሪቷን ለቀው መውጣት አይችሉም ነበር። በእርግጥ በበርካታ የባሕረ ሰላጤው አገራት አሁንም ያው ነው።
ከዚያ በኋላ ግን ኳታር በሕጎቿ ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ ጀምራለች።
ነገር ግን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሕጎቹ ተግባራዊ ባለመሆናቸው አሁንም የቤት ውስጥ ሠራተኞች የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት ማስቆም አልቻሉም ብሏል።
የግላዲስ ቀጣሪ ከእርሱ ፈቃድ ውጪ ሥራ እንዳትቀይር፣ ከአገርም እንዳትወጣ ለማድረግ ፓስፖርቷን ይዞባታል። ቢሆንም ግን ግላዲስ አሁንም ዕድለኛ እንደሆነች ነው የምታስበው።
ምክንያቱም ቢያንስ ስልኳን እንድትይዝ ተፈቅዶላታል። ይህም ብቻ ሳይሆን እንደ በርካታ ስደተኛ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ድብደባ እና አካላዊ ጥቃት አልደረሰባትም።
ግላዲስ አሁን ባለችበት ሥራ ላይ መቆየት የምትፈልግበትም ሌላም ምክንያት አላት። እርሷ ባለችበት ዕድሜ ከዚህ የተሻለ ሥራ አላገኝም ብላ ታስባለች።
አሁን በወር 1 ሺህ 500 ሪያል [412 ዶላር] ታገኛለች። በመሆኑም የምታገኘውን ሁሉ ቤተሰቧን ለመደገፍ ወደ አገሯ መላክ ትችላለች።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ከአገራቸው ወጥተው የሚሰሩ ፊሊፒናውያንን የሚረዳው ማይግራንት ኢንተርናሽናል የተሰኘው ድርጅት ባልደረባ ጆዋና ኮንሴፕሽን፣ በርካታ የውጭ አገር ሠራተኞች ያሉበትን የሥራ ሁኔታ አይናገሩም ትላለች።
ምክንያቱ ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው የሚልኩትን ገንዘብ ማግኘት የማይደራደሩበትና ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ በመሆኑ ነው።
በባሕረ ሰላጤው አገራት የሚኖሩት ግን በነጻነት ለማውራት በራስ መተማመን አላቸው ትላለች። ብዙ ጊዜም የሚደርስባቸውን የከፋ ጥቃት ይናገራሉ።
አንዲት ሴት አሰሪዋ ጭንቅላቷን ይዞ ሽንት ቤት ውስጥ እንደሚዘቀዝቃት እና ሲናደድ ምግብ እና ውሃ እንደሚከለክላት ተናግራለች።
በአንጻሩ በንጉሣውያኑ የአል ታኒ ቤተሰብ የተቀጠረች ሠራተኛ ግን በተሻለ ሁኔታ እንደሚይዟት ተናግራለች። ነገር ግን በአዲሱ ሕግ መሠረት ሁሉም ሠራተኞች የእረፍት ቀን ሊኖራቸው ቢገባም እርሷ ግን እረፍት የላትም።
አልቲያ [ስሟ የተለወጠ] ከቢቢሲ ጋር በቪዲዮ ቃለ ምልልስ ያደረገችው በንጉሣውያኑ ቤተሰብ መኖሪያ ምድር ቤት ውስጥ ሆና ነበር።
አልቲያ አገሯ ፊሊፒንስ ውስጥ ይኑረኝ ብትል እንኳን መግዛት የማትችለውን አይፎን ስልክ፣ ልብሶች፣ ጌጣ ጌጦች እና በየዓይነት ጫማዎች አሰሪዎቿ እንደሰጧት ታስረዳለች።
ግላዲስ ግን ስደት ያስመረጣትን እና ለመኖር የሚያስፈልጋትን ክፍያ እንኳን በቅጡ አታገኝም።
አልቲያ በምትሰራበት ቤት ሌሎች ፊሊፒናውያን የቤት ሠራተኞችም አሉ።
የራሳቸው መኝታ ክፍል እና የጋራ ማብሰያ ክፍል አላቸው። ይህ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ምክንያቱም አልቲያ በቲክቶክ እና በፌስቡክ የምታያቸው ሠራተኞች ምግብ ለማግኘት ሲለምኑ አሊያም የሆነ አካል ነፍሳቸውን እንዲታደግላቸው ሲማጸኑ ነው። የእርሷን ያህል ዕድለኛ አይደሉም።
“ሁልጊዜ እነዚህን ቪዲዮዎች አያለሁ። ለዚህም ነው እኔ ዕድለኛ እንደሆንኩ የሚሰማኝ። ለእኔ እያንዳንዱ ቀን ተረት ነው የሚመስለኝ” ትላለች።
ቢሆንም ግን ከፍ ያለ ጣሪያ ባላቸው፣ በወርቅ በተለበጡ ጥንታዊ እቃዎች፣ በእንቁ ያሸበረቁ ትላልቅ ጠረጴዛዎች እና በትኩስ አበቦች የተዋቡ በተረት እንደምታውቀው እና “የሲንደሬላ ቤተ መንግሥት” ስትል በገለጸችው ቤት ውስጥ መሥራት ከባድ ነው ትላለች።
ቀኗን የምትጀምረው ከማለዳው 12፡30 ነው። ቁርስ ማዘጋጀት የሚጀምሩት በዚያ ሰዓት ነው። አልቲያ ምግብ የምትበላው ቤተሰቡ በሙሉ ተመግበው ከጨረሱ በኋላ ነው።
ተመግበው ከጨረሱ በኋላ እቃውን አነሳስተው ክፍሉን ያጸዳሉ። ከዚያም እንደገና ቦታውን ለምሳ ያዘጋጃሉ።
“ሠራተኞቹ ብዙ ስለሆንን ሥራው ቀላል ነው” ትላለች።
ከዚያም ሠራተኞቹ ከቀኑ 9፡00 እስከ አመሻሽ 12፡00 ድረስ እረፍት ይወስዳሉ።
ከዚያም እራት ያዘጋጃሉ። እራት ተበልቶ ሲጠናቀቅ የአልቲያም ሥራም በዚሁ ያበቃል። ነጻ ትሆናለች። ንጉሣውያን ቤተሰቡ ፓስፖርቷን ስላልያዙባት ካሰኛት ከግቢው መውጣትም ትችላለች።
ይሁን እንጂ አልቲያ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን ጨምሮ ሁሉንም ቀናት የምታሳልፈው በሥራ ነው። የኳታር ሕግ የሚፈቅደውን የእረፍት  ቀን አታገኝም። ይህ ቤተሰቦቿን ለገንዘብ ለመደገፍ የምትከፍለው ዋጋ ነው።
ፊሊፒናውያን የቤት ሠራተኞችን ከባሕረ ሰላጤው አገራት ንጉሣውያን ቤተሰቦች እና ቱጃሮች ጋር የሚያገናኘው እና ፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ የሚገኘው ቀጣሪ ድርጅት ውስጥ የምትሰራው ሜሪ ግሬስ ሞራሌስ “ቤተ መንግሥት ውስጥ መስራት የሚያስቀና ሥራ ነው” ትላለች።
ሜሪ የቤት ሠራተኞች በቤት ውስጥ ስለሚገጥማቸው ፈተና በጽሁፍ ሃሳቧን ስታጋራ “ቤተሰቡ ለጋስ ነው፤ ሴቶቹ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ ሲቆዩ ይወፍራሉ። ጥሩ ነው የሚመግቧቸው” ትላለች። ነገር ግን ንጉሣውያኑ ጥቂት ውስን የሆኑ መስፈርቶች እንዳላቸው ትናገራለች።
ለኳታር ንጉሣውያን ቤተሰብ የሚላኩ ሠራተኞች “ዕድሜያቸው ከ24 እስከ 35 ዓመት መሆን እንዲሁም ቆንጆ መሆን አለባቸው” ትላለች።
በበርካታ አገራት በመልክ ሰዎችን መቅጠር ግን ሕግ ወጥ ነው።
ማይግራንት ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ባልደረባዋ ጆዋና ኮንሴፕሽን በበኩሏ አልቲያ የተናገረችው እውነት እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ትላለች።
“ነገር ግን ኳታር ውስጥ ሆና ለእንዲህ ዓይነት ንጉሣውያን ቤተሰብ ስትሰራ የምትኖረውን ሕይወት በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም” ብላለች።
ምክንያቱም አንዳንድ ንጉሳውያን ቤተሰብ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሠራተኞች አገሩን ለቀው ከወጡ በኋላ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።
እንደ አውሮፓውያኑ 2019 የግል ጠባቂ፣ አሠልጣኝ እና የግል አስተማሪ ሆነው የሚሠሩ ሦስት እንግሊዛውያን እና አሜሪካውያን ሠራተኞች የኢምሩን እህት ሼይክሃ አል ማያሳ ቢንት ሃማድ ቢን ካሊፋ አልታኒን እና ባለቤቷን ያለክፍያ ከሥራ ሰዓት ውጪ አሰርተውናል በሚል ኒው ዮርክ ውስጥ ክስ መስርተውባቸዋል።
የዓለም አቀፍ ሠራተኞች ድርጅት (አይኤልኦ) የአረብ አገራት ቀጠና ዳይሬክተር ሩባ ጃራዳት “ጥቃት እና ትንኮሳን የተመለከቱ ጉዳዮችን፣ የሥራ ደኅንነት እና የጤና እጦትን ማሳወቅ እንዲሁም መፍትሔ መስጠት ፈታኝ ነው” ይላሉ።
ድርጅቱ እንደሚለው ይህ አሁንም ፈታኝ ሆኖ የሚቀጥል ቢሆንም፣ ዝቅተኛ የክፍያ መጠንን፣ በሳምንት አንድ የእረፍት ቀን፣ የህመም እረፍት እና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲኖር የሚያረጋግጡትን አዲስ ሕጎች ተግባራዊ ለማድረግ ከኳታር ጋር እየሰራሁ ነው ብሏል።
በንጉሣውያኑ ቤተ መንግሥት የምትሰራው አልቲያ ረዥም ሰዓት በሥራ ብታሳልፍም በሥራዋ ግን ደስተኛ ናት ወደ መኝታዋ ከሄደች በኋላ ቤተሰቦቿን ታወራለች።
አገሯ ይናፍቃታል፤ ምክንያቱም ተረት የሚመስለው ቤተ መንግሥት የእርሷ አይደለም። ቢሆንም ወሳኝ የገቢ ምንጯ ነው። “ከዚህ ሥራ ውጪ ቤተሰቦቼን የምረዳበት ሌላ ሥራ የለኝም” ትላለች።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ የኳታር ንጉሣውያን ቤተሰብ እና በለንደን የሚገኘው ኳታር ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ፍልስጤማዊው ቡድን ሐማስ እስራኤል በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አምስት አባላቱን መገደላቸውን ቢያምንም፣ ከእስራኤል ጋር በሚደረገው ድርድር ተሳታፊ የሆኑት የቡድኑ ተወካዮችን ለመግደል የተደረገው ሙከራ ግን "ከሽፏል" ብሏል።
ሐማስ አክሎም እስራኤል ዶሃ የሚገኙትን የቡድኑን ተደራዳሪ ልዑካንን ለመግደል ድንገተኛ የአየር ጥቃት የሰነዘረችበት ተደራዳሪ ቡድኑ በቅርቡ አሜሪካ በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ባቀረበችው ሃሳብ ላይ ለመወያየት በተገናኘበት ጊዜ ነው ብሏል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኳታር የመኖሪያ ሕንጻ ላይ የተፈጸመው ጥቃት "ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያለው ነው" በማለት በጋዛ ጦርነት የቀሰቀሰውን የመስከረም 26/2016 ዓ.ም. ጥቃትን ያቀናበሩ እና የመሩ የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።
ኳታር በግዛቷ ውስጥ በእስራኤል የተፈጸመውን ጥቃት "የፈሪ ዱላ" እና "ዓለም አቀፍ ሕግን በግልጽ የጣሰ" በማለት አውግዛዋለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው የሐማስ መሪዎች ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት ባሉት ሳምንታት ውስጥ ግልጽ ያልሆነ፣ ነገር ግን ከባድ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸው ነበር።
ጋዜጣው "የግብፅ እና የቱርክ ባለሥልጣናት 'ስብሰባ በምታደርጉበት ስፍራ ያለውን የደኅንነት ጥበቃ አጠናክሩ' ብለው ነግረዋቸዋል" ሲል ዘግቧል።
እስራኤል ኳታር ውስጥ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፈጸመችው ጥቃት የኳታር የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን እና የመቁስል ጉዳት መድረሱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
ሐማስ በበኩሉ በጥቃቱ ተገድለዋል ያላቸውን ስድስት ሰዎች በስም ዘርዝሮ አሳውቋል። አምስቱ የቡድኑ አባል መሆናቸውን እና ስድስተኛው የኳታር የአገር ውስጥ ደኅንነት አባል መሆኑንም ጨምሮ አመልክቷል።
ጥቃቱን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል የአየር ጥቃት "ደስተኛ አይደለሁም" ሲሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ አሳውቀዋል። "ታጋቾች እንዲለቀቁ እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ዛሬ በሆነው ነገር [ኳታር ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት] ደስተኛ አይደለንም" ብለዋል።
አሜሪካ የእስራኤል የቅርብ አጋር ብትሆንም፣ ኳታርም በበኩሏ በባሕረ ሰላጤው አካባቢ የአሜሪካ ዋነኛዋ ወዳጅ ናት። በግዛቷ ውስጥም ግዙፍ የአሜሪካ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ይገኛል።
በተጨማሪ ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ኳታር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የሚካሄደውን ቀጥተኛ ያልሆነ ድርድር ከግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር በመሆን የምትመራው ኳታር ናት።
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ ማክሰኞ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው።
ከሰዓት በኋላ በተፈጸመው ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል።
ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።
የእስራኤል ጦር ኃይል እና የአገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት የሆነው ሽን ቤት "በሐማስ አመራሮችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት" መፈጻማቸውን የሚገልጽ መግለጫ አውጥተዋል።
በመከተል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትዝ ኢየሩሳሌም ውስጥ ፍልስጤማዊ ታጣቂዎች ስድስት ሰዎች የገደሉበትን የሰኞ ዕለት ጥቃትን እና ጋዛ ውስጥ አራት የእስራኤል ወታዳሮች መገደላቸውን ተከትሎ ዶሃ ውስጥ ለሚፈጸመው ጥቃት ትዕዛዝ መሰጠቱን ገልጸዋል።
የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ኳታር ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት 15 ተዋጊ አውሮፕላኖች የተሳተፉ ሲሆን፣ ዒላማ በተደረገው ቤት ላይ በሰከንዶች ውስጥ 10 ሚሳዔሎችን ተኩሰዋል።
አንድ የእስራኤል ባለሥልጣን በጥቃቱ ዒላማ ከተደረጉት የሐማስ መሪዎች መካከል ከእስራኤል ጋር በሚደረጉት ድርድሮች ቡድኑን በመወከል ዋነኛ ተደራዳሪ የሆኑት ኻሊል አል-ሃያ እና ዛሂር ጃባሪን ይገኙበት ነበር ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት, US Department of Defense
ሐማስ በአባላቱ ላይ ኳታር ውስጥ የተፈጸመውን ጥቃት ባወጣው መግለጫ "ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል፣ ጠብ ጫሪነት እና የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት" በማለት አጥብቆ አውግዞታል።
በተጨማሪም እስራኤል ተደራዳሪዎቹን ዒላማ ማድረጓ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት የቀረበውን አዲስ የስምምነት ሃሳብ ኔታኒያሁ እና መንግሥታቸው ለመቀበል ፍላጎት እንደሌላቸው ያሳየ ነው በማለት "ጠላታችን [እስራኤል] የተደራዳሪ ልዑካኖቻችንን ለመግደል ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል" በማለት በጥቃቱ አመራሮቹ አለመገደላቸውን አረጋግጧል።
ሐማስ ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረገው ኃላፊነቱን የወሰደችው እስራኤልን ብቻ ሳይሆን፣ ለእስራኤል ሠራዊት ድጋፍ ያደርጋል ያለውን የአሜሪካ መንግሥትን ጭምር ነው።
እስራኤል ጥቃቱን ከመፈጸሟ በፊት ለአሜሪካ ጦር ሠራዊት ማሳወቋን የገለጸው የፕሬዝዳንት ትራምፕ ጽህፈት ቤት በኳታር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተቃውሞታል።
የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ካሮላይን ሌቬት "የአሜሪካ የቅርብ አጋር በሆነችው፣ ሉዓላዊቷ እና ሰላም ለማምጣት እየጣረች ባላችው ኳታር ላይ የተፈጸመው ጥቃት የእስራኤልንም ሆነ የአሜሪካንን ዓላማ አያሳካም" በማለት ተናገራለች።
ጨምራም "ነገር ግን በጋዛ ሕዝብ ስቃይ እየቆመሩ ያሉትን የሐማስ አመራሮች መደምሰስ የሚደነቅ ግብ ነው" በማለት እስራኤል ሐማስ መሪዎች ላይ የምትወስደውን እርምጃ አሜሪካ እንደምትደግፈው ገልጻለች።
አሜሪካ ከእስራኤል ጥቃት በኋላ ጉዳዩን ለኳታር ብታስታውቅም አገሪቱ በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ ጥቃት በመሆኑ ቁጣዋን ገልጻለች። ፕሬዝዳንት ትራምፕም ከኳታር ኢሚር እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረጉት ውይይት ተመሳሳይ ጥቃት እንደማይፈጸም አረጋግጠውላቸዋል።
የኳታር መንግሥት ጥቃቱን "የወንጀል ድርጊት" በማለት ግልጽ የዓለም አቀፍ ሕግ እና ደንብ ጥሰት እንደሆነ እና በኳታር ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች "ከባድ ስጋት" ነው ሲል በጽኑ አውግዞታል።
የአረብ አገራት በእስራኤል ላይ ተቃውሞ ማሰማት የጀመሩት ጥቃቱ መፈጸሙን ተከትሎ ነው። በዚህም ዮርዳኖስ፣ ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምርትስ ጥቃቱን "ጠብ አጫሪነት" እና "ጭካኔ የተሞላበት የእስራኤል ጥቃት" ሲሉ አውግዘውታል።
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ይገኙበታል።
ከጥቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢስራኤል ካትዝ ሐማስ ታጋቾችን ለቅቆ ትጥቅ ካልፈታ በውጭ አገራት የሚገኙት መሪዎቹ "እንደሚደመሰሱ" እና ጋዛ "እንደምትወድም" አስጠንቅቀው ነበር።
ከዚህ ቀደም ብሎ ሐማስ የተኩስ አቁም ስለማድረግ እና ታጋቾች መለቀቅን በተመለከተ በአሜሪካ በቀረበው የስምምነት ሰነድ ላይ ከአደራዳሪዎች ጋር ግንኙነት እያደረገ መሆኑን አሳውቆ ነበር።
ትራምፕ ምንም ዓይነት ዝርዝር ሳይሰጡ እስራኤል የቀረበውን የስምምነት ሃሳብ እንደተቀበለችው አመልክተው ሐማስም እንዲስማማ "የመጨረሻ" ያሉትን "ማስጠንቀቂያ" ሰጥተው ነበር። ነገር ግን የትራምፕ ማስጠንቀቂያ እስራኤል ኳታር ውስጥ ከፈጸመችው ጥቃት ጋር እንደማይያያዝ የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስተባብለዋል።
የፍልስጤም ባለሥልጣናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአሜሪካ የቀረበው ስምምነት ሐማስ ሁሉንም ታጋቾች በ48 ሰዓትት እንዲለቅ፣  የ60 ቀናት ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ በእስራኤል እስር ቤቶች የሚገኙ ፍልስጤማውያን እንዲለቀቁ እና የዘላቂ ተኩስ አቁም ድርድር እንዲካሄድ ያቀደ ነበር።
በድርድር በጋዛ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት እንዲያበቃ ከማድረግ ይልቅ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሌላ መንገድን መርጠዋል። በኳታር ውስጥ ጥቃተ ከተፈጸመ በኋላ ምሽት ኢየሩሳሌመ ወስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለተሰበሰቡ ሰዎቸ ኔታኒያሁ ባደረጉት ንግግር አገራቸው ኳታር ላይ የወሰደችው እርምጃ "ጦርነቱን ለማብቃት አዲስ በር" ሊከፍት ይችላል ብለው ነበር።
እስራኤል መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ የፈጸመባትን ጥቃት ተከትሎ በከፈተችው ዘመቻ ጋዛ ውስጥ ካለቁት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ባሻገር በርካታ የቡድኑ ቁልፍ መሪዎችን በተለያዩ ቦታዎች ገድላለች።
ባለፈው ማክሰኞ ኳታር ዶሃ ውስጥ የተፈጸመው ያልተጠበቀ ግልጽ የአየር ጥቃትም የዚሁ አካል ሲሆን፣ ከቀደሙት ግን በእጅጉ የተለየ እና እስራኤል ላይ ከፍተኛ ውግዘትን ያስከተለ ነው።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
በ2016 ዓ.ም. ሐምሌ ወር በኢራን ፕሬዝዳንት ሲመተ በዓል ላይ ተገኝተው የነበሩት የሐማስ ፖለቲካዊ መሪ ኢስማኤል ሃኒዬ አርፈውበት በነበረበት ክፍል ውስጥ በፍንዳታ መገደላቸው ይታወሳል። ግድያው በእስራኤል የተፈጸመ መሆኑን ብዙዎች ቢናገሩም እስራኤል ግን የሰጠችው ማረጋገጫ የለም።
ሐማስ በአስራኤል ላይ የፈጸመው ከባድ ጥቃት አስተባባሪ እና መሪ እንደሆነ የሚታመነው ኢስማኤል ሃንዬን የተካው ያህያ ሲንዋርም ከጥቂት ወራት በኋላ ጋዛ ውስጥ ተገድሏል።
ከጋዛ ውጪ ቁልፍ የሐማስ አመራሮች የሚገኙት ኳታር ውስጥ ሲሆን፣ ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ድርድርንም የሚመሩት እነዚሁ የቡድኑ መሪዎች ናቸው።
ሁለት ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የመጨረሻ የተባለው የስምምነት ሃሳብ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቀረበ በኋላ ፍሬ አፍርቶ ታጋቾች የሚለቀቁበት፣ በመከራ ውስጥ የሚገኙት የጋዛ ነዋሪዎች እፎይታ እና እርዳታ የሚያገኙበት ዕድል ሊፈጠር ይችላል ተብሎ ሲጠበቅ እስራኤል ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት ምናልባትም ለጊዜው አጨነገፈው።
እስራኤልም፣ ሐማስም እንዳሉት ጥቃቱ በዶሃ የሚገኙትን የሐማስ ከፍተኛ አመራሮች እና ተደራዳሪዎች ለመግደል የታለመ ነበር። እስራኤል ጥቃቱ ስላለስገኘው ውጤት ያለችው ነገር ባይኖርም፤ ሐማስ ግን አመራሮቹ ከእስራኤል የሞት ወጥመድ አምልጠዋል ሲል አስታውቋል።
አሁን ዋናው ጥያቄ በገቡበት እና በወጡበት በእስራኤል የሞት ጥላ ውስጥ የሚገኙት የሐማስ መሪዎች ድርድሩን እርግፍ አድርገው ይተዉታል? ወይስ በእስራኤል እየታዳኑም ቢሆን በደርድሩ ይቀጥላሉ? የሚለው ነው።
እስራኤል ግን ለተፈጸመባት ጥቃት ተጠያቂ ናቸው ያለቻቸውን የሐማስ መሪዎች ከያሉበት እያደነች እንደምትቀጣቸው በግልጽ እና በተደጋጋሚ እየገለጸች መሆኑ ጥቃቱ ቀጣይ መሆኑን ያመለክታል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
"ላያ 'መስማት እንደማትችል' ዶክተሩ ነግሮናል፤ እና ሁሉም ነገር ባለበት የቆመ፣ ጊዜ እና ቦታ የሚባለው ስሜት የጠፋ ያህል ነው የተሰማኝ።"
ይህ ፓብሎ ጋሪጎስ እና አልሙዴና ቬላስኮ ልጃቸው ላያ ከተወለደች ገና ጥቂት ወራት እንዳስቆጠረች የሰሙት አስደንጋጭ ዜና ነበር።
በወቅቱ "በድንጋጤ ደርቀው ቀርተው" እንደነበር ይናገራሉ። ነገር ግን ተጨማሪ አስደንጋጭ ዜና እንደሚመጣ አልጠበቁም።
ላያ መስማት የተሳናት ብቻ ሳትሆን የዕድገት ውስንነትም ነበረባት። ይህንን በሚሰሙበት ወቅት አንገቷ እንኳን ፀንቶ ጭንቅላቷን መሸከም በማይችልበት፣ ራሷን ችላ በማትገለበጥበት ዕድሜ ላይ ነበረች።
ከበርካታ ዙር ምርመራዎቸ በኋላ፣ ላያ በጣም አልፎ አልፎ በሚከሰት፣ ከ10,000 ሰዎች ውስጥ ከ50 በታች የሚሆኑትን በሚያጠቃ ሕመም መያዟ ታወቀ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 7,000 የሚጠጉ የታወቁ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ በሽታዎች አሉ።
ሌሎች 2,000 በሽታዎች ደግሞ ገና ተጠንተው መሰነድ እንደሚኖርባቸው የስፔን እምብዛም የማይታወቁ ሕመሞች ፌደሬሽን (FEDER) አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታማሚዎች ለምርመራ በአማካይ አምስት ዓመት እንደሚጠብቁ ዓለም አቀፉ እምብዛም የማይታወቁ በሽታዎች የሚጠቁ ሕጻናት ምርመራ ኮሚሽን ገልጿል።
የላያ ፈጣን ምርመራ ያልተለመደ ነው። ወላጆቿ ነገሩን በመልካም ዕድል ከጥሩ ዶክተሮች ጋር የተገናኘ መሆኑን ይናገራሉ።
ይህ ቢሆንም እምብዛም ላልተለመደ ሕመም ስም ማውጣት ብዙ ጊዜ ፈውስ ወይም ሕክምናን ለማግኘት ማረጋገጫ አይሆንም።
ምክንያቱም በእነዚህ ሕመሞች ላይ ብዙም ምርምር አልተደረገም።
ብዙ ጊዜ ሁኔታው በቤተሰቦች እጅ ላይ ይወድቃል። ለቁጥር የሚታክቱ ኢሜሎችን መጻጻፍ፣ የገንዘብ ድጋፍ መፈለግ፣ እንዲሁም እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን ማሳለፍ የቤተሰቡ ዕጣ ፈንታ ይሆናል።
ከስፔን የመጡት ጥንዶች መደበኛ እርግዝና እንዲሁም የቅድመ ወሊድ ክትትል እንደነበራቸው ይናገራሉ።
በሚኖሩበት ቤልጅየም ጤናማ የወሊድ ጊዜም አሳልፈዋል።
ነገር ግን ለጨቅላ ሕፃናት በመደበኛ ሆስፒታል በሚደረገው አጠቃላይ ምርመራዎች ወቅት ላያ የመስማት ምርመራ ሲደረግላት ምንም ምላሽ አልሰጠችም።
በድጋሚ ይህንን ምርመራ ካደረጉ በኋላ ተመሳሳይ ውጤት በመገኘቱ ላያ ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት እንዲያያት ተላከች።
በቀጠሯቸው መሠረት ወደ ሕጻናት ሐኪም ዘንድ ሲሄዱ ዶክተሩ ልጃቸው ላይ ያለውን የጤና እክል አስረዳቸው።
ዶክተሩ የምርመራውን ውጤት እያነበበ ላያ መስማት እንደማትችል ገለፀ።
"መረጃዎች ማግኘት ፈልገን ነበር። በቤልጂየም ከሚገኙ ማኅበራት ጋር አገናኙን። አቅጣጫ በመጠቆም ብዙ አግዘውናል። ብዙ ቤተሰቦችን አግኝተናል፤ እና ስለ ጆሮ ማዳመጫ (cochlear) እና ንቅለ ተከላዎች ነገሩን" ትላለች አልሙዴና።
ፓብሎ በዚህ ወቅት ነገሮች የበለጠ ብሩህ ይመስሉ ነበር።
"መስማት የተሳናቸው እና የሚማሩ፣ ዩኒቨርሲቲ የገቡ፣ የሚያዳምጡ፣ የምልክት ቋንቋ የሚማሩ ልጆችን አይተናል፤ የሚገርም ነበር" ይላል።
ጥንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሕፃናት ሐኪም ዘንድ የሄዱት ላያ ጡት ለመጥባት በመቸገሯ እና ጭንቅላቷን ከፍ ለማድረግ ወይም ለመገላበጥ ጥንካሬ በማጣቷ ነበር።
በመጀመሪያ ዶክተሮች እነዚህ ችግሮች ከመስማት አለመቻል ጋር የተያያዙ የጡንቻ አለመታዘዝ ወይንም መስነፍ (hypotonia) ጋር አያይዘውት ነበር።
ስለዚህ የፊዚዮቴራፒ ሕክምና እንድታገኝ ምክር ሰጡ።
ይህም ባለመሥራቱ ጥንዶቹ የራሳቸውን ጥናት ማድረግ ጀመሩ።
አንድ የሕፃናት የነርቭ ሐኪም በቫይረሶችን እና በዘር ከሚመጡ በሽታዎች ጋር ያለውን ዝምድና ለመመልከት የተለያዩ ምርመራዎችን አደረጉ።
በመጨረሻ የደረሱበት መደምደሚያ ኬኤአርኤስ1 (KARS1) ሲንድሮም የተባለ እጅግ አልፎ አልፎ የሚከሰት በሽታ እንዳለባት ነበር።
ኬኤአርኤስ1 (KARS1) ሲንድሮም በዘረ መል ውስጥ ኤኤአርኤስ1 ያለ ጉድለት ሲሆን፣ ይህም ማለት ሴሎች በቂ ኃይል አያመነጩም፤ ይህም እንደ አንጎል፣ ዓይኖች እና ጉበት ያሉ የአካል ክፍሎች እና የነርቭ ሥርዓቶችን ይጎዳል።
ምልክቶቹ የተለያዩ ቢሆንም በጣም የተለመዱት ሴሬብራል ፓልሲ፣ የመስማት ችግር፣ የዕይታ እክል፣ የሚጥል በሽታ እና የንግግር መዘግየት ናቸው።
እክሎቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ የሚሄዱ መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ያብራራሉ።
ፓብሎ ስለ ሴት ልጁ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሲያስብ የሚያየው ብሩህ ነገር ማጣቱን ይናገራል።
"የት እንደምትወስዳት፣ ምን እንደምታስተምር ታቅዳለህ፤ ነገር ግን [በዚያን ጊዜ] ሁሉም ነገር እንደጠፋብኝ አስታውሳለሁ። ከሕመሙ ብዛት የተነሳ ፍላጎቴን አጣሁ።"
"በእርግጥ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በሕይወት ምን ያህል እንደምትቆይ ጠየቅኩኝ። ምን ሊፈጠር እንደሚችል ጠየቅሁ፤ ነገር ግን ዶክተሩ ለመናገር አልደፈረም።"
ባል እና ሚስቱ በስፔን ውስጥ ተጨማሪ የባለሙያ አስተያየት የጠየቁ ቢሆምንም መደምደሚያው ግን ተመሳሳይ ነበር።
የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ መስማት የተሳናቸው ሕጻናት ማኅበር ከ30 በመቶ እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት መስማት የተሳናቸው ሕጻናት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ተጨማሪ የአካል ጉዳት አለባቸው ይላል።
ይህ ማለት ወላጆቿ ክብደት እንድትጨምር እና ዕድገቷን ለመቀጠል እንድትችል በቂ አቅም እንዳላት ማረጋገጥ አለባቸው።
ለሁለት ሰዓታት በቆየው የቪዲዮ ቃለ ምልልሳችን ወቅት ጥንዶቹ ላያይን ያለማቋረጥ ይከታተሉ እና እሷን ለማየት ደጋግመው ይነሱ ነበር።
"አድጋለች" ይላሉ፤ ግን በሽታውም አብሮ እያደገ ነው።
ጥንዶቹ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ፍለጋ ዙሪያ ገባቸውን በሚያስሱበት ወቅት እጅግ በጣም እምብዛም የማይታወቁ የጤና እክሎች ያሉባቸው ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች የመሠረቱት የፌስቡክ ቡድን አገኙ።
ብዙ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ሲያገላብጡም በኬኤአርኤስ1 (KARS1) ላይ የተደረጉ ምንም ዓይነት ልዩ ክሊኒካዊ ሙከራዎችን ማግኘት አልቻሉም።
ስለዚህ በተቻለ መጠን ብዙ የጄኔቲክስ ባለሙያዎችን ለማነጋገር ወሰኑ።
"እነሱ [የጄኔቲክስ ተመራማሪዎች] ወላጆች እንደሚፈሩ እና ግራ እንደሚጋቡ ያውቃሉ። ስለዚህ በግልጽ ያዋሯቸዋል። ስለዚህ ስለ በሽታው፣ ለምን ላያይ እንደተያዘች መሠረታዊ ነገሮችን ነግረውናል" በማለት ፓብሎ ያስረዳል።
በመጨረሻም በስፔን የሚገኘው ካርሎስ ሳልሳዊ የጤና ተቋም ውስጥ እምብዛም በማይታወቁ በሽታዎች ላይ በሚመራመረው ተቋም ውስጥ የሚሠሩትን የዘረ መል ሕክምና ኃላፊ ዶክተር ኢግናስዮ ፔሬዝ ደ ካስትሮን አገኙ።
ከእነርሱ ጋር ተመሳሳይ ልምድ ላላቸው ወላጆች የሚመክረውን ፋውንዴሽን እንዲቀላቀሉ ወይም የራሳቸውን እንዲመሠርቱ መሆኑን መከሯቸው።
ዶ/ር ፔሬዝ ደ ካስትሮ "ለእንዲህ ዓይነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለሚሄድ እክል ጊዜ ውድ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በኬኤአርኤስ (KARS) ስም የተቋቋመ ፋውንዴሽን ስላልነበረ ጥንዶቹ ወደ መመሥረት ገቡ።
ዶ/ር ፔሬዝ ደ ካስትሮ ለቤተ ሙከራዎች የሚያቀርቡት የምርምር ምክረ ሃሳብ በማዘጋጀት ረድቷቸዋል።
በዓለም ዙሪያ የምርምር ማዕከላትን ለመደገፍ በሚል የኪዩር ካርስ ላያ ፋውንዴሽንን (Cure KARS Laia Foundation) መሠረቱ።
ፋውንዴሽኑ የኬኤአርኤስ ሲንድሮም በሽታዎችን ለመቋቋም የሚረዱ ሕክምናዎችን ለመደገፍ ዓላማ አድርጎ የተመሠረተ ነው።
የመጀመሪያ ዓላማቸው ለአራት ዓመታት ምርምር ወደ 290 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ሲሆን፣ እስካሁን 60 ሺህ ዶላር መሰብሰብ ችለዋል።
"ላያ ከአባቷ እና ከእናቷ የዘረ መል ለውጥን በመውረስ መጥፎ ዕድል ነበራት። ሁለቱ ቅጂዎች በጋራ እንዳይሠሩ ማድረግ ይቻል ነበር" ሲሉ ዶክተር ፔሬዝ ደ ካስትሮ ሁኔታውን አብራርተዋል።
ዶክተር ፔሬዝ ደ ካስትሮ "ተግባራዊ ቅጂን ወደ ሕዋሳት መተካት እና ማስተዋወቅን" ያካተተ የዘረ መል ሕክምና መጠቀም ይቻላል ብለዋል።
ነገር ግን ልውጥ ዘረ መል የማይፈለጉ ተግባራትን ሲፈጥር ለውጡን በትጋት ማረም ያስፈልጋል ሲሉ ያስረዳሉ።
ምንም እንኳን መልካም ሁኔታዎች እና በቂ የገንዘብ ድጋፍ ቢኖርም የብዙ ዓመታት ምርምር እና የላብራቶሪ ሙከራዎችን ማድረግ ይጠይቃል።
ፓብሎ እና አልሙዴና ካለው እውነታ ጋር ተጋፍጠው እየኖሩ ነው።
ልጃቸው እንደማትድን ያውቃሉ፤ ነገር ግን መልካም ሕይወት እንድትኖር ይፈልጋሉ።
"ስለዚህ ረዥም እና አስደሳች ሕይወት ይኖራታል።"
ጥረታቸው "ሌሎች ተመሳሳይ እክል ያለባቸው ልጆች አንድ ቀን እንደ ማንኛውም ሌላ ሕመም እንዲሰማቸው" ማድረግ እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የፎቶው ባለመብት, Universal Images Group via Getty Images
ሙሴ አሥርቱ ትዕዛዛትን ተቀብሎባታል የምትባለው የሲና ተራራ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን በእስልምናም ሆነ በአይሁዳውያን እምነት ዘንድ የተቀደሰች ስፍራ ናት።
በግብፅ የምትገኘው ይህች የተቀደሰች ስፍራ በአገሬው ነዋሪ ዘንድ 'ጃባል ሙሳ' ተብላ ትጠራለች ።
ስፍራዋ አምላክ መለኮታዊ ኃይልን ገልጦ ሙሴን ያነጋገረበት እንደሆነች ይገለጻል።
ሙሴን ሲያነጋግረውም ቁጥቋጦው በእሳት ይንቦገቦግ እንደነበር በቅዱሳኑ መጻሕፍት፤ መጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርዓን ተጠቅሷል።
በርካታ ጎብኚዎች ለዓመታት ይህችን ቅዱስ ተራራ ለመጎብኘት ይተሙ ነበር።
በስፍራው ሲደርሱ የአካባቢው ጥንታዊ ማኅበረሰብ፣ ቤዶዊኖች የተራራዋን መልክዓ ምድር አስደናቂነት ያስጎበኛሉ።
ይህች በሦስቱ የአብርሃም እምነት ዘንድ ቅዱስ ተብላ በምትጠራው ስፍራ ላይ የግብፅ መንግሥት ትልቅ ቅንጡ ሪዞርት ለመገንባት እና አካባቢውን አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ዕቅድ ውዝግብ አስነስቷል።
በስፍራው በስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተገነባች የቅድስት ካትሪን ገዳም አለች።
ይህችን ገዳም የምታስተዳድረው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ናት።
የግሪክ ጫናን ተከትሎ የግብፅ ባለሥልጣናት ገዳሟን ለመዝጋት የነበራቸውን ሃሳብ በመቀልበሳቸው መነኮሳቱ በስፍራው ይቆያሉ ተብሏል።
ለረጅም ጊዜ ተገልላ የቆየችው ይህች በረሃማ ስፍራ ላይ የምትገኘው ገዳም፣ ተራራ እና ከተማን የምታቅፍ ሲሆን፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግባለች።
እናም በአሁኑ ወቅት እየተገነቡ ያሉት ቅንጡ ሆቴሎች፣ ቪላ ቤቶች እና የመገበያያ መደብሮች የታሪክ አሻራውን ሊያጠፋው ይችላል የሚል ስጋትን ጭሯል።
በተጨማሪም ጥንታዊው የቤዶዊን ማኅበረሰብ ወይም የጀበሌያ ጎሳ መገኛም ነው።
የቅድስት ካትሪን ጠባቂ የሚባሉት እነዚህ ጎሳዎች መኖሪያ ቤታቸው እንዲሁም የቱሪስት ካምፖቻቸውን በአነስተኛ ወይም ያለምንም ካሳ እንዲፈርሱ ተደርገዋል።
በተጨማሪም በስፍራው ለሚገነባው አዲስ የመኪና ማቆሚያ መቃብሮቻቸውን ቆፍረው የቤተሰቦቻቸውንና የወዳጆቻቸውን አጽሞች እንዲያወጡ ተገድደዋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ይህ ፕሮጀክት ቱሪዝምን ለማጎልበት አስፈላጊ ዘላቂ ልማት በሚል ቢቀርብም በቤዶዊን ማኅበረሰብ ላይ ሳይፈልጉ እንደተጫነባቸው ከሲና ጎሳዎች ጋር በቅርበት የሠራው ብሪታንያዊው ፀሐፊ ቤን ሆፍለር ይናገራል።
ማኅበረሰቡ ይህንን ፕሮጀክት እንደ ልማት እንደማያየው እና የእነሱን ፍላጎት መስዋዕት በማድረግ በበለጠ ለውጭ ጎብኚዎች ቅድሚያ የሰጠ ነው ሲሉ ፀሐፊው ይተቻሉ።
"በማኅበረሰቡ ዙሪያ አዲስ ዓለም እየተገነባ ነው። ከዚህ ዓለም ራሳቸውን ለማራቅ መርጠው ነው የሚኖሩት። ለዚህ ፕሮጀክት ግንባታም ፈቃዳቸውን አልሰጡም፤ ኑሯቸውንም ከስር መሠረቱ የሚቀይር ነው" ሲሉ ጸሐፊው ይወቅሳሉ።
ወደ 4 ሺህ የሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች እየመጣ ስላለው ለውጥ በቀጥታ ለመናገር ፈቃደኛ አይደሉም።
ግሪክ ከገዳሙ ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ፕሮጀክቱን በቀጥታ ከተቹት የውጭ አገራት መካከል ዋነኛዋ ሆናለች።
በዓለማችን ላይ ጥንታዊ ከሚባሉት ገዳሞች አንዷ የሆነችው ቅድስት ካትሪን በመንግሥት መሬት ላይ ነው የምትገኘው የሚል ውሳኔ የግብፅ ፍርድ ቤት ግንቦት ላይ መወሰኑን ተከትሎ በአገራቱ መካከል ውጥረት ተከስቷል።
ከአሥርት ዓመታት ውዘግብ በኋላ ገዳሟ ያረፈችበትን መሬት እንዲሁም የአርኪዮሎጂ ሃይማኖታዊ ስፍራዎችን "ብቻ ነው መጠቀም" የምትችለው ብሏል።
የግሪክ ሊቀ ጳጳስ ኢሮኒሚስ 2ኛ ይህንን ውሳኔ በፍጥነት አውግዘውታል።
"የገዳሟ ንብረት እየታገደ እንዲሁም እየተዘረፈ ነው። ይህች የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ብርሃን በአሁኑ ወቅት የኅልውና ስጋት ውስጥ ገብታለች" ብለዋል።
የቅድስት ካትሪን የረዥም ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ዳሚያኖስ ባልተለመደ መልኩ ከግሪክ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ "ውሳኔው ለቤተክርስቲያናችን ከባድ ጉዳት እንዲሁም አስነዋሪ ነው" ብለዋል።
ከገዳሟ ውዝግብ ጋር ተያይዞም ሊቀ ጳጳሱ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውም ተገልጿል።
ገዳሟን በበላይነት የሚያስተዳድረው በኢየሩሳሌም የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጽህፈት ቤት በበኩሉ ገዳሟ የጥበቃ ደብዳቤ ከነብዩ መሐመድ እንደተሰጣት አክሏል።
አወዛጋቢው የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳለ ሆኖ አገራቱ ባደረጉት የዲፕሎማሲያዊ ድርድር የቅድስት ካትሪን ገዳም የግሪክ ኦርቶዶክስ ማንነነትን በጠበቀ መልኩ እንዲሁም ቅርሷም እንዲጠበቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በጋራ ባወጡት መግለጫ አትተዋል።
ግብፅ በመንግሥት የሚደገፈውን ቱሪስቶችን ማዕከል ያደረገውን ታላቁን የለውጥ ፕሮጀክት የጀመረችው ከሦስት ዓመታት በፊት ነው።
ዕቅዱ ሆቴሎች፣  ሎጆች፣ ትልቅ የጎብኚ ማዕከል፣ በአቅራቢያው ያለውን አየር ማረፊያ ማስፋፋትን ጨምሮ በሙሴ ተራራ ላይ በገመድ ላይ የሚንሸራተት መጓጓዣ መግጠምን ያካትታል።
መንግሥት ይህንን ፕሮጀክቱን "ግብፅ ለመላው ዓለም እንዲሁም ለሁሉም ሃይማኖቶች የምታደርገው ስጦታ ነው" በሚል ነው እያስተዋወቀው ያለው።
"ፕሮጀክቱ ለጎብኚዎች ሁሉንም የቱሪዝም እና የመዝናኛ አገልግሎቶችን ያቀርባል። ቅድስት ካትሪን የምትገኝበትን ከተማም የአካባቢውን ተፈጥሮ፣ ዕይታ እና ቅርስን በመጠበቅ ልማት ማካሄድ የሚል ዕቅድ ይዟል" ሲሉ የቤቶች ጥበቃ ሚኒስትር ሸሪፍ ኤል ሸርቢኒ ባለፈው ዓመት ተናግረዋል።
በገንዘብ እጥረት ምክንያት ግንባታው ለጊዜው የቆመ ቢመስልም እስካሁን በተሠሩ የግንባታ ሥራዎች የአካባቢው ገጽታ እየተቀየረ ይገኛል።
በተለይም በገዳሟ ትይዩ ያለው የኤል ራሃ ሜዳ ተቀይሯል።
ሙሴ በሲና ተራራ ላይ እያለ ተከታዮቹ የጠበቁበት ስፍራ ነው።
ተቺዎች ደግሞ የስፍራው ልዩ ገጽታ እየተበላሸ ነው ይላሉ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የቅርስ ጥበቃ ተቋም ዩኔስኮ የስፍራውን አስደናቂ መልክዓ ምድር ሲገልጽ "በዙሪያው ወጣ ገባ ያለው ተራራማው መልክዓ ምድር ለገዳሙ አስደናቂ ዕይታን የሚፈጥር ነው" ብሏል።
"የቦታው አቀማማጥ በአንድ በኩል ተፈጥሯዊው ውበት በሌላ በኩል የሰዎች መንፈሳዊነት ተቆራኝተው አንድ ላይ የሚመጡበት ስፍራ ነው" ሲል ነው ዩኔስኮ የገለጸው።
ከሁለት ዓመት በፊት ዩኔስኮ በፕሮጀክቶቹ ላይ ያለውን ስጋት ገልጾ ግብፅ ሥራውን እንድታቆም እና ተጽዕኗቸውን ፈትሻ ለአካባቢውን ቅርስ የጥበቃ ዕቅድ እንድታወጣ ጠይቋል። ሆኖም ግብፅ ይህንን አላደረገችም።
ሐምሌ ወር ላይ የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ የቅድስት ካትሪን ገዳም ለአደጋ በተጋረጡ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት የሚጠይቅ ግልጽ ደብዳቤ አውጥቷል።
በተጨማሪም የገዳሟን ቅርስ ለመጠበቅ እና ጥንታዊ የቤተ ክርስቲያኗን ጽሑፎች ለመጠበቅ ገንዘብ የሚያሰባስበው የቅድስት ካትሪን ፋውንዴሽን የበላይ ጠባቂ ንጉሥ ቻርለስ እንዲሆኑ የዘመቻው መሪዎች ጠይቀዋቸው ነበር።
ንጉሡ ገዳሟ "ለመጪው ትውልድ መጠበቅ ያለባት ታላቅ መንፈሳዊ ሃብት ናት" ሲሉ ተናግረዋል።
የግብፅ መንግሥት የአገሪቷን ልዩ ታሪክ ያላገናዘበ ፕሮጀክት አቅዷል በሚል ሲተች ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
ነገር ግን መንግሥት እነዚህን ታላላቅ ፕሮጀክቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ማነቃቂያ አድርገው ነው የሚያያቸው።
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተዳክሞ የነበረው የግብፅ ቱሪዝም ማንሰራራት ቢችልም በጋዛ ጦርነት ምክንያት እንዲሁም በቀጣናው ባለው አለመረጋጋት እየተዳከመ መጥቷል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ መንግሥት በአውሮፓውያኑ 2028 ወደ 30 ሚሊዮን የሚደርሱ ቱሪስቶችን የማምጣት ዕቅድ አለው።
ከዚህ ቀደምም ባሉ የግብፅ መንግሥታት ታሪካዊቷን የሲና ተራራን የማልማት ሥራዎችን የቤድዊን ማኅበረሰቦችን ሳያማክሩ ተካሂደዋል።
ይህች ስፍራ በአውሮፓውያኑ 1967 በነበረው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በእስራኤል ወረራ ተይዞ ነበር። ለግብፅም የተመለሰላት በአውሮፓውያኑ 1979 ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ ነበር።
የቤድዊን ማኅበረሰብ አባላት ለዓመታት እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠርን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።
ግብፅ የቀይ ባሕር መዳረሻዎች ግንባታ በሚል ፕሮጀክቷን የጀመረችው በአውሮፓውያኑ 1980 በደቡባዊ ሲና ነው።
በርካቶች በአሁኑ ወቅት በቅድሰት ካትሪን ገዳም እየተከናወነ ያለው ቀደም ካለው ፕሮጀክት ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
"የቤድዊን ማኅበረሰብ፤ የግዛቲቷ ነዋሪዎች፣ አስጎብኚዎች፣ ሠራተኞች ነበሩ" ሲል የግብፁ ጋዜጠኛ ሞሃናድ ሳብሪ ይናገራል።
የማኅበረሰቡ አባላት "ቱሪዝም በኢንዱስትሪ መልክ ተይዞ ከአካባቢው ተገፍተው እንዲወጡ ተደርገዋል" ሲል ጋዜጠኛው ይወቅሳል።
መንግሥት በበኩሉ  ለቤድዊን ማኅበረሰቦች መኖሪያ ስፍራዎችን እያሻሻለ እንደሆነ ይናገራል።
የቅድስት ካትሪን ገዳም ባለፉት መቶ ዓመታት በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፋለች።
ለበርካታ ምዕተ ዓመታት ከዓለማዊው ሕይወት ተገልላ የነበረችው ገዳም በአሁኑ ወቅት ሁኔታዎች እየቀየሯት ይገኛሉ።
ከቀይ ባሕር ሪዞርቶች መስፋፋት ጋር ተያይዞ በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ወደ ስፍራዋ እየተመሙ ይገኛሉ።
አምላክ መለኮታዊው ኃይል ገልጦበታል የሚባለውን የተቃጠለውን ቁጥቋጦ ቅሪት እንዲሁም ጥንታዊው እና የመጀመሪያው በእጅ የተጻፈ የሚባለውን የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ የያዘውን ሙዚየም ይጎበኛሉ።
ገዳሟ እንዲሁም የስፍራው ጥልቅ ሃይማኖታዊ ፋይዳ የሚቀጥል ቢሆንም እየተካሄደ ባለው ፕሮጀክት አካባቢው እና ለዘመናት የዘለቀው የማኅበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ በማይመለስ መልኩ ተቀይሯል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
እስራኤል ከአስር ቀናት በፊት የከፈተችውን ያልተጠበቀ ጥቃት "የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር አከርካሪውን የመታ" በሚል ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም አገራቸው የከፈተችው ጥቃት ዒላማ ያደረገው የኢራን ኒውክሌር ይዞታዎችን እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል።
ኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ ፕሮግራሟ ለሰላማዊ አገልግሎት ነው ብትልም እስራኤል ግን በድብቅ የጦር መሳሪያ እያመረተች ነው በማለት ትወቅሳታለች።
የኢራን የኒውክሌር ማበልጸጊያ ጥያቄ በሆነበት በአሁኑ ወቅት እስራኤልን የተመለከተ ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም።
እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አላት የሚባለውን አታረጋግጥም ወይም አትክድም።
ሆኖም ዓለም እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳላት በሰፊው ያምናል።
ግለሰቡ ከአራት አስርታት በፊት እስራኤል በድብቅ ስታከናውነው የነበውን የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ግንባታ ለዓለም አጋልጧል።
ግለሰቡ ይህንን ሲያደርግ ያለ መስዋዕትነት አይደለም። ለሁለት አስርታት በእስር ማቅቋል።
ወቅቱ መስከረም 25/1979 ዓ.ም. የብሪታኒያው 'ዘ ሰንደይ ታይምስ ጋዜጣ "የእስራኤል የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ምሥጢር ሲጋለጥ" በሚል ርዕስ በርካቶችን ያስደመመ አንድ ዘገባ አተመ።
የዚህ ዘገባ ምንጭ እስራኤላዊው የኒውክሌር ቴክኒሻን ሞርዴካይ ቫኑኑ ነው።
ሞርዴካይ በርካቶች ይጠራጠሩ የነበረውን የእስራኤልን የኒውክሌር አቅም ከማረጋገጥ በተጨማሪም የአገሪቱ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ከታሰበው በላይ ግዙፍ እና የላቀ መሆኑን አሳየ።
ቴክኒሻኑ ከእየሩሳሌም 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በኔጌቭ በረሃ ላይ በተቋቋመው፤ በከፍተኛ ደረጃ ምሥጢራዊ በሆነው የዲሞና የኒውክሌር የምርምር ማዕከል ውስጥ ሠርቷል።
ጋዜጣው እስራኤል በዓለም ላይ ስድስተኛዋ የኒውክሌር ኃይል ባለቤት ሆናለች አለ።
እንዲሁም እስከ 200 የሚደርሱ የአውቶሚክ የጦር ማስተኮሻ እንዳላትም ዘገበ።
"ውጥረት እና በከፍተኛ ድካም ውስጥ ነበርን። አብዛኞቹ እንዲህ ዓይነት ትልቅ ዘገባ ሠርተው አያውቁም" ሲል የጋዜጣው የምርመራ ዘጋቢ ፒተር ሁናም የነበረውን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልጿል።
ዘ ሰንደይ ታይምስ ዘገባውን መስከረም 25/1979 ዓ.ም. ባተመበት በዚያችው ዕለት እስራኤላዊው የመረጃው ምንጭ ደብዛው ጠፋ።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የሰንደይ ታይምስ ጋዜጠኛ ፒተር የኒውክሌር ቴክኒሻኑን ያገኘው ከዚያ ቀደም ብሎ በነሐሴ ወር ላይ ነበር። የተገናኙትም በአውስትራሊያዋ ከተማ ሲድኒ ነው።
ፒተር ሞርዴካይን ሲያየው አካላዊ ገጽታውም ሆነ ሁኔታው እንዳስገረመው አይደብቅም።
"ሞርዴካይን በአካል ሳየው አጭር፣ በጣም ትንሽ፣ ራሰ በራ፣ በራስ መተመማን የሌለው እና አልባሌ ልብስ የለበሰ ግለሰብ ነበር። በፍጹም የኒውክሌር ሳይንቲስትነት የተላበሰ ገጽታ አልነበረውም" ይላል ጋዜጠኛው።
ቴክኒሻኑ በዲሞና ስላየው ነገር ለዓለም ይፋ ለማድረግ በተነሳበት ውሳኔው ጸንቶም ዝርዝር መረጃዎችን አጋራ።
እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን በደል እንዲሁም የኒውክሌር የጦር መሳሪያ መገንባቷ ተስፋ ያስቆረጠው ሞርዴካይ ሥራውን ለመልቀቅ የወሰነው ከዚያ ቀደም ብሎ በነበረው ዓመት ነው።
ቀጣዩ ዕቅዱም ሻንጣውን ይዞ ወደ እስያን መዞር ነበር።
ሆኖም ሥራውን ከመልቀቁ በፊት ወደ ኒውክሌር ጣቢያው አምርቶ በሁለት ጥቅል ፊልሞች ፎቶዎችን አነሳ።
ይህም ብቻ አይደለም ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ የሚውሉ ራዲዮ አክቲቭ ቁሶችን ለማውጣት የሚያገለግል መሳሪያ እንዲሁም የኒውክሌር ቦምብ የላብራቶሪ ሞዴልን ወሰደ።
"ካሜራ እንዴት ደብቆ እንዳስገባ፣ ተመልሶ መጥቶ ፊልሞቹን በካልሲው ውስጥ እንደሸጎጣቸው እንዲሁም  ፎቶዎቹን በድብቅ በሌሊት እንዲሁም በጥዋት እንዳነሳ አስገራሚ ታሪክ ነገረኝ" ይላል ጋዜጠኛው።
የሰንደይ ታይምስ አዘጋጆች የሞርዴካይን ታሪክ ለማጣራት ወደ ለንደን እንዲመጣ ጠየቁት።
ፍራቻ ቢያድርበትም ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለመብረር ተስማማ።
ጋዜጣውም ከለንደን ውጪ በሚገኝ ደበቅ ባለ ሆቴል አሳረፈው።
ሆኖም እረፍት አልባነት የተሰማው ቴክኒሻኑ ለንደን መጣ እና በአንድ ሆቴል አረፈ።
በዚህም ወቅት ነው ሁኔታዎች ግልብጥብጣቸው የወጣው።
"በጎዳናዎች ላይ ሲዘዋወር አንዲት ሴትን አገኘ። የተወሰነ ጊዜ አይቷት ስለነበር አብሯት ሲኒማ ሄደ። እናም ይህቺን ሴት ማንነቷን ታውቃለህ? እውነተኛ ናት ሲል መጠየቁን" ፒተር ያወሳል።
የሞርዴካይ የለንደን ቆይታ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳስበው የነበረው ጋዜጠኛው በየጊዜው እየደወለ ይጠይቀው ነበር።
ፒተር ከሞርዴካይ ጋር የነበረውን የመጨረሻ ንግግር ያስታውሳል።
"'ወደ ሰሜን እንግሊዝ ለጥቂት ቀናት እሄዳለሁ። ምንም አልሆንም' አለኝ። እኔም ምንም ነገር ብታደርግ ደኅንነትህን እንዳውቅ በቀን ሁለት ጊዜ ደውልልኝ አልኩት" ይላል።
ሆኖም ከአንድ ወር በኋላ የእስራኤል መንግሥት ሞርዴካይ እንደታሰረ አስታወቀ።
ለንደን ላይ በተዋወቃት ሴት ነበር ወጥመድ ውስጥ የገባው። ራሱንም አስተው በጀልባ ነበር ወደ እስራኤል በድብቅ ያጓጓዙት።
ሞርዴካይ ወደ እስር ቤት እየሄደ ሳለ እንዴት ከለንደን ተጠልፎ እንደተወሰደ አንዳንድ ዝርዝሮችን በእጁ መዳፍ ላይ አሰፈረ።
ሲጠብቁት ለነበሩት ጋዜጠኞችም በመኪናው መስኮት በኩል መዳፉን ከፍ አድርጎ አሳየ።
ሞርዴካይ ሊያዝ የበቃው ለንደን ላይ ቱሪስት መስላ በቀረበችው ግለሰብ ነበር። በአሜሪካ የተወለደችው ቼሪል ቤንቶቭ ቱሪስት ሳትሆን የሞሳድ ወኪል ነበረች።
ግለሰቧ ሞርዴካይን አታልላ አብሯት ወደ ሮም እንዲመጣ መስከረም 20/1979 ጋበዘችው። ሮም ከሄደ በኋላ ታፍኖ እንዲደነዝዝ ተደረገ። ከዚያም በኋላ ነው ወደ እስራኤል የተወሰደው።
ሞርዴካይ መጋቢት 1981 በአገር ክህደት እና በስለላ ወንጀል 18 ዓመታት ተፈረደበት።
ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ጊዜም ብቻውን እንዲታሰር ተደርጓል።
"እየተከናወነ ያለውን ነገር ለዓለም ማሳወቅ ነው የፈለግኩት። ይህ የአገር ክህደት አይደለም። የእስራኤል ፖሊሲ ባይፈቅደውም ዓለምን አሳውቄያለሁ" ሲል ሞርዴካይ ከእስር ቤት ሆኖ በተቀረጸ  ቃለ ምልልስ ተናግሯል።
ሞርዴካይ ሚያዝያ 13/1996 ዓ.ም. ከእስር ቢፈታም ከእስራኤል እንዲወጣ አልተፈቀደለትም።
ነገር ግን የኒውክሌር ሳይንቲስቱ ሞርዴካይ ከእስር የተለቀቀበትን የይቅርታ ሁኔታውን በመተላለፍ በተደጋጋሚ ለእስር ተደርጓል።
በ2001 ከመታሰሩ በፊትም "ባሰራችሁኝ 18 ዓመታት ውስጥ ምንም አላገኛችሁብኝም። በሦስት ወር ምንም አታገኙም። እስራኤል ሆይ እፈሪ" በማለት ሲጮህ ተሰምቷል።
የእስራኤልን የኒውክሌር አቅም በተመለከተ ቴክኒሻኑ እስኪያጋልጥ ድረስ የቅርብ አጋሮቿ እንኳን ብዙም የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም።
እስራኤል የኒውክሌር መርሃ ግብሯን የጀመረችው በአውሮፓውያኑ 1948 እንደ አገር በተመሠረተች ማግስት ወዲያውኑ መሆኑ ይታሰባል።
በጠላቶች እንደተከበቡ ያመኑት የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ቤን ጉሪዮን የኒውክሌር መከላከያ መገንባትን ከፍተኛ ቦታ ሰጡት።
ነገር ግን ግጭት በማያጣው ቀጣና የኒውክሌር መሳሪያዎችን በማምረት ወዳጆቻቸውን ማበሳጨት አልፈለጉም።
እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚያስችላትን የዲሞና የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያን ለመገንባት ከፈረንሳይ ጋር በአውሮፓውያኑ 1960 ምሥጢራዊ ስምምነት ላይ ደረሰች።
ለዓመታት ያህል ይህ ጣቢያ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እንደሆነ እስራኤል ስትናገር ቆይታለች።
የአሜሪካ ባለሙያዎች ስፍራውን በ1960ዎቹ በተደጋጋሚ ጎብኝተው ነበር።
ሆኖም ጣቢያው የነበረበትን ከመሬት በታች ያለውን ግንባታ አልተረዱት።
እስራኤል በአሁኑ ወቅት ወደ 90 የሚጠጉ የኒውክሌር አረሮች እንዳሏት ይገመታል ሲል የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን የሚከተታተለው 'ሴንተር ፎር አርምስ ኮንትሮል ኤንድ ነን ፕሮሊፈሬሸን' አስታውቋል።
ሆኖም እስራኤል በኒውክሌር አቅሟ ዙሪያ ግልጽ ያለ መረጃ አትሰጥም።
ከዚህ ቀደም የአገሪቱ መሪዎች "እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በመካከለኛው ምሥራቅ ለማስተዋወቅ የመጀመሪያዋ አገር አትሆንም" ሲሉ በተደጋጋሚ ሲደመጡ ይሰማል።
ከአውሮፓውያኑ 1970 ጀምሮ 191 አገራት የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎች ሥርጭት እና መስፋፋትን ለመከላከል ያለመውን 'ትሪቲ ኦን ዘ ነን ፕሮሊፈሬሽን ኦፍ ኒውክሌር ዌፐንስ' የተሰኘውን ስምምነት ፈርመዋል።
አምስት አገራት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ቻይና የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እንዲኖራቸው ተፈቅዶላቸዋል።
ለዚህም ምክንያቱ ስምምነቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ገንብተው ሙከራ አድርገው በማጠናቀቃቸው ነው።
እስራኤል የስምምነቱ ፈራሚ አባል አገር አይደለችም።
የእስራኤልን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለዓለም ያጋለጠው ሞርዴካይ በእስራኤል የአገር ክህደት እንደፈጸመ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው።
ነገር ግን ደጋፊዎቹ በበኩላቸው በ1996 ዓ.ም. ከእስር ሲፈታ "የሰላም ጀግና" በሚል አክብረውታል።
ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ "ምንም የሚጸጽተኝ ጉዳይ የለም" ብሏል።
"እኔ በምሥጢር እየተከናወነ የነበረውን ነገር ለዓለም ነው ያሳወቅኩት። እስራኤልን እናጥፋ፣ ዲሞና ይውደም አላልኩም። ይሄን እየሠሩ ነው እና እዩና ፍረዱ ነው ያልኩት" ብሏል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
አብዛኞቹ አዋቂ ሰዎች ከራስ ምታት እስከ መረበሽ የሚደርስ የውጥረት ምልክት በየጊዜው ያጋጥማቸዋል።
አንዳንድ ውጥረቶች ጠቃሚ ሊሆኑ ቢችሉም፣ ሥር የሰደደ ውጥረት ግን በሰውነት ላይ ጉዳት ያደርሳል።
ለተለያዩ የሥነ ልቦና እና ሥነ አካላዊ መዛባቶች፤ የአእምሮ እና የአካል ጤናን በመጉዳት መልካም ሕይወት መምራት እንዲያቅት ሊያደርግ ይችላል ሲሉ የሕክምና ባለሙያዎች  ተናግረዋል።
ውጥረትን መቆጣጠር እና ወደ ጥንካሬ ምንጭነት መቀየር ይቻላል።
ውጥረት ሰውነታችን ለችግሮች እና ለጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ የሚያዘጋጅ ተፈጥሯዊ ክስተት ነው።
ሰውነት አስቸጋሪ ሁኔታን ለመቋቋም እንዲችል የሚያዘጋጁ ሆርሞኖችን እንዲያመነጭ ያደርጋል።
ለአጭር ጊዜ ሲሆን ይህ ምላሽ ትኩረትን ከፍ ሊያደርግ እና ውጤታማነትን ሊያሻሽል ይችላል።
ይኹን እንጂ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ውጥረት የልብ ሕመምን እና የበሽታ መከላከል አቅምን ማዳከምን ጨምሮ ከባድ የጤና አክሎቸን ያስከትላል ይላል የአሜሪካ የሥነ ልቦና ማኅበር።
ውጥረትን የሚቀሰቅሱ ምክንያቶች ሥራ፣ የገንዘብ ችግር እና የግል ግንኙነቶችን ጨምሮ ሌሎችም ሲሆኑ፤ ብዙውን ጊዜ ሊወገዱ የማይችሉ ናቸው።
ዋናው ልዩነት ውጥረት ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል የሚለው ነው። አጣዳፊ ውጥረት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እና ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።
ሥር የሰደደ ውጥረት ግን በሰውነት ላይ ዘላቂ ጫናን ያስከትላል።
"ፈጣን ውጥረት ለተወሰነ ሁኔታ የሚሰጥ የአጭር ጊዜ ምላሽ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎችም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ሳይኮቴራፒስት እና የብሪቲሽ የምክር እና ሳይኮቴራፒ ማኅበር (ቢኤሲፒ) አባል የሆኑት ራቼል ቮራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አንጎላችን "ተጋፈጥ ወይም ሽሽ የሚል ምላሽን በመፍጠር አድሬናሊን እና ኮርቲሶል ይለቀቃል። ይህም ትኩረትን ለመጨመር እና ለበሽታ የመከላከያ ሥርዓታችን ጊዜያዊ ማበረታቻ ሊሰጥ ይችላል።"
በአግባቡ ከተያዘ አጣዳፊ ውጥረት ዘላቂ ጉዳት አያስከትልም። ግለሰቦች ለፈጣን ተግዳሮቶች ውጤታማ ምላሽ እንዲሰጡ ሊረዳቸው ይችላል። ሥር የሰደደ ውጥረት ግን በሰውነት ላይ ረዘም ያለ ጫና ይፈጥራል።
ውጥረት ለረዥም ጊዜ በሚቆይበት ጊዜ ከፍ ያለ የውጥረት ሆርሞኖች ለልብ በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚጨምሩ፤ የሰውነትን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን እንደሚያዳክሙ እና በአንጀት ላይ ቁስለት በመፍጠረ ለምግብ መፈጨት ችግሮች አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ቮራ አስረድተዋል።
ሥር የሰደደ ውጥረት ከጭንቀት እና ድብርት፣ ከግንዛቤ መጓደል፣ ከእንቅልፍ መዛባት እና ከተፋጠነ የሰውነት እርጅና ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው።
እንደ ቮራ ገለጻ ከሆነ ይህ የቆይታ እና የመፍትሔ መሠረታዊ ልዩነት ወደ ሥር የሰደደ ውጥረት ቀስ በቀስ በማደግ በርካታ የሰውነት ሥርዓቶችን ይጎዳል።
የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ውጥረት ሆርሞኖችን በዋናነትም ኮርቲሶል እና አድሬናሊን በመልቀቅ አካላዊ ምላሾችን እንደሚያስነሳ ያስረዳል። እነዚህ ምላሾች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
ይኹን እንጂ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ውጥረት ጎጂ ሊሆን ይችላል። የማያቋርጥ ውጥረት ከሚከተሉት ጋር ይያያዛል፡-
የዩኬ በሔራዊ የጤና አገለገሎት የማያቋርጥ ውጥረት እንደ የልብ ሕመም፣ የምግብ መፈጨት ችግር እና እንደ ጭንቀት እና ድብርት ያሉ የአአምሮ ጤና ችግሮች ላሉ የረጅም ጊዜ ሁኔታዎች አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያስጠነቅቃል።
በካሊፎርኒያ ኧርቪን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጎልናዝ ታቢብኒያ "የመቋቋም ችሎታ ያለዎት ወይም የሌለዎት ነገር ብቻ ሳይሆን በጊዜ ሂደት ሊዳብር የሚችል ክኅሎት ነው" ብለዋል።
ተግዳሮቶችን ከመሸሽ ይልቅ በንቃት መጋፈጥ የመቋቋም ችሎታን ለመገንባት ይረዳል ሲሉ አክለዋል።
እንደ ዶ/ር ታቢብኒያ አመለካከት ሰዎች ውጥረትን ከጎጂነት ይልቅ አጋዥ አድርገው ሲመለከቱ የፊዚዮሎጂ ጭንቀት ምላሽ ይቀንሳል።
ቀላል የአስተሳሰብ ለውጥ ተአምራትን ይፈጥራል። በዚህም ጭንቀትን በመቀነስ አፈፃፀምን ያሳድጋል።
"ውጥረትን በቸልተኝነት ከማስወገድ ይልቅ በንቃት መቋቋም ወደፊት የሚፈጠሩ ጭንቀቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር አእምሮን እንደገና ያዘጋጃል። በጂም ውስጥ እንደመሆን ዓይነት ነው። ክብደት ማንሳት አስጨናቂ ነው፣ ግን የበለጠ ጠንካራ ያደርገናል" ብለዋል።
በውጥረት እና በጭንቀት መካከል ያለውን ቁልፍ ልዩነት እንዲያብራራ የጭንቀት መታወክ ያለባቸውን ግለሰቦች የሚደግፈውን 'አንዛይቲ ዩኬ' የተባለውን ብሔራዊ የበጎ አድራጎት ድርጅትን ቢቢሲ ጠይቋል።
ውጥረት ለምሳሌ እንደ የሥራ ቀነ ገደብ፣ የመንጃ ፈቃድ ፈተና ላሉ ለውጫዊ ሁኔታ የሚሰጥ ምላሽ ነው ሲል መልሷል። ከፈተናው ጋር ተመጣጣኝ ሲሆን ችግሩ ከተፈታ በኋላም ይጠፋል።
ጭንቀት ግን ሊታወቅ በማይችል ምክንያት እንኳን ሊቀጥል ይችላል።
ጭንቀት ሰዎች በአደገኛ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ ንቁ ሆነው እንዲቆዩ የሚረዳ ስሜት ቢሆንም፤ ከመጠን በላይ ወይም የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚረብሽ ከሆነ ግን ችግር ይፈጥራል።
ውጥረት እና ጭንቀት ሰውነት "እንዲጋፈጥ ወይም እንዲሸሽ" ምላሽ የሚሰጠውን የነርቭ ሥርዓትን ያንቀሳቅሳል።
ይህ ማለት ሁለቱም እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ማላብ እና መንቀጥቀጥ ያሉ ምልክቶችን ይቀሰቅሳሉ። የጭንቀት ግን የበለጠ ዘላቂ እና ከባድ ይሆናል።
አጣዳፊ የጭንቀት እና የድንጋጤ አደጋዎችን ለመቆጣጠር አንዛይቲ ዩኬ የአተነፋፈስ ልምምዶችን ይመክራል።
ቀላል ነገር ግን ውጤታማው ዘዴ አየር ከማስገባት ይልቅ ማስወጣት ላይ ጊዜ መውሰድ መሆኑን ጠቅሷል። ይህም ሰውነት ዘና እንዲል በማድረግ የነርቭ ሥርዓትን በፍጥነት ያረጋጋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ውጥረት በሰውነት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የባህሪ ልምምዶችን ጠቃሚ ውጤቶች የአካዳሚክ ጥናት አጉልቶ አሳይቷል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጭንቀት ሆርሞንን በመቀነስ ጥሩ ስሜትን ከፍ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል።
ሜዲቴሽን (አረምሞ/ተመስጦ) ደግሞ አእምሮን ለማረጋጋት ያግዛል። ማኅበራዊ ድጋፍ ስሜታዊ ጥንካሬን በማጉላት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ጥናቶች አመልክተዋል።
ዶ/ር ታቢብኒያ በበኩላቸው አመስጋኝነት እና ደግነት እንዲሁም ደግሞ በሳይንስ የተደገፉ እንደ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ከቤት ውጪ ጊዜ ማሳለፍ እና ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ያሉ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥተዋል።
በለንደን የ7ብሪዝ መሥራች የሆኑት ዩኪ ደግሞ ሁሉንም የመከተልን አስፈላጊነት ያጎላሉ።
"ውጥረትን መቆጣጠር ማለት ዘና ማለት ብቻ አይደለም። የእርስዎን አእምሯዊ እና አካላዊ ደኅንነትን የሚደግፍ የአኗኗር ዘይቤን መፍጠር ነው። ለጤንነትዎ ቅድሚያ ሲሰጡ ውጥረትን ለመቋቋም ቀላል ይሆናል" ብለዋል።
ትኩረትን ማሳደግ፣ እንቅልፍን፣ የአካል እንቅስቃሴን እና የተመጣጠነ ምግብን እንደ ውጥረትን ለመቆጣጠር አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል።
"የእርስዎ ማይክሮባዮም ጭንቀትን በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ለጤናማ ምግብ ቅድሚያ መስጠት ለአጠቃላይ ደኅንነት ቁልፍ ነው" ሲሉ አክለዋል።
እንደ ዩኪ ገለጻ ከሆነ ውጥረትን በፈጣን ጥገናዊ ለውጦች ማሻሻል አይቻልም። የዕለት ተዕለት ልማዶችን መፍጠር ነው ጥንካሬውን የሚያሳድጉት።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት "ውጥረት ያሻሽላል" የሚል አስተሳሰብን የተቀበሉ ግለሰቦች የተሻሻለ አፈጻጸም፣ የድካም ስሜት መቀነስ እና የተሻለ ስሜታዊነት አላቸው።
የሐርቫርድ ቢዝነስ ሪቪው ጥናት እንደሚያሳየው ውጥረትን እንደ አስጊ ሳይሆን እንደ ተግዳሮት መውሰድ በሰውነት ላይ ያለውን ተጽእኖ በእጅጉ ሊለውጠው ይችላል።
"ሰዎች ውጥረትን ከጎጂነት ይልቅ አጋዥ አድርገው ሲመለከቱ የፊዚዮሎጂ ውጥረታቸው ምላሽ ይቀንሳል" ሲሉ ዶ/ር ታቢብኒያ አጠቃለዋል።
"በውጥረት ላይ ያለውን አመለካከት በመቀየር ግለሰቦች ተግዳሮቶችን ወደ ግላዊ ዕድገት እና ችግሮችን የመቋቋም ዕድሎች ሊለውጡ ይችላሉ" ብለዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተካሄደባቸው 14 ዓመታት ውስጥ "እስከ 15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ሞተዋል" በሚል የተጠቀሰውን ቁጥር ለረጅም ዓመታት በሂደቱ የተሳተፉ ሁለት የግድቡ ሠራተኞች የደኅንነት ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉ።
ይህንን ቁጥር አረጋግጠዋል የተባሉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው "ጥያቄው በተሳሳተ መልኩ ተተርጉሟል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ፤ ከቀናት በኋላ እንደሚመረቅ የሚጠበቀው ግዙፉ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ 15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በግድቡ ግንባታ ሕይወታቸው ስለማለፉ እውነታነት እንዲያረጋግጡ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
ሪፖርተር የእንግሊዝኛ መጽሔት በጽሁፍ ባወጣው ቃለ መጠየቅ ላይ ሚኒስትሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ  "አዎ፤ እውነት ነው" የሚል ምላሽ እንደሰጡ ሰፍሯል።
በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ የተጠቀሰው ከሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር የተያያዘ ሞት ቁጥር ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው፤  የቀድሞው "ሳሊኒ ኢምፕሬጂሎ" የደኅንነት አስተባባሪ እና መሃንዲስ ከግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ ይህንን ያህል ሰው ሞቷል መባሉን ውድቅ አድርገዋል።
"ዊ ቢውልድ"  በሚል ስያሜውን የቀየረው ይህ የሕዳሴ ግድብ ዋና ተቋራጭ፤ በግንባታው ሂደት የሲቪል ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቷል።
የተቋራጩ የ"ኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት" መሃንዲስ የሆኑት ኢንጂነር ሞገስ የሺዋስ ከመጋቢት 2004 ዓ.ም. እስከ ባለፈው ግንቦት 2017 ዓ.ም. ድረስ በግንባታው ላይ ሰርተዋል።
"ኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት" ክፍል አስተባባሪ የነበሩት ሌላኛው ባለሙያ ምንተስኖት አየለ በበኩላቸው ከ2004 ዓ.ም. አንስቶ ለአስር ዓመታት ገደማ ግንባታው ላይ ቆይተዋል።
አብዛኛውን የሰው ኃይል የሚያሰማራው "ዊ ቢውልድ" ሠራተኞችን የሥራ ላይ ደኅንነት የመከታተል እና የመመዝገብ ኃላፊነት ያላቸው እነዚህ ባለሙያዎች፤ በግንባታው ሂደት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ።
እስከ 2014 ዓ.ም. ድረስ ኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት ኮርዲኔተር ሆነው የሠሩት ምንተስኖት "በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች የሞቱበት መንገድ አለ" ይላሉ።
"ከሥራ ጋር በተገናኘ በአደጋ የሚሞቱበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። የግድቡን ኅልውና በማስጠበቅ፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ቁሳቁሶችን በማመላለስ፣ ጥቃት ሲደርስ ስለነበር በዚያ ሰዓት የተሰዉ ወገኖችም፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትም ሊኖሩ ይችላሉ" ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት, Office of the Prime Minister-Ethiopia
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ነገር ግን በትክክል መናገር የሚችሉት ከግድቡ ግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን በተመለከተ እንደሆነ አስረድተዋል። "ከዚህ ጋር በተያያዘ የነበረው ሞት በጣም ጥቂት ነው። 15 ሺህ ከሚለው አንጻር ጋር ሲታይ በጣም ጥቂት ነው የነበረው" ብለዋል።
"እኛ ሳሊኒ ጋር የነበረው ከሥራ ጋር የተያያዘ የሞተ ሰው ከ100 የሚያልፍ አይመስለኝም። 100ም የሚደርስ አይመስለኝም" ሲሉም አክለዋል።
እስከ ግንቦት ድረስ የኮንትራክተሩ የኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት ኢንጂነር የነበሩት ሞገስም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ።
ኢንጂነሩ፤ "ሥራውም ይመለከተኝ ስለነበር፤ እንመዘገበውም ስለነበረ ዳታው [መረጃ] ነበረኝ። ባለኝ ዳታ መሠረት እስከ ነበርኩበት ጊዜ ድረስ እኔ የማውቀው ቁጥር [የሞቱ ሠራተኞች ብዛት] 25 አካባቢ ነው፤ ድርጅቱ የሚያውቀውም ይህንን ነው" በማለት የሞቱ ሠራተኞች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን አስረድተዋል።
ከእነዚህ የዊ ቢውልድ ሠራተኞች ውስጥ አብዛኞቹ ሕይወታቸው ያለፈው "በትራፊክ አደጋ" እንደሆነ ተናግረዋል። "ከከፍታ ቦታ ላይ መውደቅ" እና "ከኤሌክትሪክሲቲ ጋር የተገናኙ" አደጋዎችም ሠራተኞችን ለሞት ከዳረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሚጠቀሱ አስረድተዋል።
ምንተስኖትም በተመሳሳይ "ግቢ ውስጥ የሚከሰት የከባባድ የኮንስትራክሽን መኪናዎች የመገልበጥ እና መውደቅ"፣ "ከከፍታ ላይ መውደቅ" እንዲሁም "ኤሌክትሪክ አደጋዎችን" ጠቅሰዋል። ከሥራ ጋር በተያያዙ አደጋዎች ከሞት በተጨማሪ አካል ጉዳቶች መድረሳቸውንም ሁለቱ ባለሙያዎች አክለዋል።
የኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት ኢንጂነሩ ሞገስ፤ በተለይም በግድቡ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ሌሎች ተቋራጮች መኖራቸውን አንስተዋል። ይሁን እንጂ "በይበልጥ ለአደጋ የመጋለጥ ዕድል ያለው" የዊ ቢውልድ ሠራተኞች በሚያከናኑት የሲቪል ግንባታ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
"[የሲቪል ሥራ] እንቅስቃሴው በይበልጥ ወሳኝ ነው። በተለይም ከከፍታ ቦታ ላይ መሥራት በብዛት አለ። ከእርሱ ጋር ተያይዞ አደጋ የመድረስ ዕድሉ ሰፊ ነው" በማለት አስረድተዋል።
ከሥራ እስከለቀቁበት ግንቦት ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ "ለሰባት ገደማ ዓመታት የሠራተኞች ተወካይ" ሆነው እንዳገለገሉ የሚናገሩት ሞገስ፤ በዚህ ምክንያት የሌሎች ተቋራጮች ሠራተኞች ሕይወት ካለፈ ሊያውቁ የሚችሉበት ዕድል እንደነበርም አንስተዋል።
አክለውም፤ "አንድ ሰብ ስቴሽን ላይ የሚሠራ የቻይና ኮንትራክተር ሠራተኛ ከከፍታ ቦታ ወድቆ ሕይወቱ እንዳለፈ ሰምቻለሁ። ከዚያ የዘለለ የሰማሁት የለም" ብለዋል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "የሁሉም ሰው አሻራ ያረፈበት" መሆኑን ባስረዱበት የቃለ መጠየቅ ክፍል ላይ "ሕይወታቸውን የሰዉ የፀጥታ ኃይሎች" እና "የተገደሉ አሽከርካሪዎች" መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
የተለያዩ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘውን የሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የተለያዩ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የፌደራል መንግሥት በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኞ ዕለት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በተላለፈ የአንድ ሰዓት ገደማ ቆይታ ላይም ይህንን ጉዳይ ጠቅሰውት ነበር።
ዐቢይ፤ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በነበሩ ዓመታት "ግጭት እና ውጊያ" በዝቶ እንደነበር እንዲሁም "ተፋላሚዎች ወጥተው ከሀገር፣ ሠልጥነው [ሲያስቸግሩ]" እንደነበር አንስተዋል።
ቢቢሲ ያነጋራቸው ሁለት ባለሙያዎችም በግድቡ ግንባታ ሂደት ወቅት በተለያየ መልኩ ጥቃት ሲፈጸም እደነበር ገልጸዋል።
የሠራተኞች ደኅንነት አስተባባሪ የነበሩት ምንተስኖት፤ "በጣም ብዙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ብዙ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በአንድ ቀን መምጣት የሚቻለው መንገድ ሰባት ቀን በመኪና ታጅቦ ነው ይመጣ የነበረው። እቃ ወደ ግድቡ የሚመጣው፣ ሠራተኛውም ወደ ቤተሰቡ ሄዶ ሲመለስ አብሮ ታጅቦ ነው የሚመለሰው" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስታውሰዋል።
ምን ያህል ወይም ምን ዓይነት ጥቃት ተፈጽሟል የሚለውን በተመለከተ ግን መናገር እንደማይችሉ አስረድተዋል። በተፈጸሙ ጥቃቶች የሞቱ ሰዎችን ብዛት፤ "ከእኛ በላይ የነበሩ ሰዎች ያንን ቁጥር ሊያውቁት ይችላሉ" ብለዋል።
የኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት ኢንጂነሩ ሞገስ በበኩላቸው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት "ከሁለት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ" ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በፀጥታ ኃይሎች እጀባ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህ እጀባ ያስፈለገውም "ታጣቂዎች ጫካው ጋር ይሆኑና መኪና አልፎ ሲሄድ ጥይት ስለሚተኩሱ እና ጉዳት ስለሚያደርሱ" እንደነበር ተናግረዋል።
"በ2015 ዓ.ም." አካባቢ በተፈጸመ "የሽብር ጥቃት አንድ የዊ ቢውልድ አሽከርካሪ" ሕይወቱ ማለፉን አስረድተዋል። ሠራተኛው ይዞት የነበረው ተሽከርካሪው በእጀባ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ያስታወሱት ሞገስ፤ "መንገድ ላይ የተጠመደ ፈንጂ ነው ጉዳት ያደረሰበት። እጀባ ቢኖርም እጀባ ሊያድነው የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም" ብለዋል።
በዚህ ጥቃት ከተገደለው አሽከርካሪ በተጨማሪ "ሠራተኛ ያልነበረች አንዲት ተሳፋሪ" ጉዳት ደርሶባት እንደነበርም ጠቅሰዋል። ሞገስ ጥቃቶች ሲደርሱ እንደነበር እንደሚያውቁ ቢናገሩም፤ ከእነዚህ ጥቃቶች ጋር በተያያዘም ቢሆን የተጠቀሰው ቁጥር እንደማያሳምናቸው ተናግረዋል።
ሪፖርተር መጽሔት ትናንት ሐሙስ ነሐሴ 29 ከሰዓት በድረ ገጹ ላይ በወጣው ቃለ መጠይቅ ላይ ባደረገው ማስተካከያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ በቀረበው ጥያቄ የተጠቀሰው ቁጥር "ከኮንስትራክሽን ደኅንነት ጉዳዮች ጋር" ብቻ በተያያዘ እንዳልሆነ የሚያመለክት መልዕክት አስፍሯል።
መጽሔቱ ይህንን ማስተካከያ ያደረገው "አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እና ግለሰቦች ትክክለኛውን ገለጻ ከአውድ ውጪ ወስደው ስለተረጎሙት" እንደሆነ ገልጿል።
ቢቢሲ ይህንን ቁጥር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ፤ የቀረበላቸው ጥያቄ "በተሳሳተ መንገድ መተርጎሙን" ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ጥያቄው የቀረበላቸው "የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር በመውሰድ" እንደነበረ አክለዋል።
ዶ/ር ሀብታሙ፤ "15 ሺህ" በሚል የተጠቀሰው ቁጥር ትክክለኛ ስለመሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "ልክ ሆነም አልሆነም፤ የተጻፈበት አተረጓጎም ልክ አልነበረም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። "ጥያቄው እንደዚያ አልነበረም" ሲሉም ተናግረዋል።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከመከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማብራሪያ ለማግኘት ያደረጋቸው ጥረቶች አልተሳኩም።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ክብደት መቀነስ ለብዙዎቻችን ከባድ ፈተና ነው። ምንም እንኳ ይህንን በተለያየ መንገድ ማሳካት ቢቻልም ዋናው ግብ ግን ከምንመገበው በላይ ካሎሪ ማቃጠል መቻል ነው።
በብራዚል ሳኦ ፓውሎ በሚገኘው የኖቬ ደ ጁልሆ ሆስፒታል የስፖርት ሐኪም የሆኑት ፓብሊየስ ብራጋ "ሐሳቡ ሰውነት ያከማቸውን ኃይል ይጠቀማል የሚል ነው፤በተለይም ስብን እንደ ኃይል ምንጭነት ይጠቀማል" ይላሉ።
በሐሳብ ደረጃ፣ጤናማ አመጋገብን እና መደበኛ አካላዊ እንቅስቃሴን በማጣመር አነስተኛ የሆነ የካሎሪ መጠን ሊኖረን ይገባል።
ይሁን እንጂ የካሎሪ መጠንን መቀነስ እንዲህ እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም፤ወይንም አመጋገባችን የተመጣጠነ አይደለም።
በዚህም የተነሳ ክብደትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት መካከል የሰውነት ስብን ብቻ ሳይሆን፣ የጡንቻ መጠናችንንም ልናጣ እንችላለን።
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት የጡንቻ መጠን ማነስ ከመጠን በላይ ስብን የማከማቸት ያህል ጎጂ ነው።
የጡንቻ መጠን እየቀነሰ እየሟሸሸ ሲሄድ የምግብ ማሳለጥ (ሜታቦሊዝም) ሂደት እየቀነሰ ይሄዳል።
በዚያው መጠን ሰውነት ስብን የሚያቃጥልበት ቅልጥፍና ዝቅተኛ ይሆናል። ከዚያም አቅም እያጣን መሄዳችን ግልጽ ይሆናል።
በተጨማሪም የጡንቻ መጥፋት ጥንካሬን፣ አካላዊ ጽናትን እና የረዥም ጊዜ ጤናን ይጎዳል።
ይህም ክብደት መቀነስን ለመጠበቅ አስቸጋሪ ስለሚያደርገው ተመልሰን ወደተውነው የአመጋገብ ሥርዓት የመግባት ስጋትን ይጨምራል።
"ለዚያም ነው አግባብነት ያለው ክብደት መቀነስ የኪሎ መውረድ ብቻ የማይሆነው፤ በሰውነት ውስጥ የሚሠራ እና ጠቃሚ ነገርን መጠበቅ ጭምር ነው፤ ያ ደግሞ ጡንቻ ነው" ትላለች ከሳኦፖሎ ዩኒቨርስቲ በኢንዶክሪኖሎጂ ፒኤችዲዋን የያዘችው ኤላይን ዲያስ።
አንድ ሰው የካሎሪ እጥረት ሲያጋጥመው፣ሰውነቱ እንደ የኃይል እጥረት ይመዘግበዋል፤ እናም እንደ መከላከያ ዘዴ ወደ "ኃይል ቆጣቢ ሁኔታ" ይቀየራል ስትል ታክላለች።
ዲያስ "ጡንቻ በእረፍት ጊዜም ብዙ ኃይልን ስለሚያቃጥል፣ በካሎሪ እጥረት ወቅት ሰውነት ይህንን እንደ 'ቅንጦት' ማየት ይጀምራል። ልክ በቀውስ ውስጥ ያለ ኩባንያ ወጪን ለመቀነስ በጣም ውድ የሆኑትን ክፍሎቹን እንደሚዘጋው ማለት ነው" ስትል ትገልጸዋለች።
የካሎሪ ገደብ "በጣም ከባድ ወይም በደንብ ያልታቀደ" ከሆነ ሰውነት ጉልበትን ለመቆጠብ የጡንቻን ሕብረ ህዋስ (ቲሹ) መሰባበር ሊጀምር እንደሚችል ጨምራ ታብራራለች።
ስለዚህ ክብደት በሚቀንስበት ጊዜ ጡንቻን እንዴት በነበረበት ማቆየት እንችላለን?
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ባለሙያዎች ውሃ መጠጣት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ።
70 በመቶ ጡንቻችን ውሃ ነው፤ስለዚህ በቂ ውሃ መጠጣት በአግባቡ እንዲሠራ ለማድረግ ወሳኝ ነው።
ይህም ማለት በየቀኑ በአንድ ኪሎ ግራም ከ30 እስከ 40 ሚሊ ሊትር ውሃ መጠጣት አስፈላጊ ነው።
ውሃ ለህዋሶቻችን ሥራ እንዲሁም ለጡንቻ ዳግም እድሳት ቁልፍ ነው።
"ጡንቻዎቻችን ውሃ ካጡ፣መጠናቸው እንዲሁም ተግባራቸው ይቀንሳል" ትላለች ዲያስ።
በዚያው ልክ በቂ የሆነ ፕሮቲን መውሰድም አስፈላጊ ነው።
እንደ ዓለም አቀፉ የስፖርት ሥነ ምግብ ማኅበር ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የጡንቻ ዕድገትን ለመደገፍ እና አጠቃላይ አካላዊ ክብደትን ለመጠበቅ አዋቂ ሰዎች በሰውነታቸው ክብደት የሚሰላ በአንድ ኪሎ ግራም ከ1.4 እስከ 2 ግራም ፕሮቲን በየቀኑ መውሰድ ይኖርባቸው።
ስለዚህ አንድ የ70 ኪሎ ግራም ሰው በየዕለቱ ከ98 እስከ 140 ግራም ፕሮቲን መውሰድ ይጠበቅበታል።
ባለሙያዎቹ አክለውም የካሎሪ እጥረቱም ቢሆን መጠነኛ መሆን አንዳለበት ይመክራሉ።
"በየቀኑ እስከ 500 ካሎሪ ድረስ እጥረት ቢኖር መልካም ነው። እጅግ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት የሚገጥም ከሆነ ሰውነታችን ጡንቻን ማቃጠል ሊጀምር ይችላል።ከፍተኛ የሆነ የካሎሪ እጥረት ጡንቻን ስለሚያሟሽሽ፣ የምግብ ልመትን በማዘግየት ተመልሰን ከፍተኛ የሆነ የካሎሪ መጠን ወደ መመገብ እንድንገባ ሊያደርገን ይችላል" ትላለች ዲያስ።
ለሴቶች፣ ብዙውን ጊዜ ዝግ ያለ ሜታቦሊዝም እና አነስተኛ የጡንቻዎች መጠን ስላላቸው በተለይ ክብደት ለመቀነስ በሚሞከርበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
"በዚህ ጊዜ እስከ 500 ካሎሪ የሚደርስ እጥረት አደገኛ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በቀን 300 ካሎሪ በመቀነስ መጀመር ይኖርብናል" ስትል ዲያስ ትመክራለች።
ብራጋ በዚህ ሃሳብ ይስማማል። "ደኅነንነቱ የተጠበቀ መጠን አለ።በተለይ የፕሮቲን አወሳሰድ ተገቢ የሆነ መጠንን በመጠበቅ ላይ ይመሠረታል።"
አክሎም "የምግባችን አንድ ሦስተኛው ፕሮቲን ከሚሰጡን ምግቦች ማድረግ ጠቃሚ ነው።"
ከተመጣጠነ ምግብ ባሻገር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ጡንቻን ሳይሟሽሽ ክብደት በመቀነስ ውስጥ ዋነኛ ሚና አለው።
እና ግባችን ስብ እያቃጠልን ጡንቻን መገንባት ከሆነ የምንሠራው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው።
"የአካል ጥንካሬ ልምምድ፣ እንደ ክብደት ማንሳት ያለ፣ ጡንቻን ለመጠበቅ አልፎ ተርፎም ለመጨመር ይረዳል" ስትል ዲያስ ትናገራለች።
ሰውነት ብዙውን ጊዜ በአንድ ጊዜ አንድን ግብ ማሳካት ላይ ብቻ እንደሚያተኩር ትናገራለች።
ይህም ወይ ስብን ማቃጠል ወይም ጡንቻ መጨመር ነው። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ስብን መቀነስ የካሎሪ እጥረትን የሚጠይቅ፣ የጡንቻ መጨመር ደግሞ ትርፍ ካሎሪ ስለሚጠይቅ ነው።
"ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ዕድሜያቸው ወደ ማረጥ የደረሰ ሴቶችም ቢሆኑ እንኳን፣ሁለቱንም ለማሳካት በጥንቃቄ በተዘጋጀ ዕቅድ መሥራት ይጠይቃቸዋል" ትላለች።
ይህም ከማረጥ በኋላ የሆርሞን እና የሜታቦሊዝም ለውጦች ጡንቻን ለመጠበቅ እና የስብ መጨመርን ለመከላከል የበለጠ ፈታኝ ስለሚሆን መሆኑን ታስረዳለች።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዕቅድ ውስጥ የጥንካሬ ሥልጠናን ማካተት የመፍትሄው ቁልፍ አካል ነው።
የጡንቻዎች ብዛት ከዕድሜ መጨመር ጋር የሚመጡትን እንደ ውፍረት፣ዓይነት 2 የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት እና የልብ እና ተያያዥ ሕመሞችን ለመከላከል ይረዳል።
"ለዚህም ነው ጡንቻ ለጤናማ እርጅና አስፈላጊ የሆነው። የተለያዩ ነገሮችን ለሚያመነጩ (ኢንዶክሪን) አካሎች፣ እንደ አይሪን ያሉ ቁልፍ ሆርሞኖችን በማመንጨት የአንጎልን ተግባር ያሻሽላል። እንዲሁም የመርሳት እና ፓርኪንሰን ሕመምን ጨምሮ ለበርካታ በሽታዎች የሚኖር ተጋላጭነትን ሊቀንስ ይችላል" ስትል ዲያስ ታብራራለች።
የጡንቻን መጠን ለመጠበቅ ሌላው ቁልፍ ነገር የስሜታችንን ደኅንነት መጠበቅ ነው።
"የክብደት መቀነስ እና የተክለ ሰውነት ጉዳይ ተጨማሪ ጭንቀት ሊፈጥርብን አያስፈልግም። አንድ ሰው ከልክ በላይ ራሱን የሚተች ወይም በጣም ለመቀነስ የሚታትር ከሆነ፣ ጤንነቱን የበለጠ ሊጎዳ ይችላል" ሲል ብራጋ ያስጠነቅቃል።
በጣም አስፈላጊው ነገር ዕቅዱን ከእያንዳንዱ ግለሰብ እውነታ ጋር ማመጣጠን መሆኑን አፅንዖት ይሰጠዋል።
"የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብሮች፣ወጥ የሆነ የእንቅስቃሴ ሰዓት፣ የእረፍት ጊዜ፣ ሁሉም በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በሚስማማ መልኩ አብረው መሄድ አለባቸው።ውጤቶቹም ከመልካም ሕይወት ጋር ተጣምረው መምጣት አለባቸው። ትክክለኛው ግብ ይህ ነው።"
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ለረጅም ሰዓት ምግብ በማብሰል የዓለም የክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሰፍራ የነበረችው ናይጄሪያዊቷ ሼፍ ሄልዳ ባቺ ሌላ ክብረ ወሰን ለመያዝ እየጣረች ነው።
ሼፏ በጊነስ ዎርልድ ሪከርድ ላይ በአዲስ ሥራ ለመስፈር በግዙፍ ድስት በምዕራብ አፍሪካ ተወዳጅ የሆነውን ከሩዝ የሚዘጋጀውን ጆሎፍ የተባለውን ምግብ አብስላለች።
ሄልዳ ሌጎስ ውስጥ ይህንን ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ የምግብ ማብሰል ሥራውን ስታከናውን ለመመልከት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ተመልክተዋታል። ሼፏ በአውሮፓውያኑ 2023 አራት ቀናት ለሚጠጋ ጊዜ ያለማቋረጥ ለ93 ሰዓታት ከ11 ደቂቃ አድካሚ በሆነ ሁኔታ ምግብ በማብሰል በዓለም ለረጅም ሰዓታት ምግብ ያበሰለች ሼፍ ተብላ ተመዝግባ ነበር።
አሁን በጣም ትልቅ በሆነ ድስት ላበሰለችው ከሩዝ ለሚዘጋጅ ምግብ አራት ሺህ ኪሎ ግራም ሩዝ፣ 500 ካርቶን ቲማቲም እና 600 ኪሎ ግራም ሽንኩርት የተጠቀመች ሲሆን፣ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው ድስት ወደ 23 ሺህ የሚጠጋ ሊትር የመያዝ አቅም እንዳለው ተነግሯል።
የምግብ ማብሰሉ ሥራ በርካታ ሰዓታትን የፈጀ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ የሚቀርቡ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ከተረጋገጡ በኋላ ጊነስ ዎርልድ ሪከርድ በክብረ ወሰንነት የሚመዘግብበት ውሳኔ ይጠበቃል።
የ28 ዓመቷ ወጣት ሼፍ ሄልዳ ባቺ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ይህንን ግዙፍ ሥራ በማከናወን ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ የአንድ ዓመት የዕቅድ እና ዝግጅት ጊዜ ወስዶባታል።
"እኛ [ናይጄሪያወያን] በአፍሪካ ግዙፍ ነን እናም ምግባችን ጆሎፍ ደግሞ እንደ የአፍሪካውያን ምግብነት ይታወቃል" በማለት በትልቅ ድስት ጆሎፍ ለማብሰል ለምን እንደመረጠች ገልጻለች።
"ጆሎፍ የተሰራበት ትልቁ ድስት በእኛ ስም መመዝገቡ ትርጉም ይሰጣል፣ ለአገራችንም ጥሩ ነገር ነው።" ብላለች ሄልዳ።
ምግቡ የበሰለበት ግዙፉን የብረት ድስት ለመሥራት 300 የሚደርሱ ሠራተኞች እና ሁለት ወራት አስፈልጎታል።
ሄልዳ በትላልቅ ማማሰያዎች እና በበርካታ ረዳቶቿ በመታገዝ ክብረ ወሰን ለመያዝ ያበሰለችው ከሩዝ የተዘጋጀው ባህላዊ ምግብ ከበሰለ በኋላ በስፍራው ለተሰበሰቡ ተመልካቾች ታድሏል።
ጆሎፍ በናይጄሪያ በስፋት የሚበላ ምግብ ሲሆን፣ የበሰለ ሩዝ ከቲማቲም ስጎ ጋር የሚበስል፣ በአብዛኛው ከሥጋ ወይም ከዓሳ ጋር የሚቀርብ ነው።
ሄልዳ ባቺ በአውሮፓውያኑ 2021 በአገሪቱ የተካሄደውን የምግብ ዝግጅት ያሸነፈች ሲሆን በ2023 ደግሞ ለረጅም ሰዓት በማብሰል ክብረ ወሰን ስትይዝ በናይጄሪያ ውስጥ ታዋቂ ለመሆን በቅታለች።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ፖፕ ፍራንሲስ ራፐሮች የሚያዘወትሩትን ግዙፍ ካፖርት እና ትልቅ መስቀል አድርገው የሚያሳየው ዲፕፌክ ምሥል አነጋጋሪ ከነበሩ ሐሰተኛ ምሥሎች መካከል ይጠቀሳል።
በመጀመሪያ ዕይታ ምሥሉ ሐሰተኛ መሆኑን ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው።
ምሥሉ የተሠራው በሰው ሠራሽ አስተውሎት መተግበሪያው ‘ሚድጆርኒ’ እንደሆነ ይፋ ከመደረጉ በፊት ምሥሉን የተመለከቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነተኛ እንደሆነ አምነዋል።
ይህ ምሥል ሊያሳድር ከሚችለው በላቀ ጉዳት ያደረሱ ምሥሎች፣ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች እና የድምጽ ቅጂዎች የወደፊቱን ዓለም አስፈሪ እንዳደረጉት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የስሎቫኪያ ምርጫ ቀናት ሲቀሩት ከተወዳዳሪዎቹ አንደኛው ‘ምርጫውን አጭበርብሬያለሁ’ ሲሉ የሚሰማበት የድምጽ ቅጂ በማኅበራዊ ሚዲያ ተለቀቀ።ድምጹ ዲፕፌክ መሆኑ ከመታወቁ በፊት ተወዳዳሪው ምርጫውን ተሸነፉ።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተለያዩ ግዛቶች የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ዲፕፌኮች ላይ ዕገዳ መጣላቸው ይታወሳል።
በአሪዞና ግዛት ውስጥ አንድ የ15 ዓመት ታዳጊ ለእናቷ ስልክ ደወለች። ሳግ እየተናነቃት ‘እማዬ አጋቾች ይዘውኛል’ አለች።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
አጋቾቹ ልጅቷን ሲያስፈራሩዋት ድምጻቸው ይሰማል። እናት ልጇን ለማስለቀቅ 1 ሚሊዮን ዶላር ተጠየቀች።
እናትየው ያን ያህል ገንዘብ እንደሌላት በመንገር አጋቾቹን ተማጸነች። በድርድር ገንዘቡን ቀንሰው፣ 50 ሺህ ዶላር ካልከፈለች ልጅቷን እንደሚገድሉ ነገሯት።
ይህ ሁሉ ሲሆን ልጅቷ የዳንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበረች። እናትየው ልጇ አለመታገቷን ያወቀችው የልጇ የዳንስ መምህራን ደውለው ሲነግሯት ነበር።
‘አጋቾቹ’ የታዳጊዋን ድምጽ በዲፕፌክ በማስመሰል ነበር ለእናቷ የደወሉት።
በፕሪቶሪያ በሚገኘው ስቲቭ ቢኮ አካዳሚክ ሆስፒታል የምትሠራው ደቡብ አፍሪካዊት ዩሮሎጂስት ቢሮ ስትገባ ከሥራ ባልደረቦቿ ያልጠበቀችው ዜና ደረሳት።
‘ይህ መድኃኒት ውጤታማ እንደሆነ በጥናት አረጋግጫለሁ’ ስትል የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋረ ነበር።
ይህን አለማድረጓን ብታውቅም የተንቀሳቃሽ ምሥሉ አሳማኝነት አስደነገጣት። በእሷ ስም እየተዋወቀ የነበረው ሐሰተኛ መድኃኒት ነበር።
በሆንግ ኮንግ የአንድ ተቋም ፋይናንስ ሠራተኛ የተቋሙ ዋና የፋይናንስ ኃላፊ ነው ብሎ ላመነው ሰው 25 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቷል።
ሠራተኛው ‘የፋይናንስ ኃላፊው’ በቪዲዮ ካዋራው በኋላ ትዕዛዙን እንደሰጠው አምኗል። ኋላ ላይ ፖሊስ ሲያጣራ ግን ገንዘቡን የተቀበሉት የበይነ መረብ መዝባሪዎች ናቸው።
የቪዲዮ ጥሪ የተደረገለትም በዲፕፌክ አለቃውን በማስመሰል ነበር።
አገራት ዲፕፌክን ለመቆጣጠር የተለያዩ ሕግጋት እያወጡ ይገኛሉ። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም ሐሰተኛ ምሥል በመጠቀም ሰዎችን መጉዳት ወይም ማታለል ያስቀጣል። ይህም ሐሰተኛ የእርቃን ምሥሎችን ይጨምራል።
ሐሰተኛ የእርቃን ምሥል ወይም ሐሰተኛ የልቅ ወሲብ ተንቀሳቃሽ ምሥል በማኅበራዊ ሚዲያ በመልቀቅ ከሰዎች ገንዘብ ለማግኘት የሚሞክሩም አሉ።
የ76 ዓመቱ ሕንዳዊ እርቃኗን ካለች ሴት ጋር ምሥላቸው በዲፕፌክ ተሠርቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ተለጥፎ ራሳቸውን ለማጥፋት መሞከራቸው አነጋጋሪ ዜና ሆኖ ነበር።
በተለይም ታዳጊዎች ላይ የሚያደርሰው ጫና ቀላል አይደለም።
ሴቶች ላይ በበይነ መረብ ከሚደርሱ ጥቃቶች መካከል በዲፕፌክ የሚሠሩ ምሥሎች እና ተንቀሳቃሽ ምሥሎች ይጠቀሳሉ።
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ግጭት ለማስነሳት ወይም ሁከትን ለማባባስ ሐሰተኛ ምሥሎች ሲሠራጩ ይስተዋላል።
እውነተኛ ምሥልን ወይም ተንቀሳቃሽ ምሥልን ከሐሰተኛው ለመለየት አስቸጋሪ እንደሆነ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችም ያስረዳሉ።
ሰዎች ያዩትን ወይም የሰሙትን ነገር በቀላሉ ለማመን ቅርብ መሆናቸውን እና ሐሰተኛ ምሥሎች፣ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች እንዲሁም የድምጽ ቅጂዎች ስሜትን በመኮርኮር ማሳመን የሚችሉ መሆናቸውን እንደ ምክንያት ያነሳሉ።
በሰው ሠራሽ አስተውሎትና በሮቦቲክስ ፒኤችዲውን እየሠራ ያለው የ‘ጉዞ ቴክኖሎጂስ’ መሥራች ዳንኤል ጌታቸው ዲፕፌክ ጉዳቱ የሚጎላው “በቀላሉ የሚታመን” ስለሆነ ነው ሲል ያስረዳል።
በተለይም የፖለቲካ ይዘት ካለው “የሚያስከትለው አደጋ ከፍተኛ ነው” ይላል ባለሙያው።
ዲፕፌክ (Deepfake) የሰው ሠራሽ አስተውሎት ውጤት ሲሆን ሐሰተኛ ምሥልን፣ ተንቀሳቃሽ ምሥልን ወይም ድምጽን ለእውነት በቀረበ ሁኔታ ማዘጋጀት ይችላል።
ዳንኤል እንደሚለው፣ ከምናውቀው እውነታ ጋር በጣም በሚመሳሰል መልኩ ስለሚሠራ ለመለየት ይከብዳል።
“የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ራሱ የሚታለሉበት ደረጃ ደርሷል” ሲል ያክላል።
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሠራጩ መረጃዎች ግጭት እና ነውጥ በሚያቀጣጥሉባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ዲፕፌክ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ከፍ ያለ ነው።
“በቀላሉ በፎቶሾፕ የተቀናበረ ምሥል እንኳን ሰዎችን እያሸበረ ነው። በጣም ለእውነት የቀረበ ሲሆን ደግሞ አደጋው የባሰ ይሆናል” ይላል ዳንኤል።
ጥላቻ ከመንዛት እና ለነውጥ ከመጋበዝ በተጨማሪ በግለሰቦች ደረጃም ሕይወትን እስከማመሰቃቀል ደርሷል።
ለዚህም ነው እያንዳንዱን መረጃ በተገቢው መንገድ ማጣራት አስፈላጊ እንደሆነ ባለሙያው የሚመክረው።
በተይም ደግሞ ስሜትን የሚኮረኩሩ ወይም የሚያጋግሉ መረጃዎች ሲሆኑ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።
ከዚህ በተቃራኒው የመዝናኛው ዘርፍ ዲፕፌክን በአወንታዊ መንገድ እየተጠቀመበት ነው።
ለምሳሌ የተዋንያንን የልጅነት ወይም የእርጅና መልክ ለማምጣት ዲፕፌክ ጥቅም ላይ ይውላል።
የ‘ፋስት ኤንድ ፊውሪየስ’ ተዋናይ ፖል ዋከር ፊልሙ ተቀርጾ ሳያልቅ ቢሞትም በዲፕፌክ ምሥሉን በመጠቀም ፊልሙ ተጠናቋል።
ዳንኤል እንደሚለው፣ ለቴክኖሎጂ እምብዛም ቅርበት በሌለው ማኅበረሰብ ውስጥ ዲፕፌክ የሚፈጥረው አደጋ ከፍተኛ ይሆናል።
“በገጠሪቱ ኢትዮጵያ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ይህን ብሏል የሚል ተንቀሳቃሽ ምሥል ቢወጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ነው” ሲል የዲፕፌክ ውጤት የሚያስከትለውን ስጋት ያስረዳል።
እውነተኛውን ከሐሰተኛው ለይቶ ለማወቅ በጣም ፈታኝ በሆነ መንገድ እየተሠራ ከመምጣቱ አንጻር፣ ባለሙያዎች የጥንቃቄ ምክሮች ያስቀምጣሉ።
አንድን መረጃ ያጋራውን አካል ማንነት ማጣራት እና በምሥሉ ወይም በተንቀሳቃሽ ምሥሉ እንደ ዓይን ወይም እጅ እንቅስቃሴ ያሉ ተፈጥሯዊ የማይመስሉ ነገሮችን መለየት በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ዲጂታል ዓለም በጣም እየተራቀቀ ሲመጣ እውነተኛው ዓለም የትኛው ነው? እስከምንል ድረስ ውዝግብ ውስጥ እንደምንገባ ዳንኤል ይናገራል።
ዲፕፌክ ገንዘብ ማግኛ፣ የፖለቲካ አቋም መግፊያ፣ አንዳች አሉታዊ ስሜት መፍጠሪያም እየሆነ ነው።
ዩኒቨርስቲዎች ለምርምር እንደ ማሳያ ሥራ አድርገው የሠሯቸውን መተግበሪያዎች በአሉታዊ መንገድ የሚጠቀሙ እንዲሁም በአንዳንድ መንግሥታት ድጋፍ የሚለቀቁም ዲፕፌኮች እንዳሉ ዳንኤል ያስረዳል።
ዲፕፌክን መቆጣጠር ካባድ የሆነውም በይበልጥ ለሰው ልጆች የቀረበ ቴክኖሎጂ እየሆነ በመምጣቱ እንደሆነ ያስረዳል።
ሰዎች፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሚፈልጉትን እየፈጠሩ እና ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ጋር ያላቸው ቁርኝት እየጨመረ ነው።
“ይሄ ቅርርብ ሲጨምር ቁጥጥር ማድረግን ከባድ ያደርገዋል” ይላል ባለሙያው።
“በፍጥነት የምናምነው ነገር ነው አጥፊያችን የሚሆነው” የሚለው ዳንኤል፣ ለማረጋገጥ መሄድ ያለብንን ርቀት ከግምት ሳናስገባ በቀጥታ ያንን ነገር ማመናችን ተጋላጭ እንደሚያደርገን ያስረዳል።
“መረጃዎችን ማጣራት አስፈላጊ ነው። ከተለያየ ምንጭ ለማጣራት መሞከር አለብን” ሲል ይመክራል።
ሌላው የጥንቃቄ ምክሩ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የምናጋራውን መረጃ ይመለከታል።
የዕለት ከዕለት ሕይወታችንን እና የግል መረጃዎቻችንን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በዘፈቀደ መልቀቅ ኋላ ላይ ዋጋ ሊያስከፍለን እንደሚችልም ይናገራል።
“ማኅበራዊ ሚዲያ ለእኛው መልሶ አደጋ ሊሆን ይችላል። እያንዳንዱ የምንለጥፈው ፎቶ፣ የምናጋራው መረጃ ‘ዲጂታል ፉት ፕሪንት’ ወይም ዲጂታል አሻራ ሆኖ ይቀመጣል” ይላል።
“ሲስተሙ ስለ እኛ ማንነት እና ስለ ፍላጎታችን ከምንተወው መረጃ ይማራል። ኋላ ላይ ተጋላጭ የሚያደርገንም ይህ ነው። መረጃችን ኢንተርኔት ላይ በበዛ ቁጥር የግል ሕይወታችን ውስጥ ገብቶ እስከማቃወስ ይደርሳል” ሲል ዳንኤል ያክላል።
በተለይም የሕጻናትን ምሥል እና ተንቀሳቃሽ ምሥል ተጠቅሞ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ገጽ ከፍቶ፣ ውሏቸውን እና ሕይወታቸውን ማስተላለፍ ያለውን አደጋ ይጠቅሳል።
“ሲስተሙ መልካቸውን፣ ድምጻቸውን እና ባሕሪያቸውን እንዲማር ያደርጋል። እነዚህ መረጃዎች ልጆቹን ዒላማ የሚያስደርጉ ወይም ቤተሰብን ማጥመጃ ሊሆኑ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል” ሲልም ይመክራል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ማሱድ ፔዜሽኪያን ሐምሌ 2024 የኢራን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ ከአንድ ቀን በኋላ በቀጥታ ወደ ፖለቲካ እሳት ውስጥ ገብተዋል።
ቃለ መሃላ ከፈፀሙ ከሰዓታት በኋላ በምሥረታው ላይ ከተገኙ ታዋቂ እንግዶች መካከል አንዱ የሆኑት የሐማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬ በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ የሚለው ዜና ተሰማ።
ግድያው የተፈጸመው ደግሞ በጋዛ ሳይሆን በመሃል ቴህራን ነው። ኢራን ሐማስን በገንዘብ፣ በጦር መሳሪያ እና በፖለቲካዊ ደጋፊ ነበረች።
ግድያው በቀጠናው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል፤ እናም አልጋ በአልጋ የሆነ ሽግግርን ህልም አንኮታኩቶታል።
ይህም አለመረጋጋት በሌለው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መሪዎች ታሪክ ውስጥ ከታዩት ጅማሪዎች መካከል እጅግ አስደንጋጩ እና በቀውስ የታጀበ ነበር።
ፔዝሽኪያን በዚህ ብሔራዊ ድንጋጤ ውስጥ ሆነው ነው ወደ ሥልጣን የወጡት።
ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ጠንካራው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራኢሲ ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሄሊኮፕተር አደጋ ተገድለዋል።
ይህ ያልተለመደ ክስተት አገሪቱን በሳምንታት ውስጥ አስቸኳይ ምርጫ እንድታደርግ አስገድዷታል።
በዚያች ጠባብ ቀዳዳ የሾኩት የልብ ቀዶ ሕክምና ባለሙያው፣ የቀድሞ የጤና ሚኒስትር እና የፓርላማ አባል  ፔዝሽኪያን የአገሪቱን ከፍተኛ ሥልጣን ተረከቡ።
ፕሬዝዳንቱ በሂጃብ አለባበስ ላይ ያሉ ደንቦች  እና በማኅበራዊ ገደቦች ላይ ያላቸው የተለሳለሰ አቋም እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ከመጋጨት ይልቅ ለመነጋገር ቃል መግባታቸው በማዕቀብ ለደከመችው አገር የተስፋ ጭላንጭል የሰጠ ነው።
ነገር ግን የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ይዘው በወራት ውስጥ እስራኤል ከባድ ጥቃቶችን ፈጸመች።
አሜሪካም ይህንን ተከትላ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ድብደባ ፈፀመች።
ቀድሞውንም ደካማ የነበረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት የበለጠ ተደቆሰ።
በመላ አገሪቱ የኤሌትሪክ ኃይል እና የውሃ እጥረት ተከሰተ።
እአአ በ2024 ለአጭር ጊዜ ብልጭ ያለው ብሩህ ተስፋ ወደ ተስፋ መቁረጥ የተለወጠ መሰለ።
አጭሩ መልስ የኢራን ፕሬዚዳንት ያስተዳድራል እንጂ ገዢ ወይንም መሪ አይደለም የሚለው ነው።
እንደ ሌሎች አገራት የኢራን ፕሬዝዳንት በግዛቱ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ሰው አይደሉም።
በእስላማዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት እውነተኛው ሥልጣን ያለው በጠቅላይ መሪው እጅ ነው።
እአአ ከ1989 ጀምሮ ያ ቦታ በጦር ኃይሉ፣ በፍትሕ አካላት፣ በስለላ አገልግሎቶች እና በወሳኙ የውጭ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በሚያደርጉት በአያቶላ አሊ ኻሜኔ እጅ ተይዘዋል።
ፔዝሽኪያን የፕሬዚዳንትነት ወንበሩን አሸንፈው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሥልጣኑ ሁልጊዜ በሥርዓቱ ያልተመረጡ የሥልጣን ማዕከላት ማለትም በአብዮታዊ ዘብ፣ የበላይ ጠባቂው ምክር ቤት እና በጠቅላይ መሪው ጽ / ቤት የተገደበ ነው።
የካቢኔ አባላቱን እንኳን የጠቅላይ መሪውን ይሁንታ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።
ወደ ዲፕሎማሲው ሲመጣ፣ በኒውክሌር መርሃ ግብርም ሆነ በቀጠናዊ ውጣጥረቶች ምላሽ ሲሰጡ ፔዝሽኪያን ብዙ ጊዜ እንደ ውሳኔ ሰጪ ሳይሆን እንደ ቃል አቀባይ በሌላ ቦታ ተወስነው የመጡ ጉዳዮችን ያስፈጽማሉ።
የፎቶው ባለመብት, Majid Saeedi / Getty Images
በኢራናውያን ዘንድ "የአሜሪካ ምርጫ የሚያስከትለው ዳጋ የሚመለከተው እኛን ስለሆነ በምርጫው ላይ ድምጽ እንድንሰጥ መፈቀድ አለበት" የሚል ረዥም ዓመት ያስቆጠረ ቀልድ አለ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ሐውስ ዳግም መመለሳቸውን ተከትሎ ይህ ከመቼውም ጊዜ በላይ እውነት ነበር።
የትራምፕን ለሁለተኛ ጊዜ መመረጥ ብዙዎች ለቴህራን በጣም መጥፎ አጋጣሚ አድርገው ነው ያዩት።
የመጀመሪያው የፕሬዝዳንትነት የሥልጣን ዘመናቸው የአሜሪካ እና የኢራንን ግንኙነት ወደ ገደል አፋፍ ገፍቶታል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በአንድ ወገን ኢራን በትጋት ከተደራደረችው የኒውክሌር ስምምነት አገራቸውን አስወጥተው ከባድ  ማዕቀቦችን የጣሉ ሲሆን፣ የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን የሆኑት ጄኔራል ቃሴም ሱሌይማኒ እንዲገደሉ አዝዘዋል።
የትራምፕ ወደ ሥልጣን መመለስ ችግርን እየመጣ መሆኑን አመልክቷል፤ ኢራንም ይህንኑ ታውቃለች።
ብዙም ሳይቆይ እስራኤል በኢራን ቀጣናዊ አጋሮች ማለትም በጋዛ በሐማስ፣ በሊባኖስ በሒዝቦላህ እና በየመን በሁቲዎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻዋን አጠናክራለች።
ከዚያ በኋላ የተከተለው ዓመት በተባባሰ ግጭት የጠነከረ ነበር።
ለፔዜሽኪያን ይህ በጣም የከፋው ጊዜ ነበር። ለስላሳ የሆኑት ፕሬዚዳንት ከሁለት ወገን በሚሰነዘርባቸው ትችት እና ነቀፋ ተያዙ።
ከአሜሪካ እና እስራኤል በኩል የሚያላጋቸውን ማዕበል ለመቀየር ምንም ዓይነት አቅም አልነበራቸውም።
የፎቶው ባለመብት, Majid Saeedi / Getty Images
ከእስራኤል ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት ያሳዩት ባህሪ በሕዝብ ዘንድ ተስፋ መቁረጥን ፈጥሯል።
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት የጀመረችው ባለፈው ሰኔ መጀመሪያ ላይ በኢራን ምድር ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ በከፈተችበት ወቅት ነበር።
በርካታ የኢራን ከተሞች ከፍተኛ የአየር ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ ይህም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
በዚህ ወቅት ፔዝሽኪያን በችግር ውስጥ ያለን ሕዝብ የሚመሩ መሪ መስለው ሊታዩ አልቻሉም።
የኢራን ከተሞች በእስራኤል ቦምቦች እና ሚሳዔሎች ሲደበደቡ እና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ሲገደሉ ፕሬዝዳንቱ ልክ እንደ ጠቅላይ መሪው ዝምታን መረጡ።
ቀስቃሽ ንግግሮች የሉም፤ ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ላይ አልታዩም። እንዲሁም በእስራኤል ሚሳዔል ፍዳውን ለሚያየው ሕዝብ ተገቢ የሆነ የግንኙነት መስመር አልነበራቸውም።
በሌሎች ቦታዎች ከሚገኙ የጦርነት ጊዜ መሪዎች ጋር ያላቸው ልዩነት በጣም አስደናቂ ነበር።
አንዳንድ ኢራናውያን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ "አንተ ዜሌንስኪ አይደለህም" ሲሉ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ሩሲያ አገራቸውን በወረረችበት ወቅት ካሳዩት አመራር ጋር አነጻጽረዋቸዋል።
የኢራን ሕዝብ ማፅናናትን እና መፍትሄን በሚፈልግበት በዚያ ወቅት፣ ፔዝሽኪያን አፋቸው እንደተሸበበ ታየ፤  እና ለብዙዎች ይህ ከመሪ የማይጠበቅ እና አግባብነት የሌለው ተግባር ነበር።
የፎቶው ባለመብት, Majid Saeedi / Getty Images
በኢራን ውስጥ ያለው ማኅበራዊ ገጽታም በውጥረት የተሞላ ነው። በ2022 አገሪቱን ያናወጠው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ይመራ የነበረው "ሴት ፣ ሕይወት፣ ነፃነት" በሚል መፈክር ነበር።
ይህ በመላ አገሪቱ የተቀሰቀሰው የተቃውሞ ድምጽ በአብዛኛው ጋብ ያለ ቢሆንም፣ ነገር ግን ከኋላው ያሉት ጥያቄዎች እና ቁጣዎች አልተመለሱም።
ሴቶች ሂጃብ በግዴታ እንዲለብሱ የሚደነግገውን ሕግ መተላለፋቸውን ቀጥለዋል።
አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ተማሪዎች እየታሰሩ ነው።
ፔዝሽኪያን "ብሔራዊ እርቅ" እና "የጋራ መከባበር" እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
"ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ግንኙነትን እና የሂጃብ ሕግን ማስከበር አልችልም፤ ምክንያቱም በሰዎች ላይ ችግር ስለሚፈጥር ከሕዝቡ በተቃራኒ አልቆምም" ሲሉ በይፋ ተናግረዋል።
ነገር ግን ብዙ ኢራናውያን፣ በተለይም ወጣቶች፣ እንደዚህ ዓይነት ቃላቶች ምሳሌያዊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግን የማይጠቅሙ እንደሆኑ አድርገው ይመለከቷቸዋል።
እናም ያለ መዋቅራዊ ለውጥ፣ ለስላሳ ንግግር ፋይዳው ኢምንት ነው።
የፎቶው ባለመብት, Atta Kenare / AFP via Getty Images
ለበርካታ ኢራናውያን የፔዝሽኪያን የፕሬዝዳንትነት አንድ ዓመት ሥልጣን ምንም ለውጥ አላመጣም።
የዋጋ ንረት ጨምሯል፣ የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጡ ቀጥሏል፤ የፖለቲካ ነፃነቶች ባሉበት ደርቀው ቆመዋል።
በመንግሥት እና በሕብረተሰቡ መካከል ያለው ልዩነትም እየሰፋ ሄዷል።
ፕሬዝዳንቱ ስለ አንድነት ሊናገሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን አንድነት፣ በተለይም እውነተኛ ሥልጣን ከቢሮው ሩቅ በሆነበት በዚህ ሁኔታ በአዋጅ ሊመጣ አይችልም።
ኢራን በዲፕሎማሲያዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በይደር የማይቆይ ጥያቄ ገጥሟታል።
አመራሩ መንገዱን መቀየር ካልቻለ ወይም ካልፈቀደ ተንታኞች እንደሚናገሩት የሚቀጥለው ስብራት ከእስራኤል ሚሳዔል ወይም ከአሜሪካ ማዕቀብ ሳይሆን ከአገር ውስጥ የሚመጣ ነው።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images
ለወጣቶቹ የሜካኒካል ኢንጂነሮች ቀድሞ ቀልባቸውን የሚሰርቀው የግድቡ ግንባታ የሚካሄድበት ስፍራ ግዝፈት ነው።
አሁን በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የአፍሪካ ግዙፉ የሃይድሮ ኤሌትሪክ ግድብ በ2003 ዓ.ም. የመሠረት ሥራውን ለማስጀመር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየቆፈሩ ነበር።
ሞገስ የሺዋስ በ2003 ዓ.ም. በሙያው በቂ ልምድ ለማግኘት ተስፋ ሰንቆ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሲደርስ ገና የ27 ዓመት ወጣት ነበር።
የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ አገሩን እንደሚቀይር ተስፋ ቢያደርግም የእርሱንም ሕይወት ቀይሮታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማክሰኞ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በይፋ ሲመረቅ ለአገሪቱ የኤሌትሪክ ብርሃን መስጠት ብቻ ሳይሆን ለቀጠናውም ኃይል ያቀርባል ብለዋል።
1.78 ኪሎ ሜትር የተዘረጋው ይህ ግዙፍ ግድብ 145 ሜትር ከፍታ አለው።
11 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትሮች ካሉት ኮንክሪት የተገነባው የሕዳሴ ግድብ፣ ንጋት ተብሎ የተሰየመ ግዙፍ ሐይቅ ፈጥሯል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ይህ ግዙፍ ግድብ ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ጋር ብዙ አለመግባባቶችን ፈጥሯል።
በተለይ ከግብፅ ጋር ውጥረት የፈጠረው ይህ ግድብ፣ ወደ ግጭት የመግባባት አዝማሚያ የታየባቸው ምልልሶችም ተሰምተውበት ያውቃል።
ለኢትዮጵያውያን ይህ የሕዳሴ ግድብ የኩራት ምንጭ፣ እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመለካከት በዓለም መድረክ በጽኑ መሠረት ላይ እንድትቆም የሚያደረጋት ነው።
አሁን 40 ዓመት የሞላው ሞገስ ደግሞ "የዚህ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል" ይላል።
"ቀን በቀን የግድቡን ዕድገት ማየት ጥልቅ እርካታ የሚሰጥ ነበር።ወደዚህ ሥራ ፈልጌ ነው የመጣሁት፤ ነገር ግን ከጊዜ ብዛት ሥራ የመሆን ስሜቱ እየጠፋ መጣ። ከፕሮጀክቱ ጋር ቅርበትን አዳበርኩ ልክ እንደራሴ መጻዒ ዕድል የእርሱም ያስጨንቀኝ ጀመር።"
"ከቤተሰብ ለረዥም ጊዜ ተለያይቶ መቆየት ፈታኝ ነበር" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
ሞገስ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ወደሚኖሩት ቤተሰቦቹ በዓመት ሁለት ሦስቴ ይሄዳል።
ግድቡ የሚገኝበት ሩቅ ስፍራ፣ አንዳንዴ 45 ዲግሪ ሴንቴግሬድ የሚደርሰው ከፍተኛ ሙቀት እንዲሁም ረዥም የሥራ ሰዓት ፈተናዎች መደቀናቸው አልቀረም።
"እንሠራ የነበረው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ነበር፤ ለምሳ የአንድ ሰዓት እረፍት ብቻ ነበረን። ከዚያ ለምሽት ተረኞች እናስረክባለን። ምክንያቱም ግንባታው ሳይቋረጥ ነው መቀጠል ያለበት" ይላል ሞገስ።
የእርሱ ኃላፊነት የግንባታው ሂደት በአግባቡ መከናወኑን መከታተል እና የግንባታ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።
በፖለቲካ አለመግባባት እና በብሔር ፖለቲካ ለምትናጠው ኢትዮጵያ ይህ የሕዳሴ ግድብ ሕዝቦቿን በእኩል ስሜት እና መንፈስ አንድ አድርጎ ያነሳሳ ፕሮጀክት ነው።
እንደ ኢንጂነር ሞገስ ያሉ በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ በቀጥታ ቢሳተፉም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደግሞ የላባቸውን ጥሪት ውጤት አዋጥተዋል።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለግድቡ ግንባታ ቦንድ በመግዛት፣ ስጦታ በመስጠት የሚችለውን አድርጓል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሺንግተን የግድቡን ግንባታ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ ቢናገሩም አዲስ አበባ ግን ከኢትዮጵያውያን ውጭ የማንም ሰባራ ሳንቲም በግድቡ ላይ አልዋለም ስትል አስተባብላለች።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን  ቅዳሜ ዕለት የሕዳሴ ግድቡን ምርቃት አስመልከተው በሰጡት መግለጫ ላይ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ለግንባታው ወጥቶበታል ብለዋል።
አቶ ሞገስ ከአጠቃላይ ወጪው ውስጥ 223 ቢሊየን ብር ወይም 91 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነውም ብለዋል።
ቀሪው 9 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከሕዝብ ተሳትፎ የተገኘ ገንዘብ መሆኑን በመጥቀስ 18.9 ቢሊየን ብር በኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያዊን የቦንድ ሽያጭ፣1.6 ቢሊየን ብር በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያን የቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ፣ 3.2 ቢሊየን ብር ከስጦታ ተሰብስቧል ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images
ከደሞዛቸው በመቀነስ ለግድቡ ካዋጡ ሰዎች መካከል አንዱ ኪሮስ አስፋው ነው።
ነርስ የሆነው ኪሮስ የትግራይ ክልል ነዋሪ ሲሆን፣ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ከ2003 ዓ.ም አንስቶ በየዓመቱ ቦንድ ገዝቷል።
ከ100 ጊዜ በላይ ቦንድ ገዝቻለሁ የሚለው ኪሮስ፣ በትግራይ የባንክ እና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎት ተቋርጦ በነበረበት የሁለት ዓመቱ ጦርነት ጊዜ ብቻ ማቋረጡን ይናገራል።
ኪሮስ ለግንባታው የሚሆን ገንዘብ ያለማቋረጥ ለማዋጣት የተነሳሳው የግድቡ ግንባታን ያስጀመሩት "የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው የተከሉበት መነሳሳት" መሆኑን ያስታውሳል።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መላው ኢትዮጵያውያን የግድቡን ግንባታ ለማገዝ መረባረብ እንዳለባቸው ተናግረው ነበር።
የፎቶው ባለመብት, Amensisa Negera / BBC
የአምስት ልጆች አባት የሆነው ኪሮስ "እስከ መጨረሻው ድረስ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባሁ" ይላል።
አሁን ግድቡ ኃይል እንዲያመነጭ የተገጠሙለት ተርባይኖች ሁሉ ሥራ የጀመሩት የሕዳሴው ግድብ የሚያመጣው አስተዋጽኦ ላይ ሁሉም ዓይኑን ጥሏል።
ይህ ግድብ አገሪቱ ከምታመነጨው ግማሽ በላይ የሆነ የኤሌትሪክ ኃይል፣ 5100 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ሲሆን፣ ሚሊዮኖችን የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኤሌትሪክ ተጠቃሚ አይደለም።
"በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ መቀነስ የምንፈልገው ይህንን ነው። በአውሮፓውያኑ 2030 ቢያንስ 90 በመቶ የሚሆነው ሕዝባችን የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው የምንፈልገው" ብለዋል።
የ35 ዓመቷ ጌታነሽ ጋቢሶ የምትኖረው ከሐዋሳ በቅርብ ርቀት በሚገኝ አላሙራ የገጠር መንደር ውስጥ ነው።
የእርሷ ሕይወት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከሚኖሩ በርካታ ዜጎች ሕይወት ጋር ይመስላል።
እርሷ እና ባለቤቷ ከሦስት ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩበት ከሐዋሳ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኘው በጭቃ የተሰራው ደሳሳ ጎጆ የኤሌትሪክ ብርሃን አይቶ አያውቅም።
ምግብ ለማብሰል በአካባቢዋ ከሚገኝ ደን እንጨት ትለቅማለች።
ለመብራት የምትጠቀመው ደግሞ በጋዝ የሚሠራ ኩራዝ ነው።
ባለቤቷ ገረምሳ ጋልቻ የቤተሰቡ ጤንነት ያሳስበዋል።
"እሷ ትልልቅ እና ውብ ዓይኖች ነበሯት።ይህንን ሁሉ ዓመት በጭስ ስትጨናበስ ዓይኖቿ ሟሙ። አሁን ዝም ብለው ያለቅሳሉ" ይላል።
"ጭሱ ልጆቼን ቢያፍንብኝ ምን እንደማደርግ አላውቅም" ሲል ጭንቀቱን ለቢቢሲ አጋርቷል።
ጌታነሽ በሚመሽበት ወቅት የባሏን ሞባይል ተጠቅማ እንደምትንቀሳቀስ በመግለጽ፣ "መብራት ገብቶ ቀን ወጥቶልን" ስትል እንደምታልም ትናገራለች።
"ቤቴ በብርሃን ሲጥለቀለቅ ማየት እፈልጋለሁ። አሁን ሌሎች የኤሌትሪክ መሳሪያዎች አያጓጉኝም። ሲመሽ ተግ የማደርገው የኤሌትሪክ ብርሃን ብቻ ነው የምፈልገው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።
እርሷም ሆነች ባለቤቷ የሕዳሴ ግድቡ የሚያመጣውን ልዩነት ለማየት ጓግተዋል። የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ግን ከብሔራዊ የኃይል ማከፋፈያ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የኃይል ማስተላለፊያ ለመዘርጋት ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ።
ትንንሽ ከተሞችን እና መንደሮችን የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በአስር ሺዎች ኪሎ ሜትር የሚቆጠር የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ይጠይቃል።
ነገር ግን ይላል ኢንጂነሩ ሞገስ በሕዳሴ ግድብ የተመረተው የኤሌትሪክ ኃይል ለውጥ ማምጣት ይችላል።
ሞገስ የሕዳሴ ግድቡ ሥራ ላይ እያለ አንድ ልጅ ወልዷል።
"የሚገባኝን ያህል አጠገቡ አለመሆኔን ሳስብ የሚረብሽ ስሜት ይሰማኛል" ያለው ሞገስ "ነገር ግን ባበረከትኩት አስተዋጽኦ የተነሳ መጪው ጊዜ ብሩህ እንደሚሆን አውቃለሁ፤ ስለዚህም ሲያድግ ይህንን ስነግረው በኩራት ነው" ብሏል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ግንባታው 14 ዓመታትን የፈጀው እንዲሁም አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ የተበጀተለት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማክሰኞ፣ ጳጉሜ 4/ 2017 ዓ.ም ተመርቋል። የናይልን 55.ሚሊዮን ኪዩቢክ ውሃን የምትጠቀመውና ለዓመታት ኢትዮጵዮያ ግድብ እንዳትገነባ ስትከላከል የነበረችው ግብፅ የግድቡን ግንባታ ከጅምሩ ተቃውማዋለች። በሕዳሴ ግድብ የተካሄዱ አምስት የውሃ ሙሌቶችም ከግብፅ በኩል ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎችን ያስከተሉ ናቸው።
ከ15
ዓመታት በኋላ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውን ሆነ ያሉት የጣሊያኑ ሳሊኒ (ዊ ቢውልድ)  ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ፔትሮ ሳሊኒ፤ ግድቡን ለመገንባት የነበረውን ውጣ ውረድ እና የተከፈለውን ዋጋ ገልፀዋል።
“ለእኔ እና ለአገሪቱ ሕልማችን እውን ሆነ። ዛሬ ከዚህ በላይ እንዴት መኩራት ይቻላል?” ያሉት፤ ይህን ስኬት እውን ላደረጉ የግንባታውን ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።
የህዳሴግድብ ፕሮጀክትን “በዓለም በጣም ደኅንነት የነበረው ፕሮጄክት ነው” ያሉት ሳሊኒ፤ ሆኖም ግን ታላቅ ስኬቶች ዋጋ እንደሚከፈልባቸው ሁሉ በግድቡ ግንባታ ሂደት የሰው ዋጋ መከፈሉን አንስተዋል።
ፔትሮሳሊኒ ባለፉት 15 ዓመታት፤ 33 ሠራተኞች በመንገድ አደጋ እና በሌሎችም ሁኔታዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ አስታውቀዋል።
የግዱቡ ግንባታ ሂደት ጋር በተያያዘ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መዘገቡን ተከትሎ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
ለዚህስኬት ሕይወታቸውን ለሰጡ ሠራተኞች ያላቸውን ከበሬታ የገለፁት ሳሊኒ ለቤተሰቦቻቸውም ትውስታቸው አይጠፋም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከ10
ሺህ በላይ ሰራተኞች ተቀይረው መስራታቸውን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ 250 ሺህ ሰዓት ሠራተኞችን ስለ ደኅንነት ለማሰልጠን እንደዋለ ጠቅሰዋል።
25 ሺህ ወጣቶች በሥራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደተሰጣቸው ጠቅሰው፤ ይህም ለአገሪቱ ወደፊት መሰረታዊ አበርክቶ ይኖረዋል ሲሉ በሙሉ ልብ ተናግረዋል።
የግድቡን መሠረት ካሳረፉት እና በግድቡ ዙሪያ ሥማቸው በጉልህ ከሚነሳው ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በቅርበት መስራታቸውን የተናገሩት ሳሊኒ፤ ከመለስ ዜናዊ ጋር ያደረጉትን ንግግርም ጠቅሰዋል።
“‘ለዚህ አገር ሕልም አለኝ፤ የተትረፈረፈ የኃይል ሉዓላዊነት። ዓባይ ላይ ፕሮጀክት ልትነድፍልኝ ትችላለህ? ታላቅ ፕሮጀክት፤ ቢያንስ ስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የሚያመነጭ እፈልግላሁ’ አለኝ። ፤በፍጥነት ስራው[አለኝ]’ ፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ሕይወቱ አለፈ” በማለት የግድቡን ውጥን እንዴት እንደተጠነሰሰ ገልፀዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር በግድብ ግንባታ እስከ ቤተሰባቸው ታሪካዊ ትስስር እንዳላቸው በስሜት የገለፁት ፔትሮ ሳሊኒ፤ ኢትዮጵያ በምንያህል ፈተና ውስጥ ተከባ ሕዳሴን እንደገነባችም ዘርዝረዋል።
“አገሪቱ ይህን ግድብ እንድትገነባ ማንም አልፈለገም። ማንም ገንዘብ ለማቅረብ አልፈለገም። ብዙ ፖለቲካዊ ጉዳዮች፤ ብዙ ችግሮች [ነበሩ]፤ ቀላል መፍትሔ አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊያን ችግር ፈሪ አይደሉም። አይበገሬ ናቸው። መገዳደር ወይም ጠላት ሲገጥማቸው ጥረታቸውን በእጥፍ ይጨምራሉ፤ ማግኘት ያለባቸውን ያገኛሉ” ብለዋል።
በታላቁ
ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ላይ በእንግድነት የታደሙ በርካታ አገራት መሪዎች የመልካም መግለጫ መልዕክቶቻቸውን  አስተላልፈዋል።
የኬንያ
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ “ታሪካዊ ስኬት” ላሉት የሕዳሴ ግድብ ምርቃት ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ በበኩላቸው በግድቡ ጉብኝት ወቅት የታዘብኩት የዓድዋ ድል ተምሳሌት በምህንድስና ጥበብ ዳግም ተገልጦ ነው ብለዋል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት በቅርቡ አገራቸው እንደምትፈጽም ተናግረዋል።
ታላቁ
ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምህንድስና ምኞት ብቻ አይደለም ያሉት ሩቶ፤ አፍሪካ እጣ ፈንታዋን እንደምትወስን ደማቅ ማረጋገጫ ነው ሲሉ አብስረዋል።
“ዛሬ
ይህን ታላቅ ድል ስናከብር ዘላቂነት ላለው የወዳጅነትን ትስስርን፣ ትብብር እና የጋራ ራዕይ እናረጋግጣለን” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ሕዳሴ የአፍሪካ ቀንድ
አገሮችን እና ሰፊው የናይል ተፋሰስ አገራት አያያዥ አድርገው ገልፀዋል።
አገራቸው
ኬንያ ከጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
“.
. .ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ፕሮጀክት ብቻ አይደለም። የፓን አፍሪካን መገለጫም እንጂ። አቅም እና ምኞት በአፍሪካዊያን የተመራ መሠረተ ልማት፣ ከአፍሪካ ኅብረት ርዕይ የሆነው አህጉሪቱ በኃይል ማስተሳሰር የተሳሰረ ነው” ብለዋል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በበኩላቸው ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ የቀጠናውን አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረው፣  በቅርቡ አገራቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትፈፅም ጠቁመዋል።
ይህም በደቡብ ሱዳን ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ከተሞች ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እንደሚፈታ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ግድቡ ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ አዲስ ምዕራፍን የሚከፍት ነው ብሲኦኡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ለኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ አስተላልፈዋል።
የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ በበኩላቸው በግድቡ ጉብኝት ወቅት የታዘብኩት የዓድዋ ድል ተምሳሌት በምህንድስና ጥበብ ዳግም ተገልጦ ነው ሲሉ ታላቁ ሕዳሴ ግንባታን መጠናቀቅን
አሞካሽተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ፥ የሕዳሴ ግድብ እውን መሆን ውኃን ገድቦ ኃይል ከማመንጨት እና ከአስደናቂ የምህንድስና ውጤት በላይ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ግድቡ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊእና የደኅንነት ዘርፎችም ከሚኖረው ጥቅም በላይ የሚያኮራው ኢትዮጵያዊያን ግድቡን እውን ለማድረግ የተጓዙበት መንገድ መሆኑንም ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር በ30 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነቡ ስድስት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ዝርዝር ይፋ ያደረጉ
ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ ይውላል ያሉት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ኢትዮጵያ የሕዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት መገንባት በቅርቡ ትጀምራለች” ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ኒውክሌር ልማቱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም በቅርቡ ከአቶሚክ ኃይል ኤጄንሲ ኃላፊ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው
መነጋገራቸው ይታወሳል።
ከዚህ ባሻገርም የነዳጅ ማጣሪያ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሥራ እንደሚጀመር አብስረዋል።
የጋዝ ፋብሪካ፣ የኤርፖርት ማስፋፊያ እና የቤቶች ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቂት ዓመታት ይጀመራሉ ካሏቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች
መካከል ተካተዋል።
“የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያሰምሩ ሜጋ ሜጋ ፕሮጄክቶች፤ ያልገለፅኳቸውም ጭምር ከፊታችን ስላሉ ከዚህ ሰዓት በኋላ ኢትዮጵያውያን በሠራነው ገድል ሳይሆን ከፊታችን ለሚጠብቀን ከባድ ሥራ ታጥቀን እንድንነሳ. . . “ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
“ለዘመናት ስንመኘው የነበረው ነዳጅ የማውጣት ፍላጎታችንን፤ ህልማችንን እውን የሚያደርገው [የነዳጅ] ማጣሪያ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሥራ ይጀምራል” ብለዋል።
“የኢትዮጵያ የማንሰራራት የመጀመሪያው ቀን” ሲሉ ሁነቱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት “በትንሹ 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ለኢትዮጵያዊያን ይገነባሉ” ሲሉም አክለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዳሴው ግድብ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር ግድቡ ለጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ሆኖ የሚቆይ ነው አሉ።
ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ ሕዳሴ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን “ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ምድር እስክትሰበሰብ ታሪክ ሆኖ የሚኖር
ታላቅ ገድል ነው” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት ባደረጉት ንግግር በተለያየ አመለካከት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ግድቡን
መጥተው እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "የእኔ ምኞት ኢትዮጵያዊ ይህንን ገድል፣ ይህንን ታሪክ፣ ይህንን ሥራ ሳያይ እንዳያልፍ ብቻ ነው"
ሲሉ ተናግረዋል።
ሕዳሴን በንግግር በምሥል መግለጥ አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መጥቶ ያየ ሰው ብቻ ልኩን መገንዘብ እንደሚችል ተናግረው ኢትዮጵያውያን ይህ ትውልድ የሠራውን ገድል እየመጡ እንዲጎበኙ "ምኞቴና ፍላጎቴ ነው" በማለት ጥሪ አቅርዋል።
“ለተቀረው የጥቁር ሕዝብ ደግሞ ግብዣዬ ነው" ሲሉም አክለዋል።
"ጥቁሮች እንደምንችል፣ ጥቁሮች እንደምናሳካ በጥቁር ዘር ታሪክ የመጀመሪያው ሕዳሴ ነው።"
ሕዳሴን "የትናንት ቁጭት ማሰሪያ፣ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ" ሲሉ የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአሁኑ ወቅት 74 ትሪሊየን ውሃ መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።
የሕዳሴ ግድብ ሲመረቅ ለተገኙ አገራት መሪዎች ደግሞ  "የኢትዮጵያ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ከሃብቷ ከልምዷ የምታቋድሳችሁ
እንደሚሆን አረጋግጥላችኋለሁ" ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ለታችኛው ተፋሰስ አገራት በማለትም ኢትዮጵያ ሕዳሴን የሠራችው ለመበልፀግ፣ አካባቢውን በብርሃን ለመሙላት፣ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ
ለመቀየር እንጂ በፍፁም ወንድሞቿን ለመጉዳት አይደለም በማለት የውሃው ፍሰት እንደማይቀንስ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
ለግብፅ እና ሰለሱዳንም የአብረን እንሥራ፣ በጋራ እንቁም ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዳሴ ግድብ ለረዥም ዓመት ላገለገሉ የተለያዩ ባለሙያዎች የክብር ኒሻን ሸለሙ።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በግድቡ ግንባታን በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች አበርክቶ ያሳረፉ ኃላፊዎች
የአገሪቱን የክብር ኒሻን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተበርክቶላቸዋል።
ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ኢንጅነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን የግድቡ ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ኢንጅነር ከማል አህመድ የግድቡ ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ በላቸው ካሳ የግድቡ የፕሮጀክት ሳይት አስተባባሪ ከተሸለሙት መካከል ናቸው።
ይሁን እንጂ ግድቡን ከተጀመረበት 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ዓመታት በሥራ አስኪያጅነት የመሩት እና በአዲስ አበባ
መስቀል አደባባይ በአነጋጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ የተገኘው ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ሽልማት አልተበረከተላቸውም።
እስከ 2014 ዓ.ም. ድረስ ኸልዝ ኤንድ ሴፍቲ ኢንቫይሮመንት ኮርዲኔተር ሆነው የሠሩት ምንተስኖት "በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች የሞቱበት መንገድ አለ" ይላሉ።
"ከሥራ ጋር በተገናኘ በአደጋ የሚሞቱበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። የግድቡን ኅልውና በማስጠበቅ፣ ከተለያዩ ቦታዎች ላይ ቁሳቁሶችን በማመላለስ፣ ጥቃት ሲደርስ ስለነበር በዚያ ሰዓት የተሰዉ ወገኖችም፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትም ሊኖሩ ይችላሉ" ብለዋል።
ነገር ግን በትክክል መናገር የሚችሉት ከግድቡ ግንባታ ሥራ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን በተመለከተ እንደሆነ አስረድተዋል። "ከዚህ ጋር በተያያዘ የነበረው ሞት በጣም ጥቂት ነው። 15 ሺህ ከሚለው አንጻር ጋር ሲታይ በጣም ጥቂት ነው የነበረው" ብለዋል።
"እኛ ሳሊኒ ጋር የነበረው ከሥራ ጋር የተያያዘ የሞተ ሰው ከ100 የሚያልፍ አይመስለኝም። 100ም የሚደርስ አይመስለኝም" ሲሉም አክለዋል።
በሕዳሴ ግድብ ግንባታ "15 ሺህ ሰዎች ሞተዋል" ስለመባሉ የግድቡ የሠራተኞች ደኅንነት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
የደም፣ የላብ እና የውሃ ጠብታ ምልክት ሆኖ የተሰራው የጠብታ ሐውልት ተመረቀ።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መገኛ የተሰራው ይህ የጠብታ ሐውልት በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና በባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ
ሞትሊ ነው የተመረቀው።
ይህ ሐውልት በግንባታ የተሳተፉትን የኅብረተሰብ ክፍሎች
የሚያሳይ ነው ተብሎ።
በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የሕዳሴ ግድብ በ2003 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ይህ የኤሌትሪክ
ኃይል ማመንጫ ግድብ 233 ቢሊየን ብር ለግንባታ እንደወጣበት ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የተናጠል እርምጃ ወስዳ የግድቡን ሙሌት
ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ይህም ሁልጊዜም በታችኛው ተፋሰስ አገራት ዘንድ ስጋትን ሲያጭር ቆይቷል።
የሕዳሴ ግድብ 13 ተርባይኖች የሚኖሩት ሲሆን
አጠቃላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅሙ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት እንደሚደርስ ተገልጿል።
ታላቁ የሕዳሴ ግደብ ዛሬ ማለዳ የጎረቤት አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የክልል ባለሥልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው
ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ከተገኙ የአፍሪካ መሪዎች መካከል የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት
ኢስማኤል ኡማር ጌሌ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይገኙበታል።
እንዲሁም የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አሞር ሞትሊ እና የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ተገኝተዋል።
ይህ ግድብ በብሔር ግጭት በምትናጠው አገር ውስጥ ሕዝቧን በአንድ መንፈስ በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው የፀጥታ ጥናት ተቋም ተንታኝ ሞሰስ ክሪስፐስ ኦኬሎ "ኢትዮጵያውያን እንጀራን እንዴት መበላት አንዳለበት ላይስማሙ ይችላሉ፤ በግድቡ ላይ ግን ይስማማሉ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። የሚመለከቱትም በወንዝ መሀል እንደቆመ የኮንክሪት ክምር ሳይሆን ለስኬታቸው እንደቆመ ሐውልት ነው። ግንባታው በ2003 ዓ.ም. ሲጀመር ግድቡን በገንዘብ ለመደገፍ በርካቶች ቃል ገብተዋል።"
ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ የበላይነት የተቀዳጀችበት ግዙፉ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የሕዳሴ ግንባታን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከሱዳን እና ግብፅ ጋር አለመግባበት ውስጥ ቆይታለች።
ግብፅ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ላለፉት አስራ አራት ዓመታት በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ሲደራደሩ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ሦስቱንም አገራት የሚያስማማ ሁሉን አቀፍ መግባባት ላይ መድረስ አልተቻለም።
በ2003 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረው ይህ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ 233 ቢሊየን ብር ለግንባታ እንደወጣበት ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የተናጠል እርምጃ ወስዳ የግድቡን ሙሌት ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ይህም ሁልጊዜም በታችኛው ተፋሰስ አገራት ዘንድ ስጋትን ሲያጭር ቆይቷል።
ኢትዮጵያን ከግብፅ እና ከሱዳን ጋር ሲያወዛግብ የቆየው የሕዳሴ ግድብ ቁልፍ ክስተቶች
ባልደረቦቻቸው፣ የሚያውቋቸው፣ የቤተሰብ አባሎቻቸው ስለ እርሳቸው ሲጠየቁ ሳይጠቅሱ የማያልፉት ሙሉ ጊዜያቸውን ለግድቡ መስጠታቸውን ነው። ይህ ግብራቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተመሰከረለት ነው።
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን በአንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ "ስመኘው ልጆቹን፣ ሚስቱን እና ቤተሰቡን ትቶ ያገባው ሕዳሴን ነበር" ብለዋል።
የቤተሰብ አባሎቻቸውም የሚያስረግጡት ይህንኑ ነው።
የኢንጂነሩን ሕልፈት ተከትሎ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የቤተሰብ አባል "እሱ አገሬን ሥራዬን እያለ ሁሉም ሰው ረስቶታል። እሱ ሁሉ ነገሩ ሥራው ላይ ነበር። ዘመድ አይልም . . ." ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እኚህ የቤተሰብ አባል እንዳሉት ኢንጂነሩ ማኅበራዊ ሕይወት የሚባል ነገር እንኳን አልነበራቸውም።
ኢንጂነሩ ለሕጻናት ልጆቻቸው፣ ለደካማ ቤተሰቦቻቸው፣ ለራሳቸው እንዲሁም ለማኅበራዊ ሕይወታቸው መስጠት ያለባቸውን ጊዜ ሁሉ ለግድቡ ገብረዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ "ፊት" የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሲታወሱ
ለወጣቶቹ የሜካኒካል ኢንጂነሮች ቀድሞ ቀልባቸውን የሚሰርቀው የግድቡ ግንባታ የሚካሄድበት ስፍራ ግዝፈት ነው።
አሁን በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የአፍሪካ ግዙፉ የሃይድሮ ኤሌትሪክ ግድብ በ2003 ዓ.ም. የመሠረት ሥራውን ለማስጀመር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየቆፈሩ ነበር።
ሞገስ የሺዋስ በ2003 ዓ.ም. በሙያው በቂ ልምድ ለማግኘት ተስፋ ሰንቆ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሲደርስ ገና የ27 ዓመት ወጣት ነበር።
የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ አገሩን እንደሚቀይር ተስፋ ቢያደርግም የእርሱንም ሕይወት ቀይሮታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማክሰኞ ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በይፋ ሲመረቅ ለአገሪቱ የኤሌትሪክ ብርሃን መስጠት ብቻ ሳይሆን ለቀጠናውም ኃይል ያቀርባል ብለዋል።
የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ እና የፈጠረው ተስፋ
የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዛሬ ማክሰኞ ጳጉሜ 4
2017 ዓ.ም. የተለያዩ የጎረቤት አገራት መሪዎች በተገኙበት ተመረቀ።
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የጂቡቲው
ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ እንዲሁም የሶማሌው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ ተገኝተዋል።
የጂቡቲው እና የኬንያው
ፕሬዚዳንት በሕዳሴው ግድብ የተቀመጠውን የምረቃ መጋረጃ ከፍተው መርቀውታል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ
ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች
እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
የሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠው በ2003 ዓ.ም ሲሆን ለማጠናቀቅ 14 ኣመታትን ፈጅቷል።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ለግንባታው ወጥቶበታል።
ከአጠቃላይ ወጪው ውስጥ 223 ቢሊየን ብር ወይም 91 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ሲሆን ቀሪው 9 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከሕዝብ ተሳትፎ የተገኘ ገንዘብ ነው።
18.9 ቢሊየን ብር በኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያዊን የቦንድ ሽያጭ፣1.6 ቢሊየን ብር በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያን የቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ፣ 3.2 ቢሊየን ብር ከስጦታ ተሰብስቧል።
1.78 ኪሎ ሜትር የተዘረጋው ይህ ግዙፍ ግድብ 145 ሜትር ከፍታ አለው።
ግድቡ 13 ተርባይኖች ያሉት ሲሆን ከ5000 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጫል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በየሳምንቱ በባለሙያዎች የሚመከረው ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ብዙዎች ይቸገራሉ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለልብ ጤና ጠቃሚ ነው። የደም ግፊትንን፣ በስትሮክ የመጠቃት አጋጣሚን እና የኮሌስትሮል መጠንንም ይቀንሳል።
ሁሌም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ተነሳሽነት እና ጊዜ ላይገኝ ይችላል።
አበረታች ውጤት ለማየት ምን ያህል ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ ነው የሚመከረው? የሚለውን ብዙዎች ይጠይቃሉ።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ አነስተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልማድ ያላቸው ሰዎች ውጤት ለማየት ብዙ መሥራት አይጠበቅባቸውም።
እንቅስቃሴ የማያዘወትር ሰው ትንሽ መንቀሳቀስ ሲጀምር የልብ ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል።
ምንም እንቅስቃሴ ካለማድረግ ተነስቶ በሳምንት ውስጥ ከአንድ ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት ሳይክል መንዳት ወይም በእግር መጓዝ መጀመር ይቻላል።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ በዚህም ከልብ ሕመም ጋር የተያያዙ በሽታዎች ተጋላጭነትን በ20 በመቶ መቀነስ ይቻላል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አብዝቶ በማድረግ ሰውነቱን ያስተካከለ ሰው ለልብ እና ተያያዥ ሕመም ተጋላጭነቱን የመቀነስ መጠኑ እንደሚቀንስ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ምንም የማይንቀሳቀስ ሰው በአንጻሩ በሳምንት ሁለት ሰዓት ገደማ ሲንቀሳቀስ ለልብ እና ተያያዥ ሕመም ተጋላጭነቱን ዝቅ እያደረገው ይሄዳል።
እንቅስቃሴው ወደ አራት ሰዓት ከፍ ካለ የሕመም ተጋላጭነትን የመቀነስ ምጣኔው  ወደ 10 በመቶ ይወርዳል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሳምንት ወደ ስድስት ሰዓት ከፍ ሲል የልብ እና ተያያዥ ሕመሞችን የመቋቋም አቅም የበለጠ ከፍ ይላል።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ ከዚህ ያለፈ ጥቅም ማግኘት ግን የማይቻል ነው።
ብዙም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸው እንደ ማራቶን ያሉ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ጥናት ተሠርቷል።
ተሳታፊዎቹ በሳምንት ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ሥልጠና ሲያደርጉ በልባቸው ላይ ለውጥ ታይቷል።
በዚህ መጠን እንቅስቃሴ የልብና ተያያዥ ሕመሞችን ለመቀነስ ያለው ሚና በሳምንት ለስድስት ሰዓት እንቅስቃሴ ከማድረግ ጋር እኩል ነው።
የጥናቱ ተሳታፊዎች የልባቸው ጡንቻ መጠን ጨምሯል። ደም አዘዋዋሪ ሕዋሳቸውም እንዲሁ።
ልብ እንደማንኛውም ጡንቻ በሥልጠና መጠኑ ሊጨምር ይችላል።
ከሚመከረው ሳምንታዊ የእንቅስቃሴ ሰዓት በተጨማሪ እንቅስቃሴ ማድረግ ውጤት ባይኖረውም የልብና ተያያዥ ሕመሞችን ለመቀነስ ዋጋ አለው።
በከፍተኛ ፍጥነት ማራቶን በመሮጥ የልብን አቀማመጥ ማስተካከልም ይቻላል።
እንዲህ ያለ ለውጥ ማሳየት የሚችሉት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ አትሌቶች ናቸው ተብሎ ይታሰብ ነበር።
ሆኖም ግን ጥናቱ እንደሚያሳየው ማንኛውም ሰው የልብ ጤናውን መጠበቅና እንደ አትሌቶች ያለ ልብ ማግኘት ይችላል።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ በሳምንት ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት እንቅስቃሴ በማድረግ ጀምሮ የልብ ጤናን ማሻሻል ይቻላል።
በሳምንት አራት ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ የበለጠ የልብ ጤናን ለመጠበቅ ያግዛል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሚወዱት የስፖርት ዓይነት መተካት ይቻላል።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ እንቅስቃሴ ካለማድረግ ተነስቶ በሳምንት አራት ሰዓት እንቅስቃሴ ወደ ማድረግ መሻገር ቀላል አይደለም።
በተለይ ደግሞ ጊዜ ለሌላቸው ሰዎች ፈታኝ ይሆናል።
ከፍተኛ መጠን ያለው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የልብ ጤናን ለመጠበቅ የግድ ነው።
ለ20 ደቂቃ የሚሠራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውስጥ ከ30 እስከ 60 ሰከንድ ከባድ እንቅስቃሴ በማከል መሀል ላይ እረፍት እየወሰዱ ማገባደድ ይቻላል።
የሚሠራበት ጊዜ አጭር ቢመስልም የእንቅስቃሴው ጠንካራ መሆን ለውጥ ያመጣል።
የተለያየ ዓይነት የልብ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ከፍተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ይመከራል።
አነስተኛ ወይም መካከለኛ ደረጃ እንቅስቃሴ ነው ማድረግ የሚጠበቅባቸው። ራስን ሳይጎዱ ጤናን መጠበቅ የሚቻልበት መንገድ ነው ብለው ባለሙያዎች ይመክራሉ።
በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊድስ የልብ ጤና ባለሙያ ፒተር ስዎቦባ እንደሚለው፣ ሙሉ ሳምንቱን እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችል ሰው በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቢያደርግም ውጤት ያገኛል።
37 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው፣ ሳምንቱን በሙሉ የሚደረግ እንቅስቃሴ በአንድ ወይም ሁለት ቀናት እንቅስቃሴ ተተክቶ ተመሳሳይ ውጤት ያሳያል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ወግ አጥባቂውን አክቲቪስት ቻርሊ ከርክን በመግደል የተጠረጠረው የ22 ዓመቱ ታይለር ሮቢንሰን፣ ዩታ ግዛት ውስጥ ከወላጆቹ ጋር ለረጅም ጊዜ ይኖር የነበረ የአካባቢው ተወላጅ መሆኑን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ከከርክ ግድያ በኋላ የተሠራጨውን የደኅንነት ካሜሪ ምሥል የተመለከቱት አባቱ ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መስከረም 2/2016 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲደረግ የነበረውን አደን ለማስቆም ወሳኝ እንደሆነ መርማሪዎች ገልጸዋል።
የተጠርጣሪው አባት የልጃቸውን ምሥል በተሠራጨው ምሥል ላይ ከተመለከቱ በኋላ እጁን እንዲሰጥ እንዳበረታቱት በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ሁለት የሕግ አስከባሪ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ከዚያም አባትየው ጉዳዩን ለፖሊስ ለጠቆመው የቤተሰባቸው ወዳጅ አሳውቀዋል።
ኤፍቢአይ ታይለር ሮቢንሰን በቁጥጥር ስር መዋሉን ባሳወቀበት ጊዜ ምርመራው በመቀጠሉ የተጠርጣሪውን የኋላ ታሪክ፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ለግድያው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ጉዳይ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።
የኤፍቢአይ ቃል አቀባይ "ትክክለኛ ተፈላጊ በቁጥጥራችን ስር እንዳለ እርግጠኞች ነን፣ ነገር ግን ስለማንነቱ እና ለምን እርምጃውን እንደወሰደ ሙሉ መረጃ ለማግኘት አሁንም እየሰራን ነው" ብለዋል።
የዩታ ግዛት አገረ ገዢ ስፔንሰር ኮክስ ለመርማሪዎች ቃላቸውን የሰጡ አንድ የቤተሰብ አባል ሮቢንሰን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ "የበለጠ ወደ ፖለቲካ እያዘነበለ" እንደመጣ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከጥቃቱ በፊት በእራት ላይ በነበረ ውይይት ወቅት ሮቢንሰን በዩታ ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ስለሚካሄደው የኪርክ ስብሰባ አንስቶ ነበር ተብሏል።
ቢቢሲ የተመለከታቸው ይፋዊ መዛግብት እንደሚያሳዩት ሮቢንሰን ቀደም ሲል በዩታ ውስጥ ለየትኛውም ፓርቲ ያልወገነ ወይም ገለልተኛ መራጭ ሆኖ ተመዝግቧል።ወላጆቹ ማቲው ካርል ሮቢንሰን እና አምበር ዴኒስ ሮቢንሰን የተመዘገቡ የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች መሆናቸውን መንግሥታዊ ሰነዶች ያሳያሉ።
የግድያው ተጠርጣሪ የሆነው ሮቢንሰን ከርክ ለተማሪዎች ንግግር እያደረገ በተገደለበት ዩታ ቫሊ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተማሪ አይደለም።
የዩታ የከፍተኛ ትምህርት ቦርድ ባወጣው መግለጫ ታይለር ጀምስ ሮቢንሰን በዲክሲ የቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሙያ ልምምድ ፕሮግራም የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ነበር ብሏል።
የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሮቢንሰን አባት የማዕድ ቤት መገልገያዎችን የሚሠሩ ባለሙያ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የማኅበራዊ አገልግሎት ሠራተኛ ናቸው።ቤተሰቡ የሞርሞን እምነት ተከታይ ሲሆን በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
መርማሪዎች በግድያው የተጠረጠረው ሮቢንሰን በበይነ መረብ ረጅም ጊዜ የሚያጠፋና በዚህ ልማድ የተዘፈቀ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎችን አግኝተዋል።
በቻርሊ ከርክ ግድያ የተጠረጠረው ታይለር ሮቢንሰን መያዙን መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ናቸው። አርብ ዕለት ፐሬዝዳንቱ ለፎክስ ቴሌቪዥን ተጠርጣሪው በአባቱ ተጠቁሞበት በቁጥጥር ስር መዋሉን አሳውቀዋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ተጠርጣሪው በተያዘበት ጊዜ የለበሰው ልብስ ጥቃቱን ፈጽሞ ከዩኒቨርስቲው ሲወጣ በታየበት ቪዲዮ ላይ ያደረገው እንደነበር መርማሪዎች አረጋግጠዋል።
ተጠርጣሪው ከቤተሰቦቹ ጋር በነበረው ውይይት ወቅት ቻርሊ ከርክን "በጥላቻ የተሞላ እና ጥላቻን የሚያሠራጭ" በማለት ሲወቅሰው ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ መረጃዎች ሮቢንሰን ላለፉት አስርት ዓመታት በአሜሪካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉት እና ብዙ ጊዜ በትራምፕ ፖሊሲዎች እና የቀኝ ፅንፈኛ ቡድኖችን የሚቃወሙት አክራሪ የግራ አክቲቪስቶች ስብስብ የሆነው አንቲፋ ወይም ፀረ ፋሺስት እንቅስቃሴ ደጋፊ ተደርጎ ሊታሰብ እንደሚችል ያመለክታሉ።
ባለሥልጣናት እንዳሉት ሮቢንሰን አሁን በሌሎች ማኅበረሰቦች ዘንድ ታዋቂ በሆነው በዋናነት በኢንተርኔት ጌሞች ወዳጆች የሚዘወተረው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በሆነው ዲስኮርድ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሳይሆን እንደማይቀር አመልክተዋል።
አብሮት የሚኖረው ጓደኛው በዚሁ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ "ታይለር" በሚል ስም ስለ ጠመንጃ አጠቃቀም እና መሳሪያውን ስለመደበቅ የሚገልጹ መመሪያዎችን በተመለከተ ተከታታይ መልዕክቶችን ለመርማሪዎች አሳይቷል።
ዲስኮርድ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በታይለር ስም ያለው አካውንት መታገዱን ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ". . . ፖሊሲያችንን በመጣሱ የተጠርጣሪውን መለያ አስወግደነዋል" ብሏል።
በአሁኑ ወቅት ዐቃቢያን ሕጎች መደበኛ ክሶችን አዘጋጅተው እስኪጨርሱ ድረስ ሮቢንሰን በእስር ላይ ይገኛል።
በቅርብ ጊዜ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ከሆኑ የፖለቲካ ግድያዎች አንዱ እንደሆነ በሚነገረው ግድያ አላማ እና የታሪክ ግንኙነት ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
በቻርሊ ከርክ ግድያ ተጠርጥሮ በተያዘው በ22 ዓመቱ ወጣት ታይለር ሮቢንሰን የኋላ ታሪክ፣ ለግድያው ያለው ምክንያት እና ፖለቲካዊ ዝንባሌውን በተመለከተ የሚደረገው ምርመራም ይቀጥላል።
ይህ የቻርሊ ከርክ ግድያ በቅርቡ የአሜሪካ ታሪክ ውስጥ በተከሰተ ጉልህ ፖለቲካዊ ግድያ ላይ የሚደረግ ምርመራ ይሆናል ሲሉ ባለሥልጣናት ገልጸውታል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ያለብንን በሽታ በትክክል ለማወቅ በጣም ውድ እና ወደ ሰውነታችን ዘልቆ በመግባት ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ የሚያስችሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች እንደሚያስፈልጉ እናስባለን።
በእርግጥ እነዚህ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቁ የህክምና መሣሪያዎች የሚሰጡት ጠቀሜታ አስገራሚ ነው።
ሆኖም ያለንበትን የጤና ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችሉ ብቸኛ ዘዴዎች አለመሆናቸውን ብንነግራችሁስ?
ሌሎቹ በሰውነታችን ውስጥ ያለን በሽታ ለማወቅ የሚረዱን ቤታችንን የሚጋሩ እንስሳት ናቸው።
በበሽታ እንደተያዙ ያላወቁ የቤት እንስሳት አሳዳሪዎች የጤና ችግር እንደነበረባቸው ኋላ ላይ ከእንስሳቶቻቸው መረዳት እንደቻሉ በርካታ የሕክምና ክስተቶች አስረድተዋል።
ለምሳሌ ውሻዎች የአሳዳሪዎቻቸውን ቆዳ [በኋላ ላይ የቆዳ ካንሰር ሆኖ የተገኘ] በመላስ፣ በማሽተት እና በአሳዳሪዎቻቸው ቆዳ ላይ ያለን ምልክት ለመንከስ በመሞከር ምልክት ሲሰጡ ነበር።
ይህንን የሚያደርጉ በርካታ የእንስሳት ዝርያዎች ቢኖሩም ጉንዳኖች፣ አይጦች እና ውሾች በሰው ልጅ ውስጥ ያለን በሽታ እና በምርምር ላይ ያሉ ናሙናዎችን የመለየት አቅማቸውን አሳይተዋል።
በእነዚህ እንስሳት የተለዩ በሽታዎች የተለያዩ ሲሆኑ ካንሰር፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ ኮቪድ 19 እና የሆድ ኢንፌክሽን ይገኙበታል።
አብዛኞቹ እነዚህ በሽታዎች በተለይ በሽታ የመከላከል አቅማቸው በተዳከመ ሰዎች ዘንድ ወደ ከፋ ደረጃ ሊሸጋገሩ ስለሚችሉ በጊዜ በሽታዎችን ማወቅ አስፈላጊ ነው።
በመሆኑም መሰል የሰው ልጆችን የሚያጠቁ  በሽታዎችን የሚለዩ ጥቂት አስገራሚ እንስሳትን እንመልከት።
ውሾች ፓርኪንሰን የተባለውን የነርቭ ህመም፣ የሽንት ፊኛ ካንሰር እና የወባ በሽታን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎችን ለመለየት ባላቸው ችሎታ ይታወቃሉ።
ለሕክምና አገልግሎት በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑ ውሾች የሚጥል በሽታን እንዲሁም የስኳር በሽታ ታማሚዎች በደማቸው ውስጥ የስኳር መጠን ዝቅተኛ መሆኑን መለየት ይችላሉ።
ውሾች በተፈጥሮ የተቸራቸው አስደናቂ የማሽተቻ የስሜት ህዋሳቸው ለመለየት የሚያዳግቱ የጠረን ውህዶችንም ቢሆን የተወሰኑትን ይለያሉ።
የውሾች የማሽተት ችሎታ ሰዎች ካላቸው የማሽተት ችሎታ ከ10 ሺህ ጊዜ በላይ የተሻለ ነው። የአፍንጫ ቀዳዳዎቻቸውን በመጠቀምም ያለምንም ተጨማሪ እርዳታ አዲስ ጠረኖችን የመመርመር ብቃት ተፈጥሮ ችራቸዋለች።
በሕክምናው ዘርፍ ባዮዲቴክሽን (በየቀኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚካሄዱ የኬሚካል ለውጦች) እና ለጤና ማስጠንቀቂያ የሚውሉ ውሾች አሉ።
እነዚህ ውሾች ቀደም ብለው ሽልማት እየተሰጣቸው ከተወሰኑ ጠረኖች ጋር የተያያዙ ሥልጠናዎች የተሰጣቸው ናቸው። ከዚያም የጠረኖችን ወይም የአካል እና የባህርይ ለውጦችን እንዲለዩ ተደርገው ይሠለጥናሉ።
በዚህም ሥነ ሕይወታዊ ለውጥን የሚለዩ - ባዮዲቴክሽን ውሾች የሆነ ጠረን በሚለዩበት ወቅት ሽልማት እንዲሰጣቸው ለመጠበቅ ባሉበት ይቆማሉ።
ለጤና ማስጠንቀቂያ የሚውሉ ውሾች ደግሞ ብዙውን ጊዜ ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ምልክት ለመስጠት ከባለቤታቸው ጋር ይተሻሻሉ፣ ይላፋሉ።
አይጦችም ልዩ ጠረኖችን የመለየት ብቃታቸው ከፍተኛ ነው።
ትልቅ የአፍሪካ ዝርያ ያላቸው አይጦች በሞዛምቢክ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ እና የተተው ፈንጂዎችን በጠረን ለመለየት ሲሠለጥኑ ቆይተዋል።
በሕክምናው ዘርፍም ወሳኝ አጋር መሆናቸውን እያረጋገጡ ነው። እያገገሙ ካሉ ህሙማን ከተወሰደ የምራቅ ናሙና ውስጥ የሳንባ በሽታን (ቲቢ) ለመለየት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ነው።
አይጦች በጣም ፈጣን ሲሆኑ የ100 ህሙማንን ናሙናዎች ለማሽተት የሚወስድባቸው ጊዜ 20 ደቂቃ ብቻ ነው። ቲቢን ከናሙና ውስጥ ለመለየትም የሚያሸቱበትን የስሜት ህዋሳቸውን ይጠቀማሉ።
ለዚህ ለሠሩት ጥሩ ሥራም አቮካዶ እና ሙዝ እንደ ሽልማት ይቀርብላቸዋል። ይህም እነዚህን የሠለጠኑ አይጦች ጊዜ እና ገንዘብ ውስን በሆነባቸው የሕክምና እና የምርምር ተቋማት ጥሩ አማራጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
81 በመቶ ለሚሆን ጊዜ በቲቢ በሽታ የተያዙ ሰዎችን በትክክል በመለየት አስገራሚ ውጤትም አስመዝግበዋል።
እነዚህ ነፍሳት የሳንባ ካንሰርን፣ ቲቢን እና ኮቪድ-19ን ጨምሮ የተወሰኑ በሽታዎችን ምልክቶች መለየት ይችላሉ።
ንቦች ዝቅተኛ መጠን ያላቸው ጠረኖችን ጭምር የማሽተት አቅማቸው ከፍተኛ ነው። ይህም ልክ እንደ ውሾች እና አይጦች  የኬሚካል ለውጦችን መለየት ያስችላቸዋል።
ተመራማሪዎችም ለንቦች እንደ ሽልማት ስኳር በመስጠት የተወሰኑ ጠረኖችን እንዲለዩ ማሠልጠን ችለዋል።  በሥልጠናው ይህ ምላሻቸው ጤናማ ያልሆነ አናቶሚ (የሰውነት ቅርጽ) እና ፓቶሎጂ (በሽታ) ጋር ለተያያዙ ጠረኖች 'ሴንሲቲቭ' ሲሆኑ የሚሰጡትም ምላሽ ቋሚ ሆኗል።
ይህ ችሎታቸውም ንቦች በተመሳሳይ መልኩ እንደ ሌሎች እንስሳት በሽታዎችን ለመለየት ጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
በተለይም በአካል መጠናቸው አነስተኛ መሆናቸው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በፍጥነት ለሚሠሩ የናሙና ትንተናዎች ብዙም ገንዘብ የማያስወጡ አማራጮች ሊያደርጋችው ይችላል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
እንስሳት በሽታዎች መከሰታቸውን መለየት የሚችሉት እንዴት ነው?
ይህ የሚሆነው በአንድ ሰው ውስጥ ያለውን ጥቃቅን ኬሚካላዊ ለውጦች የመለየት ባላቸው ተፈጥሯዊ ችሎታ ምክንያት ነው።
ውሾችን፣ አይጦችን እና ንቦችን ጨምሮ በርካታ የእንስሳት ዝርያዎች ቮላታይል ኦርጋኒክ ኮምፓውንድስ የሚባሉትን ወደ አየር የሚለቀቁ ጋዞችን እንዲሁም ውህዶችን ጠረኖች መለየት ይችላሉ።
እነዚህ ጠረኖች ጤነኛ የሆነ ሰውም ከሰውነቱ በአነስተኛ መጠን የሚለቃቸው ሊሆኑ ይችላሉ።
ከሰው ልጅ በትንፋሽ መልክ የሚወጣው አየር ወደ 3500 የሚጠጉ ቮላታይል ኦርጋኒክ ኮምፓውንዶችን የያዘ ነው።
ከሰውነት የሚለቀቁት እነዚህ ጋዞች እንደ አንድ ሰው የጤና ሁኔታ የሚለዋወጡ ሲሆን፣ ጤነኛ ባልሆነ ሰው ዘንድ አሊያም ከበሽታ ጋር እየታገለ ያለ ሰው የእነዚህ ውህዶች ጠረን የተለየ ይሆናል።
በነገራችን ላይ የእነዚህ እንስሳት በሽታዎችን የመለየት ችሎታ የሚጠቅመው ለሰው ልጆች ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ሲ ኢሌጋንስ ትል (ሲ ዎርም) ከሰው ከተወሰዱ ናሙናዎች የካንሰርን በሽታ ብቻ አይደለም የሚለየው።
ሲ ዎርም ባለው የአካላዊ እና የአካል ክፍል ለውጦችን የማወቅ ችሎታው ከውሾች እና ከድመቶች የተወሰዱ ናሙናዎች ውስጥ በሽታዎችን መለየት ይችላል።
የተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች በተለይም የሠለጠኑ በሽታ አነፍናፊ እንስሳት፣ በሽታዎችን በትክክል በመለየት ችሎታቸው ውጤታማ፣ ጎጂ ያልሆኑ፣ ብዙ ገንዘብ የማይፈጁ እና ፈጣን በሽታ የመለያ መንገድ ሆነዋል።
በሰዎች እና በእንስሳት መካከል አዎንታዊ የሆነው ይህ ግንኙነት ከዚህ በላይም ሊያድግ ይችላል።
አሁን ላይ ባሉ ሕጎች ምክንያት እንስሳት በሽታዎችን የመለያ መንገድ ተደርገው ጥቅም ላይ የሚውሉት ከሕክምና ዘዴዎች ጋር በማቀናጀት ነው። ሆኖም የሕጉ ማዕቀፍ የሚፈቅድ ከሆነ አነፍናፊ እንስሳት አንድ ቀን ወሳኝ የሕክምና አካል ሊሆኑ ይችላሉ።
አነፍናፊ ውሾች ኮቪድ-19ን ለመለየት  ከተለመደው ‘ፒሲአር ምርመራ በበለጠ ፈጣን እና ርካሽ ነበሩ። እንስሳት ያላቸውን በሽታዎች የመለየት ችሎታ በመረዳት እና አስገራሚ ችሎታቸውን ተግባር ላይ በማዋል በቤተ ሙከራ የሚሠሩ ምርመራዎችን በተሻለ መልኩ ማሻሻልም ይቻላል።
ሆኖም እነዚህን እንስሳት ለዚህ ዓላማ ጥቅም ላይ ስናውል ጤናቸው እና ደኅንነታቸው ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም መዘንጋት የለበትም። የሠለጠኑ እንስሳት ሥነ ምግባር ጉዳይም ሁልጊዜም ቢሆን ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።
ሰላማዊ ትግልን እንደ ስልት የያዘው ጃዋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞን በመምራት ስሙ ይጠቀሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ስርዓቱን በቅርብ ርቀት በሰላ ሲተች ቆይቶ ነበር።
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በተነሳው ግርግር ሳቢያ ከተገደለ ፖሊስ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶበት የነበረው ጃዋር በእስር ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ አሳልፏል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል።
ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙ በጎ ነገሮች በንግግርም፣ በተግባርም ታይቶ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የትግራይ ጦርነት ተከሰተ፤ አሁንም በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልሎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነው። ረሃብ፣ መፈናቀል እንዲሁም የከተማ ኑሮ ውድነት የአገሪቱ ገጽታ ሆኗል። በአንተ እምነት ኢትዮጵያ መስመር ስታ እዚህ ውስጥ የገባችው የቱ ጋር ነው?
ጃዋር፡- ዐቢይ ከመጀመርያውም መስመር ላይ አልነበረም። . . .  [መጀመርያ አካባቢ] እኛ ከህወሓቶች ጋር እንደራደር ነበር፤ ስልጣን እንደሚለቁ፤ ማዕከላዊ ስልጣን እንደሚለቁ፣ ስምምነት ላይ ከደረስን በኋላ፣ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ማን ይሁን? የሚለው ሲመጣ የዐቢይ ስም በመምጣቱ አነጋግሬው ነበር።ያኔ ለእኔ ግልጽ ነበር።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ኢትዮጵያ ከኢህአዴግ አንድ ፓርቲ አገዛዝ፣ ወደ መድብለ ፓርቲ፣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሄድ፣ መሻገር ነበረባት፤ ወደ ግጭት የማያደርስ ያለው ብቸኛ አማራጭ እርሱ ብቻ ነበር።
ገና ስልጣን ሳይይዝ፣ገና ስሙም ሳይታወቅ፣ለእኔ ከእርሱ ጋር በነበረኝ ውይይት የዲሞክራሲ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ግልጽ ነበር።አምባገነናዊ ስርዓትን ከአንድ ፓርቲ ወደ አንድ ግለሰብ የማሻገር ህልም እንዳለው ለእኔ ግልጽ ነበር። ለዚያ ነው የተቃወምኩት።
በወቅቱ ግን ሰዉ የሚያየው ነገር የለውጥ ስሜቱ ወያኔ [ህወሓት] ብቻ ትጥፋ እንጂ ማንም ይምጣ  የሚለው ስሜት በጣም ጠንካራ ስለነበር እኔ ሰዉን ማሳመን አልቻልኩም። መጀመርያ ኦህዴዶችን፣ ቀጥሎ ሕዝቡን ማሳመን አልቻልኩም። በዚያ ምክንያት አቆምኩ እንጂ ለእኔ በጣም ግልጽ ነበር
ከዚያ በኋላ የመጀመርያው አንድ ዓመት ሲደረግ የነበረውን ሳየው ነበር። ተወያይተን ይህንን ሽግግር እንምራ የሚለው ሲመጣ እኔ አሻግራችኋለሁ ማለት፤ የጋራ ፍኖተ ካርታ ይምጣ ሲባል አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ተሰማ።በጎ በጎው በሚታይበት ወቅት ራሱ በውስጥ በውስጡ ወደ ዲሞክራሲ የሚያሸጋግረው ኃዲድ ተስቶ ነበር። መጨረሻ ላይ የለየለት ወደ ምርጫ ሲገባ፣ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ኃይሎችን ወደ መምታት ሲገባ ነው ሰዉ የነቃው እንጂ ከጅምሩም ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲ የማሻገር ፍላጎት ፈጽሞ ኖሮት አያውቅም።
ቢቢሲ፦በአገሪቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች እንደቀጠሉ ናቸው፤ በትግራይ ክልልም ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልሆነም። . . . አሁንም ወደ ዲሞክራሲ የመመለስ፣ አገሪቱን ወደ መስመር የመመለስ እድል አለ ብለህ ታምናለህ?
ጃዋር፦ ቢጠብም እድል አለ። ግን አሁን እነ ዐቢይ በያዙት አመለካከት እና ትምክህተኛነት ወደ ትክክለኛው መስመር መመለስ የሚችሉ አይመስለኝም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን አይረዷትም። ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ብሔር ብሔረሰቦች ያሉበትን (Multi ethnic) የሆነን አገር፣ አሁን ባለው ዓለም ተጨባጭ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አይረዱም። ለመረዳትም ፍላጎት የላቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የብልጽግና ደሴት የሚባል ተፈጥሯል። ዐቢይ እና እርሱ አካባቢ ያሉ ሰዎች ብቻ የሚንሸራሸሩበት፣ ሌላውን ሕዝብ ፈጽሞ ያገለለ፣ የሌላውን ሕዝብ አኗኗር የማይረዳ።
በቅርቡ [አዲስ አበባ] ሄጄ የሆነ ነገር  ፌስቡክ ላይ ጽፌ ነበር። 'ሕዘቡ ጠውልጓል እነርሱ ደንዝዘዋል' የሚል፤ እውነቴን ነበር።  ሕዝቡን ተዘዋውሬ አየሁት። ከተማ ውስጥ ቀንም ማታም እየዞርኩ ሕዝቡን አየው ነበር። ከዚያ ደግሞ ቱባ ቱባ ሚኒስትሮችን አገኘኋቸው።
ስለ ኢኮኖሚ ስታወራ፣ 'ኢኮኖሚውማ እንደዚህ አድጎ አያውቅም'  ይሉሀል. . . በየቤቱ ማር እና ወተት በቧንቧ የሚፈስ ነው የሚያስመስሉት።
ስለ ጦርነት ስታወራ አማራ ክልል. . እነሱ እኮ ተከፋፍለዋል፤ እየጠፉ ነው። ኦሮሚያ ክልል ምንም ችግር የለም። ትግራይ የራሳቸው ጉዳይ. . .  ያምኑታል ደግሞ [ጠቅላይ ሚኒስትሩን]። . . . የራሳቸውን ውሸት ያምኑታል። እነርሱ በያዙት አመለካከት ወደ መስመር መመለስ አንችልም። ነገር ግን ዝም ብለን እንመለከታለን? ዝም ብለን ደግሞ አንመለከትም። አገራችን ነው ሕዝባችን ነው። የለፋንበት ነው፤ እድሜያችንን ያጠፋንበት ነው። We are not going let them take us down [ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድላቸውም]።  ራሳቸው ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው። እኛ ኢትዮጵያን ሕዝቦቿ ወደ መንገድ መመለስ እንችላለን? አዎ መመለስ እንችላለን። እነሱን ግን ይመልሱናል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ባለፉት ስድስት ዓመታት አገሪቷን ከከተተበት መከራ ወደባሰበት ነው ይዘውን እየሄዱ ያሉት።
ቢቢሲ፦ ጃዋርን ከመታሰሩ በፊት የሚያውቁት ሰዎች መንግሥት ላይ የሠላ ትችት ሲያቀርብ ፣ ፖለቲካው ላይ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ነው ።ከእስር በኋላ ግን መሀል ላይ ያለ የአሸማጋይነት ሚና ያለውን ጃዋር ነው ያየነው። እስር ቤት አንተ ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው?
ጃዋር፦በእስር ቤት ወቅት እኔ ብቻ እስር ቤት መሆኔ አይደለም ትልቁ ነገር። ባለፈውም እንዳልኩት እኔ ትቻት የታሰርኩት ኢትዮጵያ እና እኔ ከእስር ቤት ወጥቼ ያገኘኋት ኢትዮጵያ የተለያዩ ነበሩ።
እስር ቤት ከመግባቴ በፊት የችግር ዳመናው፣ የጦርነት ዳመናው የተሰበሰበ ነበር። ከእስር ቤት ስወጣ እሳት በየቦታው ተቀጣጥሎ ነበር። ስለዚህ እንደ አንድ ተሰሚነት እንዳለው እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ምን ባደርግ ነው አገር እና ሕዝብ ማዳን የምችለው? ብዬ አሰብኩ። ወጥቼ ወደ አክቲቭዝም እና ወደ ትችት ብመለስ በእሳቱ ላይ ሌላ ቤንዚን መጨመር ሆኖ ታየኝ። ስለዚህ ያንን ተወት ላድርገው እና ያለኝን ተሰሚነት፣ ያለኝን ትስስር፣ መስተጋብር በማማከር፣ በመገሰጽ፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም እንዲረባረብ፣ መስራት ላይ አተኮርኩ። ከእስር ከወጣሁም በኋላ ሕዝቡንም ወደ ዲያስፖራው ሄጄ ስለ ሠላም ስናገር ከፍተኛ ተቃውሞ ይደርስብኝ ነበር። ያንን ማድረግ የምችለው እኔ ብቻ ነበርኩ።
ከትግሉ ጋር ተያይዞ ያለኝ የፖለቲካ ካፒታል ነበር።ያንን የፖለቲካ ካፒታል ውጪ አገር ሄጄ በመመንዘር፣ በወቅቱ ሕዝቡ በተለያየ ወገን ያለውን ጦር በመደገፍ በጣም ተከፋፍሎ ስለነበር፣የጦርነት ገበያ እንዲጠብ እና የሠላም ገበያ እንዲሰፋ፣ መንግሥትም ሆነ ጫካ ያሉት አማፂያን ጫና ተደርጎባቸው ወደ ሠላም ይመጣሉ በሚል ነበር ያንን ስሰራ የነበረው።
መጀመርያ ለሕዝቡ ስለ ሠላም በመናገር፣ ከዚያ ደግሞ ዲፕሎማቶቸን በመቀጠል ደግሞ የአገሪቱን ባለሥልጣናት የአማፂ አመራሮችን በማግኘት የተቻለኝን ሳደርግ ነበር። ብዙ ሞከርኩ። ግን እያየሁት የመጣሁት ነገር፣ ጊዜ ለመግዣ እንጂ አገሪቱን ወደ አጠቃላይ ሠላም፣ ሥር ነቀል ሠላማዊ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኝነቱም ፍላጎትም እንደሌለ፣ እንዳውም ነገሮች ረገብ ሲሉ ወደ ነበረበት ሲመለሱ ስላየሁ ይህ ነገር በዚሁ ከቀጠለ እየተባባሰ ነው የሚሄደው፤ ዝም ማለቱ እና መምከሩ፣ መለማመጡ፣ መለመኑ ብዙም አላስኬደም። . . .  እኔ በዚያ መቀጠሉ ዋጋ ስለሌለው ነው።
ቢቢሲ፡- ስለዚህ ወደ ቀደመው የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎህ ተመልሰሃል?
ጃዋር፦ ወደ ቀደመው መመለስ አይቻልም። ወደፊት ብቻ ነው መሄድ የሚቻለው።(ሳቅ)
ቢቢሲ፡- ይህንን ያነሳሁት ቀጣዩ ምርጫ ብዙም ሩቅ አይደለም በሚል ነው። አንተ ደግሞ በኦፌኮ ውስጥ አባል እና አመራር ነህ፤ በቀጣይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ምን ሚና ይኖርሃል ለማለት ነው?
ጃዋር- ቀልጣፋ ሚና ይኖረኛል። እኔ አሁን መናገር እና መጻፍ የጀመርኩት እነዚህ ልጆች[የብልጽግና ሰዎች] በጣም አደገኛ ነገር ውስጥ ነው የገቡት። Total ignorance and arrogance (እልም ያለ ድንቁርና እና እብሪተኝነት)።
ጃዋር-የብልጽግና ሰዎች ዐቢይ እና በአካባቢው ያሉ ሰዎች Total ignorance and arrogance[እልም ያለ ድንቁርና እና እብሪተኝነት] ውስጥ ናቸው። ይህ ነው የማይባል ጥጋብ ውስጥ ገብተዋል።
ጥጋብ ደግሞ ጆሯቸውንም አእምሯቸውን ደፍኖታል። ይሄ ለእነሱም ለአገርም አደጋ አለው። ስለዚህ እኔ  የምፈልገው እንድንነጋገር ነው። ልንነጋገር ይገባል።
በተለይ አሁን ምን እያደረጉ መሰለህ እኛን እና ትግራይን ሲመቱ የአማራውን የፖለቲካ 'ካምፕ' ነው የተጠቀሙት። አሁን ደግሞ አማራ ጋር ሲጋጩ ኦሮሞ ውስጥ ተወሽቀው፤ ኦሮሞን ፊት ለፊት እየያዙ በኦሮሞነት ስም አማራን ለመምታት ይፈልጋሉ።
ይኼ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ አደጋ ነው የሚዳርጋት። የኦሮሞ ሕዝብ ይህንን አይፈልግም። የኦሮሞ ሕዝብ ትናንት ከአማራው ውስጥ በወጡ ገዢ መደቦች ሲጨቆን ታግሏል። ከትግራይም በወጡ ሲጨቆን ታግሏል። የታገለው ግን አንድ አምባገነን ሥልጣን ላይ ወጥቶ በእርሱ ስም ትግራይን እንዲመታ፣ አማራን አንዲመታ አይደለም።
እኛ ከአማራ ጋር፣ ከተጋሩ ጋር፣ ከሶማሌ ጋር ያለንን የፖለቲካ ልዩነት  በውይይት፣ በክርክር በመፍታት ለእኛም ለሁሉም የምትሆነንን ኢትዮጵያን መመስረት ነው።
ፍትሐዊ፣ ዲሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ኢትዮጵያን መመስረት ነው። እንጂ አሁን እንደ እኔ አይነት ተሰሚነት ያለን ሰዎች ዝም ካልን የኦሮሞን ስሜት በመኮርኮር ከአማራ ጋር በሚያደርጉት ጦርነት ለመጠቀም የሚያደርጉትን ማንዣበብ ስላየሁ ይኼ መክሸፍ አለበት በሚል ነው የሄድኩበት [እየሰራሁ ያለሁት]።
ጃዋር፡- ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ምርጫ ቅንጦት ነው። አንድ ተረት አለ። ጭንቅላት ካለ ነው ጥምጣም የምትጠመጥምበት። ጭንቅላቱ ከሌለ ግን ምኑ ላይ ትጠመጥመዋለህ? ምርጫ ሊካሄድ የሚችለው መንግሥት የሚቆጣጠረው ቦታ ሲኖር ነው።
ዛሬ አማራ ክልል ውስጥ መንግሥት ባህር ዳር እና የተወሰኑ ጥቂት ቦታዎች እንጂ ክልሉ በቁጥጥሩ ስር አይደለም። በኦሮሚያ ክልል ውስጥም ከተወሰኑ ዋና ዋና ከተሞች ውጪ ሌላው የአማፂያን መፈንጫ ነው። ኢትዮጵያ ካላት 547 የፓርላማ የምርጫ መቀመጫዎች ውስጥስንቱ ቦታ ውስጥ ነው ምርጫ ሊካሄድ የሚችለው? ኢትዮጵያ ካላት 547 የፓርላማ ወንበሮች ውስጥ ቢያንስ በ2/3ኛው በትንሹ ምርጫ ካልተካሄደ ያ ምርጫ ተቀባይነት አይኖረውም።
ስለዚህ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ስለ ምርጫ ማውራት ዋጋ የለውም። መጀመርያ አገራችንን ወደ ሠላም መመለስ መቻል አለብን። አንጻራዊ ሰላም ከመጣ ስለ ምርጫ ማውራት እንችላለን። አንጻራዊ ሠላም መጥቶ የምርጫ እድል ከመጣ የመጀመርያው ረድፍ ላይ እሰለፋለሁ።
ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ስለ ምርጫ የምናወራው እኛ ነበርን። አገር ነበረን። ስርዓት ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ስለ ምርጫ ማውራት ሕዝብን ማዘናጋት ስለሚሆን ነው። ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ላይ ጫና ተደርጎ፣ ምክንያቱም የሰላም ድርድር እና ንግግር እንዳይመጣ ዋነኛ ጋሬጣ የሆነው መንግሥት ነው።
ቢቢሲ - መንግሥት በተደጋጋሚ ከታጣቂዎች ጋር ለሚደረግ የሠላም ድርድር እና ውይይት ዝግጁ መሆኑን ሲናገር ይደመጣል። ታጣቂዎችም ለሠላም ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩባቸው አጋጣሚዎች አሉ። ነገር ግን የሚታሰበው ሠላም እስካሁን ድረስ ሊመጣ አልቻለም። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው ትላለህ?
ጃዋር፡- መንግሥት የችርቻሮ ሠላም ነው የሚፈልገው። ይህንን አማፂ በዚህ ጋር በገንዘብ በሌላ ነገር ደልሎ ለማምጣት። ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ወይም ትግራይ ክልል የዛሬ አምስት ስድስት ዓመት እኮ አማፂ አልነበረም። ምንድን ነው ወደ አመጽ የመራው? ጎንደር ውስጥ ወለጋ ውስጥ አማፂ ሳይመጣ እኮ ልብ የሸፈተው አዲስ አበባ፣ ፊንፊኔ ላይ ነው።
የፖለቲካ አለመስማማት፣ የነበረውን የፖለቲካ ልዩነት በጠረጴዛ ዙርያ ለመፍታት ፍላጎት ከማጣት እና የፖለቲካ ምህዳሩን በመዝጋት የግለሰብ አምባገነናዊ ስርዓት ለመመስረት ዐቢይ በመወሰኑ ነው። በአገሪቱ እምብርት ዋና ከተማ ላይ ሊፈታ የሚገባው ልዩነት ነው ወደ ጫካ ለመግባት ምክንያት የሆነው።
እኛ እያልን ያለነው አጠቃላይ ሠላም፣ አጠቃላይ የፖለቲካ 'ሴትልመንት' [ፖለቲካዊ እልባት]፤ ወደ ጦርነት ያስገቡን የፖለቲካ ልዩነቶች በጠረጴዛ ዙርያ በድርድር እና በንግግር መፈታት አለባቸው ነው። እነርሱ ይህንን አይፈልጉም። በዚህ ጋር ቄሱን ሼኩን ልከው፣ በዚህ ጋ ነጋዴውን ገንዘብ አስይዘው ልከው ሊያመጡ ነው የሚፈልጉት። ይመጣሉ የተወሰኑ ወታደሮች። እኛም እኮ ሞክረናል ከአባ ገዳዎች ጋር ሆነን ከግማሽ በላይ የሆኑ የኦነግ ጦርን ይዘን መጥተናል። የፖለቲካ ምህዳሩ ጠብቦ በመቀጠሉ እና ዋና የግጭቱ መንስዔ የሆነውን ጉዳይ ለመፍታት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከዚያ ወዲህ እጥፍ ተስፋፍተው ዛሬ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ መንግሥት ካለው ጦር በላይ የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ነው ያለው።
ስለዚህ እኛ ሰላም እያልን ያለነው የምላስ ሰላም ሳይሆን ስር ነቀል የፖለቲካ ልዩነቶችን ከየጫካው ከጠመንጃ አፈ ሙዝ ወደ ጠረጴዛ ላይ የሚያመጣ ሰላም ነው እያልን ያለነው።
ቢቢሲ- የታጣቂዎችን ጥያቄ ስላነሳህ እዚህ ጋር ይህንን ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። ታጣቂዎች የሚያነሱት ጥያቄ አንተ ተቃውሞ ውስጥ ገብተህ ኦሮሚያ ላይ ታነሳቸው ከነበሩት ጥያቄዎች ብዙም የራቁ አይደሉም። እነዚያ ያኔ ስታነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል ወይስ ወደ ጎን ተገፍተዋል?
ጃዋር - ተድበስብሰዋል። መድበስበስ ብቻ ሳይሆን ከእነዚያ ጥያቄዎች የባሱ ሆነዋል። ያኔ እኮ የሚነሱ ጥያቄዎች የእኩልነት፣ የቋንቋ፣ የከተማ ምናምን ዛሬ እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ያንን የሚጠይቅ የለም። ዛሬ ጥያቄው የሕልውና ሆነ። ሕዝብ በቀዬው አርሶ መግባት አልቻለም። በሺዎች ሚሊሻዎችን እያሰለጠነ፣ ሚሊሻው ደሞዝ የለውም፣ ሰዉን ይዘርፋል። ጫካ ያለውም ሰውን ይዘርፋል።መንግሥትን ወክሎ ስርዓት ለማስከበር የሚላከው ሠዉን ይገላል። ሠዉን ይዘርፋል። ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዘብ በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ አንተ የምትላቸውን እኛ ስናነሳቸው የነበሩትን ጥያቄዎች አይደለም የሚያነሳው።
መሰረታዊ ወጥቶ የመግባት እና ያለመግባት ጥያቄ ነው እያነሳ ያለው። ብዙዎቹ ወጣቶች በኦሮሚያ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መሪ ድሪባ ኩምሳ፣ ጃል መሮ ጋር የገቡት፣ በአማራ እነ እስክንድር  ነጋ ጋር ሌሎቹ ጋር የተቀላቀሉት የፖለቲካ ጥያቄያቸውን 'አርቲኩሌት' [ስላንጸባረቁ] ስላደረጉ አይደለም። አንደኛ የፖለቲካ ምህዳሩ መዘጋት መፈናፈኛ አሳጣቸው። ሁለተኛ ወደ ቀያቸው ሲገቡ የሚደረገው አፈና፣ ግድያ፣ እርግጫ፣ መኖርያ ከለከላቸው። የግል ሕይወታቸውንም ለመታደግ፣ የፖለቲካ ጥያቄያቸውንም ለማራመድ የግድ መግባት ነበረባቸው። . . .  ስለዚህ የፖለቲካ ጥያቄው ተድበስብሶ የሕልውና ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄውን ሸፈነው፤ አፈነው ማለት ነው።
ቢቢሲ- ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውን ሁኔታ ስትመለከት የበለጠ የሚያሳስብህ እንቅልፍ የሚነሳህ የሚያስጨንቅህ ነገር ምንድን ነው?
ጃዋር፦የአገር መበተን ነው። ምክንያቱም ያኔ እኛ ስንታገል አገረ መንግሥት ነበር። እኛ አገረ መንግሥቱን እየጎነተልንም እየቦቀስንም አፈናው እንዲቀንስ፣ ለዜጎች እና የቡድኖችን መብት እንዲሰጥ ነበር የምንጠይቀው። ግንዱ ስለነበር ነው። አሁን ግንዱ ምስጥ በልቶት እያለቀ ነው።
የአገር መፍረስ አደጋው በጣም አደገኛ ደረጃ ላይ ነው። . . . ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉ ሰዎች በየዕለቱ እያፈረሷት ነው። አገር ከፈረሰ፣ ምናልባትም እድሜዬ እየሄደ ነው መሰለኝ እና የአገር መፍረስ ያሳስበኛል።
መጽሐፌም ውስጥ ብዙም ጊዜ ደጋግሜ እንደምናገረው፣ ከ2007 እስከ 2012 ድረስ በነበረው ጊዜ የቄሮን እንቅስቃሴ ስትራቴጂ ሳወጣ የስርዓት ፍንቀላ 'ሪጂም ቼንጅ' ነበር ሳስብ የነበረው።
ይኼ እያለ ከእኔ ጋር ሲማሩ የነበሩ፣ እኔም ሳስተምራቸው የነበሩ ልጆች 'የአረብ ስፕሪንግ' [የአረብ አመጽን] አስነሱ። ከዚያ በፊት የነበረው አስተሳሰብ ምንድን ነው በሕዝባዊ ዓመጽ አምባገነናዊ ስርዓትን ትገረስሳለህ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ትገነባለህ ነበር። ሦስተኛ አማራጭ እንደበር አላየንም። የስቴት ኮላፕስ [የአገር መፍረስ]። የሊቢያ መፍረስ፣ የየመን መፍረስ፣ የሶሪያ መፍረስን ሳይ መለስ ብዬ ኢህአዴግን ካፈረስን የአገር መፍረስ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ጫና ፈጥረን ከኢህአዴግ ውስጥ ለዘብተኛ የሆነ ለውጥ የሚፈልጉ ኃይሎች ወደ ሥልጣን ይምጡ ወደሚል ሄድን። ከዚያ ጊዜ የተጠናወተኝ ፍራቻ ለ'ስቴት' የመሳሳት ጉዳይ አሁን ደግሞ እያየሁት መጣሁ። እና አሁን እንቅልፍ የሚነሳኝ አንዴ ስቴት ከፈረሰ፣ አምባገነናዊ የሆነን መንግሥት ማስተካከል ትችላለህ፤ ኢኮኖሚው የተበላሸን ስቴት ሰውዬውን [መሪውን] አንስተህ ልታስተካክል ትችላለህ። አገር ከፈረሰ መልሶ መገንባት በጣም ከባድ ነው።  . . .  እንደ ኢትዮጵያ ውስብሰብ የሆነ እና ብዙ የውጪ ኃይሎች ፍላጎት ያሉበት አገር አንዴ ከተበተነ. . .  አገር መፍረስ ስል ግን ሰው መጠንቀቅ አለበት። ኢትዮጵያ ፈርሳ ኦሮሚያ አይቀርም፣ አማራ አይቀርም፣ ትግራይ አይቀርም። የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ከፈረሰ ብትንትን ነው። . . .  ከጣርያ ላይ እንደለቀቀከው ጀበና ነው የሚሆነው።
ቢቢሲ- አሁን አንተ ያነሳሃቸውን ጥያቄዎችንም ለመመለስ  እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎች ላይ ለመነጋገር በሚል መንግሥት ብሔራዊ የእርቅ እና ምክክር ኮሚሽን አቋቁሟል። በርግጥ እስካሁን ድረስ አጀንዳ ማሰባሰቡን አልጨረሱም። ከ10 በላይ የሚሆኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ቅሬታቸውን አቅርበው እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል። ከእነዚህ መካከል አንተ አመራር የሆንክበት ኦፌኮ አንዱ ነው። ይህንን ግን አንተ እንደ ጃዋር ነው አንድትመልስልኝ የምፈልገው። አንተ የምክክር ኮሚሽኑ የሚፈለገውን ለውጥ ያመጣል ብለህ ታምናለህ?
ጃዋር- የአገራዊ ውይይት ጉዳይ ገና ለውጡ ሲመጣ ሦስት ጉዳዮችን ነው 'ፕሮፖዝ [ያቀረብነው] ያደረግነው። አንደኛው አገራዊ ውይይት ነው። የብሔራዊ እርቅ እና የማንነት እና የድንበር ጉዳዮችን ከዚያ የሚወጡ ብለን ነው ያስቀመጥነው። Part of our transition plan [እንደ መሸጋገሪያ ዕቅድ]። የብሔራዊ ውይይቱን ትተው የብሔራዊ እርቅ እና የማንነት እና የድንበር ኮሚሽንን ለጊዜው አቋቁመው ለሦስት ዓመት ከቆዩ በኋላ ፈረሰ። 'ናሽናል ዲያሎግ' [ብሔራዊ ምክክር] በአንድ አገር ውስጥ በሁለት ምክንያት ነው የሚደረገው። አንዱ ጦርነትን ለማስቀረት። የፖለቲካ ልዩነቶች በጣም ተጋግለው ሲወጠሩ ያንን ውጥረት ለማርገብ እና ወደ ጦርነት እንዳያመሩ ለማድረግ።
ቅድመ ጦርነት የመከላከል መንገድ ሊሆን ይችላል። አንዱ ደግሞ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ ጦርነት ሲቆም ወደ ጦርነት ያስገቡ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወደ ሌላ ጦርነት እንዳያመሩ በጦርነት ጊዜ የተፈጸሙ በደሎች እና ስህተቶች እንዲታከሙ፣ ቁስል እንዲሽር የሚደረግበት ድህረ ጦርነት 'ናሽናል ዲያሎግ' ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ሲጀመር በጦርነት መካከል ነው የተመሰረተው፥ ትግራይ ጦርነት እየተካሄደ ነበር። ኦሮሚያም ውስጥ እየተካሄደ ነበር። እስር ቤት እያለሁም ጠይቄያለሁ። ከወጣሁም በኋላ ለ'ናሽናል ዲያሎግ' የተመረጡት ሰዎች መጥተው ጠየቁኝ። የእኔ ምክረ ሀሳብ ምን ነበር? ሀሳቡ በጣም ጥሩ ነው።
ከስድስት ዓመት በፊት፣ 2018 ላይ ማድረግ ነበረብን። እሺ ከመቅረት መዘግየት ይሻላል።ብሔራዊ ዲያሎግ (ምክክር) ሊሰራ የሚችለው መነሻው ወሳኝ ነው። ሊወያዩ የሚወስኑ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የፖለቲካ አደረጃጀቶች አወያዮቹን መረጣ ላይ፣ የመወያያ ሕጉ ላይ ግብዓታቸውን ሊካተት እና ሊስማሙበት ይገባል። ስለዚህ አትሩጡበት አትቸኩሉበት።
አንድ እርሱ ነው። ሁለተኛ ቅድም እንዳልኩት 'ናሽናል ዲያሎግ' [ብሔራዊ ምክክር] ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ጦርነት ካለቀ በኋላ ሲሆን ነው። ስለዚህ ጦርነት እንዲቆም፣ የትግራይ ጦርነት እንዲቆም፣ የኦሮሚያ ጦርነት አንዲቆም፣ እነዚያ የሚዋጉ ሰዎች ወደ መድረክ  እንዲመጡ ስሩበት እኛም አንደግፋለን የሚል ነው። ያ ሳይሰራ ቀጠሉበት። የአማራ ክልል ጦርነት ተጨመረበት ማለት ነው። ዛሬ እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ 'ናሽናል ዲያሎግ' ሊካሄድ አይችልም፤ ዐቢይ መስታወት እያየ እንደማውራት ማለት ነው።
ጃዋር፡-ያለቀለት ጉዳይ ኦኮ ነው። ፕሮፌሰር መረራ እንደሚለው 'ዴድ ኦን አራይቫል'። ከጅምሩ የተበላሸ ነገር ስለሆነ አሁን ባለው ሁኔታ በዋናነት ምንድን ነው የሚሆነው ስርዓቱ ፕሬዝዳንታዊ ይሁን በማለት ዐቢይን ፕሬዝዳንት ከማድረግ ያለፈ ውጤት ሊኖረው አይችልም።
ቢቢሲ- የምታስበው ሁሉ ቢስተካከል ኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነህ የመምራት ፍላጎት አለህ?
ጃዋር፡- ቅድም እንዳልኩህ ነው። 'Mataa jirutti sabbata marani' ባለ ጭንቅላት ላይ ጥምጣም የሚጠመጠመው። ለእኔ ትልቁ ነገር እስቲ አገር ይኑረን።
አገር የለንም የምንልበት ደረጃ ላይ እየገባን ነው። . . .  አገር ይመለስና የጠቅላይ ሚኒስትርነትም የገበሬነት ችግር የለውም። ችግር የፈጠረው አንዱ ምንድን ነው? አገር ለመምራት የሚያስፈልገው እውቀት፣ ብስለት፣ ብልሀት፣ ምንድን ነው ብሎ ራስን ሳያዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን፣ ሚኒስቴር ለመሆን ብቻ የሚደረግ ያለ ዕቅድ የአገሪቱን ውስብስብነት፣ የዓለምን ውስብሰብነት ሳይረዱ የሚደረግ ነገር አደጋ አለው። ስለዚህ ለእኔ ማን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሁን? የሚለው ሁለተኛ ደረጃ ነው።
እኔ አሁን አምፁ እያልኩ አይደልም ያለሁት። መነጋገር አለብን ነው የምለው። አገር ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ገብታለች። ኢኮኖሚያችን ዳሽቋል። ሕዝቡ ኢትዮጵያ ድሮም ደሀ ነች አሁን ባለው ደረጃ ግን ሕዝቡ ተቸግሮ አያውቅም። . . .  ይህ ደግሞ ምን ውጤት ነው። አንዱ የጦርነት ውጤት ነው፥ ከጦርነት የተረፈውን ገንዘብ ቅንጡ ሪዞርቶች እና ቤተመንግሥት ላይ ውሏል ።
የፈጣሪ ያለህ. . .  ኢትዮጵያ ለምንድን ነው አዲስ ቤተ መንግሥት የሚያስፈልጋት? የኢትዮጵያ ሕዘብ ችግር ሪዞርት ነው?
የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር በቂ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ማዳበርያ አለማግኘት ነው። የኢትዮጵያ ሕዘብ ችግር ገበሬው ተረጋግቶ ማረስ የሚችልበት ሠላም አለመኖር ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የመንገድ ትራንስፖርት በሰፊው አለመኖር ነው። . . . . ስለዚህ ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የቅድሚያ መዛባት አለ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያንን ማስተካከል የግድ ነው።
ቢቢሲ፡ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውጥረት እና የፖለቲካ ሽኩቻ ስትመለከት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበራትን ተሰሚነት እንዲሁም የአደራዳሪነት ሚና እያጣች እንደሆነ ይሰማሃል?
ጃዋር፦በጣም ነው ያጣችው። ኢትዮጵያ ሴኩሪቲን [ደህንነትን] ለሌሎች አገሮች የምታዳርስ አገር ነበረች። ያን የምታደርገው ጠንካራ ጦር ስለነበራት ብቻ አይደለም። በአገር ውስጥ መረጋጋት ስለነበር ነው። የአገር ውስጥ ጦርነቱ የአገሪቱን አቅም በጣም አዳክሞታል። ለጎረቤቶቿ ጸጥታን ሳይሆን ብጥብጥን የምታከፋፍል ሆናለች። ያ አንሶ ከጎረቤቶቻችን ጋር አላስፈላጊ ግብግብ ውስጥ ገብተናል። አገራዊ ራዕይ፣ አገራዊ ፕሮጀክት የለም። . . .  ከኤርትራ ጋር፣ ከሶማሊያ ጋር ልዩ ግንኙነት ነው ያለን። ከሁለቱ አገራት ጋር ያለን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከሌሎች ጋር የሚነጻጸር አይደለም። በጣም የተወሳሰበ ነው። ለሁለቱ አገራት ኢትዮጵያ መሀከል ነች ። የእኛ ሚና መሆን የነበረበት ከእነዚህ አገራት ጋር የነበረንን ታሪካዊ ቁርሾ በመጠገን በማዳን የበለጠ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ግንኙነት ማጠናከር ነው።
. . . ከሶማሊያ ጋር ሴንሲቲቭ [ሰሱ] የሆኑ ታሪካዊ ሁኔታዎች አሉ። በመጀመርያው የዐቢይ አምስት ዓመት የነበረን ግንኙነት ጥሩ ነበር። ከሶማሊያ ጋር የነበረንን ግንኙነት አረጋግተነው ነበር። ግን ከማረጋጋት ባለፈ ሊኖረን የሚገባውን ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና የሴኩሪቲ [የደህንነት] ግንኙነት ስርዓት አላስያዝነውም። አልተነጋገርንበትም፤ አልተጻፈም። . . . ስለዚህ አገራዊ ከመሆን ወረደ እና ግለሰባዊ ሆነ።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልጋታል። አዎ! ለንግድ ብቻ ሳይሆን የባሕር ኃይልም ያስፈልገናል። የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል መኖር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናውም አስፈላጊ ነው። ሰፊ ሕዝብ ያላት፣ ትልቅ ወታደር ያላት፣ ሰፊ የቆዳ ስፋት እና ሰፊ ኢኮኖሚ ያላት አገር ናት ኢትዮጵያ። የሕንድ ውቅያኖስም ሆነ የቀይ ባሕር በተለያዩ ከሩቅ በሚመጡ ኃይሎት ተጋላጭ ሆኗል። ብዙ ኃይሎች እየመጡ ነው። ሶማሊያ በራሷ የዚህን አካባቢ ጥቅም ልታስከብር አትችልም። ኤርትራም አትችልም።
ከኢትዮጵያ ጋር ቢተባበሩ ግን፣ ኢትዮጵያ እቀማለሁ በሚለው ፉከራ ሳይሆን፣ ለሶማሊያም፣ ለኤርትራም ለጂቡቲም ሊሆን በምትችለው ቀጠናዊ ትስስር ላይ ማዕከል ያደረገ የጋራ ጥቅም ላይ ያተኮረ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል። . . .  ከዚህ ይልቅ ግን ከዚህ በፊት የሰለቸንን ዓይነት በፉከራ መሄዱ አደጋ ውስጥ ከትቶናል። . . . .  ድንገት ከሶማሌላንድ ጋር ተስማምተናል ተባለ። ገና ለመስማማት እኮ ነው የተስማማነው። ኢትዮጵያ ወደብ አገኘች ተብሎ ሕዝብን ለማሞኘት። እና ሕዝብ ሴንሴቲቭ  [ስስ] ነው። ወደብ ይፈልጋል። ያንን የሕዝቡን ፍላጎት 'ሚስ ዩዝ' [ያለ አግባብ ነው የተጠቀሙበት]ነው ያደረጉት። አዋረዱን። ከገቡበት በኋላ እንኳ ተደራድረው ሌላ መንገድ ከማምጣት ይልቅ ወደ ሚታየው ነገር ውስጥ ገባን። በዓለም ላይ ቻይና እና አሜሪካ፣ ምስራቁ እና ምዕራቡ ተስማማብን። ረባሽ አገር አስባሉን። . . .  በአካባቢው የችግር መንስዔ ሆነን እየታየን ነው።
በአካባቢው ያሉ አገራት አሁን አዲስ አበባ ካለው መንግሥት ጋር አንዳቸውም ጤነኛ ግንኙነት የላቸውም። . . .  እዚህ አካባቢ አንደሚንቀሳቀስ እና ጉዳዩን በንቃት አንደሚከታተል 'አይ ፊል ፔይን' [ሕመም ይሰማኛል]። ስለ አገራችን እና ስለ አገራችን አመራር የሚነገረውን ስትሰማው እንደ አንድ ዜጋ ሕመም ይሰማኛል። በአገሬ መኩራት ነው የምፈልገው። በአመራሮቼ ልኮራ ነው የምፈልገው።
ኢትዮጵያ የሚመጥናት አመራር ያስፈልጋታል። ኢትዮጵያን እመራለሁ ብሎ ስልጣን የያዘ ኃይል ለዚያች አገር እና ሕዝብ የሚመጥን አመራር መስጠት አለበት። ካልቻለ ግን አልቻልኩም ብሎ መልቀቅ መቻል አለበት አንጂ አገርንም ራስንም በዚህ ደረጃ ማዋረድ በጣም የሚያሳዝን ነው።
ቢቢሲ፦ በአሁኑ ወቅት ኑሮህን  ኬንያው ውስጥ ነው ያደረግከው ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር የደህንነት ስጋት አለብህ?
ጃዋር- ለስጋት ብቻ አይደለም። አንደኛ ለስራዬ እዚህ ይሻለኛል። ሁለተኛ ከእስር ቤት ከወጣሁ በኋላ ወደ እሬቻ ሲሄድ ጠባቂዎቼን አዋክበው በሙሉ አሰሯቸው።
ከዚያ ከብዙ ሰዎች ጋር፣ ከፓርቲ ሰዎችም ጋር ስንወያይ በወቅቱ የነበረኝም አቋም ምንድን ነው፣ ምንም ቢሆን በእኔ ምክንያት አሁን ባለው እሳት ላይ ችግር መፈጠር የለበትም የሚል ነበር።
ስለዚህ እነዚህ ሰዎች እኔን ተተናኩለው ነገሮችን ማባባስ የሚፈልጉ ስላሉ የሚሻለው ምንድን ነው ብለን ወደ ናይሮቢ መጣሁ። ግን ሁሌ እዚህ አልኖርም። አውሮፓ ነው የምሰራው። አውሮፓ ብዙ ጊዜ እመላለሳለሁ። ግን ናይሮቢ ውብ ስፍራ ነች። አያስቀናም! (ፈገግታ)
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የ35 ዓመቷ ሳርቬሽ ታምማ አልጋ ከያዘች ቆይታለች።
"ያለማቋረጥ ያስመልሰኝ ነበር። ሁልጊዜም ድካም እና ሕመም ነበረኝ" ትላለች።
ሳቬሽ መጀመሪያ በተደረገላት የአልትራሳውንድ ምርመራ ሕመሟ ምን እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም።
እርሷም "ምን እንዳመመኝ ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነበር" ትላለች።
በሕንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ከቡላንድሻህር አውራጃ የመጣችው ሳርቬሽ ሕመሟ መጀመሪያ ላይ የሆድ ኢንፌክሽን መሆኑ ስለተጠረጠረ የፀረ ባክቴሪያ መድኃኒት እንድትወስድ ተደረገ።
መድኃኒቱን አንድ ወር ከወሰደች በኋላ ለውጥ ስላላየች ተመልሳ ሄደች።
በዚህ ጊዜ ግን በተደረገላት ምርመራ ዶክተሯ ያየውን ነገር ማመን አልቻለም። ለእርሷም ቢሆን ዱብ ዕዳ ነው የሆነባት።
ዶ/ር ኬኬ ጉፕታ በሕንድ ላለፉት 20 ዓመታት የራጅ ባለሙያ ሆኖ አገልግሏል። የሳርቬሽን የምርመራ ውጤት ሲመለከት ግን እጅግ መደነቁን መሸሸግ አልቻለም።
ከዚህ በፊት በኤምአርአይ ምርመራ አጋጥሞ የማያውቀው እና በሳርቬሽ ላይ የታየውን የምርመራ ውጤት ሲናገር "በቀኝ ጉበቷ በኩል የ12 ሳምንት እርግዝና ያሳያል" ነበር ያለው።
"የምርመራ ውጤቱን የተለያዩ ክፍሎች በተደጋጋሚ በመውሰድ ትክክለኛ እርግዝና መሆኑን ለማረጋገጥ ጥሬያለሁ" ይላሉ ዶክተሯ።
እንዲህ ዓይነት እርግዝና የሚፈጠረው ከወንዴ ዘር ጋር የተገናኘው እና የዳበረው የሴቷ እንቁላል ከማህጸን ውጪ፣ ብዙ ጊዜ በማህጸን ቱቦ ውስጥ ማደግ በሚጀምርበት ወቅት ነው።
እርግዝና አንዳንድ ጊዜ በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ማለትም በእንቁላል ማኩረቻ (ኦቫሪ)፣ የሆድ እቃ ወይም የማህጸን ጫፍ ላይ ይከሰታል።
ከ80 እርግዝናዎች ውስጥ አንዱ ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ የእናቲቱን ሕይወት አደጋ ላይ ሊጥልም ይችላል።
ሳርቬሽ ጽንሱ በማህጸኗ ውስጥ ከማደግ ይልቅ በጉበቷ ላይ ነበር ማደግ የጀመረው።
ጉበት ደግሞ ከደም ውስጥ መርዛማ ነገሮችን በማስወገድ የስኳር መጠንን እና የደም መርጋትን በመቆጣጠር ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
ኢንትራሄፓቲክ (intrahepatic) የሚባለው በጉበት ውስጥ የሚፈጠረው ከማህጸን ውጪ እርግዝና በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት በመሆኑ ሳርቬሽ የዓለም አቀፍ የሕክምና ማኅበረሰብ ትኩረት እንድታገኝ አድርጓታል።
ጥንዶቹ ያለፉባቸው ሦስት ወራት ለመላው ቤተሰባቸው በጣም ፈታኝ እንደነበር እና ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ እንደከተታቸው ይናገራሉ።
ቢቢሲ እርሷን ለማግኘት በዳስቱራ መንደር ወደሚገኘው የሳርቬሽ ቤት አምርቶ ነበር።
በአልጋዋ ላይ እረፍት እያደረገች ቢሆንም ሕመሟ ግን አልቀነሰም።
ሆዷ ላይ 21 ቦታዎች ላይ ያሉትን ስፌቶች ለመሸፈን ሰፊ የሆነ ፋሻ ታስሮላታል።
መታጠቢያ ቤት ለመጠቀም፣ አልጋ ላይ ለመቀመጥ እና ልብስ ለመቀየር በባልዋ ፓራምቪር መታገዝ አለባት።
ሳርቬሽ በተለይ በዶክተሮች የተነገራትን መቀበል በጣም ከባድ እንደሆነባት ተናግራለች።
ምክንያቷ ደግሞ የወር አበባ ዑደቷ የተለመደ እና ጤናማ ነበር።
በእንደዚህ ዓይነት ከማህጸን ውጪ እርግዝና ሴቶች ብዙ ደም ይፈስሳቸዋል።
ዶ/ር ኬኬ ጉፕታ "ስለዚህ እርግዝና መከሰቱን ለማወቅ ጊዜ ይወስዳል" ሲሉ ያስረዳሉ።
ከበርካታ ምርመራዎች በኋላ ዶክተሮቿ ጽንሱን ለማስወገድ ከቀዶ ሕክምና ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ወሰኑ። ጽንሱ ማደጉን ከቀጠለ ጉበቷ ተቀድዶ ለህልፈት ትዳረጋለች የሚል ስጋት ነበራቸው።
ከሕክምናው ውስብስብነት የተነሳ ጥንዶቹ ለቀዶ ሕክምና ወደ ሕንድ ዋና ከተማ ዴልሂ እንዲሄዱ ቢመከሩም ወጪውን መሸፈን ግን አልቻሉም።
ፓራምቪር "እኛ ድሆች ነን፤ እና ወደ ዴልሂ ሄደን ወጪውን መሸፈን አንችልም ነበር" ብሏል።
በመጨረሻም ሰርቬሽ ከሦስት ወራት ሕመም በኋላ፣ ዶክተሮች በምትኖርነት አካባቢ በሚገኝ የግል ሆስፒታል ውስጥ 90 ደቂቃ የፈጀ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ተስማሙ።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
አንዲት ሴት እንቁላሏ ከእንቁላል ማኩረቻዋ (ኦቫሪ) ወጥቶ ከወንዴ ዘር ጋር ሲገናኝ እና ሲዳብር እርግዝና እንደሚፈጠር የማህጸን እና የጽንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ማምታ ሲንግ ይናገራሉ።
ይህ የዳበረ እንቁላል በማህጸን ቱቦዎች በኩል ጽንሱ ወደ ሚያድግበት ወደ ማህጸን ይሄዳል።
በአንዳንድ ሁኔታዎች ይላሉ ዶ/ር ሲንግ፣ ይህ የዳበረ እንቁላል ወደ ማህጸን ከመድረስ ይልቅ በማህጸን ቱቦ ውስጥ ይቀራል ወይም በጣም አልፎ አልፎ ከሌላ አካል ላይ ይጣበቃል።
ለሳርቬሽ ጽንሱ ከጉበቷ ጋር ተጣብቋል። ጉበቱ ለጽንሱ ያለው የደም አቅርቦት ጥሩ ነው። ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ ቀናት ለጽንሱ "ምቹ" ሆኖ ማገልገሉን ዶ/ር ሲንግ ያስረዳሉ።
ነገር ግን ውሎ ሲያድር የጤና እክል መፈጠር ጀመረ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ አንድ በመቶ የሚጠጉት እርግዝናዎች ከማህጸን ውጪ የሚከሰቱ ናቸው የሚሉት ደግሞ ሌላኛዋ የጽንስና የማህጸን ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ሞኒካ አናንት ናቸው።
"ከሰባት እስከ ስምንት ሚሊዮን ከሚሆኑት እርግዝናዎች መካከል አንዱ ብቻ ከማህጸን ውጪ ጉበት ላይ ሊከሰት እንደሚችል ይገመታል" ብለዋል።
ከሳርቬሽ በፊት፣ ዶ/ር አናንት በዓለም አቀፍ ደረጃ 45 በጉበት ላይ የተከሰቱ እርግዝናዎች ተመዝግበዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ ሦስቱ በሕንድ ውስጥ ነበር የተከሰቱት። የመጀመሪያው እርግዝና በአውሮፓውያኑ 2012 በሕንድ ዴልሂ መከሰቱን ተመዝግቦ ይገኛል።
በሕክምና ተቋም ውስጥ ከማህጸን ውጪ የተፈጠረ እርግዝና በሦስት ዓይነት የምርመራ ዘዴ ይለያል።
የምርመራ መንገዶቹም ሽንት፣ ደም እና አልትራሳውንድ ናቸው።
እናቶች ወደ ሕክምና ተቋም ለመሄድ በዘገዩ ቁጥር ለተለያዩ ችግሮች እና ጉዳቶች የመጋለጥ ዕድላቸው ይጨምራል። ከጉዳቶቹ መካከል በቀዶ ሕክምና የማህጸን ቱቦ እንዲወጣ ሊያደርግ (ሊያሳጣ) ይችላል።
ጽንስ ሆድ ውስጥ እንዲፈነዳ ወይም በሆድ ውስጥ ደም እንዲፈስ ያደርጋል። ሆድ ውስጥ ደም ሲፈስ ደግሞ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ደም ሊያልቅ ይችላል። ይህም የእናትን ሕይወት ያሳጣል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
The BBC is recognised by audiences in the UK and around the world as a provider of news that you can trust. Our website, like our TV and radio services, strives for journalism that is accurate, impartial, independent and fair.
Our editorial values say: "The trust that our audience has in all our content underpins everything that we do. We are independent, impartial and honest. We are committed to achieving the highest standards of accuracy and impartiality and strive to avoid knowingly or materially misleading our audiences.
"Our commitment to impartiality is at the heart of that relationship of trust. In all our output we will treat every subject with an impartiality that reflects the full range of views. We will consider all the relevant facts fairly and with an open mind."
We know that identifying credible journalism on the internet can be a confusing experience. We also know that audiences want to understand more about how BBC journalism is produced.
For these reasons, BBC News is making even greater efforts to explain what type of information you are reading or watching on our website, who and where the information is coming from, and how a story was crafted the way it was. By doing so, we can help you judge for yourself why BBC News can be trusted.
We are also making these indicators of trustworthy journalism "machine-readable", meaning that they can be picked up by search engines and social media platforms, helping them to better identify reliable sources of information too.
The BBC has long had its own Editorial Guidelines that apply to all of our content and set out the standards expected of our journalists.  To make it easier to see how BBC guidelines are used in our newsroom, we have listed all the relevant sections on this page.
Mission Statement: The mission of the BBC is to act in the public interest, serving all audiences through the provision of impartial, high-quality and distinctive output and services that inform, educate and entertain. Full details are in the BBC Charter.
Ownership Structure, Funding and Grants: We are independent of outside interests and arrangements that could undermine our editorial integrity.  Our audiences should be confident that our decisions are not influenced by outside interests, political or commercial pressures, or any personal interests. Learn more about how BBC News is funded, in the UK and internationally, in the BBC Charter on the independence of the BBC.
Founding Date: The BBC was founded on 18 October 1922. Read more about the history of the BBC.
Ethics Policy: The BBC's Editorial Guidelines outline the editorial values and practices that all our output is expected to conform to.
Diversity Policy: Learn about BBC News' commitment to diversity in the BBC Charter.
Diversity Staffing Report: Find out about how BBC News is working to increase diversity in the BBC's Equality Information Report.
Corrections: The BBC is committed to achieving due accuracy.  Policies relating to corrections can be found in the following sections of our Editorial Guidelines.
Our output must be well sourced, based on sound evidence, thoroughly tested and presented in clear, precise language.  We should be honest and open about what we don't know and avoid unfounded speculation.  Claims, allegations, material facts and other content that cannot be corroborated should normally be attributed.
We are open in acknowledging mistakes when they are made and encourage a culture of willingness to learn from them.
If an article has been edited since publication to correct a material inaccuracy, a note will be added at the end of the text to signal to the reader there has been an amendment or correction with the date of that change. If there is a small error in a story that does not alter its editorial meaning (eg name misspelling), the correction will be made without an additional note.
Unless content is specifically made available only for a limited time period, there is a presumption that material published online will become part of a permanently accessible archive and will not normally be removed. Exceptional circumstances may include legal reasons, personal safety risks, or a serious breach of editorial standards that cannot be rectified except by removal of the material.
Verification/Fact-checking Standards: The BBC's accuracy and verification policy is outlined in the Editorial Guidelines on Accuracy.
Unnamed Sources:  The BBC's policy and guidance on the use of anonymous sources is detailed in the Editorial Guidelines.
Actionable Feedback: The BBC's complaints procedure is outlined in the BBC Complaints Framework.
Leadership: Meet the senior executive team that runs the news division: BBC News Board.
BBC News articles based on original reporting carry bylines (the name of the journalist), as often do those authored by journalists who have a subject specialism.
General news stories, which tend to combine information from a variety of sources, including news agencies, BBC Newsgathering and BBC broadcast output, or which may have been produced by several members of staff over the course of the day, do not as a rule carry bylines.
BBC News distinguishes between factual reporting and opinion. We use machine-readable labels in six categories:
Our output, as appropriate to its subject and nature, should be well sourced, based on sound evidence, thoroughly tested and presented in clear, precise language.  We strive to be honest and open about what we don't know and avoid unfounded speculation.
Where BBC News relies on a single source for a key aspect of its coverage, we will strive to credit that source, where possible. We usually link to official reports, sets of statistics and other sources of information, to enable you to judge for yourself the underlying information that we are reporting on.
Whenever appropriate, we also offer links to relevant third-party websites that provide additional information, source material or informed comment.
For in-depth pieces of work, such as complex investigations or data journalism projects, we will help you understand how we went about our work by showing the underlying data and by disclosing any caveats, assumptions or other methodological frameworks used - for example, the study-design; the sample size; representativeness; margins of error; how the data was collected; geographical relevance and time periods.
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ቻይና በወታደራዊ ትርዒቷ ላይ የተለያዩ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን፣ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሌሎች ወታደራዊ መሳሪያዎችን ይፋ አድርጋለች። አንዳንዶች ይህ ለአሜሪካ እና ለአጋሮቿ ግልፅ መልዕክት ነው ሲሉ ይናገራሉ።
በዝግጅቱ ላይ ከ20 በላይ የውጭ አገራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ቻይና ላይ በኢኮኖሚ እና በሌሎች ድጋፎች ጥገኛ የሆኑት የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ይገኙበታል።
ትርዒቱ በዓለም መድረክ ላይ የዢ ጂንፒንግን ኃያልነት እና የቻይናን ወታደራዊ ብቃት ማሳያ ነበር።
በወታደራዊ ትርዒቱ ላይ ከታዩት የጦር መሳርያዎች መካከል "ጉዋም ኪለር" የተሰኘ ሚሳዔል፣ "ሎያል ዊንግማን" የተሰኘ ሰው አልባ አውሮፕላን እና 'ሮቦት ዎልቭስ' የተባለው ሮቦት ለዕይታ ቀርበዋል።
ግዙፍ እና ደማቅ ከሆነው አስደናቂ ወታደራዊ ትርዒት እና አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች ባሻገር ዓለም ስለ ቻይና ምን ተረዳ?
ረቡዕ ዕለት በነበረው ወታደራዊ ትርዒት ላይ ግልጽ የሆነው ነገር ቻይና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በፍጥነት ማምረት እንደምትችል ነው።
ከአሥር ዓመታት በፊት ቻይና ለዕይታ ያቀረበቻቸው ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች የአሜሪካ የላቁ መሳሪያዎች ቅጂ እንደነበሩ በሲንጋፖር ናንያንግ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመከላከያ ፕሮግራሞች ልማት ረዳት ፕሮፌሰር ሚካኤል ራስካ ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህ ትርዒት የበለጠ ፈጠራ እና ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች የታዩበት፣ በተለይም ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳዔሎችን በማምረት ረገድ የመከላከያ ኢንዱስትሪዋ ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የፓስፊክ ፎረም ተባባሪ አጥኚ አሌክሳንደር ኒል ደግሞ ቻይና ከከፍተኛ አመራር እስከ ታችኛው ካድሬ ድረስ ያላት መዋቅር እና ጉልህ ሃብት ከሌሎች አገራት በበለጠ ፍጥነት አዳዲስ መሳሪያዎችን ለማምረት ያስችላታል ሲሉ ያስረዳሉ።
እንዲሁም የጦር መሳሪያዎችን በከፍተኛ መጠን በማምረት ጠላትን የምታሸንፍበት የጦር ሜዳ የበላይነትን ሊሰጣት ይችላል።
ኒል "ቻይና ጥይቶችን፣ መርከቦችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን በፍጥነት ማምረት ትችላለች።…ምክንያቱም ያላት መዋቅር መሳሪያዎቹ እንዲመረቱ በቀጥታ መመሪያዎች እና ትዕዛዞችን መስጠት ይችላል" ብለዋል።
ነገር ግን ቻይና እነዚህን የጦር መሳሪያ ሥርዓቶች ከጦሯ ጋር እንዴት አድርጋ ታቀናጃቸዋለች?
"እነዚህን የላቁ መሳሪያዎች ለዕይታ ማቅረብ ትችላለች፣ ነገር ግን በፈለጉት መንገድ ለመጠቀም ድርጅታዊ ቅልጥፍና አላቸው ወይ?" ሲሉ ዶ/ር ራስካ ይጠይቃሉ።
የቻይና መከላከያ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ጉልህ የሆነ ጦርነት ውስጥ ባለመግባቱ፣ ጦሩ ግዙፍ እና ያልተፈተነ በመሆኑ ቀላል እንደማይሆን ጨምረው ያስረዳሉ።
ቻይና አንዳንድ አዳዲስ ምርቶችን ጨምሮ ብዙ ሚሳዔሎችን ለዕይታ አቅርባለች።
እነዚህም በሚሳዔሉ ጫፍ ላይ ብዙ አረሮችን መያዝ የሚችለው ዶንግፌንግ-61፣ ከሰሜናዊ ቻይና ተነስቶ አሜሪካን ሊመታ የሚችለው አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ዶንግፌንግ-5ሲን ይጨምራል።
እንዲሁም በጉዋም የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮችን ሊመታ የሚችል ዶንግፌንግ-26ዲ እና  መካከለኛ ርቀት የሚተኮስ ሚሳዔል የሆነው "ጉአም ኪለር" ናቸው።
እንዲሁም በፍጥነት የሚምዘገዘጉ እና ፀረ ሚሳዔሎችን ማምለጥ የሚችሉት እንደ ዋይጄ-17 እና ዋይጄ-19 ያሉ በርካታ ሃይፐርሶኒክ ፀረ መርከብ ሚሳዔሎች ለዕይታ በቅተዋል።
ቻይና በሚሳዔሎች ምርት ላይ እንድታተኩር የሚያደርጋት ምክንያት ምንድን ነው?
ኒል ቻይና የመከላከያ ስልቷ ቁልፍ አካል እንዲሁም የአሜሪካን የባሕር ኃይል የበላይነት ለመመከት ሚሳዔሎችን እና ሮኬቶችን በማምረት ላይ ትገኛለች ይላሉ።
ቻይናን የአሜሪካ የባሕር ኃይል በዓለም ላይ ካሉት የአውሮፕላን ተሸካሚዎች እና ማስወንጨፍያዎች ጋር ማወዳደር የማይታሰብ ነው።
ቻይና አሁንም በዚህ ረገድ በእጅጉ ወደ ኋላ ቀርታለች።
ነገር ግን ኒል እንዳስረዱት፣ በምዕራቡ ዓለም የመከላከያ ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባለሙያዎች እነዚህ ማስወንጨፊያዎች ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ብለው ይከራከራሉ።
ምክንያቱም ለማንኛውም የሚሳዔል ጥቃት "ተጋላጭ ሆነው ተቀምጠዋል።"
ቤይጂንግ የመከላከል አቅሟን ማጠናከር ብቻ ሳይሆን "የመልሶ ማጥቃት አቅሟን" እየፈጠረች ነው ብለዋል።
አክለውም አንድ አገር ጥቃት ካደረሰባት የአጸፋ እርምጃ እንድትወስድ የሚያስችላትን አቅም እየገነባች ነው ብለዋል።
ሌሎች ለዕይታ ከቀረቡት መካከል ብዙ ከተነገረላቸው የጦር መሳሪያዎች መካከል ኤልዋይ-1 የተሰኘው የጨረር ጦር መሳሪያ ይገኝበታል።
ይህ የጦር መሳሪያ ኤሌክትሮኒክሶችን ወይንም ከዕይታ የተሰወሩ የጦር ጄቶችን ሊያቃጥል ወይም ሊያስተጓጉል የሚችል ግዙፍ የጨረር መሳሪያ ነው።
እነዚህ የጨረር ጦር መሳሪያዎች ጄ-20 እና ጄ-35 አውሮፕላኖችን ጨምሮ የአምስተኛው ትውልድ ስውር ተዋጊ ጄቶችን ያካተቱ ናቸው።
በወታደራዊ ትርዒቱ ላይ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙትን ጨምሮ ብዙ ዓይነት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ነበሩ።
ግን የበርካቶችን ቀልብ የሳበው ኤጄኤክስ-002 (AJX-002) ግዙፉ የባሕር ሰርጓጅ ሰው አልባ አውሮፕላን ነው።
እስከ 20 ሜትር ርዝመት ያለው እጅግ ግዙፍ ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪ (XLUUV) በመባልም ይታወቃል።
ምናልባት የቅኝት እና የስለላ ተልዕኮዎችን ሊያከናውን ይችላል።
ቻይና "ሎያል ዊንግማን" የሚል ስያሜ የተሰጠውን ጂጄ-11 በስውር ጥቃት የሚፈጽም ሰው አልባ አውሮፕላኗንም ለዕይታ አቅርባለች።
ይህም ድሮን ሰው ከሚያበረው የጦር አውሮፕላን ጎን ለጎን በመብረር ለጥቃቱ እገዛ ያደርጋል።
ከተለመዱት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተጨማሪ "ሮቦቲክ ዎልቭስ" በወታደራዊ ትርዒቱ ላይ ለዕይታ ቀርበው ነበር።
እነዚህም ሮቦቶች ከስለላ እና ፈንጂዎችን ከመጥረግ ጀምሮ የጠላት ወታደሮችን እስከ ማደን ድረስ ለተለያዩ ወታደራዊ ግዳጆች ሊውሉ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ቻይና ለዕይታ ያቀረበቻቸው ድሮኖች በወታደራዊ ስልቷ ልትከተል የምትፈልገውን ግልፅ አቅጣጫ ያሳያል።
ይህም የመከላከያ መሳሪያዎቿን ቁጥር "ለመጨመር ብቻ ሳይሆን የተለመደውን የጦር ሠራዊቷን መዋቅር በአዲስ ለመተካት" ትፈልጋለች።
ዶ/ር ራስካ ቻይና ከዩክሬን ጦርነት ትምህርት ወስዳለች ይላሉ። ይህም አንድ አገር "በጠላት ላይ ድሮኖችን ብቻ በመልቀቅ" የመከላከያ አቅሟን ለማዳከም እንደሚችል ተገንዝባለች ሲሉ ያብራራሉ።
ኒል በበኩላቸው "በጦርነት ውስጥ ፈጣን ውሳኔ ሰጪነት ወሳኝ ተግባር ነው" ካሉ በኋላ፣ በፍጥነት በሚካሄድ ጦርነት መካከል ጠላትን ለማሸነፍ እና የበላይነቱን ለመያዝ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ማድረግ እንደሚችለው በ"ቅጽበት" ውሳኔዎች መሰጠት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ብዙ አገራት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በወታደራዊ ሥርዓታቸው ውስጥ ስለማሰማራት እና "ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በውጊያ ውስጥ ለማስገባት ምን ያህል ዝግጁ ነን" ሲሉ ይጠይቃሉ።
ቻይና ግን በዚህ ረገድ "በጣም ተዘጋጅታለች" ይላሉ ዶ/ር ራስካ። "ኤአይን መቆጣጠር እንደሚችሉ ያምናሉ። በሥርዓታቸው ውስጥ ለማካተትም እስከ መጨረሻው ርቀት ድረስ እየሄዱ ነው።"
ወታደራዊ ትርዒቱ ቻይና በቴክኖሎጂ አሜሪካ ላይ ለመድረስ በፍጥነት እየተጓዘች መሆኗን እና ግዙፍ የጦር መሳሪያ የመገንባት አቅም እንዳላት ያሳየ ነው።
ነገር ግን አሜሪካ አሁንም በወታደራዊ ግዳጆች በኩል የበላይነት እንዳላት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ዶ/ር ራስካ የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል "የላቀ" የሆነበት ምክንያት በግዳጅ ላይ ያሉ ሠራዊቶች ውሳኔ በመስጠት እና በመዋጋት ረገድ "ከታች ወደ ላይ" የሆነን የዕዝ ሰንሰለት የመከተል ባሕልን ስላዳበሩ ነው ብለዋል።
ይህ በጦርነት ውስጥ የበለጠ ፈጣን እና ቀልጣፋ ያደርጋቸዋል።
በሌላ በኩል ቻይና "ከላይ ወደ ታች" የሚወርድ አመራርን የምትከተል ሲሆን "ውድ እና ዘመናዊ የሆኑ መሳሪያዎች እና ሥርዓቶች ሊኖራቸው ቢችልም ከላይ ትዕዛዝ እስኪቀበሉ ድረስ ምንም ነገር ማንቀሳቀስ አይችሉም" ብለዋል።
ዶ/ር ራስካ ባለፈው ወር የቻይና የጦር መርከብ የፊሊፒንስ የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎችን ሲገጥም የተፈጠረውን በማስታወስ የሚገጥሟቸውን ታግዳሮቶች ይጠቅሳሉ።
"ቻይናውያን ቴክኖሎጂያችን የሚከላከል ነው ብለው ያስባሉ። ይህ አሜሪካን እንደሚገዳደር ያምናሉ...ነገር ግን በውጊያ ወቅት፣ እነሱ እንደሚሉት ብቁ ቁመና ላይ ላይሆኑ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች አሉ" ብለዋል።
ኒል በቻይና ግዙፍ ወታደራዊ ትርዒት ላይ የበርካታ አገራት መሪዎች መታደማቸውን ላስተዋለ፣ የጦር መሳሪያዎቹ እና ታንኮቹ ለዕይታ መቅረብ የቻይና የጦር መሳሪያ ገዥዎችን ለማማለል መሆኑን አያጣውም ሲሉ ያስረዳሉ።
እንደ ምያንማር ያሉ አንዳንድ አገራት የቻይና ጦር መሳሪያን በብዛት እንደሚገዙ ይታወቃል።
ዶ/ር ራስካ ለቻይና አዳዲስ ደንበኞች ማፍራት ወይንም ትዕዛዞችን መጨመር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተፅዕኖ እንዴት ማስፋት እንደምትችል ያሳያል ብለዋል።
ከዋና ደንበኞቻቸው መካከል ከዢ ጂንፒንግ ፊት እና መካከል የቆሙት ቭላድሚር ፑቲን እንዲሁም ኪም ጆንግ ኡን ይገኙበታል።
ሦስቱም በአንድነት ወደ ወታደራዊ ትርዒቱ ሲሄዱ እና መድረክ ላይ ሲቆሙ የጋራ ግንባር መፍጠራቸውን ያሳያል።
ኒል እንደሚሉት ከሆነ ይህ ለአሜሪካ የተላለፈ መልዕክት ነበር።
አሜሪካ በእውነት ቻይናን ለመገዳደር ከፈለገች "በተመሳሳይ ጊዜ በበርካታ ስፍራዎች በኮሪያ፣ በታይዋን ሰርጥ እና በዩክሬን እነርሱን መዋጋት ማለት ነው።"
"እና ይህንን ግምት ውስጥ ካስገባን በሦስቱም ጎራዎች አሜሪካ ውጊያ ውስጥ ከገባች፣ ከእነዚህ በአንዱ ዐውደ ውጊያ ላይሳካላት ይችላል።"
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ከተካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ላይ አስተላልፈውት የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለበት እንዲቀጥል ወሰኑ።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ ረቡዕ ዕለት የተፈረመው እና ባለበት እንዲጸና የተወሰነው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች ተስፋፍቶ የነበረው የእርስ በርስ ጦርነት አሳሳቢ በነበረበት ወቅት ነበር ተግባራዊ እንዲሆን በቀድሞው ፕሬዝዳንት የተወሰነው።
የተለያዩ ዕቀባዎችን የሚጥለው ይህ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲቀጥል የተወሰነበት ሰነድ "በኢትዮጵያ እና በአጠቃላዩ የአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋትን ስጋት ላይ የጣለው በሰሜን ኢትዮጵያ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ ያለው ሁኔታ ለዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ደኅንነት እና የውጭ ፖሊሲ አሳሳቢ እና የተለየ ስጋት ደቅኗል" ሲል አመልክቷል።
በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያን በሚመለከት ከአራት ዓመት በፊት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ተላልፎ የነበረው እና ተግባራዊነቱ መስከረም 7/2018 ዓ.ም. ሊያበቃ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲቀጥል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወስነዋል።
ይህ በሰሜን ኢትዮጵያ ከተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንት ባይደን ጥሰቶችን ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል 14046 የተሰኘ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ መስከረም 7/2014 ዓ.ም.  ነበር ያስተላለፉት።
በዚህ ትዕዛዝ ጦርነቱ እንዲራዘም አስተዋጽኦ ያደረጉ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ያደናቀፉ፣ ተኩስ አቁም እንዳይደረግ እንቅፋት በመሆን በቀጥታ ተጠያቂ የሆኑ ወይም ተባባሪዎቻቸው ላይ ዕቀባ እንዲጣል ይፈቅዳል።
ፕሬዝዳንቱ የፈረሙት ትዕዛዝ በዋናነት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት ባለሥልጣናት እንዲሁም በአማራ ክልል አስተዳደር እና በህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ነበር።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ትዕዛዙ መውጣቱን ተከትሎ የትዕዛዙ አስፈጻሚ የሆነው የአሜሪካ ግምጃ ቤት (ዲፓርትመንት ኦፍ ትሬዠሪ) በጦርነቱ ተሳታፊዎች ናቸው ባላቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የጦር ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንታዊው ትዕዛዝ ለአንድ ዓመት የሚጸና በመሆኑ ውሳኔው ከተላለፈበት መስከረም ጀምሮ በየዓመቱ በፕሬዝዳንቱ ትዕዛዝ ሲታደስ ቆይቷል።
በአሜሪካ ሕግ መሠረት አንድ "ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ" ድንጋጌ የተቀመጠለት ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ባሉት 90 ቀናት ውስጥ ባለበት እንዲጸና የሚያደርግ ጥያቄ ካልቀረበበት በስተቀር ተግባራዊነቱ ስለሚያበቃ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔው ባለበት የሚያዘውን ደብዳቤ ረቡዕ ዕለት የፈረሙት።
ፕሬዝዳንታዊው ትዕዛዝ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉንም ወገኖች የሚመለከት ሲሆን፣ የተለያዩ ጥሰቶችን የፈጸሙ እና ሰላም እንዳይወርድ እንቅፋት ሆነዋል የተባሉ ወገኖችን ተጠያቂ ለማድረግ ለአሜሪካ ግምጃ ቤት ሥልጣን የሚሰጥ ነው።
ይህ ትዕዛዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት አሜሪካ በያዘችው አቋም የተሰማውን ቅሬታ በመግለጽ የተቃውሞ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል።
ለተጨማሪ አንድ ዓመት በአዲሱ ፕሬዝዳንት እንዲራዘም የተወሰነው ይህ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ እንዲወጣ ምክንያት የሆነው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተጠናቀቀ ወደ ሦስተኛ ዓመት እየተቃረበ ቢሆንም አሜሪካ በውሳኔዋ ጸንታለች።
አሜሪካ በሰሜኑ ጦርነት ተሳታፊዎች ናቸው ባለቻቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የጦር አመራሮች እና ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ከመጣሏ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ መርሃ ግብር - አጎዋ- ተጠቃሚነት እንድትወጣ ካደረገቻት ዓመታት ተቆጥረዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ውስጥ 40 የሚሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ሲገደሉ፣ ከ200 በላይ የሚሆኑት እገታን ጨምሮ ሌሎች ጉዳቶች እንደደረሰባቸው አንድ የአሽከርካሪዎች ማኅበር ለቢቢሲ ገለጸ።
ጉዞ የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ማኅበር እንዳለው በአገሪቱ በግጭት ውስጥ በሚገኙ ክልሎች ውስጥ በጭነት ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎቻቸው ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እየተባባሱ መጥተዋል።
ይህ በአሽከርካሪዎች ላይ የደረሰው የሞት እና የአካል ጉዳት አሃዝ ማኅበሩ መረጃ የደረሰው እና ለማረጋገጥ የቻላቸውን ብቻ የሚያመለክት ነው።
የማኅበሩ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ታምራት፣ ከዚህ ቀደም አሽከርካሪዎችን በማገት ገንዘብ የመጠየቅ ሁኔታዎች እንደነበሩ ጠቅሰው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰላማዊ አሽከርካሪዎች "መሪ ጨብጠው በተቀመጡበት መኪና ውስጥ" እየተገደሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
"በዚህም ምክንያት ሙያውን የሚጠሉ እና ሥራቸውን የሚለቁ አሽከርካሪዎች እየተበራከቱ መጥተዋል" ብለዋል።
ጥቃቶቹ በአብዛኛው በተለይ የመንግሥት ኃይሎች ከታጣቂ ቡድኖች ጋር በሚፋለሙባቸው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እንደሚፈፀሙ አቶ ዮሐንስ አመልክተዋል።
በቅርቡም በአማራ ክልል በሚገኘው አዲስ ዘመን ከተማ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ታጅበው እየተጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ የአንድ አሽከርካሪ ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኘው ግዮን የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር መጋዘን እህል ጭነው ለመውጣት "እናጅማ" ወደተባለ ቀበሌ የገቡ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች መቃጠላቸው እና አሽከርካሪዎቹ ከእነ ረዳቶቻቸው ለቀናት ታግተው መቆየታቸውን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
"ወደ አካባቢው ማዳበሪያ ዘግይቶ በመግባቱ ምክንያት ከአካባቢው እህል ተጭኖ አይወጣም" የሚል ተቃውሞ እንደነበር ያወሱት እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ፣ ተሽከርካሪዎቹ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል ታጅበው ለመውጣት እየተጠባበቁ ሳለ ጥቃቱ እንደተፈፀመባቸው አስረድተዋል። በወቅቱ የተኩስ ልውውጥ እንደነበርም ነዋሪው ተናግረዋል።
"ታጣቂዎቹ እህሉን ከተሽከርካሪዎቹ ላይ ካወረዱ በኋላ ሌሎች ተሽከርካሪዎች ተመልሰው እንዳይመጡ በሚል ነው ያቃጠሏቸው።" ብለዋል።
በአካባቢው የተለያዩ ታጣቂዎች በመኖራቸው ድርጊቱን ማን እንደፈፀመው መናገር አስቸጋሪ ነው ያሉት ነዋሪው፣ አሽከርካሪዎቹ ግን "የፋኖ ታጣቂዎችን" ተጠያቂ እንዳደረጉ ገልጸዋል።
እንደ ነዋሪው ከሆነ ጥቃቱ የተፈፀመበት ቦታ ከደጀን ከተማ 26 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚርቅ ሲሆን በቅርብ ርቀት ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ካምፕ ይገኛል።
የግዮን የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር አንድ አመራርም በሁለት ተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጠዋል። ሆኖም አመራሩ "ለደኅንነቴ እሰጋለሁ" በማለት ስለ ክስተቱ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በጭነት ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎቻቸው ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በአማራ ክልል፣ መተማ፣ ሁመራ፣ አዲስ ዘመን እንዲሁም ከወልዲያ ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር በሚወስዱ መንገዶች ላይ፤ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ መተሃራ፣ ወለንጭቲ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም መስመር ባሉ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚፈፀሙ የጉዞ አሽከርካሪዎች ማኅበር ሊቀ መንበሩ አቶ ዮሐንስ ጠቅሰዋል።
ምንም እንኳን በኦሮሚያ ክልል ወለንጪቲ እና መተሃራ ይፈፀሙ የነበሩ ጥቃቶች መንግሥት በሥፍራው የፀጥታ ኃይሎችን በማሰማራቱ እና ከፍተኛ ጥበቃ በማድረጉ ጋብ ቢልም፣ በአማራ ክልል የሚፈፀሙ ጥቃቶች ግን ተባብሰው መቀጠላቸውን ተናግረዋል።
አቶ ዮሐንስ እነዚህ ጥቃቶች በታጣቂዎች እንደሚፈፀሙ የገለጹ ሲሆን፣ ለጥቃቶቹ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም በማለት የታጣቂዎቹን ማንነት እንደማያውቁ ተናግረዋል።
"ይህ ጥቃት እንዴት እንደሚቆም አናውቅም፤ ከመንግሥት አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው" ብለዋል።
ጉዞ የአሽከርካሪዎች ማኅበር በሥሩ አንድ ሺህ አባላት ያሉት ሲሆን፣ አባል አሽከርካሪዎቹ ኬንያ እና ጂቡቲን  ጨምሮ ከጎረቤት አገራት ነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች ጭነቶችን የሚያጓጉዙ ናቸው።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ብርሃኔ ዘሩም በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ በተለይም በጭነት ተሽከርካሪዎች እና አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።
የዘርፉ ሰላም እንዳይበላሽ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ግፊት እያደረግን ነው የሚሉት አቶ ብርሃኔ፣ ይህንን በማስመልከትም ለተወካዮች ምክር ቤት ደብዳቤ መጻፋቸውን ጠቅሰዋል።
"ጉዳዩ ትኩረት ካልተሰጠው እና የመንገዶቹ ደኅንነት ካልተጠበቀ አሽከርካሪዎች በሥራው ላይ የመሰማራታቸው ነገር አጠያያቂ ሊሆን ይችላል" ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አሽከርካሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተክሌ ሽፈራው በበኩላቸው በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቃቶች እንደሚፈፀሙ ገልጸው፤ "በአገሪቱ ባለው የሰላም እጦት ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አሽከርካሪዎች ነጻ ሆነው ማሽከርከር አልቻሉም፤ የተሰጣቸውን ጭነት በአግባቡ እና በሰዓቱ ለማድረስ እየተቸገሩ ነው" ብለዋል።
በቅርቡ ከጂቡቲ ነዳጅ ጭነው በእጀባ እየተጓዙ ባሉ ተሽከርካሪዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ የአንድ አሽከርካሪ ሕይወት ማለፉን አቶ ተክሌ ተናግረዋል።
በአብዛኛው ተሽከርካሪዎች ከጂቡቲ ነዳጅ ጭነው ወደ ባሕር ዳር እና ጎንደር የሚገቡት ጋሸና እና ገረገራ የተባሉ አካባቢዎችን አቆራርጠው እንደሆነ የገለጹት አቶ ተክሌ፣ ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡብ ጎንደር፣ ገረገራ በተባለ አካባቢ መሆኑን ጠቅሰዋል።
"መንስኤው የዘራፊ መበራከት ነው" ሲሉም መንግሥት ጥበቃውን አጠናክሮ አሽከርካሪዎች ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እንዲያስችል ጠይቀዋል።
በአማራ ክልልም ሆነ በአሮሚያ ክልል በአሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን በተመለከተ የክልሎቹን ባለሥልጣናት ለማነጋገር ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
በክልሎቹ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችም እነዚህን ጥቃቶች በተመለከተ ያሉት ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እና በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚቀርብባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
በቅርቡ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን "በታቀደ ጥቃት" የአፈር ማዳበሪያ ጭነው በእጀባ ሲጓዙ የነበሩ ቢያንስ 16 ሹፌሮች ሲገደሉ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ መታገታቸውን የአካባቢው አስተዳደር እና የአሽከርካሪዎች ማኅበር መናገራቸው ይታወሳል።
ከእነዚህ አሽከርካሪዎች አብዛኞቹ ሟቾች ከጂቡቲ ማዳበሪያ ጭነው በፀጥታ ኃይሎች ታጅበው ሲጓዙ የነበሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች መሆናቸው ተነግሯል።
ስለ ጥቃቱ ሰፋ ያለ መግለጫ ያወጣው የዞኑ አስተዳደር መከላከያ ሠራዊት እና የፀጥታ ኃይሎች ላይ "ታቅዶ፣ ሆን ተብሎ፤ ታስቦበት የተዘጋጀ" ሲል ጥቃቱን የገለፀ ሲሆን፤ ሾፌሮች መገደላቸውን አስታውቋል።
ለዚህም "ጽንፈኛ" ሲል የጠራቸውን በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የዓለማችን ኃያላን ሶቭየት ኅብረት እና አሜሪካ ፉክክር ላይ የነበሩበት።
የካፒታሊስቱ የምዕራቡ ዓለም እና የኮሚኒስቱ ምሥራቅ የርዕዮተ ዓለማቸውን የበላይነት ለማስፈን የተንቀሳቀሱበት፤ በተለምዶ ቀዝቃዛው ጦርነት ተብሎ የሚጠራው ጊዜ።
በዚህም ወቅት ከሶቭየት ኅብረት የተበረከተው እና የማዳመጫ መሳሪያ የተደበቀበት የጥበብ ሥራ (በእጅ የተሠራ ቅርጽ) በአሜሪካ የደኅንነት እና የስለላ ተቋማት ሳይታወቅ ለሰባት ዓመታት ቆይቷል።
ከ80 ዓመታት በፊት፤ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት እየተገባደደ የነበረበት ጊዜ ነበር።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የሩሲያ ስካውት ቡድን አባላት በሞስኮ ተቀማጭነታቸውን ላደረጉ የአሜሪካ አምባሳደር ስጦታ አበረከቱ።
ስጦታው በእጅ የተቀረጸ የአሜሪካ መንግሥት ዓርማ ነበር።
የስካውት ቡድኑ አባላት ስጦታቸውን ስፓዞ ሐውስ ወደተሰኘው የአምባሳደሩ መኖሪያ ቤት ሄደው ነበር ያበረከቱት።
ስጦታው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት አሜሪካ እና ሶቪየት የነበራቸውን ትብብር የሚያመለክት ነበር። የወቅቱ የአሜሪካ አምባሳደር ደብልዩ አቭሬል ሃሪማንም ይህንን ስጦታ እስከ አውሮፓውያኑ 1952 ድረስ በቤታቸው ውስጥ በኩራት ሰቅለውት ነበር።
ነገር ግን አምባሳደሩም ሆነ የፀጥታ ቡድናቸው ሳያውቁ ዓርማው ድብቅ የማዳመጫ መሳሪያ ተገጥሞበት ነበር።
መሳሪያው ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ሳይቀር ማንም ሳያወቅ ለሰባት ዓመታት ወደ ሶቪየቶች ሲያስተላልፍ ቆይቷል።
ሶቪየት ኅብረት የጠላትን መረጃ ለማወቅ የጥበብ ሥራን ሰርጎ የመግቢያ መሳሪያ በማድረግ ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማግኘት ችላለች።
የእንጨት ፈረስ ገንብተው በውስጡ ተደብቀው ጠላታቸውን ማሸነፍ ከቻሉት የግሪከ አፈ ታሪከ የትሮጃን ፈረስ በኋላ ድንቅ የሚባል ብልጠት ነበር ሶቭየት ኅብረት ያሳየችው።
ምንም እንኳን የስለላ ልብወለድ ቢመስልም ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው።
የአሜሪካ የደኅንነት ሰዎች 'ዘ ቲንግ' የሚል ስያሜ የሰጡት ይህ መሳሪያ እንዴት ሊሠራ ቻለ?
ጆን ሊትል የተሰኙት የ79 ዓመቱ የስለላ እና የደኅንነት ባለሙያ በዚህ መሳሪያ ለረጅም ጊዜ ሲደነቁ ቆይተዋል።
ይህንን ሥራ የሚያሳይ የሊትል ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ የወጣ ሲሆን፣ በመጪው ወርም በባኪንግሃምሻየር በሚገኘው ብሔራዊ ሙዝየም ለዕይታ ይበቃል።
ባለሙያው 'ዘ ቲንግ' የተሰኘውን ድብቅ የማዳመጫ መሳሪያ የሚገልጹት በሙዚቃ መሳሪያዎች ነው።
ልክ እንደ ዋሽንት እስትንፋስ ወደ ሙዚቃ የሚቀየርበት፣ ወይም የከበሮ ቆዳ ሲመታ ንዝረት ወደ ጆሮ ገብቶ ድምጽ የሚቀየርበትን መንገድ በመግለጽ ነው።
መሳሪያዋ በጣም አነስተኛ እንደ ወስፌ መሳይ ወይም የሴቶች ባርኔጣ ላይ የምትሰካ ጌጥ መሳይ ናት።
መሳሪያዋ የትኛውንም ክትትል ማለፍ ከመቻሏም በተጨማሪ፣ የተገጠመላት "የኤሌክትሮኒክስ ባትሪ" የላትም፤ እንዲሁም አትግልም።
እያንዳንዷ እርዝማኔ ተለክታ በጥልቀት ነበር የተሠራችው።
የታሪክ ምሁሩ ኤች ኬ ኪት ሜልተን እንደሚሉት 'ዘ ቲንግ' "የድምጽ ክትትል ሳይንስን ከዚህ ቀደመ የማይቻል ነው ተብሎ ወደሚታሰብ ደረጃ ያላቀች ናት" ብለዋል።
በአምባሳደሩ መኖሪያ ቤት ነበር በስጦታ በተበረከተው ዓርማ ውስጥ የተቀመጠችው መሳሪያዋ፤  በአቅራቢያው ባለ ሕንጻ የርቀት ማስተላለፊያም እንዲበራ ተደርጎ ነው የተዘጋጀው።
ይህም ከፍተኛ ፍሪኩዌንሲ በመላክ ከመሳሪያዋ አንቴና ንዝረቶች እንዲወጣ ማድረግ ቻለ።
በዚህ የጥብብ ሥራ ላይ የድምጽ መሳሪያ መገጠሙ የታወቀው በአውሮፓውያኑ 1951 ነበር።
በሞስኮ መቀመጫውን ያደረገው የብሪታንያ ወታደራዊ ሬድዮ አፕሬተር 'ዘ ቲንግን' የሚጠቀምበትን ትክክለኛ ሞገድ (ዌቭ ሌንግዝ) በአጋጣሚ በማግኘቱ ነበር ማዳመጫው መኖሩ የታወቀው።
እናም ኦፐሬተሩ ከሩቅ ክፍል ንግግር መስማቱን ተከትሎ ክትትል ተደረገ።
በዓመቱ የአሜሪካ ቴክኒሻኖች የአምባሳደሩ መኖሪያ ላይ ፍተሻ ጀመሩ።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ይህ በእጅ የተቀረጸው ታላቁ ዓርማ ያረፈበት የጥበብ ሥራ ከመጋረጃ ጀርባ የአምባሳደሩን ውይይቶች የሚያዳምጥ የማይታይ ጆሮ መሆኑን የተረዱ።
የ'ዘ ቲንግ'ን ስኬታማነትን አስመልክቶ ሩሲያዊው ቴክኒሻን እና መሳሪያዋን የሚቆጣጠራት ቫዲም ጎንቻሮቭ "ለረጅም ጊዜ፣ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት፣ አገራችን በጣም ጠቃሚ የሆኑ እና ልዩ መረጃዎችን በማግኘት በተወሰነ መልኩ አደራጅቶን ነበር" ይላል።
እንደ 'ዘ ቲንግ' ያሉ የሶቭየት ኅብረት መሳሪያዎች ምዕራባውያኑን ለመሰለል ምን ያህል ጥቅም ላይ እንደዋሉ እስካሁን ድረስ ከሶቭየት ኅብረት የስለላ ተቋማት ውጪ ማንም አያውቅም።
የስለላ መሳሪያዋ ዋነኛዋ ስኬት ቴክኒካዊ ሁኔታዋ ነበር።
ውበት ላላቸው ነገሮች ያለውን አመለካከት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነበር የተነደፈችው።
የሥነ ጥበብ ሥራዎችን ወይም ማስጌጫዎችን ከባህላዊ ፍላጎት ማሳያ ወይም የባህል መገለጫ ውጪ ሌሎች ዓላማዎች የላቸውም የሚለው እምነት አለ።
የሶቪየት የደኅንነት አካላትም ይህንን እሳቤ ከግምት ውስጥ በማስገባት በእንጨት የተቀረጸውን ዓርማ መጠቀሚያ አድርገውታል።
'ዘ ቲንግ' ብቸኛው ቅርጽ ብቻ አይደለችም ለስለላ እና ለወታደራዊ ስልት መጠቀሚያ የተደረገች።
የሥነ ጥበብ ታሪክን በምንመረምርበት ወቅት ታዋቂው ሠዓሊ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሞናሊዛን ከመሳል በተጨማሪ ታንኮች እና ምሽግ መስበሪያ የጦር መሳሪያዎችን ነድፏል።
ታዋቂው ሰዓሊ ፒተር ፓውል ሬበንስ በሰላሳ ዓመታት ጦርነት ወቅት ሰላይ ነበር።
በአንደኛው እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ አርቲስቶች ጥበብን እንደ ሽፋን በመጠቀም ለዓላማቸው መጠቀሚያ አድርገዋል።
ስመ ጥሩ የብሪታንያ የጥበብ ታሪክ ተመራማሪው አንቶኒ ብለንት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የሶቭየት ኅብረት ሰላይ ነበር።
ወደ 'ዘ ቲንግ' ስንመጣም የሙዚቃ ታሪክ የጉዳዩ ማዕከል ሆኖ እናገኘዋለን። የዚህች መሳሪያ ፈጣሪ ሌቭ ሰርጌይቪች ተርመን ወይም ሊዮን ቴርሚን እየተባለ የሚጠራው የሶቪየት ዜጋ የሆነ ጎበዝ መዚቀኛ እና የፈጠራ ሥራዎችን ያበረከተ ሰው ነው።
ይህ ሙዚቀኛ የዓለማችን የመጀመሪያ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ የፈለሰፈም እንደሆነ ይነገርለታል።
የሙዚቃ መሳሪያውም በስሙም ቴሬሚን በመባል ይታወቃል።
መሳሪያውን ሳይነኩ፣ በአየር ላይ እጅ በማንቀሳቀስ አንቴናዎቹ የሙዚቃዎቹን ኖት እንዲያዙ በማድረግ መጫወት የሚችሉት መሳሪያ ነው።
'ዘ ቲንግ' ከተገኘች በኋላ ጉዳዩ በአሜሪካ የስለላ ሰዎች ምሥጢር ሆኖ ቆይቶ ነበር።
ነገር ግን በአውሮፓውያኑ 1960 የኒውክሌር የጦር መሳሪያ እሽቅድድም ጣሪያ በነካበት ወቅት የአሜሪካ ዩቱ የተሰኘ የስለላ አውሮፕላን በሶቪየት ምድር ላይ ተመትቶ ወደቀ።
በዚህ የዲፕሎማሲ ቀውስ ወቅት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት የቀዝቃዛው ጦርነት ስለላ የአንድ ወገን ብቻ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ሩሲያ በጥበብ ሥራ ውስጥ የቀበረችውን የማዳመጫ መሳሪያ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አጋለጡ።
የአምባሳደሩን መኖሪያ ቤት መደፈሩ አሳፋሪ የደኅንነት ጥሰት በመሆኑም ጆን ሊትል እንደሚናገሩት "ነገሩን በይፋ ለመናገር የስለላ አውሮፕላን ተመትቶ መጣል ነበረበት" ይላሉ።
ነገር ግን 'ዘ ቲንግን' የተደበቀበችበትን የላቀ መንገድ በወቅቱ ለሕዝብ አልተነገረም ነበር።
ሆኖም በድብቅ የብሪታኒያ የስለላ ባለሙያዎች መሳሪያዋን "SATYR" በሚል የኮድ ስም በጥልቅ ጥናት አካሂደውባታል።
ዝርዝሮቹ መንግሥታዊ ምሥጢር ተደርገው ቢቆዩም የቀድሞ የደኅንነት መኮንን ፒተር ራይት በአውሮፓውያኑ 1987፣ 'ስፓይካቸር' በሚለው ማስታወሻው ላይ ይፋ አድርጎታል።
'ዘ ቲንግ' በቴክኒክ መራቀቋ፣ የቀዝቃዛውን ጦርነት የስለላ ጨዋታን በመቀቀር በርካታ የታሪክ ምሁራንን ያስደመመች ናት።
የክላሲካል ሙዚቀኞች እንዲህ ዓይነት የስለላ መሳሪያ መፍጠራቸው፣ በእጅ የተቀረጸ የጥብበ ሥራ ወታደራዊ መረጃዎቸን ለመሰብሰብ መዋሉን የሚያስታውስም የድብቁ ታሪክ አካል ነው።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው።
ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት።
ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን።
በኦቲዝም ኅብር (Autism spectrum) ውስጥ ያሉ ሰዎች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
ብዙ ጊዜ 'ኦቲዝም' የአእምሮ ውስንነት ተብሎ በግርድፉ በስንፍና ይተረጎማል። ዶ/ር ወንድወሰን ይህ ትርጓሜ ይጎረብጣቸዋል።
''የአእምሮ አሠራር ልዩነት'' በሚል ቢገለጽ ይመርጣሉ።
ለምን ሲባሉ፣ 'ኦቲዝም' ውስንነት ሳይሆን 'የአእምሮ የአሠራር ልዩነት' ስለሆነ ነው ይላሉ። እንዲህ ያብራሩታል።
"እኔ ለምሳሌ ስሜቴን መግራት ችግር ሊኖርብኝ ይችላል። አንተ ደግሞ ቁጥር ስሌት ጊዜ ሊወስድብህ ይችላል። ሌላ ሰው ተግባቦት ላይ ደከም ይላል። የዕድገት ውስንነት ነው ከተባለ ከእኛ ውስጥ ማን 'ውስንነት' የሌለበት አለ? "
ለዚህ ጽሑፍ የዶ/ር ዮናስ ባሕረ ጥበብን አገላለጽ ተውሰን ብንቀጥልስ?
ዶ/ር ዮናስ የአእምሮ ሕክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። በጉዳዩ ላይ "ዓይኔን ተመልከተኝ'' የሚል ግሩም መጽሐፍ ጽፈዋል።  ይህን 'ኦቲዝም' የሚለውን እክል ''የአእምሮ ዕድገት ሥርዓት መዛባት'' በሚል ይገልጹታል።
ይህ ነገር በዓለም እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም። ለምን ለሚለው ማንም ምላሽ የለውም።
በአሜሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ36 ሕጻናት አንዱ የአዕምሮ ዕድገት መዛባት አለበት።
ከ20 ዓመት በፊት ከ500 ልጆች አንዱ ብቻ ነበር ይህ የዕድገት መዛባት የሚገጥመው።  ከ80 ዓመት በፊት ግን ከ10ሺህ ልጆች አንዱ ብቻ።
በዓለም 75 ሚሊዮን፣ በአገራችን 5 ሚሊዮን ሰዎች ይህ ' ''የአእምሮ ዕድገት ሥርዓት መዛባት''' አለባቸው ይላሉ መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚወጡ ሰነዶች።
ለምንድነው እየጨመረ የመጣው የሚለው ትልቅ ጥያቄ ይቆየን።
'የኦቲዝም ኅብር' ውስጥ ያሉ ኑሯቸው እንዴት ይሻሻል የሚለው አጀንዳ ላይ ይበልጥ እናተኩር።
ብዙዎቹ  በዚህ የአእምሮ ዕድገት መዛባት ኅብር ጥላ ሥር ያሉ ሰዎች በሌሎች ላይ ጥገኛ ናቸው። ይሄ እንዲያበቃ ሳይንስ ብዙ ርቀት እየሄደ ነው።
በኳታር ዩኒቨርስቲ የሚመራመሩት ዶክተር ወንድወሰን፣ 'የአእምሮ ዕድገት መዛባቱ ያለባቸው' መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ምርምር የጀመሩት ከአራት ዓመት በፊት ነበር።
የኳታሩ ዩኒቨርስቲ ከቤልጂየሙ ሐሰልት ዩኒቨርስቲ ጋር በቅንጅት ይሠራል።
እርሳቸው የዚያ ፕሮጀክት አካል ሆነው ነው  ከስምንት ባልደረቦቻቸው ጋር ጥናት የጀመሩት።
አሁን በኳታር መንግሥት ተቀባይነት ያገኘ በ'ኦቲዝም ኅብር ሥር'  ለሚኖሩ ሰዎች' የሚሆን የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ማንዋል አቅርበዋል።
በአረብኛ እና በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ በኳታር የአሽከርካሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለአገልግሎት ተሰናድቷል።
ምርምሩ ግብ አድርጎ የተነሳው በዕድገት መዛባት ኅብር ሥር ያሉ ሰዎችን በከፊልም ቢሆን ከጥገኝነት ለማላቀቅ ነው።
''እነሱ መሪ ሲጨብጡ እና ራሳቸውን ሲችሉ ማየት ትልቅ እርካታ የሚሰጥ ነው" ይላሉ፣ ዶ/ር ወንድወሰን።
ጥናታቸው ሰው ሠራሽ አስተውሎት በተገጠመላቸው መኪናዎች ላይ ያተኮረ አይደለም።በዚያ ረገድ ሳይንስ ብዙ ርቀት ሄዷል።
የርሳቸው ጥናት በተለምዶ 'ማንዋል እና አውቶማቲክ' በሚባሉት መደበኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ያተኮረ ነው። የዕድገት መዛባቱ ያለባቸው በራሳቸው እነዚህን መኪናዎች እንንዲያሽከርክሩ ማስቻል ነው፣ የጥናቱ ዋና ግብ።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች በባሕረ ሰላጤው አገራት ቁጥራቸው ትንሽ ከፍ ይላል።
ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግርድፍ ጥናቶች ነገሩ ከቅርብ ዘመድ ጋብቻ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ይጠቁማሉ። ምርምሩ ግን እንደቀጠለ ነው።
በኳታር ዕድሜያቸው ከ6 እስከ 11 ባሉ አዳጊዎች ከ87ቱ አንዱ 'በኦቲዝም ኅብር (Autism Spectrum) ጥላ ሥር ነው።
በዚህም የተነሳ የኳታር መንግሥት ከፍተኛ በጀት መድቦ ከሚሠራባቸው ዘርፎች አንዱ እነዚህን ዜጎች ማገዝ ላይ ነው።
ኳታር ፋውንዴሽን በዚህ ረገድ ስሙ በበጎ ይነሳል። በኦቲዝም ጉዳይ ለሚደረግ ጥናት እና ምርምር ሳይሰስት በጀት ይመድባል።
እንዳለመታደል በኦቲዝም ኅብር (Autism Spectrum) ጥላ ሥር የሚኖሩ ሰዎች  ብዙዎቹ በዕለታዊ ኑሮ  አድራሽ-መላሽ- አጉራሽ ያስፈልጋቸዋል።
ለምን ግን መኪና በራሳቸው እንዲያሽከረክሩ አይሞከርም? የሚለው በአንድ ዘመን ለብዙዎች 'የእብድ ሐሳብ' ነበር የሚመስለው።
በኳታር ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የትራንስፖር ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ወንድወሰን ከዚህ 'ያልተለመደ' ጥያቄ ነው የተነሱት።
ዶ/ር ወንድወሰን ይህን ኮስተር ብለው እንዲያስቡ ያደረጋቸው ምናልባት በቀደመ ሙያቸው የሥነ ልቦና አጥኚ መሆናቸው ሊሆን ይችላል።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እና ከዚያ በኋላ በተለያዩ የአውሮፓ ዩኒቨርስቲዎች የሠሯቸው ሁለት ተከታታይ የማስተርስ ዲግሪዎች በልጆች ዕድገት እና ሥነ ልቡና ላይ ያተኮሩ ነበሩ።
ሦስተኛው ማስተርሳቸው ደግሞ የትራንስፖርት ሳይንስ ነው።
ይህ ጥምዝምዝ የትምህርት ጉዞ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር በሚኖሩ ሰዎች የመኪና ማሽከርከር ጉዳይ ላይ እንዲያተኩር አደረገው።
ዶ/ር ወንድወሰን በቤልጂየም ሐሰልት ዩኒቨርስቲ በትራንስፖርት ዘርፍ በከፍተኛ ማዕረግ ከተመረቁ በኋላ ነው ወደ ኳታር ያቀኑት።
በታዋቂው ሐሰልት ዩኒቨርሰቲ ያቀረቡት የጥናት ወረቀትም 'የዓመቱ ምርጥ የምርምር ሥራ' በሚል ሽልማት ተበርክቶለታል።
እርሳቸው በመሩት እና ኳታር ፋውንዴሽን ባገዘው በዚህ ምርምር የአሽከርካሪ ትምህርት ቤት መምህራን እና በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር የሚኖሩ ዜጎች ተሳትፈውበታል።
የአእምሮ ዕድገት መዛባት ያለባቸው ወጣቶች እንዴት መኪና ሊያሽከረክሩ ይችላሉ የሚለው የምርመሩ ዋና ማጠንጠኛ ሆነ።
"መጀመሪያ ያደረግነው የመኪና መለማመጃ ትምህርት ቤቶችን መገምገም ነበር" ይላሉ፣ ዶ/ር ወንድወሰን።
ከዚያ በኋላ ነው 'በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር' ያሉ ሰዎች  በትምህርት ቤቶቹ የሚገጥማቸውን ፈተና ወደመመርመር የገቡት።
"ኦቲዝም ሲባል ሁሉም አንድ አይደሉም፤ በአንድ አይጨፈለቁም፤ እንደ ቀስተ ደመና ኅብረ ቀለም (ስፔክትረም) ያለ ነው" የሚሉት ዶ/ር ወንድወሰን እርሳቸው የመሩት ጥናት በተወሰኑት ላይ ብቻ እንዳተኮረ ያብራራሉ።
"እኛ የወስድነው የአእምሮ ልኬታቸው [IQ] አማካይና ከዚያ በላይ የሆኑትን ብቻ ነው" ይላሉ።
የሚያሳዩት መገለጫ የተለያየ ነው፤ የተጣባቸው ባሕሪና ልማድ፣ የተግባቦት ተግዳሮት ደረጃ፣ የሚፈጽሙት የድግግሞሽ ድርጊት ዓይነት ወዘተ. . . ለየቅል ነው፤ ጥናቱን ከባድ የሚያደርገውም ይህ በመሆኑ ነው።
ከሚያመሳስሏቸው ባህሪያት መካከል ደግሞ ብዙዎቹ ድምጽ ይረብሻቸዋል። በተለይ የመኪና ጡሩንባ ያውካቸዋል።
ከመኪና የሚረጭ ብርሃን መቋቋም ያቅታቸዋል፣ አንዳንዶች ደግሞ ለረዥም ሰዓት በትንሽዬ ነገር ላይ አተኩሮ የመቆዘም አዝማሚያ ያሳያሉ።
ከለመዱት ነገር ውልፍት አይሉም። አዲስ ከባቢ ያስጨንቃቸዋል።
መንገዱ ላይ ባለች ጠጠር ወይ የመኪና መስታወት ላይ ባረፈች አንዲት ዝንብ ላይ ብቻ ፈዘው ሊቀሩ ይችላሉ።
መኪና ማሽከርከር ደግሞ አካባቢን በንቃት መቃኘት እና ከባባዊ ሁኔታን ፈጥኖ መረዳት ይሻል።
ይህ በመሆኑ ለነርሱ በተለየ የሚዘጋጅ የማሽከርከር ክኅሎት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው።
የጥናቱ አንድ ግብ የነበረው ለእነርሱ የሚመች የአሽከርካሪ ሥልጠና ማሰናዳት ነበር።
በአንጻሩ በኳታር የአሽከርካሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራኑ ስለ 'ኦቲዝም' ያላቸው ግንዛቤ በጣም አናሳ ሆኖ ተገኘ።
አንዳንዶቹ  መምህራን በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር ያሉ መኪና ተለማማጆችን ቀሰስ ሲሉባቸው ይጮኹባቸዋል።
''ያላ! ያላ!' (ዳይ ዳይ!) እያሉ ያዋክቧቸዋል። ይሄ ደግሞ ለአንድ 'በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር ላለ እጅግ  የሚያውክ ነው።"
የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰናዳ። አሰልጣኖች ሰልጣኞቹን እንዴት ማስተማር እንዳለባቸው ተማሩ።
ይህ ሥልጠና በዓይነቱ አዲስ ስለነበረ በኳታር ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ያገኘ ነበር።
እንደ 'መርሃባ'፣ 'ገልፍ ታይምስ' እና ኳታር ትሪቢዩን ሳይቀሩ ብዙ የአገሬው ጋዜጦች ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል።
ለዚህ ጥናት የተመረጠው የኳታሩ ''ካርዋ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ'' ነበር።
84 መምህራን እና ጥቂት በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር የሚኖሩ ልጆች ለጥናቱ ተመረጡ።
ለግማሾቹ በኦቲዝም ዙሪያ ከፍተኛ ሥልጠና ተሰጣቸው።
ለምሳሌ የአእምሮ ዕድገት መዛባት ያለባቸው እንዴት በሰከነ መንገድ ማስተማር እንዳለባቸው፣ ልዩ ፍላጎታቸውን እንዴት መለየት እንደሚችሉ፣ የታመቀ አቅማቸውን በተመለከተ በጥሩ ሁኔታ እንዲረዱ ተደረጉ።
ሌሎቹ መመህራን ደግሞ ድሮ በሚያስተምሩበት ሁኔታ ማስተማር እንዲቀጥሉ ተደረገ።
ለ28 ቀናት ሥልጠና በወሰዱ መምህራን የተማሩት የመንጃ ፈቃድ ፈተናን ሁሉም ባይሆን ብዙዎቹ አለፉ።
ባልሠለጠኑ መምህራን የተማሩት ደግሞ ሁሉም ወደቁ።
በኳታር የመንጃ ፈቃድ ፈተና  የሚሰጠው በትራፊክ ፖሊስ መሥሪያ ቤት አማካኝነት ነው። ይህም የጥናቱን ገለልተኝነት የሚያጎላ ሆኖ ተወስዷል።
"ብዙዎቹ በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር የሚኖሩ ተማሪዎች የጽሑፍ ፈተናውን 40 ጥያቄ ለመመለስ 10 ደቂቃም አልፈጀባቸውም። ውጤቱ አስደናቂ ነበር" ይላሉ ዶክተር ወንድወሰን።
ይህን ለመረዳት ዶ/ር ወንድወሰንና የጥናት ቡድናቸው ምናባዊ የሬንጅ ሮቨር መኪና (Simulator) ተጠቅመዋል።
ይህ 'ሲሙሌተር' እውናዊውን ዓለም የሚያካትት ዘመናዊ መሣሪያ ነው።
''ንፋሱን፣ የሞተር ድምጽን፣ የተሽከርካሪ ትርምሱን፣ የእግረኛ ግርግሩን ሁሉ የሚወክሉ ነገሮች ተገጥመውለታል።"
ይሄ መሣሪያ ታዲያ ፍጥነትን፣ መንቀርፈፍን (deceleration)፣ የብርሃን ፍልቅታን፣ ርቀትን አደጋን ወዘተ መለካት ይችላል።
ሌላው ለምርምር የተጠቀሙት መሣሪያ የዓይን ብሌን ተቆጣጣሪ መሣሪያ (Eye tracker) ነበር።
የዚህ ዘመናዊ መሣሪያ ጥቅም በተገጠሙለት ካሜራ አማካኝነት የዓይን እርግብግቢት እና ውልውልን መለካት ነው።
"እየነዳህ የሆነች ነገርን ለስንት ሚሊ ሰከንድ ተመልክተህ በምን ፍጥነት እርምጃ ወሰድክ የሚለውን ጭምር ይለካል" ይላሉ ዶ/ር ወንድወሰን።
ለምሳሌ አንድ ሰው በዚህ ጋር ትንኝ እልፍ ስትል አይተሃል ተብሎ ቢጠየቅ "እረ በጭራሽ" ሊል ይችላል። ነገር ግን ብሌን ተቆጣጣሪው መሣሪያ ማየቱን ብቻ ሳይሆን ለስንት ማይክሮ ሰከንድ እንዳያት ይመዘግባል።
በጥናቱ እንደተመላከተው ተለማማጆቹ ከሌሎች በተለየ "መሪ ስጨብጥ የልብ ምቴ ይጨምራል፣ አደጋ አደርሳለሁ ብዬ እሰጋለሁ፣ ሰዎች ጎበዝ መኪና አሽከርካሪ እንዳልሆንኩ ያስባሉ ብዬ እጨነቃለሁ" ይሉ ነበር።
በዚህ ጥናት የተሳተፉት ሌላው የዶ/ር ወንድወሰን ባልደረባ የኳታር ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር፣ ዶ/ር ዋኢል አልሐጂያሲን "በተሻለ ደረጃ ያሉ ኦቲስቶች ሳይቀር መኪና ማሽከርከርን እንደቀላል አያዩትም፣ ለዚህም ምክንያት አለው" ሲሉ 'መርሃባ' ለተሰኘው የኳታር ጋዜጣ አስተያየት ሰጥተው ነበር።
እነዚህ ተማሪዎች ችግራቸው እና ስጋታቸው ከተለየ በኋላ በሠለጠኑ መምህራን አዲስ ሥልጠና ሲሰጣቸው የሚያሳይዋቸው ያለመረጋጋት ስሜቶች ረገብ ብለው መታየታቸው በጥናቱ ተፈትሿል።
ይህ በዶክተር ወንድወሰን እና በረዳት ፕሮፌሰሩ የተመራው ጥናት ያረጋገጠው አንድ አቅም ይኸው ነው። በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር ያሉ የተለየ የሥልጠና ከባቢን ይሻሉ።
ከዚያ ሌላ ግን ይህ ጥናት እነሱ የችሎታ ማነስ አለባቸው የሚለውን ጥናቱ ውድቅ አድርጎታል። ነገሮችን የሚረዱበት መንገድ የተለየ ሊሆን ይችላል እንጂ የችሎታ ማነስ አልነበረም በአመዛኙ የተስተዋለው።
እሱን ከግምት ያስገባ ሥልጠና ከተሰጣቸው ከዕለታዊ ድጋፎች መላቀቅ እንደሚችሉ፣ በራሳቸው መቆም እንደሚችሉ ጥናቱ አረጋግጧል።
የፎቶው ባለመብት, The Peninsula Qatar
ለአደጋ ቢጋለጡስ? የሚለው ጥያቄ የአእምሮ ዕድገት መዛባት ያለባቸውን ብቻ የሚመለከት መሆን የለበትም ይላሉ ዶክተር ወንድወሰን።
ጥያቄው መሆን ያለበት አደጋው የደረሰው መኪናው የተዘወረው 'በኦቲዝም ጥላ ሥር ባለ ሰው ስለሆነ ነው ወይ? የሚለው ነው።
በዚህ ዓመታትን በወሰደው የነ ዶ/ር ወንድወሰን ጥናት መሠረት አደጋ የመከሰት ዕድሉን ለመቀነስ መደረግ ያለባቸውን ምክረ ሐሳቦች አቅርበዋል።
ለምሳሌ ለአንድ ድንገተኛ ክስተት ፈጣን ምላሽ  የመስጠት ችግር (Reaction Limitation) ያለባቸው ለማጅ አሽከርካሪዎች የመጀመሪያውን ሦስት ወር መሀል መንገድ እንዳይነዱ ይደረጋል።
በዚህ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሰው የማይኖርበት ሰፈር ከአስተማሪ ጋር እንዲያሽከረክሩ ይደረጋል።
ሆን ተብሎ ድንገተኛ አደጋዎች (ሐዛርድ) እንዲያጋጥማቸው እየተደረገ ምላሻቸው ይታያል።
ሌላ ሦስት ወራት ደግሞ የጎዳና መሀል መስመርን (Middle Lane) ይዘው ያሽከረክራሉ። ይህም ከአስተማሪ ጋር የሚሆን ነው።
ዝርዝር ማኑዋሉ እንዲህ እንዲያ እያለ ችግሮቻቸው ላይ መሠረት ያደረገ ሥልጠና እንዲሰጣቸው ያስችላል።
መኪና ማሽከርከር በጊዜ ርዝማኔ 'ልማዳዊ ተግባር' (Habit) የሚሆን ክኅሎት ነው።
''አንዳንዴ እየነዳህ እንደሆነ ሳታስብ ብዙ ርቀት ትነዳና እንዴት እዚህ ድረስ ነዳሁ ብለህ ለራስህ ትደነግጣለህ"
ይህ ነገር በኦቲዝም ጥላ ላሉ ተለማማጆችም ይሠራል። ''ብዙዎቹ በ7 ወር ውስጥ እዚያ ደረጃ ይደርሳሉ'' ይላሉ ዶ/ር ወንድወሰን።
የሚገርመው ብዙዎቹ በኦቲዝም ኅብር ሥር ያሉ በባህሪያቸው ሕግ አክባሪ (Rule Bound) ናቸው።
ለምሳሌ ርቀት ጠብቀው ያሽከረክራሉ። ለምሳሌ ከተነገራቸው የትራፊክ ሕግ ወልፈት አይሉም። በእርግጥ ይህ ጥቅምም ጉዳትም ሊኖረው ይችላል።
ጉዳቱ እንዳያመዝን ግን በሥልጠና የሚገራ ይሆናል።
''ዓይኔን ተመልከተኝ'' የሚል መጽሐፍ የጻፉት ዶክተር ዮናስ ባሕረ ጥበብ በመጽሐፋቸው ይህ ውስነነት 'ኅብረቀለም' እንደሆነ በስፋት አመላክተዋል።
እክል ያለባቸውን ልጆች ጨፍልቆ በአንድ ማየት እንደማይገባም ያወሳሉ።
ለምሳሌ አንዳንዶች ጽኑ የአእምሮ ብስለት ችግር አለባቸው። ሌሎች ደግሞ በሆነ አንድ ጉዳይ ላይ እጅግ የላቀ እና የረቀቀ ዕውቀት ይኖራቸዋል።
የእድገት እክሉን በአንድ መፈረጅ እንደማይገባም ይመክራሉ።
ይህን ሐሳብ የሚጋሩት ዶ/ር ወንድወሰን ምርምር ካደረጉባቸው ወጣቶች መካከል አንድ የኳታር ዜጋ እንዴት እንዳስደመማቸው ያስታውሳሉ።
"ወጣት ነው፤ እናቱ አስተዋወቁን። ልጃቸው ልዩ የስሌት ችሎታ እንዳለው ጠቆሙኝ። የልደቴን ቀን ጠየቀኝ፤ ነገርኩት። ከዚያ የዛሬ 10 ዓመት በምን ቀን እንደዋለ አስልቶ ነገረኝ። ይህን ሊነግረኝ ሰከንድ አልወሰደበትም" ይላሉ።
እሳቸው ግን ልጁ የነገራቸው ነገር ልክ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ኮምፒውተር ውስጥ ገብተው ስሌት መስላት ነበረባቸው።
"የልጁን መልስ ትክክል ሰለመሆኑ ለመረዳት ዘለግ ያለ ጊዜ ወስዶብኛል።"
ሌላ የምርምሩ አካል የነበረና በኦቲዝም ኅብር ጥላ ሥር የሚኖር ልጅ ሲናገር ይርበተበታል፣ ዐረፍተ ነገሩ ይቆራረጣል። ነገር ግን አእምሮው ስል ሆኖ አግኝተነዋል ይላሉ።
"የብስለት ምጣኔውን (IQ) ለክተነው 109 ነበር። እኛ ፕሮፌሰሮቹ እንኳ ይህን ያህል የለንም።"
ዶ/ር ወንድወሰን የጥናቱ ትሩፋት ወደ ኢትዮጵያም እንዲዘልቅ ይመኛሉ።
"ዋናው ነገር ልጆቹ የአንድ ልዩ ክኅሎት ባለቤት መሆናቸውን መረዳት ነው። አሪፍ ከባቢ ከተመቻቸላቸው ታላቅ ፈጣሪዎች ናቸው።"
ምቹ ሁኔታ ካልተፈጠረላቸው ግን ለዓለም አዲስ ነገር ማበርከት ቀርቶ መንጃ ፈቃድ ለማውጣትም ይቸገራሉ።
"በእነርሱ አቅም የትየሌለነት ማመን ማቆም አይገባንም።ልዩነት ነው እንጂ ውስንነት አይደለም የምለውም ለዚሁ ነው።"
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ኢትዮጵያ ባለፉት 14 ዓመታት ስትገነባው የነበረውን ግድብ ባስመረቀችበት ዕለት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያን የተናጠል እርምጃን በመቃወም ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ።
ባለፉት ዓመታት የግድቡን ውሃ አሞላል እና ቀጣይ ሥራን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ተደጋጋሚ ንግግሮች ቢካሄዱም ከሚያስማማ ነጥብ ላይ ሳይደረስ የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ በይፋ ተመርቋል።
የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት የተካሄደውን የግድቡን ምረቃ ተከትሎ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የአገራቸውን ተቃውሞ የሚገልጽ ደብዳቤ ልከዋል።
ግብፅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት ለተባበሩት መንግሥታት ተደጋጋሚ ደብዳቤ የጻፈች ሲሆን፣ የግድቡ ምርቃት በተካሄደበት ጳጉሜ 4/2017 ዓ.ም. በላከችው ደብዳቤ ላይ በግድቡ ላይ ያላትን ተቃውሞ አስፍራለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለየፀጥታው ምክር ቤት በላኩት ደብዳቤ ላይ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ግንባታዋ "የዓለም አቀፍ ሕግጋትን እና የምሥራቅ አባይ ተፋሰስን የሚመሩትን ደንቦችን የሚጥስ የአንድ ወገን ፕሮጀክት ነው" ብለዋል።
በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ 14 ዓመታት የወሰደ ሲሆን፣ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ለበርካታ ጊዜያት ለድርድር ተቀምጣ እንደነበር ይታወሳል።
ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የወጣበት ግድብ የውሃ አቅርቦታችንን ይቀንሰዋል የሚል ስጋት ያደረባቸው ሱዳን እና ግብፅ የውሃ ሙሌቱ እና አስተዳደሩን በተመለከተ ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ቢወተውቱም ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ የምትወስዳቸውን ሁሉንም የተናጠል እርምጃዎችን እንደማትቀበል እና "በሁለቱ የታችኛው የተፋሰሱ አገራት ሕዝቦችን የኅልውና ጥቅሞች ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል" ያለችውን ግድብ እንደማትቀበል ግብፅ አመልክታለች።
ነገር ግን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባቸው የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ለመጉዳት ሳይሆን አለመሆኑን እና በጋራ በመጠቀም ዓላማ "አብረን ተካፍለን ከመብላት" ነው በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም ለወደፊት ለሚሠሩ ትላልቅ ሥራዎች፣ አገራቱ በትብብር እና በጋራ እንዲቆሙ ለግብፅ እና ለሱዳን ጥሪ አቅርበዋል።
ግብፅ በግድቡ የምረቃ ዕለት ለተባበሩት መንግሥታት በጻፈችው ደብዳቤ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ትብብር የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ስጋት ከግምት ባስገባ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት ብላለች።
"በተቃራኒው ግን ኢትዮጵያ ግትር አቋም በመያዝ ድርድሮቹ እንዲጓተቱ በማድረግ ግድቡን በማጠናቀቅ አማራጭ የሌለው ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጋለች" ያለው የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ኢትዮጵያ ግድቡን "ለልማት ፍላጎት ሳይሆን ለፖለቲካ አጀንዳ" እየተጠቀመችበት ነው ሲል ከስሷል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ አስተዳደር ላይ በተናጠል የበላይነት ለመያዝ የምታደርገውን ጥረት ግብፅ እንዳላየ እንደማታልፈው አስጠንቅቋል።
"በዓለም አቀፍ ሕግ እና በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር እንደተመለከተው የሕዝቧን የኅልውና ጥቅም ለማስጠበቅ ግብፅ ሁሉንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ ያላትን መብት ትጠቀማለች" ማለቷን መግሥታዊው አል አህራም ጠቅሷል።
ግብፅ የሕዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ የአሁኑን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት፣ ለአፍሪካ ኅብረት እና ለአረብ ሊግ በማቅረብ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ሞክራለች። በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያ ግንባታውን አጠናቃ አሁን ለምረቃ አብቅታዋለች።
በዓለማችን በርዝመቱ የሚታወቀው የአባይ ወንዝ ከ85 በመቶ በላይ ውሃውን የሚያገኘው ከኢትዮጵያ ነው።
የወንዙን አብዛኛውን ውሃ የምትጠቀመው ግብፅ ስትሆን በኢትዮጵያ የተገነባው ግድብ በበላይነት ስትጠቀምበት የነበረውን የውሃ መጠን ያሳጣኛል የሚል ስጋት ፈጥሮባታል።
ግብፅ በአውሮፓውያኑ 1959 የተፈረመው እና የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት በመጥቀስ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት የምትለው ኢትዮጵያ ይህ ሁኔታ መለወጥ እንዳላበት ስትከራከር ቆይታለች።
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላት ድርሻዋን ባረጋገጠ መልኩ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ስምምነት እንዲደረስ እና ግንባታው የግብፅን የውሃ ደኅንነት ላይ አደጋ እንደማይጥል በተደጋጋሚ ገልጻለች።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
197ኛው የማንቸስተር ደርቢ ኢትሃድ ላይ በሲቲ እና በዩናይትድ መካከል ይከናወናል።
"ይህንን ጨዋታ ለመገመት በጣም ከባድ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ" ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን።
"ማንቸስተር ዩናይትድ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በፊት በርንሌይን ማሸነፉ ሊያነሳሳው ቢችልም ግን ማንቸስተር ሲቲ ከብራይተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ ስመለከት ጥርጣሬ ገብቶኛል" ይላል።
ሱተን ይህንን ጨምሮ የሳምንቱን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።
አንጅ ፖስትኮግሉ በመጀመሪያው የፎረስት ጨዋታቸው ብዙ ነገር ይለውጣሉ ብዬ አልጠብቅም።
በማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን ቢመርጡም ከጎላቸው ርቀው የሚከላከሉበትን መንገድ በመጀመሪያው ጨዋታቸው የሚከውኑት አይመስለም።
አርሰናል ቡካዮ ሳካን፣ ዊሊያን ሳሊባን እና ካይ ሃቨርትዝን በጉዳት ቢያጣም እነሱን የሚተኩ ተጫዋቾች አሉት።
መድፈኞቹ ሊከብዳቸው ቢችልም ጨዋታውነ በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ።
ሁለቱም ቡድኖች ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በፊት ማሸነፍ ችለዋል።
ቦርንመዝ ቶተንሃምን ሲያሸነፍ ብራይተን ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን መርታት ችሏል።
ባለፈው ዓመት ብራይተን በሜዳውም ከሜዳው ውጭም 2 ለ 1 አሸንፏል።
በዚህ ጨዋታ ቦርንመዝ ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘግባል ብዬ አላስብም።
ማርክ ጉየ ወደ ሊቨርፑል አለመዘዋወሩ ለፓላስ ጥሩ የሚባል ዜና ነው።
ተጫዋቹም የዝውውሩን ወቅት በመልካም መንገድ አሳልፏል።
የፓላሶቹ አዳም ዋርተን እና ኢስማኢላ ሳር በጉዳት ባይሰለፉም አሰልጣኝ ኦሊቨር ሳር ቡድናቸውን በደንብ ማዋቀር ይችሉበታል።
ሰንደርላንድ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል።
ወደ ድንቅ አቋሙ በመመለስ ላይ የሚገኘው ጃክ ግሪሊሽ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።
ግሪሊሽ እና ኢሊማን ንዳዬ ኤቨርተን ድንቅ የማጥቃት አንቅስቃሴ እንዲያደርግ እያገዙ ላይ ይገኛሉ።
ከአቋም አንጻር ኤቨርተን ጨዋታውን ያሸንፋል ማለት ቢቻልም ቪላ መሸነፉን አይቀጥልም።
ቪላ በጥሩ አቋም ላይ አይገኘም። አዳዲስ ተጫዋቾችንም ባለቀ ሰዓት አስፈርሟል። ቡድኑ ወደ ጥሩ አቋሙ መመለሱ አይቀርም።
የሁለቱን ቡድኖች ተጫዋቾች እርስ በእርስ ማወዳደር አስፈላጊ ነው።
ፉልማ ከቼልሲ ባደረገው ጨዋታ በተሰጡት ውሳኔዎች ዕድለኛ አልነበረም።
ሊድስ የተቀናቃኙን ያህል ጥልቀት ያለው ቡድን የለውም።
ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ጨዋታ ቢሆንም  ውጤቱ የተለየ አይሆንም።
ኒውካስል ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቶ በሊቨርፑል ተሸንፏል።
አሌክሳንድር ኢሳቅን በመሸኘት አዲስ የፈረሙት ኒክ ዎልሜድ እና ዮዋን ዊሳ ከቡድኑ ጋር የሚፈጥሩት ቅንጅት ይጠበቃል።
በየርገን ስትራንድ የሚመራው የዎልቭስ አጥቂ መስመር ጠንካራ መሆኑን አሳይቷል።
ዌስት ሃም ወደ ኖቲንግሃም አቅንቶ 3 ለምንም ያሸንፋል ብዬ አልገመትኩም ነበር።
ቡድኑ በዚሁ መቀጠል ቢኖርበተም የሚያሳካው አይመስለኝም።
ቶተንሃም በሜዳው በበርንመዝ ከተሸነፈ በኋላ ጥንካሬውን ማስመስከር ይኖርበታል።
የቶማስ ፍራንክ ቡድን ሚዛኑን የጠበቀ ሲሆን ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ብሬንትፎርድ በሰንደርላንድ መሸነፉ ለቡድኑም የሚዋጥ አይመስልም።
ቼልሲ ካለው አጀማመር እና ከቡድኑ አንጻር በቀላሉ ሊያሸንፍ ይችላል ቢባልም ብሬንትፎርድ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል።
ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ኢሳቅ በዚህ ጨዋታ በቋሚነት የሚሰለፍ አይመስለኝም።
ሊቨርፑል ለማሸነፍ የተጫዋቹን መሰለፍ የሚጠብቅበት ጨዋታም አይሆንም።
በርንሌይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እንዳደረገው ተጋጣሚውን እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ይሞክራል።
የአርን ስሎት ቡድን ወደ ጥሩ አቋሙ መድረስ ባይችልም ሦስቱንም ጨዋታዎቹን ማሸነፍ ችሏል።
ይህ ደግሞ ለቡድኑ ጥሩ ስሜትን የሚፈጠር ሲሆን ለተጋጣሚዎች ደግሞ አስጊ ይሆናል።
ብሪያን ምቡሞ በመልሶ ማጥቃት ሲቲን ሊቀጣ የሚችል ሲሆን የሲቲው ግብ ጠባቂ ጀምስ ትራፎርድ አስተማማኝ አይደለም።
ዩናይትድ ጎል ማስቆጠር ቢችልም ሲቲ በሜዳው በርካታ ዕድሎችን ይፈጥራል።
ሲቲ ከመጀመሪያዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን ተሸንፏል። በሻምፒዮንስ ሊግ በቀጣይ ሳምንት አጋማሽ ናፖሊን ቀጥሎ ደግሞ አርሰናልን ይገጥማል።
አዲስ ፈራሚው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ በቋሚነት ከተሰለፈ ቡድኑ ይሻሻላል።
ዩናይትድ ያስፈረመው ግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ ያለው አቋም እና በሊጉ የሚኖረው ተጽዕኖ ተጠባቂ ነው።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የፎቶው ባለመብት, CLEMENT AASMANN STORKSEN
ከኢትዮጵያ ወደ ኖርዌይ ከሄደ አስር ዓመት ሆኖታል። ኢትዮጵያ ሳለ በጅማ ዩኒቨርስቲ ለ11 ዓመታት የቋንቋ እና ሥነ ልሳን መምህር ነበር።
የሦስተኛ ዲግሪውን ለመሥራት ነበር ወደ ኖርዌይ ያመራው። በእርግጥ በኢትዮጵያ ሳለ ለፖለቲካ ባዕድ አልነበረም።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል በመሆን በፓርቲው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፏል።
ወደ ኖርዌይ ለትምህርት ሲሄድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተቃዋሞ እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ነበር።
የቀድሞው የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር አማኑዔል ራጋ ወደ አገሩ መመለስ ስጋት ሲፈጥርበት በኖርዌይ ኑሮውን አደረገ።
በኖርዌይ ዜግነት አግኝቶ መኖር ከጀመረ ወዲህ ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ መሳተፍ እንዳለበት ወሰነ።
ከዚያም በኋላ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ አባል ሆኖ መሳተፍ ጀመረ።
ከሁለት ዓመት በፊት ፓርቲውን ወክሎ ለኦስሎ ከተማ ምክር ቤት ተወዳድሮ ነበር።
ያ ተሳትፎ በፈጠረለት ዕድል የኦስሎ አንድ ክፍለ ከተማ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ።
በዚያውም በአካባቢው የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ አስተዳደር አባል መሆን ቻለ።
ኖርዌይ ወደ አገራዊ ምርጫ ስታመራ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ፓርቲው እንዲሁም ግለሰቦችም ፓርቲውን ወክሎ እንዲወዳደር መረጡት።
አሁን ደግሞ በአገራዊ ምርጫ ላይ ፓርቲውን ወክሎ እየተሳተፈ ነው።
የኖርዌይ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ እጅጉን የተለየ ነው የሚለው አማኑዔል በአገር ቤት የነበረው የፖለቲካ ተሳትፎ ምንም እንዳልረዳው ይናገራል።
"ዲሞክራሲ እና አካታች የሆነ መንፈስ መፍጠርን፣ ተቃዋሚ ቢመጣ እንደ ጠላት ማየት ሳይሆን የራሱ ዕይታ ያለው የአገሪቱ ዜጋ መሆኑን መቀበልን የተማርኩት እዚህ ነው" ሲል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል።
በአገሪቱ ውስጥ በርካታ ዕድሎች አሉ የሚለው አማኑዔል "ቁጭ ብሎ ከመመልከት ይልቅ በመሳተፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ በማድረግ የምፈልገውን ለመለወጥ ለማምጣት መጣር እንዳለብኝ ወሰንኩ" ይላል።
አማኑዔል በኖርዌይ ፖለቲካ ውስጥ ሰፊ አንቅስቃሴ የሚያደርጉ ፓርቲዎች ቢኖሩም የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲን የመረጠበት ምክንያት በቤተሰብ ዕሴቶች፣ በሰው ልጆች መብት እና በሰብዓዊነት ላይ አተኩሮ ስለሚሠራ መሆኑን ይናገራል።
አማኑዔል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የእንግሊዝኛ እና የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ውስጥ ተምሮ በዚያው ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪውን ይዟል።
በ1993 ዓ.ም. በዩኒቨርስቲው ተማሪ በነበረበት ወቅት በወቅቱ አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት "በመንግሥት ላይ አምጻችኋል በሚል ለአንድ ዓመት አባረረን" ይላል።
ያኔ ታድያ አማኑዔል ወደ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ በማምራት ኮምፒውተር እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተማረ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነበረው ቆይታም ለሁለት ዓመት ያህል ጣልያንኛ ተምሯል። በእርግጥ በወቅቱ ቋንቋውን ከቤተብ ጋር በተገናኘ በጣልያንኛ የነበሩ ሰነዶችን አንብቦ ለመረዳት በሚል የተማረው መሆኑን ያስታውሳል።
ስለዚህ ከአማርኛ፣ ከኦሮምኛ እና ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ ጣልያንኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ትንሽ ትንሽ አረብኛ ይናገራል።
ኖርዌይ ሄዶም መኖር ሲጀምር "ምንም እንኳን እንደ ልጆች ባይሆንም" ቋንቋውን ለመደበኛ ሥራ ማስኬጃ ያህል መልመድ እንዳልከበደው ይናገራል።
"እንደ ሥነ ልሳን ሰው ከበደኝ ማለት ይከብዳል። በዕድሜ ገፍቶ መጀመር እና ልጅ ሆኖ ቋንቋ መልመድ ልዩነት አለው። ነገር ግን ለሥራ መግባቢያ የሚሆን መልመድ ለማንኛውም ሰው አይከብድም።"
ደግሞም ይላል አማኑዔል የአገሩ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ትንሽ ለየት ስለሚል አያስቸግርም።
ከዚያ በኋላ ቋንቋውን ለሥራ መግባቢያነት ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በጉልህ ለመሳተፍ በሚያስችለው ልክ ለመደ።
በኖርዌይ ውስጥ "የራስህ ዕጣ ፈንታ በራስህ እጅ ነው። በሠራኸው ልክ ነው የምታገኘው" የሚለው አማኑዔል፤ አገሪቱ በመግባባት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ስለምታራምድ በንቃት ለመሳተፍ ተግዳሮት አላጋጠመውም።
በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ "ርዕዮተ ዓለም ነው የሚያስፈልገው" በማለት የእርሱ የቆዳ ቀለም፣ ወይንም በስደት ወደ አገሪቱ መግባቱ ተጽዕኖ አለማድረጉን ያስረዳል።
"ለሰው ልጅ እሴት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች የሚገኙት በዚህ ፓርቲ ነው" የሚለው አማኑዔል፤ በፓርቲው ውስጥ በመሳተፍ ለአገሬ ኖርዌይ ማበርከት የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ ይላል።
"ኖርዌይ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሁሉ ነገር የተስተካከለ ይመስላል። እርግጥ ከሌሎች አንጻር ጥሩ ደረጃ ላይ ብትገኝም ውስጣዊ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከወንጀል ከቤተሰብ ጋር ያሉ ነገሮች መስተካከል አለባቸው። ተወዳድሬ የማሸንፍ ከሆነ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚፈቅድልኝ መሠረት እሠራለሁ።"
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የኖርዌይ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ፈጽሞ መለየቱን አማኑዔል አስተውሏል። ከገዢው ፓርቲ የተለየ ሃሳብ ስላለ መሸማቀቅ፣ እታሰራለሁ፣ እሳደዳለሁ ብሎ መስጋት የለም።
የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል የተለየ ዕይታ እንዳለው አንድ ዜጋ ነው የሚታየው ይላል።
አማኑዔል በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ አብላጫ ድምጽ ያገኙትም ሆነ አነስተኛ ድምጽ ያገኙት እኩል በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ድርሻ እንዳላቸው ይመሰክራል።
የኖርዌይ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቀኝ ዘመም (Center right) መሆኑን የሚናገረው አማኑዔል ከዚህ በፊት አብላጫ ድምጽ በማግኘት ለስምንት ዓመታት አገሪቱን ማስተዳደሩን ይናገራል።
ያኔ በተለይ በስደተኞች ላይ መልካም ሥራዎችን እንደሠራ ይነገራል።
ይህ ደግሞ የአማኑዔልን ትኩረት ስቦታል። በክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ዘር፣ ሃይማኖት ቦታ የላቸውም የሚለው አማኑዔል "ከየት መጣህ ሳይሆን ምን ሃሳብ አለህ" የሚለው ቅድሚያ ያገኛል።
በእርሱ የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥም በመጀመሪያው ምርጫ ብዙ ሰዎች እንዳገዙት ይናገራል።
"በተለይ ስደተኛ ሆነህ ስትመጣ መቼ ተረጋጋቼ ገንዘብ እሠራለሁ? እንጂ ፖለቲካውን ተቀላቅዬ የሚል ሃሳብ ስላልነበር የእኔን በፖለቲካ የመሳተፍ ፍላጎት ሲያዩ ለልጆቻቸው ጥሩ ምሳሌ ይሆናል በሚል አግዘውኛል።"
በተለይ ለከተማው ምክር ቤት ሲወዳደር እንደ አገሪቱ ልምድ የተለያየ የፖለቲካ ፓርቲ ቢደግፉም እንደ ግለሰብ ግን እርሱን የሚደግፉ በርካታ እንደነበሩ እና ይህም ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገለት ያስረዳል።
በኖርዌይ የትኛውም የፖለቲካ አመለካከት አይጣልም የሚለው አማኑዔል አገሪቱ የምትመራው "መግባባት ላይ በተመሠረተ ፖለቲካ" መሆኗን ይናገራል።
በኖርዌይ ሕገ መንግሥት መሠረት የመራጮችን አብላጫ ማለትም 85 በመቶ ድምጽ ያገኘ አገሪቱን ብቻውን ያስተዳድራል።
ሌሎች ደግሞ ባይመረጡም እንደ የተሳትፏቸው በኮታ የፓርላማ መቀመጫ በማግኘት መንግሥትን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ ይሠራሉ።
አለበለዚያ ግን ፓርቲዎች እንዳገኙት ድምጽ ጥምር መንግሥት በመመሥረት ያስተዳድራሉ።
አማኑዔል በዚህ ምርጫ አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ቢያሸንፍ በጤና፣ በቤተሰብ፣ በወንጀል መቀነስ ላይ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚፈቅድለት ልክ ለመሥራት አቅዷል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ከሳምንት በፊት እስራኤል በሌሊት ጥቃት በመፈጸም የጀመረችው ግጭት በቀላሉ የሚቋጭ አይመስልም። ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የሁለቱ አገራት አገር አቋራጭ መጠቃቃት ጋብ ሳይል ቀጥሏል።
እስራኤል ከመጀመሪያው የኒውክሌር ማዕከላትን እና ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ በማድረግ ጥቃት እንደምትፈጽም ስትገልጽ፣ ኢራንም በረጅም ርቀት ሚሳዔሎች እና ድሮኖች በእስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት እኣካሄድች ነው።
እስራኤል ከመሬት በታች የሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን ለማውደም የአሜሪካንን ድጋፍ ስትጠይቅ ቆይታ እሁድ ማለዳ ላይ አሜሪካ ኢራን ውስጥ ጥቃት በመፈጸም ከእስራኤል ጎን መቆሟን በይፋ አሳውቃለች።
አሁን ቀጥሎ የሚከሰተው ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከባሕረ ሰላጤው ባሻገር ከፍተኛ ተጽእኖ የሚኖረው ቀውስ ምን ሊያስከትል ይችላል? የሚለውን ለማወቅ ዓለም በስጋት ጉዳዩን እየተከታተለ ነው።
ይህ እየተጠናከረ እና መልኩን እየቀየረ የመጣው የእስራኤል-ኢራን ግጭት ሰኔ 6/2017 ዓ.ም. ሲጀምር የእስራኤል የስለላ ተቋም ሞሳድ ሚናው ምን ነበር? ከጥቃቱ በፊትስ ኢራን ውስጥ ምን ሲያደርግ ነበር?
የኢራን ሕዝብ 90 ሚሊዮን ነው። የእስራኤል ሕዝብ 10 ሚሊዮን አይሞላም። በቆዳ ስፋትም እንዲሁ ናቸው። በወታደራዊ አቅም ምናልባት ተመጣጣኝ ሊባሉ ይችላሉ።
ያልተመጣጠኑት በስለላ ነው። ሞሳድ ልቆ ተገኝቷል። ዱካ የለውም፤ ጥላ ነው። ከኢራን ሳይንቲስቶች ጋር አብሮ ይራመዳል። ግን አይጨበጥም።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ከኢራን ጄነራሎች ጋር አብሮ ይታደማል፤ ግን አይተኮስበትም። ለኢራኖች መንፈስ ሆኖባቸዋል። አንዳንድ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሌላቸው መረጃ ሞሳድ ሊኖረው ይችላል።
ሞሳዶች የጦርነቱ መባቻ ላይ ወይም የግጭቱ ዋዜማ አይደለም የገቡት። ኢራን ነው የከረሙት። 'ሰርገው ገቡ' የሚለው አገላለጽም ልክ የሚኾነው በከፊል ነው።
ምክንያቱም ሞሳድ ዜግነት አለው እንዴ? የአገሬው ሰው መልምሎ ነው የራሱ የሚያደርገው። ምናልባት የአንድ አገር ምክትል መከላከያ ሚኒስትር የሞሳድ መኮንን ሊኾን ይችላል።
ምናልባት የኢራን ከፍተኛ የደኅንነት ኃላፊ የሞሳድ ተከፋይ ሊሆን ይችላል። ምሥጢሩ የሚወጣው ከዓመታት በኋላ ነው። ተቀብሮ ሊቀርም ይችላል።
የሞሳድ ሰላዮች ኢራን በስቅላት ቀጥታ የምትጨርሳቸው አይደሉም። ረቂቅ ናቸው።
በቴህራን ታላቅ ሳይንቲስት በጠራራ ፀሐይ መኪና መንገድ ላይ ተገድሎ ሊገኝ ይችላል። ገድሎ የሚሸሽ የሞሳድ ሰላይ ግን አይታይም።
ድምጽም፣ ጠረንም፣ ዱካም የለም። ይህን ምን ይሉታል?
የሐማሱ የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሐኒያ ለእርሱ በተዘጋጀለት ዘወትር በሚያርፍበት፣ ጥበቃው በተጠናከረበት እንግዳ ማረፊያው ውስጥ ሳለ ነበር ቴህራን ውስጥ የተገደለው።
እሱን ጨምሮ ጎምቱ የኢራን ሳይንቲስቶች ከዚህ ቀደም በተጠና መንገድ በሞሳድ ተገድለዋል።
የሞሳድ መናኸሪያ ከቴል አቪቭ ይልቅ ቴህራን ነው።
ኢራን የሞሳድን ዋና መሥሪያ ቤት በቴል አቪቭ ከምትደበድብ ራሷን ብትደበድብ-ጉያዋን ብታጸዳ ይሻል ነበር የተባለው ለዚያ ይሆን?
ለመሆኑ ሞሳዶች በዚህ ግጭት የመጀመሪያ ቀናት ምን አሳኩ?
በአጭር ቀናት አስገራሚ ሥራ ሠርተዋል፤ ጥበባቸው ሲታይ ደራሲ ማሞ ውድነህ አላጋነኑም ያስብላል።
በሁለት ቀን ደርዘን የኒውክሌር ሳንቲስት እና ሌላ ሁለት ደርዘን ጄኔራል መግደል የትኛውም አገር የሚያሳካው ነገር አይደለም። በዓለም ጦርነቶች እንኳ ተሰምቶ አያውቅም።
የሞሳድ የስለላ መኮንኖች ሁለት ቁልፍ ተልዕኮ ነበር የተሰጣቸው።
የኒውክሌር እና ሚሳኤል ቀጠናዎችን መሰለል አንዱ ነው። የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ እና የኒውክሌር ሳንቲስቶችን ማምከን ሌላው ተልዕኮ ነው።
ኔታንያሁ እንዳመኑት የኢራንን የኒውክሌር እና የሚሳኤል ፕሮግራሞችን አፈር ለማድረግ የወራት ዝግጀት ተደርጓል። ሰፊ ልምምድ ሲደረጉ ነበር።
በተለይም በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ዝግጅቱ ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድጎ ነበር። የሚጠበቀው ዶናልድ ትራምፕ እስኪፈቅዱት ብቻ ነበር።
ትራምፕ ኢራንን በ60 ቀናት ስምምነት ካልደረሳችሁ 'ውርድ ከራሴ' ሲሉ ቆይተዋል። 61ኛው ቀን ኔታንያሁ የልባቸው ሳይደርስ አልቀረም።
የቋመጡለትን ነገር ለማሳካት ከፍተኛ ጉጉት ነበራቸው። ኢራን ምናልባት ስምምነት ላይ ከደረሰች ትራምፕን ማሳመን ፈተና ይሆንባቸው ነበር።
ኢራን በዚህ ጊዜ 6ኛውን ዙር ድርድር ለማድረግ ዝግጅት ላይ ነበረች።
የኢራን አመራር በፍጹም በኦማን የሚደረገው ድርድር ሳይለይለት ኔታንያሁ ይደፍሩናል አላለም። ከፍተኛ መዘናጋት ነበር፤ ከአያቶላህ ጀምሮ፤ አማካሪዎቻቸውን ጨምሮ።
ትንሽ ድንጋጤ የገባቸው አሜሪካ ከባህሬን እና ከኩዌት የዲፕሎማት ቤተሰቦቻችን ማስወጣት ስትጀምር ነው።
አሜሪካ እና እስራኤል በነገታው ኢራን ላይ ስለሚደርሰው መብረቃዊ ጥቃት ሁሉን ጨርሰው ነበር።
የእስራኤል ፓይለች እና ሰላዮች በጥንቃቄ ያደረጉት ዝግጅት እና ለወራት የዘለቀው ልምምድ ፍሬ አፈራ። ኢራን ምንም ምልክት ማየት ያልቻለችውም ለዚሁ ነው።
በመጨረሻው ሰዓት ታዲያ የኢራን ከፍተኛ ጄነራሎች እሰራኤል ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች የሚለው ነገር አሳስቧቸው ስብሰባ ጠሩ።
የኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የአየር ኃይል ጄነራሎች ናቸው።
ሁልጊዜም እንደሚያደርጉት 'የእስራኤል ነገር አይታወቅም' ብለው ከመሬት ሥር በተዘጋጀ የምድር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ገቡ።
ሞሳድ ግን ይህን ያውቅ ነበር። ቁልፍ ስብሰባዎች እዚህ ምድር ቤት እንደሚደረጉ መረጃ ነበረው።
ሁሉም ኮማንደሮች በአንድ ጊዜ ተገደሉ። የአየር እና የድሮን ስምሪት ዋና አዛዥ ይገኙበታል።
አንድ የኢራን ከፍተኛ መኮንን ለቢቢሲ ሲናገሩ "ሁሉም በአንዴ መገደላቸው ኢራን ፈጥኖ ምላሽ ለመስጠት አልቻለችም፤ ትዕዛዝ ማን ይስጥ? የዕዝ ሰንሰለቱ ከላይ ተቀነጠሰ'' ብለዋል።
እነዚህ ጄነራሎች በአንድ የምድር ቤት ቢሮ ለስብሰባ በተቀመጡበት መገደላቸው ነው ልዩ የሚያደርገው። ሌሎች ኮማንደሮች ደግሞ በቤታቸው ተገድለዋል።
ከቤተሰባቸው ጋር አገር ሰላም ብለው በተኙበት ተገድለዋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ፣ የኢራን የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አዛዥ እንዲሁም የእነዚህ ማዘዣ ዋና መሥሪያ ቤቶች ሁሉ በተቀናጀ ሁኔታ ከጥቅም ውጪ ተደርገዋል።
ከዚህ በኋላ ዋናው ተልዕኮ የኢራንን የአየር መቃወሚያ እና ራዳር ማምከን ነበር።
የእስራኤል ስለላ መሥሪያ ቤት እነዚህ መቃወሚያዎች የት እንደሚገኙ አጥንቶ ጨርሷል። ይህ መረጃ ለእስራኤል አየር ኃይል ተላልፎ ተሰጠ። ገና ከመነሻው እንዳልነበረ አደረጉት።
በዚህ የተነሳ ነበር የእስራኤል መከላከያ በኢራን ሰማይ ላይ እንዳሻው መምነሽነሽ የቻለው።
የእሰራኤል አየር ኃይል ይህን ዘመቻ በሚፈጽምበት ቅጽበት የእሰራኤል ሰላዮች በሌላ ተግባር ተጠምደው ቆዩ። ይህም የቦሊስቲክ ሚሳዔል ማስተኮሻዎችን በጥንቃቄ ከጥቅም ውጪ ማድረግ ነበር።
ይህን ለማሳካት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሞሳድ መኮንኖች ግማሾቹ በኢራን ቀሪዎቹ በቴል አቪቭ ቢሮ፣ የተቀናጀ ተሳትፎ አድርገዋል። በዚህ ተግባር ላይ በተለይ ለሞሳድ የሚሠሩ ኢራናዊያንን ብቻ የያዘች አንዲት የስለላ ቡድን ተሳትፋለች።
በማዕከላዊ ኢራን አንዲት የሞሳድ ኮማንዶ ጓድ ራሷን አሰናዳች። በዚህች ጓድ ሥር የሚገኙ የሞሳድ ኮማንዶዎች ኢራን ውስጥ በራሳቸው የሚመሩ የጦር መሳሪያዎችን ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፉ የኢራን ሚሳዔሎች በተጠመዱባቸው ማስተኮሻዎች አቅራቢያ ተክለው ነበር።
ሞሳድ ከዚህ ሌላ ወደ ኢራን አስርጎ ያስገባቸው እና የርቀት መቆጣጠሪያ የተበጀላቸው ድሮኖችን ጠምዶ ሲጠባበቅ ነበር። ድሮኖቹ የገቡት ከዚህ ጦርነት በጣም ቀደም ብሎ ነው።
ጊዜውን በትክክል ለመናገር ከጉዳዩ ስሱነት የተነሳ የእሰራኤል የመረጃ ምንጮች ፍቃደኛ አይደሉም።
እነዚህን ድሮኖች ያጠመደበት መለስተኛ የዕዝ ጣቢያም ከፍቶ ነበር። አሜሪካ ሠራሽ ጄቶች ከዚህ ማዘዣ እየታገዙ በቀላሉ ዒላማቸውን መምታት ቻሉ።
ከሰማይ ተመትተን እንጣላለን የሚል ስጋት ሽው ሳይልባቸው ማለት ነው።
የኢራን አብዛኞቹ የአየር መቃወሚያዎች የተመቱት በጥቅምቱ ጥቃት ጊዜ ነው። በረዥም ርቀት ተመዘግዛጊ ሚሳዔሎች። የኢራን ኤስ 300 ሚሳዔል ሥርዓት ከጥቅም ውጪ የተደረገው ያኔ ነው።
በቅርብ ቀናት የእስራኤል አየር ኃይል ትኩረት ያደረገው ከመሬት በሚተከሉ ራዳር እና ማስተኮሻ (ላውንቸርስ) ላይ ነው።
ጥቃቱ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ እስራኤል ይህን ሥርዓት ሽባ የሚያደርጉ የስለላ መኮንኖች አሰናድታ ነበር።
የሞሳድ መኮንኖች የተቀረውን የኢራን የሚሳኤል ሥርዓት ለማፍረክረክ ቀደም ብለው አስርገው ያስገቧቸው ድሮኖችን በጥቅም ላይ አውለዋል።
እስራኤል ጥቃት ስትጀምር፣ ድሮኖቹ ሥራቸውን እንዲጀምሩ እና ቴህራን አቅራቢያ ኢስፋጃባድ ወታደራዊ ጦር ሠፈር ወደሚገኙት ከምድር ወደ ምድር የሚወነጨፉ ሚሳዔሎች ወደተጠመዱባቸው ማስተኮሻዎች መወርወር ጀመሩ።
በዚህ ጥቃትም፣ ድሮኖቹ የኢራን ባልስቲክ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ከመተኮሳቸው በፊት ሊያወድሟቸው ችለዋል። የእስራኤል መከላከያ ዝግጅት ያደረገው የከፋ ነገር ከኢራን ይገጥመኛል ብሎ ነው።
ምናልባት ኢራን ከ300 እስከ 500 ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ልትተኩስ ትችላለች በሚል ነው ስሌቱ የተሠራው። ይህን አድርጋ ቢሆን ኢራን እስራኤል ላይ ተሰምቶ የማይታወቅ ጉዳት ታደርስ ነበር።
ኢራን በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት አቅም አጣች። በብዙ ጥረት እና መደናበር ያውም ከሰዓታት በኋላ መቶ ድሮኖችን ወደ እስራኤል ተኮሰች። በቀላሉ ተመከቱ።
ከመጀመሪያው ጥቃት በኋላም የእስራኤል ጦር የኢራን ባለስቲክ ሚሳዔሎችን መደብደቡን ቀጠለበት። ይህም ኢራን አገግማ ጥቃት እንዳትሰነዝር አቅሟን ለማሽመድመድ ነበር።
"በርካታ ማስተኮሻዎች፣ ከምድር ወደ ምድር ተመዘግዛጊ ሚሳዔል ማከማቻዎች.፣ ተጨማሪ የወታደራዊ ቁሳቁሶች አውድመናል፤ በምዕራብ ኢራን አንድ የተለየ ማስተኮሻ በኮንቴይነር ውስጥ ተደብቆ አግኝተን አውድመነዋል" ብሏል የእስራኤል መከላከያ በሰጠው መግለጫ።
የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ 'እስራኤል ዋጋዋን ታገኛለች' ብለው ለበቀል ዝተዋል።
ኢራን በእስራኤል ጥቃት ከተከፈተባት ዕለት አንስቶ በእስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ አሜሪካ በጥቃቱ ውስጥ መሳተፏ አገሪቱ መረር ወዳለ እርምጃ እንድትገባ ሊገፋት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
እንደ መርፌ ጫፍ የሾሉ፣ 11 ሜትር ዝርመት ያላቸው፣ 15 ቶን የሚመዝኑ እና እያንዳንዳቸው "ዲኤፍ-17" የሚል ጽሑፍ የሰፈረባቸው የቻይና ሕዝብ ነጻነት ሠራዊት ሚሳኤሎች በቤይጂንግ በተካሄደ ወታደራዊ ሰልፍ ላይ በመኪና ተጭነው ሲጓዙ ታየ።
ቻይና የዶንግፌንግ የተባሉትን ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎቿን ለዓለም ይፋ ያደረገችው በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2019 ባካሄደችው በዚህ ብሔራዊ ሰልፍ ላይ ነበር።
አሜሪካ እነዚህ መሳሪያዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ቀድሞውንም ታውቅ የነበረ ቢሆንም፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ቻይና መሳሪያዎቹን ይበልጥ በማሻሻል ወደፊት እየገሰገሰች ነው።
ከድምፅ ፍጥነት ከአምስት እጥፍ በላይ በሆነ ፍጥነት የመጓዝ እና ከተወነጨፉ በኋላ አቅጣጫቸውን የማስተካከል አቅም ያላቸው እነዚህ ሚሳዔሎች፤ እጅግ በጣም ኃይለኛ የጦር መሣሪያ ናቸው። ጦርነቶችን የሚካሄዱበትን መንገድም ለመለወጥ አቅም አላቸው።
ሚሳዔሎቹን ለመታጠቅ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ውድድር እየጨመረ የመጣውም ከዚህ የተነሳ ነው።
'ካውንስል ኦን ጂኦስትራቴጂክ' በተባለው ቲንክ ታንክ የብሔራዊ ደኅንነት ተመራማሪ የሆኑት ዊልያም ፍሪር፤ "ይህ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ያልነበረ እና በመንግሥት ተዋናዮች መካከል እየታየ ያለው የጂኦፖሊቲካዊ ፉክክር አንድ አካል ብቻ ነው" ይላሉ።
የፎቶው ባለመብት, AFP via Getty Images
በቤይጂንግ የተካሄደው ሥነ ሥርዓት ቻይና በሃይፐርሶኒክ ቴክኖሎጂ እያስመዘገበችው ያለው ዕድገት የሚያስከትለው ስጋት እየጨመረ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬን አስነስቷል።
ዛሬ ቻይና በሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች መስክ ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች። ሩሲያም ትከተላለች። አሜሪካ ግን እዚህ ላይ ለመድረስ እየጣረች ነው። ዩናይትድ ኪንግደም ደግሞ ገና ምንም የላትም።
ተመራማሪው ፍሪር፤ ቻይና እና ሩሲያ ቀድመው የተገኙበት ምክንያት ቀላል መሆኑን ይናገራሉ። ምክንያቱ "ከጥቂት ዓመታት በፊት በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ለማድረግ መወሰናቸው ነው" ሲሉ ያስረዳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ብዙ ምዕራባውያን ሀገራት በዚህ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹን ሁለት አስርት ዓመታት ያሳለፉት ከጂሃዲስት ሀሳብ የመነጨ የሀገር ውስጥ ሽብርተኝነትን ሲዋጉ እንዲሁም በውጭ አገር በፀረ አማጺያን ጦርነቶች ላይ ሲያተኩሩ ነው።
የፎቶው ባለመብት, KCNA/EPA-EFE/REX/Shutterstock
ከቻይና እና ከሩሲያ በተጨማሪ ሌሎች ሀገራትም ወደፊት እየገሰገሱ ነው። እስራኤል 'አሮው 3' የተባለ የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል አላት።
የሃይፐርሶኒክ የጦር መሳሪያ እንደታጠቀች የምትናገረው ኢራን፤ በሰኔ ወር በተካሄደው የ12ቱ ቀናት ጦርነት ወቅት በእስራኤል ላይ የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ገልጻለች።
በእርግጥም መሳሪያው በከፍተኛ ፍጥነት ይጓዝ የነበረ ቢሆንም እውነተኛ ሃይፐርሶኒክ ተብሎ ለመመደብ በሚያስችል ሁኔታ በበቁ መልኩ አቅጣጫውን የመቀየር እና የማስተካከል አቅም እንደሌለው ታስቧል።
ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ ከአውሮፓወያኑ 2021 ጀምሮ አዋጭ እና የሚሠራ ባለቸው የራሷ መንገድ መሳሪያውን እየገነባች መሆኑን  ትገልጻለች።
የፎቶው ባለመብት, Morteza Nikoubazl/NurPhoto via Getty Images
አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይን እና ጃፓንን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት በሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ቴክኖሎጂ ላይ ገንዘባቸውን እያፈሰሱ ነው።
የመከላከያ ኃይሏን አቅም በማጠናከር ላይ ያለች ምትመስለው አሜሪካ፤ "ዳርክ ኢግል" ስትል የጠራችውን ሃይፐርሶኒክ መሳሪያ ይፋ አድርጋለች።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር፤ ዳርክ ኢግል "የሀገራችን እና የጦር ሠራዊቷን ኃይል እንዲሁም ቁርጠኝነት የሚያስገነዘብ" ነው ያለ ሲሆን፣ "የጦር ሠራዊቱ እና የባሕር ኃይሉ ሃይፐርሶኒክ የጦር መሳሪያ ግንባታ ጥረቶችን መንፈስ እና ገዳይነት የሚያመለክት" እንደሆነም ተናግሯል።
በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ እየመሩ ግን ያሉት ቻይና እና ሩሲያ ናቸው። አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ግን ይህ ሁኔታ አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ።
'ሃይፐርሶኒክ' ማለት ከድምፅ ፍጥነት አምስት እጥፍ ወይም በሰዓት 6,210 ኪሎ ሜትር በሆነ ፍጥነት የሚጓዝ መሳሪያ ማለት ነው። ይህ ፍጥነታቸው ከድምጽ ፍጥነት እኩል ከሚጓዙት ሱፐር ሶኒክ መሳሪያዎች በተለየ መደብ ውስጥ ይከትታቸዋል።
ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥሩበት አንዱ ምክንያት ይህ ፍጥነታቸው ነው።
እስካሁን ድረስ በጣም ፈጣኑ ሚሳዔል የሩሲያው 'አቫንጋርድ' ነው። 'አቫንጋርድ' በሰዓት ከ33 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ እንደሚወነጨፍ የሚነገር ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ ግን የሚጠቀሰው በሰዓት 15 ሺህ ኪሎ ሜትር ይጓዛል ተብሎ ነው።
እንደ ተመራማሪው ፍሪር ገለጻ፤ የሚያደርሱትን ውድመት በተመለከተ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች ከሱፐርሶኒክ ወይም ሰብሶኒክ ክሩዝ ሚሳዔሎች ብዙም የተለየ አይደለም፥
"በጣም የተለየ የሚያደርጋቸው ለመለየት፣ ለመከታተል እና ለመጥለፍ አስቸጋሪ መሆናቸው ነው" በማለት ያስረዳሉ።
ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች በዋነኝነት ሁለት ዓይነት ናቸው። ቻይና ይፋ እንዳደረገችው 'ዲኤፍ-17' ዓይነት ሚሳዔሎች ሮኬት ላይ የሚገጠሙ ሲሆኑ፣ አንዳንዴም ከምድር ከባቢ አየር በላይ ሊወነጨፉ ይችላሉ። ከዚያም በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች በመውረድ ወደ ዒላማቸው ይምዘገዘጋሉ።
ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች፤ የተለመዱት የባሊስቲክ ሚሳዔሎች ከሚጓዙበት ተገማች አካሄድ ተቃራኒ በሆነ መልኩ ወጥ እና ተገማች ባልሆነ (ኢራቲክ) መንገድ ከተጓዙ በኋላ ወደ ዒላማቸው አቅራቢያ ሲደረሱ አቅጣጫቸውን ማስተካከል ይችላሉ።
ከዚህም በተጨማሪ በራዳር እንዳይለዩ ወደ ምድር ዝቅ ብለው የሚወነጨፉ ሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳዔሎችም አሉ።
በተመሳሳይ መልኩ ሮኬቶችን በመጠቀም በፍጥነት የሚወነጨፉት እነዚህ ሚሳዔሎች፤ ሃይፐርሶኒክ ፍጥነት ላይ ከደረሱ በኋላ የተገጠመላቸው 'ስክሪምኤት ኢንጅን' የተባለ ልዩ ሥርዓት መሥራት ይጀምራል።
ይህ ሥርዓት ከአየር ላይ የሚያገኘውን ኦክስጅን በመጠቀም ዒላማቸው ጋር እስከሚደርሱ ድረስ ረጅም ርቀት እንዲጓዙ ያስችላቸዋል።
እነዚህ ሚሳዔሎች "ሁለት ጥቅም ያላቸው መሳሪያዎች" ናቸው። ይህም ማለት በሚሳዔሎቹ ላይ የሚጫነው ኒውክሌር ወይም መደበኛው ዓይነት ፈንጂ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን እነዚህ የጦር መሳሪያዎች አደገኛ የሚያስብላቸው ፍጥነታቸው ብቻ አይደለም።
በወታደራዊ አገላለጽ አንድ ሚሳዔል "ሃይፐርሶኒክ" ተብሎ ለመመደብ በሚበርበት ወቅት አቅጣጫውን የሚቀይር መሆን አለበት።
ያስወነጨፈው አካል፤ ሚሳዔሉ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዒላማው እየበረረ ባለበት ጊዜ እንኳ በድንገት እና ባልተጠበቀ መንገድ አቅጣጫውን መለወጥ የሚችል መሆን አለበት።
ይህ አቅማቸው ለመጠለፍ አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል። አብዛኞቹ በመሬት ላይ የተተከሉ ራዳሮች የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሉ በርሮ መጨረሻ ዒላማው ጋር ሳይቀርብ በፊት ይለዩታል በሚል የሚተማመኑባቸው አይደሉም።
የዩናይትድ ኪንግደም ሮያል ባሕር ኃይል የቀድሞው አዛዥ እና እና የፀረ አየር ጦርነት ባለሙያ የሆኑት ቶም ሻርፕ፤ ሃይፐርሶኒክ መሳሪያዎች ከድምፅ ፍጥነት በአምስት እጥፍ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ፍጥነት የሚጓዙ ቢሆንም እነርሱን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎች እንዳሉ ይናገራሉ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት "ውጤታማ" እንደሆኑም ጭምር ይከራከራሉ።
የመጀመሪያው አማራጭ የሚሳዔሎቹን ዒላማ ለመከታታል እና ለመለየት ይበልጥ አስቸጋሪ ማድረግ እንደሆነ ያስረዳሉ። በዚህ ረገድ መርከቦች ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ይገልጻሉ።
"ከንግድ ሳተላይቶች የሚገኙ በደንብ ግልጽ ያልሆኑ የሳተላይት ምሥሎች እንኳ ዒላማ ለማድረግ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለማድረግ ሲባል ለገበያ የሚቀርቡት ከጥቂት ደቂቃዎች መዘግየት በኋላ መሆን አለበት" በማለት ሌላኛውን መፍትሔ ያስረዳሉ።
ዒላማን ለመወሰን በሚያስችል ደረጃ የሆኑ አሁናዊ እና ትክክለኛ የሳተላይት ምሥሎችን ማግኘት አስቸጋሪ እና ውድ እንደሆነም ይገልጻሉ።
ነገር ግን ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) እና ሌሎች እየመጡ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ከጊዜ በኋላ ይህንን ሊለውጡ እንደሚችሉ ጠቁሟል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 2022 ሁለት ሰዎች በኢስቶኒያ ወደሚገኘው ታርቱ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጽሐፍት ገብተው በሁለት የ19 ኛው ክፍለ ዘመን ደራሲዎች የተጻፉ ስምንት መጽሐፎችን ለማንበብ ጠየቁ።
እነዚህ መጽሐፍቶች የሩሲያ ገጣሚ እና ፀሐፌ ተውኔት አሌክሳንደር ፑሽኪን እና የሥመጥሩ ደራሲ ኒኮላይ ጎጎል ናቸው።
ሁለቱ ሰዎች ራሽያኛ ይናገሩ የነበረ ሲሆን ታናሽ ወንድማቸው በአሜሪካ ትምህርቱን ለመቀጠል የተለያዩ ነገሮችን እየተመለከተ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከሦስት ወራት በኋላ የቤተ መጻሕፍቱ ሠራተኞቹ ሁለቱ መጽሐፍቶች በሐሰተኛ መጽሐፍት እንደተተኩ አስተዋሉ።
የቤተ መጻሕፍት መዛግብት እነዚህ የጠፉ መጽሐፍት ለመጨረሻ ጊዜ የተወሰዱት በእነዚሁ ሰዎች በሚያዝያ ወር መሆኑን ያሳያሉ።
የቤተ መጻሕፍት ባለሙያዎቹ የቀሩትን ስድስት የሩሲያ ዘመን አይሽሬ መጽሐፍት ለማየት ሄዱ።
በተደረገው ምርመራ መረዳት የተቻለው መጽሐፍቶቹ ተመሳስለው በተዘጋጁ ሌሎች ቅጂዎች ተተክተዋል።
መጽሐፍቱ እውነተኛ እንዲመስሉ የቤተ መጻሕፍቱ ማህተም እና ቁጥሮች አርፎባቸዋል።
በዘራፊዎች ዒላማ የተደረገው የታርቱ ቤተ መጽሐፍት ብቻ አይደለም።
ከሳምንታት በኋላ በኢስቶኒያ ዋና ከተማ ከሚገኘው የታሊን ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍት አሥር የማይገኙ  መጻሕፍት ጠፍተዋል።
ከ18 ወራት በላይ፣ በርካታ የሩሲያ ዘመን አይሽሬ  እና ሌሎች በሩሲያኛ የተጻፉ ጥንታዊ ጽሑፎች ከ12 የአውሮፓ ቤተ መጻሕፍት፣ ከባልቲክስ፣ ፊንላንድ፣ ስዊዘርላንድ እና ፈረንሳይ ተሰርቀዋል።
በአንዳንድ ቦታዎች ዋና መጽሐፍቶቹ በቅጂዎች ሲተኩ  በሌሎች ቦታዎች ደግሞ መጽሐፍቱ ከቤተ መጽሐፍት በውሰት ተወስደው አልተመለሱም።
በምላሹ ዩሮፖል የአውሮፓ ኅብረት የሕግ ማስከበር ትብብር ኤጀንሲ "ዘመቻ ፑሽኪን" የተባለ ምርመራ ጀምሯል።
ይህ ከ100 በላይ ፖሊሶች በተለያዩ አገራት የሚገኙ በርካታ ንብረቶች ላይ ፍተሻ እንዲያደርጉ አስገድዷል።
በአጠቃላይ እስካሁን ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ክትትል ተደርጎባቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
እነዚህን ታሪካዊ እና ብርቅዬ መጽሐፍት በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረው የመጀመሪያው ግለሰብ የ48 ዓመቱ ቤቃ ስሬኪዜ ነው። ግለሰቡ በተመሳሳይ ጊዜ ላትቪያ እና ኢስቶኒያ ውስጥ ከታርቱ እና ታሊን ቤተመፃሕፍት ስርቆት ጋር በተያያዘ  በሦስት ወንጀሎች ክስ ተመስርቶበት ተፈርዶበታል።
ስሬኪዜ በአሁኑ ጊዜ ኢስቶኒያ ውስጥ የተፈረደበትን የሦስት ዓመት ከሦስት ወር እስራት እየተቀበለ ይገኛል።
ስሬኪዜ ማረሚያ ቤት ሆኖ  ለቢቢሲ እንደተናገረው በ2008 ቤተሰቡን ለመመገብ ጥንታዊ መጽሐፍትን በመሰብሰብ እና በመሸጥ ለመሳተፍ ወሰነ።
መጻሕፍቱን በመሰብሰብ ረገድ ስላለው መደበኛ ትምህርት ሲጠየቅ ሁሉንም በተግባር መማሩን ይናገራል።
"እኔ መጽሐፍ እንዳለው አስማተኛ ነኝ። በእጄ የገባ መጽሐፍ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እና በጨረታ ላይ ምን ያህል እንደሚያወጣ ወዲያውኑ መናገር እችላለሁ" ብሏል።
ስሬኪዜ ከሕግ ጋር መጀመሪያ የተላተመው እአአ በ 2016 ጆርጂያ ውስጥ ከተብሊሲ የታሪክ ሙዚየም ጥንታዊ መጽሐፎችን ሰርቆ በተከሰሰበት ጊዜ ነው።
በወቅቱ ጥፋተኛነቱን ያመነ ሲሆን በገደብ ቅጣት ተጥሎበት ቆይቷል።
እአአ በጥቅምት 2023 ሁለት ወጣቶች ጥቁር ኮፍያ ያደረገ ወንድ እና ቀይ ፀጉር ያላት ሴት፣ በዋርሳው ዩኒቨርስቲ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ቁጭ ብለው እያነበቡ ነበር።
የአሮጌ መጽሐፍቱን ገጾች እያገላበጡ እያለ ወንዱ አብራው ያለችውን ሴት ጉንጭ አጥብቆ ሳመ።
ይህ ሁሉ የታየው በቤተ መጽሐፍቱ ውስጥ በተተከለ የደህንነት ካሜራ ነው።
ወጣቱ ልጅ የስሬኪዜ ልጅ ሜት ሲሆን ሴቷ ደግሞ የሜት ባለቤት አና ጎጎላድዜ ነች።
ሁለቱም በኋላ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ከቤተ መጻሕፍቱ 100,000 ዶላር የሚያወጣ መጽሐፍ በመስረቅ ወንጀል ተከስሰዋል።
ዩኒቨርስቲው በቅድመ እና ድህረ ሶቪየት መጽሐፍት የደለበ ክምችት የሚገኝበት ነው።
በዚህ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ እአአ በ1944 በነበረው ሕዝባዊ አመጽ ሕንጻው እና በርካታ ንብረቶች ሲቃጠሉ የተረፉ መጽሐፍት ይገኙበታል።
ፕሮፌሰር ሔሮኒም ግራላ "የሆነ ትውልድ እነዚህን መጽሐፍት ለእኛ እንዳተረፈልን የምንረዳ ትውልዶች ነን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜው ውስጥ እንደልብ የማይገኙ እና 600 ሺህ ዶላር እንደሚያወጡ የተገመቱ 73 ውድ መጽሐፍት ከቤተ መጻሕፍቱ ተሰርቀዋል።
አንዳንዶቹ የመጽሐፍ ቀበኞች እስካሁን ድረስ አልተያዙም።
ፕሮፌሰር ግራላ የወንጀሎቹን መጠን ለመገናኛ ብዙኃን ሲያስረዱ "ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ ዝርፊያ ነው"  ብለዋል።
"ከዘውድ ላይ ጌጣጌጦቹን ሰብሮ እንደመውሰድ ነው" ሲሉ የወንጀሉን ግዝፈት ለማሳየት ሞክረዋል።
የቤተ መጻሕፍቱ ሠራተኞች እንደዚህ ዓይነት በሐሰተኛ ቅጂዎች የተተኩ መጽሐፍትን ወዲያው አላስተዋሉም።
"ኮድ አለ፤ ተመሳሳይ መጠን ያለው መጽሐፍ አለ፤ በመደርደሪያው ላይ ምንም ክፍተት የለም" ብለዋል ፕሮፌሰር ግራላ።
ፕሮፌሰር ግራላ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "በመጀመሪያው ላይ የመጣው የሌቦች ቡድን (የተለዩ መጽሐፍት ላይ ያነጣጠሩ ነበሩ) እና በደንብ ተዘጋጅተው እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ማጭበርበሮችን ፈጽመዋል" ብለዋል።
በዚህ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ የተተገበሩት የቅርብ ጊዜ ማሻሻያዎች ለስርቆቶች ቁጥር መጨመር ሚና ተጫውተው ሊሆን ይችላል ብለዋል ፕሮፌሰር ግራላ።
በተለይም ውድ እና የማይገኙ አሮጌ መጽሐፍትን በሚጠቀሙ አንባቢዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር መላላቱ አስተዋጽኦ ሳያደርግ አልቀረም።
ይህ አሰራር የተዘረጋው ለአንባቢዎች የበለጠ ተደራሽ ለመሆን በሚል ዓላማ ነበር።
በተለምዶ ሁሉም ቤተ መጻሕፍት መጻህፍቱ ላይ ማህተማቸውን ያሳርፋሉ። መጠናቸው እንደ አገሩ እና እንደ ቤተመጻሕፍቱ ይለያያል።
የማይገኙ መጽሐፍትን በመሰብሰብ የሚታወቁት ፒዮትር ድሩዝህኒን ሩሲያውያን "ደመቅ ያሉ ማህተሞችን" በማድረግ እንደሚታወቁ ይናገራሉ።
ባለሙያው እነዚህን ማህተሞች ዓይቶ ብቻ መጽሐፍቱ የተሰረቁ መሆናቸውን መለየት ይቻላል ባይ ናቸው።
ይህ ግን ሁሌም ይሆናል ማለት አይደለም። ቤተ መጽሐፍቱ በሶቪየት ዘመን እንደሆነው ቦታ ሲጠባቸው ካሏቸው ተመሳሳይ መጽሐፍት የተወሰነውን ቀንሰው ይሸጣሉ።
ወይም ቤተ መጽሐፍቱ ሊበተኑ እና ሊዘጉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በፔሬስትሮይካ ዘመን የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ሲዘጉ አጋጥሟል።
እንደ ድሩዝህኒን ከሆነ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን እና ከዚያም ቀደም ብሎ ያሉትን ደግሞ ማህተሞቻቸውን በመመልከት ብቻ መነሻቸው ከየት ነው የሚለውን መለየት አስቸጋሪ ነው።
"ማህተሞቹ የ18ኛው ወይም የ19ኛው ክፍለ ዘመን ከሆነ መጽሐፉ ምን እንደገጠመው አናውቅም። እውነት ነው መጽሐፉ ከቤተመጽሐፍቱ ነው የወጣው፤ ነገር ግን እንዴት እንደወጣ ማንም ሊያውቅ አይቸልም።"
ማህተሞቹ ኬሚካልን በመጠቀም ሊወገዱ ወይም ያረጁ ገጾች በአዲስ ሊተኩ ይችላል። እንደዚህ ዓይነት መረጃን የማጥፋት እርምጃ ሊጋለጡ የሚችሉት በባለሙያዎች ወይም የጠፉ መጽፍትን በሚያሰባስቡ ግለሰቦች ብቻ ነው።
አሮጌ መጽሐፍት ማህተም ላይኖራቸው የሚችለው አልፎ አልፎ ብቻ ነው። ምክንያቱ ደግሞ መጽሐፍቱ ላይ ማህተም መደረግ ከመጀመሩ በፊት ወደ መጽሐፍ ሰብሳቢዎች እጅ ገብተው ሊሆን ስለሚችል ነው።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ኢስቶኒያ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኘው ስሬኪዜ "60,000 ዶላር የሚያወጣ፣ ግማሽ ኪሎ ወርቅ በ22 የታጠቁ ፖሊሶች ይጠበቃል። 60,000 ዶላር የሚያወጡ ሁለት መጽሐፍት አውሮፓ ውስጥ በሚገኝ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ፤ እናም አንዲት በዕድሜ በገፋች ሴት ይጠበቃሉ። ብዙ ጊዜ ደግሞ የደህንነት ካሜራ ክትትል እንኳን የለም" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።
ስለዚህ ባልተለመደ መልኩ ለ19 ኛው ክፍለ ዘመን የሩሲያ ዘመን አይሽሬ መጽሐፍት ከፍተኛ ዋጋ ለማውጣታቸው እና ለስርቆቱ እየጨመረ መምጣት ምክንያቱ ምንድን ነው?
ድሩዝሂኒን ብርቅዬ የሩሲያ መጽሐፍት ላይ ስርቆት የተጧጧፈው እአአ በ2022 እና 2024 መካከል የአውሮፓ የወንጀል ማዕበል ከፍተኛ ደረጃ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ይላሉ።
ባለሙያዎች "ይህ የሚሸጠው ከግል ስብስብ እየወጣ እንዳልሆነ" ሊያውቁት ይገባ ነበር ብለዋል።
ድሩዝሂኒን የውድ መጽሐፍት ገዢዎች አነስተኛ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ምናልባትም ሲገዙ እንደ የአገር ፍቅር ስሜት ተመልክተውት ሊሆን ይችላል ይላሉ።
"አሁን እነዚህ ጠቃሚ መጽሐፍት ወደ አገራቸው የተመለሱበት ወቅት ነው" ብለዋል።
በሰኔ ወር በሊትዌና ከሚገኘው የቪልኒየስ ዩኒቨርስቲ ቤተ መጻሕፍት ውድ መጽሐፍትን በመስረቅ እና በመሸጥ የተከሰሰውን ሌላውን የጆርጂያ ዜጋ ሚካሂል ዛምታራድዜን የተጭበረበሩ ሰነዶችን ተጠቅሞ የቤተመጻሕፍት አባል በመሆን 17 የማይገኙ መጻሕፍትን ወስዷል።
አብዛኛዎቹ ማህተሞች ነበሯቸው። ከዚያም 12 መጽሐፍትን በሌሎች ቅጂዎች ተክቷል፤ አምስቱን ደግሞ ከቤተ መጽሐፍት አውጥቶ አልመለሳቸውም።
የተሰረቁት መጽሐፍት አጠቃላይ ዋጋ ወደ 700,000 ዶላር ይገመታል።
ዛምታራዴዝ መጽሐፍቱን ከሞስኮ ትዕዛዝ ከተቀበለ በኋላ መስረቁን እና ወደ ቤላሩስ በአውቶብስ እንደላካቸው ገልፆ 30,000 ዶላር በክሪፕቶከረንሲ እንደተከፈለው ተናግሯል።
ከሞስኮ ሌሎች የመጽሐፉ ቅጂዎች እና ሐሰተኛ ሰነዶች እንደተላከለት የሚናገረው ዛምታራዴዝ፣ ደንበኛው በሞስኮ የጨረታ ማዕከል ውስጥ ከፍተኛ አባል የሆኑ ግለሰብ መሆናቸውንም ገልጿል።
የጨረታ ማዕከሎቹ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ስማቸው ሲነሳ ይህ የመጀመርያው አይደለም።
ከዋርሶ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍት የተወሰዱ ቢያንስ አራት የተለያዩ መጻሕፍት ሊትፈንድ  በተባለው የጨረታ ማዕከል ውስጥ በሞስኮ በ2022 መጨረሻ እና በ2023 ተሽጠዋል ሲሉ ፕሮፌሰር ግራላ ተናግረዋል።
ቢቢሲ፤ ፕሮፌሰር ግራላ ከጨረታ ማዕከሉ ድረ ገጽ የወሰዷቸውን ስክሪንሾቶችን ተመልክቷል።
በምስሉ ላይ ከዩኒቨርስቲው ቤተ መጻሕፍት እንደተሰረቁ የተገለፁት መጽሐፍት ይታያሉ።
ከመጻሕፍቱ አንዱ የፑሽኪን 'ዘ ቴልስ ኦፍ ኢቫን ቤኪን' ሲሆን በ19ኛው ክፍለ ዘመን የታተመ ማህተም በመጽሐፉ ፎቶዎች ላይ በግልጽ ይታያል።
ሌላው በዚሁ ጨረታ ላይ የቀረበው ባለ አራት ጥራዝ የፑሽኪን ግጥሞች ስብስብ ነበር።
አሁን በተዘጋው የጨረታ ማዕከሉ  ድረ ገጽ ላይ ባሉ ምስሎች የዋርሶ ዩኒቨርሲቲ ማህተምም ይታያል።
የሊትፈንድ ዳይሬክተር ሰርጌይ በርሚስትሮቭ እንዳሉት ጨረታው የሚሠራው በሩሲያ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ነው፤ እናም ማህተም ያረፈባቸውን መጽሐፍት ለሽያጭ አይቀበልም።
በርሚስትሮቭ አክለውም የመጽሐፉ ባለቤቶች ለጨረታ ተቀባይነት ያለው የትኛውንም መጽሐፍት ሕጋዊ አመጣጥ ለማረጋገጥ ከጨረታ ማዕከሉ ጋር ውል ይፈራረማሉ።
እያንዳንዱ መጽሐፍ ከጨረታው ማዕከሉ በመጡ ባለሞያዎች በቅርበት ምርመራ ይደረግበታል። በዚህም በስራ ላይ ካሉ ቤተ መጻሕፍት ጋር የተገናኙ ምንም ማኅተሞች ወይም ሌሎች ምልክቶች አለመኖራቸውን ያረጋግጣሉ።
በርሚስትሮቭ፤ "ከአብዮቱ በኋላ በነበሩት ዓመታት እጅግ በጣም ብዙ ከሩስያ ቤተ መጻሕፍት የወጡ መጽሐፍት በመላው ዓለም ተሰራጭተው በብዙ የመንግሥት እና የግለሰቦች ስብስብ ውስጥ ተካትተዋል። ስለዚህ በግለሰቦች እጅ ያሉ እንደዚህ ያሉ መጽሐፍት በዓለም ገበያ ላይ ተሰራጭተዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር ግራላ የድሮ ማህተሞች ጉዳይ ውስብስብ መሆኑን ያስረዳሉ።
"የዋርሶ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መጻሕፍት ታሪካዊ ማህተም ካለ እና የታሪካዊው ኮድ ተጠብቆ ከተቀመጠ፣ ይህ በራሱ እንደ ቅርስ ይቆጠራል። [ማንም ሰው] አዲስ ማህተም ወይም አዲስ ኮድ በላያቸው ላይ ማሳረፍ አይችልም። እነዚህ ማህተሞች ለ200 ዓመታት ያህል ኖረዋል፤ ከአክብሮት የተነሳ እንደገና አይታተሙም" በማለትም አብራርተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ "ዘመቻ ፑሽኪን" ገና አልተጠናቀቀም። ቢያንስ አንድ ተጠርጣሪ እዚያ ከሚገኙ ቤተ መጻሕፍት መጽሐፍትን በመስረቁ በፈረንሳይ ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ነው።
ባለሥልጣናቱም ብዙ ወንጀለኞች አሁንም አለመያዛቸውን እንዲሁም አንዳንድ የአውሮፓ ውድ መጽሐፍት አለመገኘታቸውን ያምናሉ።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
እስራኤል በባለፉት ስድስት ቀናት በኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች፣ ወታደራዊ ተቋማት እንዲሁም የመኖሪያ ስፍራዎች ላይ ያልተቋረጠ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች።
አብዛኞቹ ጥቃቶች የተፈጸሙት በአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል እንዲሁም በመዲናዋ ቴህራን ውስጥ ነው።
በኢራን ላይ የተፈጸሙት ጥቃቶች የአየር ላይ ቢሆኑም የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ዒላማዎችን በማመላከት እንዲሁም ጥቃቶችን ከመሬት ላይ ሆኖ በመምራት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ተብሎ ይጠረጠራል።
የሞሳድ ወኪሎች የኢራንን የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን ለማጥቃት ወደ ኢራን በድብቅ የገቡ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ተጠቅመዋል ተብሎ ይታመናል።
ከዚህ ቀደም የኢራን ባለሥልጣናትም ቢሆኑ የፀጥታ ኃይላቸው የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሠራተኞች ሰርገው ገብተውበታል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረው ነበር።
እስራኤል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በፈጸመችው ጥቃት ቁልፍ የሚባሉ የኢራን የጦር አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸው እስራኤል ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ በተመለከተ መረጃ እንዳላት የሚያሳይ ነው።
ሞሳድ በእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ ያለውን ሚና እስራኤል ስለስለላ ድርጅቱ እንቅስቃሴ ምንም አስተያየት ስለማትሰጥ መገምገሙ ቀላል አይሆንም።
ሆኖም የደኅንነት ተቋሙ ከዚህ ቀደም ያቀነባበራቸው ግድያዎች እንዲሁም የፈጸማቸው 'ኦፕሬሽኖች' የሚከተሉት ናቸው።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒያ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም. በኢራኗ መዲና ቴህራን በአንድ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ውስጥ ሳሉ ተገድለዋል። እስማኤል የተገደሉት ከአንድ ጠባቂያቸው ጋር ነበር።
እስራኤል መጀመሪያ ላይ ለመሪው ግድያ ኃላፊነቱን አልወሰደችም ነበር። ነገር ግን ከወራት በኋላ የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ከሃኒያ ግድያ ጀርባ አገራቸው እንዳለች አምነዋል።
ሆኖም በሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒያ ግድያ ዙሪያ በርካታ ያልጠሩ ነገሮች አሉ።
የሐማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ኻሊል አል ሃያ አብረዋቸው የነበሩ የዓይን እማኞችን ዋቢ አደርገው እንደተናገሩት እስማኤል ሃኒያ በቀጥታ በተነጣጠረባቸው ሚሳዔል እንደተመቱ ነው።
በሌላ በኩል ኒውዮርክ ታይምስ ሰባት ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው የሐማሱ የፖለቲካ መሪ የተገደሉት ከሁለት ወራት በፊት በድብቅ ወደሚኖሩበት ሕንጻ ውስጥ በገባ ቦምብ ነው።
ቢቢሲ የሐማሱ መሪ ግድያን በተመለከተ የሚባሉ ጉዳዮችን ማረጋገጥ አልቻለም።
አልጀዚራን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ የእስራኤል ዘመናትን ያስቆጠረ ወረራ፣ መዋቅራዊ ጭቆና፣ የፍልስጤምን የነጻነት እንቅስቃሴን በተመለከተ በመናገር የሚታወቁት እና የሐማስ መለያ የነበሩት የ62 ዓመቱ ኢስማኤል ሃኒያ ወደ ኢራን ያቀኑት በአዲሱ ፕሬዚዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ነበር።
እስራኤል ለመግደል ስታድናቸው የነበረው ሃኒያን ብቻ ሳይሆን ቤተሰባቸውንም ጭምር ነው። ከዚህ ቀደም  በሰሜን ጋዛ ሻቲ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አስር ቤተሰቦቻቸውን ገድላለች።
በዚያን ወቅትም የጋዛ ጦርነት ከተጀመረበት ከመስከረም 2016 ዓ.ም. መጨረሻ በኋላ 60 የሚሆኑ የቤተሰብ አባሎቻቸው ተገድለውብኛል ሲሉ ተናግረዋል።
በሚያዝያ ወር ሦስቱ ልጆቻቸው እና አራት የልጅ ልጆቻቸውም በጋዛ ሻቲ ካምፕ መኪና ውስጥ ሳሉ በእስራኤል ቦምብ ጥቃት ተገድለዋል።
እስራኤል ሐማስን እንዲሁም የሐማስን አመራሮች ለማጥፋት በተደጋጋሚ ስትዝት ቆይታለች።
ሃኒያ እንዲሁም የሐማስ መሥራች እና መንፈሳዊ መሪ የሆኑትን ሼክ አህመድ ያሲን በአውሮፓውያኑ 2003 ከእስራኤል የግድያ ሙከራ ተርፈዋል።
ሐማስ ከዓመት በፊት መስከረም መጨረሻ ላይ በእስራኤል ላይ ከፈጸመው ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ የሚገኘው የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር፣ ወንድሙ መሀመድ ሲንዋር፣ የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ኃላፊ መሐመድ ዴይፍ እና ምክትሉ ማርዋን ኢሳን ገድላለች።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ መስከረም ላይ የሔዝቦላህ አባላት መረጃ ለመለዋወጥ የሚጠቀሙባቸው በእጅ የሚያዙ ፔጀሮች በአብዛኛው ጠንካራ የሔዝቦላህ ይዞታ የሚባሉ ስፍራዎችን ጨምሮ በመላው ሊባኖስ ፈነዱ።
ፍንዳታዎቹ የያዟቸውን ሰዎች ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያቸው ያሉ ሌሎች ሰዎችንም ገድለው፣ እንዲሁም አቁስለው ግራ መጋባት እና ሽብርን ፈጥረዋል።
በቀጣዩ ዕለትም ዋኪ ቶኪ የሚባሉ ገመድ አልባ ስልኮች ፈንድተው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል፣ ጎድተዋል።
ትላልቅ የመገበያያ መደብሮችን ጨምሮ በየስፍራው የፈነዱት ፔጀሮች እና ዋኪ ቶኪዎች በመላው ሊባኖስ ከፍተኛ ድንጋጤን እና ሽብር የፈጠሩ ናቸው።
ሆስፒታሎች በተጎጂዎች የተጨናነቁ ሲሆን፣ በርካቶቹ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ቮልከር ቱርክ ይህንን የእስራኤልን ጥቃት የጦር ወንጀል ሲሉ ጠርተውታል።
በጋዛ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ፍልስጤማውያንን የሚደግፈው ሔዝቦላህ እና እስራኤል ግጭት ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ሔዝቦላህ ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሁለት ወራት በኋላ አገራቸው ለእነዚህ ፍንዳታዎች ተጠያቂ መሆኗን አምነዋል ሲሉ የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ሁለት የቀድሞ የሞሳድ ወኪሎች የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር አጋር ከሆነው ሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሞሳድ በእነዚህ ዋኪ ቶኪዎች ውስጥ የሚፈነዱ መሳሪያዎችን መቅበራቸውን አረጋግጠዋል።
ሔዝቦላህ ከ10 ዓመት በፊት ከ16 ሺህ በላይ ዋኪ ቶኪዎችን ከሐሰተኛ ድርጅት ሳያውቅ እንደገዛ ወኪሎቹ ገልጸው 5 ሺህ ፔጀሮችንም እንዲሁ ገዝተዋል።
ከአራት ዓመት በፊት ታዋቂውን የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስት ሞህሸን ፋክሪዛዴህን የጫነ ተሽከርካሪ ከዋና ከተማይቱ ቴህራን በስተምሥራቅ በምትገኘው አብሳርድ ከተማ ተኩስ ተከፈተበት።
የኒውክሌር ሳይንቲስቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሚታገዝ የርቀት መቆጣጠሪያ ጠመንጃ ነበር የተገደሉት።
"በሚንቀሳቀስ ዒላማ ላይ ምንም ዓይነት የሰላማዊ ሰዎች ጉዳት ሳይደርስ በዚህ መንገድ ግድያ መፈጸም መሬት ላይ የስለላ መረጃዎችን በጥንቃቄ ማሰባሰብ ይጠይቃል" ሲል የቢቢሲ የፐርሺያ [ፋርስ] ዘጋቢ ጂያር ጎል ጽፏል።
ከዚያ ቀደም ብሎ በአውሮፓውያኑ 2018 ሞሳድ ከወራት በፊት የሰረቃቸው የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብርን የሚመለከቱ በርካታ ሰነዶችን ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ አሳይተው ነበር።
ሞሳድ እነዚህን ሰነዶች ከቴህራን 30 ኪሎ ሜትር  ርቀት ላይ ከሚገኝ የእቃ ማከማቻ መጋዘን መስረቁ የተገለጸ ሲሆን፣ በኋላም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ይህንኑ አረጋግጠዋል።
ኔታንያሁ እነዚህን ሰነዶች ባቀረቡበት ጋዜጣዊ መግለጫ "ያልተገለጸ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ፕሮግራም ነው" ካሉ በኋላ አገራቸው የገደለቻቸው የኒውክሌር ሳይንቲስት ሚና ነበራቸው ብለዋል።
ኢራን ከዚያ ቀደም ብላ በአውሮፓውያኑ 2010 እና 2012 አራት የኒውክሌር ሳይንቲስቶቿን እስራኤል መግደሏን ገልጻለች።
ሞሳድ ከሚታወቅባቸው የስለላ ሥራዎች አንዱ በአውሮፓውያኑ 1960 የናዚ ጀርመን የጦር መኮንን የሆነው አዶልፍ ኢክማንን ከአርጀንቲና አፍኖ ያመጣበት ሴራው አንዱ ነው።
ሆሎኮስት ተብሎ የሚጠራው የአይሁዶች ጭፍጨፋን ካቀናበሩ የናዚ መኮንኖች መካከል አንዱ የሆነው ኢክማን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ማጎሪያዎች አይሁዶች እንዲገደሉ አድርጓል።
በወቅቱ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች በናዚ ጀርመን ተገድለዋል።
ኢክማን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተገባደደ በኋላ በተለያዩ አገራት ሲደበቅ ቆይቶ በስተመጨረሻም መኖሪያውን አርጀንቲና አደረገ።
14 ሰላዮች ያሉት የሞሳድ ቡድን ኢክማንን አፈላልጎ፣ ከደቡብ አሜሪካዊቷ አገር አርጀንቲና አፍኖ ወደ እስራኤል በማምጣት ለፍርድ በማቅረብ በሞት ተቀጥቷል።
በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ ውስጥ በእስራኤል የስለላ ድርጅት የተካሄደው የኢንቴቤ ኦፕሬሽን ሞሳድ ካከናወናቸው አንዱ ነው።
ሞሳድ የደኅንነት መረጃዎችን ሲያቀርብ የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ደግሞ እጅግ ውስብስቦቹን ተልዕኮ አጠናቅቋል።
ከእስራኤል ቴል አቪቭ በግሪክ አቴንስ በኩል ወደ ፓሪስ እያቀና የነበረው አውሮፕላን ተጠልፎ ነበር ወደ ኡጋንዳ የመጣው።
አውሮፕላኑ 250 መንገደኞች አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፣ 103 የሚሆኑት እስራኤላውያን ናቸው።
ሁለት የፍልስጤም ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር አባላት እና ሁለት ጀርመናውያን ጠላፊዎቹ አውሮፕላኑ አስገድደው ወደ ኡጋንዳ እንዲያበር አስገደዱት።
አገራትን አቋርጠው የዜጎቻቸውን ሕይወት ለመታደግ የተሰማሩት የእስራኤል ኮማንዶዎች በሞሳድ ድጋፍ ታጋቾቹን ማስለቀቅ ችለዋል።
ይህን የአውሮፕላን ጠለፋ ለማክሸፍ በተወሰደ እርምጃ ሦስት ታጋቾች፣ ጠላፊዎቹ፣ በርካታ የኡጋንዳ ወታደሮች እና የአሁኑ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ወንድም ዮናታን ኔታኒያሁ ተገድለዋል።
ሌላው ሞሳድ ካከናወናቸው ኦፕሬሽኖች መካከል አንዱ 7 ሺህ ኢትዮጵያውያን አይሁዶችን ከኢትዮጵያ በምሥጢር በማስወጣት በሱዳን በኩል ወደ እስራኤል ለመውሰድ የተደረገው ነው።
ይህ የሆነው በ1980ዎቹ ሲሆን ሞሳድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሜናኼም ቤጊን በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሐሰተኛ ‘የዳይቪንግ ሪዞርት’ (የመዝናኛ ስፍራ) ሽፋንን ተጠቅሞ ቤተ-እስራኤላውያኑን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ማጓጓዝ ችሏል።
ሱዳን በወቅቱ እስራኤል ጠላቴ ነው የምትለው የአረብ ሊግ አባል ነበረች።
የሞሳድ አባላት በሱዳን የቀይ ባሕር ወደብ አካባቢ ሪዞርት አቋቁመው ነበር። ይህ ሪዞርት ለሰላዮቹ እንደ ካምፕ ሆኖ ነበር የሚያገለግለው።
ሰላዮቹ ቀን ቀን የሆቴል ሠራተኛ ሆነው ያገለግላሉ። ማታ ማታ ደግሞ ከኢትዮጵያ በእግራቸው የመጡ አይሁዶችን በድብቅ በአውሮፕላን እና በባሕር ያጓጉዛሉ።
ይህ ኦፕሬሽን ቢያንስ ለአምስት ዓመታት የቆየ ሲሆን፣ የሰላዮቹ እንቅስቃሴ በተጋለጠበት ወቅት የሞሳድ ቡድን አባላት ሱዳንን ለቅቀው ወጥተው ነበር።
በአውሮፓውያኑ 1972 የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ‘ብላክ ሴፕተምበር’ በሙኒክ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሄዱ ሁለት የእስራኤል ኦሊምፒክ ቡድን አባላትን ገድሎ ዘጠኙን ደግሞ አገታቸው።
በወቅቱ የምዕራብ ጀርመን ፖሊስ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረት ቢያደርግም ባለመሳካቱ ዘጠኙም ታጋቾች ተገደሉ።
በዚህ ጥቃት ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉትን ለመበቀል ዓላማ የያዘውው ሞሳድ፣ ሞሐመድ ሀምሻሪን ጨምሮ በርካታ የፍልስጤም ነፃ አውጭ ቡድን አባላትን ዒላማ ማድረግ ጀመረ።
ሞሐመድ ሀምሻሪ ፓሪስ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ስልክ ላይ በተጠመደ ፈንጂ አማካይነት ተገደለ።
ሀምሻሪ በፍንዳታው አንድ እግሩን ካጣ በኋላ ነው ከቀናት በኋላ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ለሞት የበቃው።
በተመሳሳይ በ1996 በተካሄደ ኦፕሬሽን ያህያ አያሽ የተባለው ለሐማስ ቦምብ የሚሠራው ግለሰብ ሞቶሮላ አልፋ የተሰኘው የግንኙነት ሬዲዮው ላይ በተጠመደ 50 ግራም በሚመዝን ፈንጂ አማካይነት ተገደለ።
የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሪ የነበረው አያሽ ቦምብ በመሥራት ጥበቡ እና የእስራኤል መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ ውስብስብ ጥቃቶች አቀነባብሯል ተብሏል።
በዚህ ድርጊቱ ምክንያት ነው በእስራኤል የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ዘንድ እጅግ ተፈላጊው ሰው የሚል መዝገብ ላይ አስፍረውት ነበር።
በአውሮፓውያኑ 2019 እስራኤል ግድያውን በተመለከተ ደብቃው የነበረውን መረጃ ለሕዝብ ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ ቻነል 13 የተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ አያሽ ከመሞቱ በፊት ከአባቱ ጋር ያደረገውን የስልክ ልውውጥ አስደምጧል።
የአያሽ እና የሀምሻሪ ግድያ የረቀቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚፈፀም ግድያ ምሳሌዎች ናቸው።
በአውሮፓውያኑ 2010 የሐማስ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪ የነበረው ማህሙድ አል ማብሁህ በዱባይ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ተገደለ።
መጀመሪያ ላይ ሞቱ ተፈጥሯዊ ቢመስልም ነገር ግን የዱባይ ፖሊሶች የጸጥታ ቪዲዮዎችን ከመረመረ በኋላ በሰዎች መገደሉን ለመለየት ቻለ።
ፖሊስ ቆየት  አል ማብሁህ በኤሌክትሪክ ንዝረት እንዲሁም ከዚያ ታንቆ መገደሉን አጋለጠ።
ግድያው በሞሳድ የተቀነባበረ ነው ተብሎ መጠርጠሩም ጋር ተያይዞ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዘንድ ዲፕሎማሲያዊ ቁጣ ቀስቅሶ ከእስራኤል ጋር ያለው ግንኙነት ሻክሯል።
የእስራኤል ዲፕሎማቶች በበኩላቸው ሞሳድን ከጥቃቱ ጋር የሚያገናኘው ምንም አይነት ማስረጃ የለም ሲሉ አስተባብለዋል።
ምንም እንኳ ሞሳድ በርካታ ኦፕሬሽኖች ቢፈጽምም ታዋቂ የሆኑ ያልተሳኩ የግድያ ሙከራዎችን አካሂዷል።
በአውሮፓውያኑ 1997 እስራኤል የሐማስ ፖለቲካዊ ቢሮ ኃላፊ ኸሊድ ሜሻል ዮርዳኖስ እያሉ በመርዝ ለመግደል ያደረገችው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ተከስቷል።
የሞሳድ ሰላዮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ  እስራኤል ለሜሻል የተሰጠውን መርዝ የሚያረክስ መድኃኒት ለመስጠት ተገዳለች።
በዚህ ሙከራ ሳቢያ በዮርዳኖስ እና በእስራኤል መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ ነበር።
በ2003 እስራኤል በጋዛ ከተማ የሚገኘውን የሐማሱ መሪ ማህሙድ አል-ዛሃርን ቤት በአየር ጥቃት አወደመች። ምንም እንኳ አል-ዛሃር ከጥቃቱ ቢተርፍም ሚስቱ እና ወንድ ልጁ እንዲሁም በርካታ ሰዎች በጥቃቱ ተገደሉ።
አውሮፓውያኑ ጥቅምት 1973 ግብፅ እና ሶሪያ በሶቪየት ኅብረት ታግዘው እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈታቸው ይታወሳል።
ከ50 ዓመታት በኋላ እስራኤል ድጋሚ ድንገተኛ ጥቃት ተከፈተባት። መስከረም 26/2016 ዓ.ም. የሐማስ ታጣቂዎች ከጋዛ ተነስተው ወደ እስራኤል በመግባት ያልተጠበቀ ጥቃት ፈፀሙ።
ሞሳድ ይህ ከባድ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል ቀድሞ ሊደርስበት አለመቻሉ በአንዳንዶች ዘንድ ወቀሳ እንዲሰነዘርበት እያደረገ ነው።
የእስራኤል ባለሥልጣናት መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ ባደረሰው ጥቃት1200 ሰዎች ገድሎ ከ250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አግቶ ወደ ጋዛ ወስዷል ይላሉ።
እስራኤል በጋዛ ውስጥ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት ከ53 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸውንም በሐማስ አስተዳደር ሥር ካለው የጤና ሚኒስቴር የወጣው መረጃ አመልክቷል።
እስራኤል በጋዛ ጦርነት በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመች ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጹ ይታወሳል። እስራኤል ይህንን አልተቀበለችውም።
በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ በተደረገው ግምገማ መሰረት በጋዛ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል።
እስራኤል በከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ከሶስት ወር እገዳ በኋላ የተወሰነ እርዳታ ጋዛ ሂውማኒታሪያን ፋውንዴሽን በሚባል ድርጅት አማካኝነት እንዲሰራጭ ፈቅዳ ነበር።
ድርጅቱ በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚደገፍ ሲሆን በቅርቡም እርዳታ ሊቀበሉ ወደ ማዕከሉ በተሰባሰቡ ፍልስጤማውያን ላይ የእስራኤል ጦር ተኩስ ተከፍቶ በርካቶች ተገድለዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በናይጄሪያ ለማረፍ ሲሞክር በድንገት አቅጣጫውን የሳተው አውሮፕላን አብራሪ እና ረዳቱ የአልኮል መጠጥ ጠጥተው እንደነበር ተረጋገጠ።
የናይጄሪያ የደኅንነት ምርመራ ቢሮ ሐምሌ ወር ላይ በፖርት ሃርኮርት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ካጋጠመው ክስተት ጋር ተያይዞ በአብራሪዎቹ እና በበረራ ቡድኑ አባላት ላይ ምርመራ አድርጓል።
በዚህም አብራሪዎቹ የአልኮል መጠጥ መጠጣታቸውን እንዲሁም የበረራ ቡድኑ አባላትም ካናቢስ የተባለ እፅ መጠቀማቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
ንብረትነቱ የኤር ፒስ በሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላኑ ውስጥ 103 ሰዎች ተሳፍረው የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ባጋጠመው ክስተት የደረሰ ጉዳት የለም።
ኤር ፒስ እንዳለው የ64 ዓመቱ አብራሪ የደኅንነት መመሪያዎችን ባለማክበሩ ከሥራው የተባረረ ሲሆን፣ ረዳት አብራሪው ግን ወደ ሥራው ተመልሷል።
ኤር ፒስ በሰጠው መግለጫ ላይ ረዳት አብራሪው ብሔራዊ ተቆጣጣሪ በሆነው የናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራዎች እና የጤና ምርመራ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ በመገኘቱ ነጻ መውጣቱን ገልጿል።
ሆኖም በደኅንነት ምርመራ ቢሮው የተደረገው ምርመራ አብራሪው እና ረዳት አብራሪው በቅርብ ሰዓት ውስጥ የአልኮል መጠጥ መውሰዳቸውን የሚያመለክት ንጥረ ነገር ተገኝቶባቸው እንደነበር ገልጿል።
የበረራ ቡድኑ አባላትም በካናቢስ ውስጥ የሚገኘው አእምሮን የሚያነቃቃው ቲኤችሲ የተባለ ንጥረ ነገር ተገኝቶባቸዋል።
ኤር ፒስ ግን በመግለጫው ከደኅንነት ምርመራ ቢሮው ተጠቀሰው እፅ እንደተገኘባቸው የሚያሳዩ የደም እና የሌሎች ምርመራ ውጤት እንዳልደረሰው ገልጿል።
"ክስተቱ ካጋጠመ ከአንድ ወር በላይ በኋላ እና አደጋው ከማጋጠሙ ከአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የበረራ ቡድኑ አባላት አልኮል መጠጣታቸውን በተመለከተ ከደኅንነት ምርመራ ቢሮው ምንም ዓይነት ይፋዊ መረጃ እስካሁን አልደረሰንም" ብሏል።
የአውሮፕላኑ አብራሪ ከ18 ሺህ ሰዓታት በላይ የረራ ልምድ ያለው ሲሆን፣ የ28 ዓመቱ ረዳት አብራሪው ወደ 1200 ሰዓታት የበረራ ሰዓት አለው።
ምርመራው አሁንም በሒደት ላይ እንደሚገኝ የገለጸው የናይጄሪያ የደኅንነት ምርመራ ቢሮ፣ ሥልጠናዎች እና የውስጣዊ ደንቦች አፈፃፀም እንዲሻሻሉ መክሯል።
ለበርካታ ዓመታት በናይጄሪያ ውስጥ የተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ ባይኖርም ከመንደርደሪያ የመውጣት እና በሚያርፉበት ወቅት የጎማ መፈንዳት ክስተቶች አጋጥመዋል።
ከሳምንት በፊት የአቪዬሽን ባለሥልጣናት የአውሮፕላን ደኅንነትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የበረራ መረጃ ማዕከል የከፈቱ ሲሆን፣ አጋር ድርጅቶች ግን ተጨማሪ የደኅንነት መጠበቂያ እርምጃዎች እና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች በዘርፉ ውስጥ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ብለዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጠናው የፖለቲካ ትኩሳት ከመሆኑ ባሻገር ከምዕራባውያን ጋር ሆድና ጀርባ አድርጓታል።
የዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እአአ በ2003 ለ18 ዓመታት በምሥጢር ኢራን የኒውክሌር ተቋማቷን ስትገነባ መቆየቷን ከደረሰበት ወዲህ ደግሞ ተከታታይ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተካሄዱ ነው።
ይህ ግኝት ኢራን የፈረመችውን የኒውክሌር ጦር መሳርያዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ያለ ማስፋፋት ስምምነት የሚጥስ ነው።
በዚህም የተነሳ ከእስራኤል ጋር የጎሪጥ ከመተያየት በተጨማሪ በምዕራባውያን ግፊት በኢራን ላይ የዲፕሎማሲ ውግዘትን፣ ማዕቀብን እንዲሁም ሌሎች ጫናዎችን ሲያሳድሩ ቆይተዋል።
ይህ ደግሞ የምዕራባውያኑን አገራትን ብቻ ሳይሆን የቴህራን ወዳጅ የሆኑትን ቻይና እና ሩሲያንም ያካተተ ነው።
ኢራንን እዚህ ውዝግብ ውስጥ ያስገባት የኒውክሌር ፕሮግራም በወቅቱ ሥልጣን ላይ የነበረው የፕሬዝዳንት መሐመድ ኻታሚ መንግሥት ለሰላማዊ ዓላማ ነው በማለት ቢምል ቢገዘትም ሰሚ አላገኝም ነበር።
የእንቅስቃሴው አስተባባሪ የሆነችው አሜሪካም ኢራን ውስጥ የተገኙትን ማስረጃዎች በመጥቀስ ቴህራን የአውቶሚክ ጦር መሳሪያ ለመታጠቅ ትፈልጋለች ለሚለው ጥርጣሬዋ እንደ ማረጋገጫ ታቀርበዋለች።
የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር የጆርጅ ደብልዩ ቡሽ፣ የባራክ ኦባማ፣ የዶናልድ ትራምፕ እና የጆ ባይደን ተከታታይ የአሜሪካ አስተዳደሮች ማዕከላዊ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል።
እነዚህ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን የኃይል ሚዛን የሚቀይር መሆኑን በመጥቀስ መፍትሄ ለማበጀት የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመዋል።
ፕሬዝደንት ቡሽ በ2002 "አክሲስ ኦቭ ኢቭል" (የክፋት ማኅበር) በተሰኘው ዝነኛ ንግግራቸው ኢራንን የጠቀሱ ሲሆን፣ ያንንም ተከትሎ የተጠናከረ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣልባት አድርገዋል።
ኦባማ በስምንት ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን ከቴህራን ጋር ሲደራደሩ አሳልፈዋል።
ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከፈረንሳይ፣ ከሩሲያ፣ ከቻይና እና ከጀርመን መንግሥታት ጋር በመሆንም አጠቃላይ የድርጊት መርሃ ግብር በአውሮፓውያኑ 2015 ተፈራርመዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካን ከዚህ ስምምነት በማስውጣት አዲስ የአንድ ወገን ማዕቀብ በኢራን ላይ ጥለዋል።
በምላሹ ቴህራን በፈረመችው ስምምነት ላይ የተጣሉትን ገደቦች ችላ ማለት ጀመረች።
ከዚያም ዩራኒየም የምታበለጽግበት ደረጃን ወደ 60 በመቶ አሳደገች።
ይህም በተለምዶ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ከሚያስፈልገው 4.5 በመቶ እጅጉን የራቀ እና ቦምብ ለመሥራት ከሚያስፈልገው 90 በመቶ ጋር በጣም የቀረበ ነው።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢራን የፈረመችው ስምምነት በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፣ ትራምፕ የሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸውን ሲጀምሩ ጠንካራ አቋም ወስደዋል።
በቅርቡም አሜሪካ እስራኤል በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ የተቀላቀለች ሲሆን፣ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማትን በከባድ ቦምቦች ደብድባለች።
አሜሪካ ዛሬ የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን ብትደበድብም በ1950ዎቹ ግን ድጋፍ በማድረግ ከፊት ተሰላፊ ነበረች።
ይህ ሁሉ የተጀመረው በፕሬዝዳንት ድዋይት አይዘንአወር ንግግር ነበር።
በአውሮፓውያኑ ታኅሣሥ 8/1953 በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ፕሬዝዳንት አይዘንአወር ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውለው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ያለውን ስጋት ጠቅሰው ንግግር አድርገዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ስጋት ለመቀነስ ከመፈለግ ባለፈ ቴክኖሎጂው ለሰው ልጅ አገልግሎት እንዲውል ሃሳብ አቅርበዋል።
"ይህን መሳሪያ ከወታደሮች መዳፍ መንጠቁ ብቻውን በቂ አይደለም። ወታደራዊ ጭምብሉን እንዴት እንደሚያወልቁ በሚያውቁ ሰዎች እጅ እናስቀምጠው እና ከሠላም ጋር እናላምደው" ብለዋል።
በመቀጠልም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥላ ስር የአውቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንዲቋቋም ሀሳብ አቀረቡ።
በዚህም ኒውክሌር "ለሰው ልጆች ሰላማዊ አገልግሎት" እና አውቶሚክ ኢነርጂን እንደ ሕክምና እና ግብርና ላሉ ፍላጎቶች መዋል የሚችልበትን መንገድ እንዲፈልግ ሃሳብ አቅርበዋል።
አክለውም "ልዩ ግቡ የኤሌክትሪክ ኃይል ለተቸገሩ የዓለም ክልሎች አትረፍርፎ ማቅረብ ነው" ብለዋል።
ሃሳቡ የኒውክሌር ቁስ የማምረት አቅም ያላቸው ኃይሎች ለተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ ያንን እንዲሰጡ እና ይህም ደኅንነቱ በተጠበቀ እና በተመራማሪዎች እጅ ውስጥ እንዲቀመጥ ያስችለዋል።
ያ የአይዘንአወር ንግግር ለዓለም አቀፉ የአውቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) መፈጠር መንገድን ጠርጓል።
ከዚህም ባሻገር 'አተምስ ፎር ፒስ' (አተሞች ለሰላም) በመባል የሚታወቀውን ፕሮግራም እንዲጀመር አድርጓል።
በዚህም አሜሪካ በማደግ ላይ ላሉ አገራት የአውቶሚክ ኢነርጂ ሰላማዊ አጠቃቀምን ለመርዳት ትምህርት እና ቴክኖሎጂን እንድትሰጥ ያስችላታል።
ይህ ንግግር በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ከተደረገ በኋላ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ የአውቶሚክ ኢነርጂ ሕግን በማሻሻል የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እና ቁሳቁሶችን ለጦር መሳሪያ ልማት ላለመጠቀም ለተስማሙ ሌሎች አገራት መላክን የሚያስችላትን ሕግ አፀደቀች።
በአውሮፓውያኑ 1955 በመጋቢት ወር የአይዘንአወር አስተዳደር አንድ እርምጃ ሄዶ የአሜሪካ የአውቶሚክ ኢነርጂ ኮሚሽን በ"ነፃው ዓለም" ውስጥ ላሉ አገራት በተወሰነ መጠን የኒውክሌር ማምረቻ ቁሳቁስ እንዲያቀርብ እንዲሁም የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት እንዲያግዝ አደረገ።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት ፒተር አር ላቮይ በጦር መሳሪያዎች ቁጥጥር ማኅበር በታተመ ጽሑፋቸው ላይ ይህንን ዓላማ አብራርተዋል።
"እነዚህ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች የአሜሪካን ዓለም አቀፋዊ አመራር ለማስጠበቅ፣ የሶቪየት ተጽእኖን ለመቀነስ እና የዩራኒየም እና የቶሪየም አቅርቦቶችን ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የታሰቡ ነበሩ" ሲሉ ጽፈዋል።
ሕንድ ከዋሽንግተን የኒውክሌር እርዳታ የተቀበለች የመጀመሪያዋ አገር ነች።
ሌሎች ተጠቃሚዎች ደግሞ ደቡብ አፍሪካ፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ፓኪስታን፣ ፖርቱጋል፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል እና ኢራን ይገኙበታል።
በአውሮፓውያኑ መጋቢት 5/1957 ዩናይትድ ስቴትስ  በወቅቱ በመሐመድ ሬዛ ፓህላቪ ከምትመራው ኢራን ጋር ለሲቪል የአውቶሚክ ኢነርጂ አጠቃቀም የትብብር ስምምነት ተፈራረመች።
በ'አተምስ ፎር ፒስ' መርሃ ግብር ጥላ ስር የነበረው ይህ ስምምነት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለመጀመር መሠረት ጣለ።
ለዋሽንግተን፣ በዚያ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ኢራን ተጨማሪ መስህብ ነበራት።
ጆናህ ግሊክ ኡንተርማን በ2018 በዊልሰን ሴንተር በታተመ ትንታኔያቸው ላይ "በቤተ መዛግብት የተቀመጡ ሰነዶች ከማንም ጋር ወገንተኛ ያልነበረችው ኢራን፣ የሶቭየት ኅብረትን ተጽዕኖ ለመቀነስ የማዕዘን ድንጋይ ተደርጋ ትታይ እንደነበር ያሳያሉ። 'አተምስ ፎር ፒስ' የተሰኘው ፕሮግራም ደግሞ ለምዕራቡ ዓለም የሚኖራትን ታማኝነት ያረጋግጣል።"
እአአ በ1967 ዩናይትድ ስቴትስ ለቴህራን ባለ 5 ሜጋ ዋት የኒውክሌር ምርምር ማብላያ፣ እንዲሁም የተወሰነ መጠን ያለው ከፍተኛ የበለፀገ ዩራኒየም ሰጠች።
ከሦስት ዓመት በኋላ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለመያዝም ሆነ ለማልማት እንደማትፈልግ የሚያስገድደውን የኒውክሌር መከላከል ስምምነትን አፀደቀች።
ቢሆንም ግን የኒውክሌር ፕሮግራም ማበልጸግ ሃሳብ የምዕራባውያኑ ወዳጅ በነበሩት በኢራኑ ንጉሥ ሙሉ በሙሉ አልተተወም ነበር።
የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም አባት ተደርገው የሚወሰዱት አክባር ኢተማድ እአአ በ2013 ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የንጉሑን ሃሳብ አብራርተው ነበረ።
"በወቅቱ ሻህ ኢራን በቂ ጥንካሬ ካገኘች እና በቀጣናው ጥቅማችንን ማስጠበቅ የምንችል ከሆነ የአውቶሚክ መሳሪያ አያስፈልግም የሚል ሃሳብ ነበረው። ይህ ከተለወጠ ግን 'ኒውክሌር ሊኖረን ይገባል' የሚል አቋም ነበረ" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢተማድ በ1974 የተቋቋመው የኢራን የአውቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን፣ የአገሪቱን የኒውክሌር መርሃ ግብር የመጀመሪያ እንቅስቃሴን መርተዋል።
በዚያው ዓመት ንጉሡ ሬዛ ፓህላቪ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት እያንዳንዳቸው 23 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው 23 የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ለመገንባት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። የተሟላውን የኒውክሌር ነዳጅ ምርት ለማዳበርም ፈለጉ።
ነገር ግን ኢራን በዚህ መንገድ ወደፊት ለመራመድ የሚያስችል ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች ስለሌሏት ትልቅ እንቅፋት ተፈጠረ።
አሪያና ሮውቤሪ በብሩኪንግስ ኢንስቲትዩት ባሳተመው ጽሑፍ ላይ "ኢራን በኒውክሌር ምህንድስና እና በፊዚክስ የሰለጠኑ በርካታ ባለሙያዎች ስለሌሏት የቴህራን የኒውክሌር ማብላያ ለአስር ዓመታት ያህል ውጤታማ አልነበረም" ብለዋል።
አሁንም ይህንን መሰናክል ለማሸነፍ የአሜሪካ እርዳታ ቁልፍ ነበር።
በነሐሴ ወር 1974 የኢራን ባለሥልጣናት ለታዋቂው የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ኤምአይቲ) በኢራን የአውቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ለተመረጡ ተማሪዎች፣ የኢራን የኒውክሌር መሀንዲሶች የመጀመሪያ ትውልዶችን ለማሠልጠን የማስተርስ ፕሮግራም እንዲከፍት ሃሳብ አቀረቡ።
ኢራን ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት 1.3 ሚሊዮን ዶላር (በአሁኑ ምንዛሪ ስሌት 8.5 ሚሊዮን ዶላር) የከፈለች ሲሆን፣ የትምህርት ፕሮግራሙ ንጉሡ (ሻህ) በሰብዓዊ መብት ረገጣ በመክሰሳቸው እና ለኒውክሌር መስፋፋት አስተዋፅዖ ያደርጋል በሚል ፍራቻ በኤምአይቲ ፕሮፌሰሮች እና ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው።
ያም ሆነ ይህ፣ ይህ የትምህርት ስምምነት እና በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የነበረው የኒውክሌር ትብብር በ1979 በኢራን አብዮት በመፈንዳቱ ብዙም ሳይቆይ ተቋረጠ። ውጤቱ ግን አሁንም ድረስ ዘልቆ ቀጥሏል።
የቴክኖሎጂ ታሪክ ፀሐፊዎቹ ስቱዋርት ደብሊው ሌስሊ እና ሮበርት ካርጎን በአንድ ጽሑፋቸው ላይ "በኤምአይቲ ውስጥ ለሻህ የተነደፈው ፕሮግራም በእስላማዊ አብዮተኞች እጅ ይወድቃሉ ብሎ የገመተ ማንም የለም። የሚያሰለጥኗቸው የኢራን ተማሪዎች እና ፋካልቲው አብዮቱን ይደግፋሉ ተብሎ አልታሰበም" ሲሉ ጠቅሰዋል።
በኤምአይቲ አምሳያ የተቋቋመው የአርያመህር የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AMUT) የአብዮታዊ የተማሪ እንቅስቃሴ ዋና ማዕከል ሆነ።
መጀመሪያ ላይ በአያቶላህ ሩሆላህ ኾሜኒ የሚመራው አዲሱ አገዛዝ የሻህን የኒውክሌር ፕሮጀክቶች ውድቅ አድርጎታል።
ያንንም ተከትሎ በዚህ ዘርፍ የሠለጠኑ ብዙ ፕሮፌሰሮች ከአገር ተሰደዱ።
በፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር የሆኑት መሐመድ ሆማዩንቫሽ ከ1979ኙ አብዮት በኋላ ኢራናውያን እጅግ በጣም ፀረ ኒውክሌር እንደነበሩ ያስረዳሉ።
"ፕሮጀክቱ የሻህ ተቀጥላ ችግር መስሏቸው ነበር። እንዲያውም የኒውክሌር መርሃ ግብሩን አቁመው ሙሉ ለሙሉ ከሞላ ጎደል አፈረሱት" ሲሉ ለቢቢሲ ሙንዶ ተናግረዋል።
አክለውም "ኢራናውያን ከኒውክሌር ኃይል ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን አግልለው ለአምስት እና ለስድስት ዓመታት ያህል በዝምታ ውስጥ ነበሩ። ለኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ይውላል የሚለውም ኢራን የተትረፈረፈ የነዳጅ ሀብት ስለነበራት እንደ ብክነት ቆጥረውት ነበር" ሲሉ አክለዋል።
ሆኖም የኢራን አብዮት ከጊዜ በኋላ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ዋጋ በመገንዘብ ጥለው የሄዱትን ብዙ ባለሙያዎችን ለመመለስ መሞከር ብቻ ሳይሆን፣ የራሱን ምሥጢራዊ የአውቶሚክ ፕሮግራም ማካሄድ ጀመረ።
ነገር ግን 'አተም ለሰላም' በሌሎች አገሮች የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ግንባታ ላይ እና በአሁኑ የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ አሳድሯል?
እንደ ሆማዩንቫሽ ገለፃ፣ ከዚህ ተነሳሽነት ጀርባ የአይዘንአወር ስጋት በጦር መሳሪያዎች መስክ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን መጠቀም ያለው አንድምታ ነበር።
"በመሆኑም ብዙ አገራት በዚያ መንገድ እንዳይጓዙ ለመከላከል፣ ለሲቪል ዓላማ ሲባል የተወሰነ ደረጃ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ቢሆኑ፣ ይህ በተወሰነ ደረጃ ቁጥጥር ሊደረግበት ይችላል ተብሎ ይታሰብ ነበር፤ ተገቢው ጥበቃም ተዘጋጅቷል" ሲሉ ያክላሉ።
ለምሳሌ አሜሪካ ለአገራት ያቀረበችውን ለዩራኒየም ማብላያ ማንቀሳቀሻ፣ ለላብራቶሪ ፍጆታ ብቻ አከራየች እንጂ አልሸጠችም።
ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሰላሳ አገሮች ውስጥ የኒውክሌር ኃይልን ለማጥናት እና ምርምርን ለማካሄድ የረዳችው በዚህ መንገድ ነበር።
ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት ግን ይህ ተነሳሽነት ለኒውክሌር መስፋፋት ምን ያህል አስተዋጽኦ እንዳበረከተ በባለሙያዎች መካከል ስምምነት የለም።
ሆማዩንቫሽ 'አተምስ ፎር ፒስ' የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ማስተላለፍ የሚቻልበትን ሁኔታ ፈጥሯል ብሎ መከራከር እንደሚቻል ያምናሉ።
እና አገራት ይህን ቴክኖሎጂ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ከተማሩ በኋላ በተለያዩ አቅጣጫዎች ለመራመድ የራሳቸውን እርምጃዎች መውሰድ ችለዋል።
ይሁን እንጂ 'አተምስ ፎር ፒስ' ባይኖን ኖሮ አንዳንድ አገራት በኒውክሌር ልማት ረገድ ዛሬ ያሉበት ደረጃ ላይ አይደርሱም ነበር ብሎ መከራከር ቀላል እንዳልሆነ ያምናሉ።
ሌሎች ባለሙያዎች ግን የአይዘንአወር ተነሳሽነት የኒውክሌር መስፋፋትን መደገፉ ግልጽ ነው ብለው ይከራከራሉ።
በጆርጂያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፕሮፌሰር የሆኑት ጆን ክሪጅ "ይህ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ እና የ'አተም ፎር ፒስ' ተነሳሽነት እንዴት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልማትን እንዳበረታታ እና እንዳሳተፈ የሚያሳዩ ብዙ አዳዲስ ጥናቶች አሉ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"የሲቪል ኒውክሌር ቴክኖሎጂን ማጋራት ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ አንፃር ጉልህ የሆነ አንድምታ አለው። ስለዚያ ምንም ጥያቄ የለም" ሲሉ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠኑት ክሪጅ ተናግረዋል።
ይህንን አመለካከት የሚጋሩት እንደ ሕንድ እና ፓኪስታን ያሉ አገራትንም ይጠቅሳሉ።
የአውቶሚክ ቦምብ የሠሩ አገራት የመጀመሪያዎቹ የኒውክሌር ሳይንቲስቶቻቸው የሠለጠኑት በ'አተምስ ፎር ፒስ ኢኒሼቲቭ' ስር ነው።
"በሳይንስ ወይም በኢንዱስትሪ የኒውክሌር ቁሳቁሶችን ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውል የተደረጉበት አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። እነዚህ በ'አተምስ ፎር ፒስ' ስር በተገኙት መሳሪያዎች እና ፅንሰ ሀሳቦች መሠረት የደረጁ ናቸው። አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ታይዋን እና ደቡብ ኮሪያ ለዚህ ምሳሌዎች ናቸው" ሲሉ ፒተር አር ላቮይ ጽፈዋል።
የኢራንን ጉዳይ በተመለከተ፣ ከእስራኤል እና ከአሜሪካ የቦምብ ጥቃት በኋላ ከኒውክሌር መርሃ ግብሯ ምን ያህሌ እንደቀረ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ምን እንደሆነ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። እነዚያን የስቃይ ቀናት እያስታወሰች ስትተርክ፤ ከተፈጸመባት ጥቃት ይልቅ ጎልቶ የሚታየው ጥንካሬዋ ነበር።
ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ማሳሰቢያ - ይህ ታሪክ አንባቢዎችን ሊረብሹ የሚችሉ ገለፃዎችን ይዟል።
ነጻ ለመውጣት በመስኮት ስሾልክ ራሴን አገኘዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።
ተጠልፌ በተቀመጥኩባት ጨለማ ክፍል ውስጥ በእኔ እና በነጻነቴ መካከል ያለችው ማምለጫ አንዲት ትንሽ መስኮት ሆና ተገኘች።
እንዲለቅቁኝ ብዬ ያደረግኩት ልመና እና ለቅሶ ሰሚ አልነበረው። ምግብ ሊያቀርቡልኝ ወደ ክፍሉ የሚመጡ ሴቶች እንኳ በእንባዬ ልባቸውን አልራራም።
አመሻሽ ላይ ዋናው ጠላፊ እና ተባባሪዎቹ ከክፍሉ ሲወጡ ጠብቄ በትንሿ መስኮት አማተርኩ። አንዲት ሴት ቁጭ ብለዋል። በስጋት እና ነጻ በመውጣት ተስፋ መሃል ልቤ እየራደ ሴትዮዋ ዘወር እስከሚሉ ጠበቅሁ።
ሴትዮዋ ወደ ጎጇቸው ሲገቡ የሞት ሞቴን በትንሿ መስኮት ሾልኬ ወጣሁ። መጀመሪያ ኮቴዬ እንዳይሰማ ቀስ ብዬ ተራመድኩ። ቀጥሎ ግን ድንጋጤ እና ፍርሃት ውስጤን ስለሞላው የደመ ነፍስ ሩጫ ጀመርኩ።
በዚህ ጊዜ ጎጆ ውስጥ ያሉት ሴት ኮቴዬን ሰምተው ጮኹ። ፍጥነት ጨምሬ ሩጫዬን ከቀጠልኩ። ጩኸቱን ሰምተው ከቤት የወጡ ወንዶች ይከተሉኝ ጀመር። ዋነኛው ጠላፊ መካከላቸው አልነበረም።
ከግቢው ወጥቼ ዋና መንገድ ላይ ደረስኩ። የአድኑኝ ጩኸቴን የሰሙ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ። ዘወር ስል የሚያልፍ ሞተር ሳይክል ተመለከትኩ። ነጂውን አስቁሜ ሞተሩ ላይ ልወጣ ስል ሲያሯሩጡኝ ከነበሩት መካከል አንዱ ደርሶ ሞተሩን አስቆመው። እኔ ወደቅኩ።
ተስፋ አልቆረጥኩም። ጩኸቴን ሰምተው የተሰበሰቡትን ሰዎች እግር ይዤ ልመና ገባሁ። የሥራ መታወቂያዬን ከኪሴ አውጥቼ “የባንክ ሠራተኛ ነኝ። የማላውቃቸው ሰዎች አፍነው አምጥተውኝ ነው። እባካችሁ እርዱኝ” እያልኩ ተማፀንኩ።
ትልቅ ሰዎች፣ ሴቶች፣ ሕጻናት ተሰብስበዋል። አንዳንዶቹ፤ “ማንም አይነካሽም፤ ደርሰንልሻል” ሲሉ ቃል ገቡልኝ። ከሰዎች መካከል ጎትተው አይመልሱኝም ብዬ አሰብኩ።
የእኔ እምቢታ እና የሰዎች መሰብሰብ ይበልጥ ትኩረት እየሳበ ሲመጣ ዋነኛው ጠላፊ መጣ። ሊረዱኝ ቃል የገቡልኝ ሰዎች ወደ ጎን ወስዶ የፖሊስ መታወቂያውን እያሳየ አናገራቸው።
ይህንን ጊዜ የተሰበሰቡት ሰዎች ሀሳብ ተቀረ። “ጓደኛው አይደለሽ? ለምን ታስቸግሪያለሽ?” አሉኝ። “ይረዱኛል” ያልኳቸው ሰዎች ከእርሱ ጋር ተባብረው፣ ተሸክመው ወዳመለጥኩበት ቤት መለሱኝ።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
በጣም ብዙ ሰው ነበር። ነገር ግን ያለሁበትን ሁኔታ፣ የለመንኩትን ልመና ከቁብ የሚቆጥር አንድም ሰው አልነበረም።
ጠልፈው ሲወስዱኝም የሆነው እንዲሁ ነው። የጠለፈኝ ሰው እና አጋሮቹም ያበሩት በእኔ ላይ ነበር። አግተው የወሰዱኝም እንዲሁ በአመሻሽ  ነው።
ግንቦት 15/2015 ዓ.ም. ከምሠራበት የሐዋሳ ከተማ ዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ የወጣሁት አምሽቼ ነበር። ተከራይቼ ወደምኖርበት ቤት ለመሄድ እንደተለመደው ወደ ታክሲ ተራ ሄጄ አንዱ መኪና ውስጥ ገባሁ።
የተሳፈርኩበትን ታክሲ የሞሉት ስቃዬን የደገሱልኝ ሰዎች እንደነበሩ አልጠረጠርኩም። ታክሲ ውስጥ ገብቼ ቁጭ እንዳልኩ አንድ ሰው ተሯሩጦ ገብቶ፤ ፈቅ አድርጎኝ አጠገቤ ተቀመጠ።
ታክሲውን የሞሉት ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ወንዶች መሆናቸውን ያስተዋልኩት አጠገቤ ለተቀመጠው ሰው ሌላ ክፍት ወንበር ለማመልከት ወደ ኋላ ስዞር ነበር።
“ወራጅ አለ” ስል ከቀኝ እና ከግራ ያሉት ሰዎች አንገት እና እጄን ይዘው እንዳልንቀሳቀስ ነገሩኝ። በዚያ ሰዓት ሳስብ የነበረው ጉዳዩ ዘረፋ እንደሆነ ስለነበር ቦርሳዬን ወስደው እንዲለቅቁኝ እጠይቃቸው ነበር።
መኪናው ትንሽ መንገድ እንደተጓዘ ከመካከላቸው አንዱ “ጓደኛችንን አላናግርም ያልሽው ለምንድነው?” አለኝ።
የኋላመብራት ወልደማርያም የዋና ሳጅንነት የፖሊስ ማዕረግ ያለው የቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አጃቢ ነው። በምሠራበት የሐዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ በደንበኝነት ይመጣ የነበረው የኋላመብራት፤ “ላናግርሽ፣ እንገናኝ” እያለ ያስቸግረኛል። መግቢያ መውጫዬ ላይ ይጠብቀኝ፣ ስልክ እየቀያየረ በተደጋጋሚ ይደውልም ነበር።
መሥሪያ ቤት ውስጥ ባለች ባልደረባዬ በኩል ዛቻ አዘል መልዕክት ይደርሰኝ የነበረ ቢሆንም እንደዚህ አፍኖ እስከ መውሰድ ይደርሳል ብዬ አላሰብኩም።
የተሳፈርኩበት መኪና የሐዋሳ ከተማን ለቅቆ ወደ ገጠር አከባቢ ጉዞውን ሲቀጥል ፍርሃቴ እየጨመረ መጣ። ወዴት እንደምሄድ፣ ምን ሊያደርጉኝ እንደሚወስዱኝ አላውቅም። በማላቃቸው ሰዎች ቁጥጥር ውስጥ ሆኜ ሁሉም ነገር ጭልምልም አለብኝ።
መኪናው ጫካ የሆነ አካባቢ ሲደርስ በኋላ ወንበር ተደብቆ የነበረው የኋላመብራት አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ። በዚህ ጊዜ የእኔ ልመና ብቻ ይሰማበት የነበረው መኪና፤ የሰርግ ዘፈን ተከፍቶ ይጨፈርበት ጀመር።
“ጠለፋ ይሆን እንዴ?” ብዬ አሰብኩ። ኋላ እንደተረዳውትም ጉዳዩ ይህ ነበር።
ብዙ ተጉዘን አንድ የገጠር ቤት አቅራቢያ ስንደርስ ለእሱ ጋቢ ሰጥተው፤ ፊቴን ነጠላ ሸፈኑኝ። ከመኪናው ወርደን ወደ ቤቱ ስንገባ ደጅ ላይ የቆሙት ሰዎች በእልልታ ተቀበሉት። የኋላመብራት፤ ሽጉጥ አውጥቶ ወደ ሰማይ መተኮስ ጀመረ። ሁኔታው የሰርግ ድባብ ነበረው።
ሰው ሁሉ ይበላል፣ ይጠጣል፣ ይጨፍራል። የአሸናፊነት ስሜት ላይ ነበሩ። እኔ አለቅሳለሁ፣ እለምናለሁ. . .  ሰሚ አልነበረም። ሁኔታቸው ምርኮ ይዞ እንደመጣ ጀግና ነበር።
ኩራዝ ብቻ የበራበት ጨለማ ክፍል ውስጥ አስገቡኝ። ጠባቡ ክፍል ውስጥ ሊወቅድ የደረሰ አልጋ ተቀምጧል። አሁን ላይ ክፍሉን ሳስበው መቃብር መስሎ ይታየኛል። እያለቀስኩ፣ እየጸለይኩ ሌሊቱ ነጋ።
በማግስቱ ዋነኛው ጠላፊ የኋላመብራት እና አባሪዎቹ ቤቱ ደጅ ላይ ስብሰባ መሰል ነገር አድርገው ሲጨርሱ አስጠሩኝ።
“ከዚህ በኋላ የኋላመብራት ሚስት ነሽ። ሽማግሌዎችን አዘጋጅተናል። ለቤተሰቦችሽ ትደውያለሽ። ሽማግሌዎችን ይቀበሏቸዋል” ብለው በእኔ ላይ ያጸቀዱትን ውሳኔ ነገሩኝ። ያዘዙኝን ለመፈጸም ወደ ቤተሰቦቼ ደወልኩ።
ቤተሰቦቼ መጥፋቴን አውቀው ስለነበር፤ ያወሩኝ የነበረው በድንጋጤ ነበር። የት እንዳለሁ ለማወቅ በጥያቄ እያጣደፉኝ ስልኩ ተዘጋ። እኔንም መልሰው ወደዚያች ክፍል አስገቡኝ።
በዚህ ምሽት ነበር በትንሿ መስኮት ወጥቼ ለማምለጥ የሞከርኩት። እዚህ ውሳኔ ላይ የደረስኩት ሌላ አማራጭ እንደሌለኝ በመረዳቴ ነው።
በራሱ ውሳኔ ሚስቱ ያደረገኝ ጠላፊ ግን ነጻ የመውጣት መፍጨርጨሬን የቆጠረው ክብሩ ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ነበር። የማምለጥ ሙከራዬ ከሽፎ፤ ተሸክመው ወደ ቤት በሚመለስሱኝ ሰዓት በእልህ እሳት የነደዱ ዓይኖቹን አያቸው ነበር።
“እንዴት ታመልጫለሽ?...  ልታዋርጂኝ ነው?... ከእጁ ሴት አመለጠች ልታስብዪኝ ነው?... ማንም ከእኔ እጅ አያመልጥም” ደጋግመው ከአፉ የሚወጡ ቃላት ነበሩ።
ተሸክመው ወደ ቤት የመለሱኝ ሰዎች ሳሎን ውስጥ እንደተቀመጡ ወዳመለጥኩባት ጨለማ ክፍል ይዞኝ ገባ። እንዳይሆንብኝ የፈራሁት ከባዱ ነገር ሊሆንብኝ ሆነ።
ከባድ ነበር . . . በእልህ ነበር . . . ወንድነቱን ለማሳየት በትግል ነበር። አቅሜ ተፈተነ።
ራሴን በመጠበቅ ውስጥ ነበር ያቆየሁት። ከዚህ በፊት ወንድ አላውቅም ነበር። በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ለማግባት ዝግጅት ላይ ነበርኩ።
ከዚህ ድርጊት በኋላ ሲመሽ የሚሆነው እያሰብኩ ቀኑን ሙሉ ሳለቅስ እውላለሁ። በመሸ ቁጥር ወንድነቱን ይጠቀም ነበር።
“ምግብ በልታለች ወይ? ተጨንቃለች? እያለቀሰች ነው” የሚል ርህራሄ የለውም። በተደጋጋሚ ይደፍረኝ ነበር። ራሴን እስክስት ድረስ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ይጠቀመኝ ነበር።
ለቀናት በዚህ ሁኔታ ወስጥ እያለፍኩ ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ቤት ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ተባብሮ ጨካኝ ሆኖብኛል። እጮሃለሁ፣ እርዳታ እጠይቃለሁ፤ ህመሜን የሚረዳ አልነበረም።
“ተው” የሚል ከልካይ፣ “ምን እየሆነች ነው?” የሚል ጠያቂ አልነበረም። በየቀኑ ብዙ ሰዎች ወደ ቤቱ ቢመጡም ስለ እኔ ሁኔታ ግድ አላላቸውም።
መሽቶ በነጋ ቁጥር ያስፈራል። እጠባበቅ የነበረው መውጣቴን ነው።
በአንዱ ቀን ምግብ እንድታበላኝ የተላከችን ልጅ “ያለንበት ሰፈር ምን ያባላል” ብዬ አግባብቼ ጠየቅኳት። “ቡርሳ” ብላ ነገረችኝ።
ይህንን ከነገረችኝ ከሰዓታት በኋላ እንዴት እንደሆነ በማላውቀው ሁኔታ አጠገቤ የተረሳ ስልክ አገኘሁ። ለሰከንዶች እጄ በገባው ስልክ “ቡርሳ” የሚል መልዕክት ወደ ቤተሰቦቼ ላክሁ። መልዕክቱን ከስልኩ ላይ አጠፋሁት።
ቤተሰቦቼ መልዕክቱ የደረሳቸው ለጉዳዩ ትኩረት የሚሰጥ አጥተው፤ በራሳቸው ላይ ታች በሚሉበት ጊዜ ነበር። መሥሪያ ቤት ውስጥ አብራኝ የምትሠራው ልጅ ስለ እኔ መጥፋት ስትጠየቅ “የኋላመብራት እንደወሰደኝ” በመናገሯ ጠላፊው የፖሊስ አባል እንደሆነ አውቀዋል። ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያሏቸው ቢሮዎችን ደጅ እየጠኑ ነበር።
በኢትዮ ቴሌኮም ትብብር መልዕክት የተላከበት ቁጥር አድራሻው “ቡርሳ” እንደሆነ አወቁ። መልዕክቱ ያለሁበት ቦታ ስም መሆኑን ስለተረዱ ያገኙትን መረጃ ለፖሊስ አቀረቡ።
በማግስቱ ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ ፖሊሶች እና ወንድሜ ቡርሳ ፖሊስ ጣቢያ ደረሱ። እስከ አራት ሰዓት ድረስ አጋቹን በምን ዓይነት መንገድ ይዘወት ነጻ እንደሚያወጡኝ እያቀዱ ነበር። የአካባቢውን ሰዎች አጠያይቀው ወደ ነበርኩበት ቤት ሲደርሱ ግን እኔም ሆነ ጠላፊዬ አልነበርንም።
የኋላመብራት፤ ፖሊሶች አካባቢው ላይ ስለመድረሳቸው አስቀድሞ መረጃ ደርሶት ነበር። እነሱ ወደ ቤቱ ከመድረሳቸው በፊት ከአካባቢው ይዞኝ ሸሽቷል። ሰውነቴ ቁስል ሆኖብኝ ብደክምም፤ ረጅም መንገድ በእግር እና በሞተር ሳይክል እንጓዝ ነበር።
በሽሽት ያስቀመጠኝ አካባቢ ላይ ፖሊሶች በተቃረቡ ቁጥር የሚያስፈሩ መንገዶችን በሌሊት፣ በጉም እንድጓዝ ተገድጄ ነበር። ምንም እንኳ የርሃብ ስሜት ባይሰማኝም፤ እየተመገብኩ ስላልነበር ሰውነቴ ዝሏል።
በጣም በሚያሰቅቀው ደግሞ በዚያ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እንኳ ወንድነቱን ይጠቀም ነበር። እኔ ላይ ስቃዩን በማብዛት ቤተሰቦቼ ጋር ደውዬ “ሽማግሌ ተቀበሉ፤ የሚሏችሁን አድርጉ” ብዬ እንድናገር ይደረግ ነበር።
ቀናት እየገፉ፣ የእኔም ድምፅ እየጠፋ ሲመጣ ቤተሰቦቼ በተጠለፍኩ በሰባተኛው ቀን ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ አወጡት። ጉዳዩ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱ እና መነጋገሪያ መሆኑ ፖሊሶች በጠላፊው ላይ ጫና እንዲፈጥሩ አደረጋቸው። የየኋላመብራት ቤተሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል ጀመሩ።
እነዚህ የፖሊስ እርምጃዎች እርሱ ላይ ጫና ስለፈጠረ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ጠለፋውን እንድቀበል ሊያግባቡኝ ሞከሩ። ለማሳመን ሲያቅታቸው፤ “እንለቅሻለን፣ ወደ ቤተሰቦችሽ ትሄጃለሽ። ከዚያ ግን በእርቅ ያልቃል” አሉኝ። ጉዳዩ በእርቅ እንደሚያልቅ ለማረጋጋጥ መሃላ እንደምፈፅም አስረዱኝ።
የመሃላ ሥነ ሥርዓቱ በንጋታው ጠዋት እንዲፈጸም ተቀጥሮ እያለ ፖሊሶች ወደነበርኩበት ከተማ እንደደረሱ ለየኋላመብራት መረጃ ደረሰው። እኔን ቤት ውስጥ ትቶኝ ሸሸ።
በማግስቱ ሌሎቹ ሰዎች የትራንስፖርት ብር አስይዘው ወደ መናኸሪያ ወሰዱኝ። እንዴት የተለያዩ መኪናዎችን ተሳፍሬ ሐዋሳ ከተማ እንደምደርስ ነገሩኝ። ሐዋሳ ከተማ ስቃረብ ለቤተሰቦቼ እንድደውል ሲም ሰጥተው ለቀቁኝ።
ሰውነቴም፣ አዕምሮዬም አቅማቸውን ስጨረሱ አድርጊ የሚሉኝን አደርግ ነበር። በደመነፍስ ጽፈው በሰጡኝ መሠረት ሦስት መናኸሪያዎች ውስጥ እየወረድኩ፣ እየተሳፈርኩ ወደ ሐዋሳ ተቃረብኩ። ቤተሰቦቼ ጋር ደውዬ “ተለቅቄያለሁ እየመጣሁ ነው፤ ሐዋሳ መግቢያ ላይ ጠብቁኝ” አልኩ።
ሐዋሳ መግቢያ ላይ ስደርስ ከባድ ፍተሻ ነበር። ብዙ የፖሊስ መኪኖች ቆመው፣ የሚመጣው ሰው ሁሉ ከመኪና እየወረደ ይፈተሻል። የነበርኩበት መኪናም ቆሞ ስወርድ ፖሊሶች ጠሩኝ።
“የምንፈልገው አንቺን አይደል እንዴ” ብለው ከጎን እና ከጎን እንደ ወንጀለኛ ይዘው የፖሊስ መኪና ውስጥ ሊያስገቡኝ ሲሉ “ቤተሰቦቼን ሳላገኝ አልገባም” አልኩ። በስልክ አገናኝተውኝ፤ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱኝ።
የፎቶው ባለመብት, Alemayehu Timotewos
ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ባለሥልጣናት እና የፖሊስ ኃላፊዎች ተሰብስበው ከየት እንደመጣሁ፣ እንዴት እንደተለቀቅኩ ጠየቁኝ። የተነሳሁበትን ቦታ እንደማላውቅ አስረድቼ አቆራርጬ የመጣሁባቸውን ቦታዎች ነገርኳቸው።
ከዚያ በኋላ ወደ ማረፊያ ክፍል ላኩኝ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ መልሰው ጠሩኝ።
“ያገኘንሽ እኛ ነን። ከተለቀቅሽበት ቦታ ጀምሮ እየተከታተልንሽ ነበር። ሐዋሳ እስከምትገቢ የጠበቅነው ሌላ ግርግር ላለመፍጠር ነው” አሉኝ። እኔ ወደ ሐዋሳ ስመጣ እነሱ ካሳፈሩን በተጨማሪ በራሴ ሁለት መናኸሪያዎችን አቋርጫለሁ። ጉዞ የጀመርኩት መኪና እስኪሞላ እየጠበቅኩ ነበር።
የመጀመሪያው መናኸሪያ ላይ “ግርግር ላለመፍጠር ነው” ተብሎ ከታሰበ ቀጣዮቹ ሁለቱ መናኸሪያዎች ላይ ራሳቸው ፖሊሶች ይዘውኝ ሊመጡ ይችሉ ነበር።
ኃላፊዎቹ ይህንን ብለውኝ ወደ ማረፊያ ክፍሉ ተመለስኩ። ትንሽ ቆይቶ ወንድሜ ዜና ሲሰማ “በተቀናጀ ኦፕሬሽን እሷን ይዘናት እርሱ ጫካ ገባ” ይላል። እኔ የወጣሁት ግን ተሸኝቼ ነበር።
ቆይቶ ወደ ሆስፒታል ተወስጄ ምርመራ ተደረገልኝ። ምርመራው ሲያበቃ አብረውኝ የነበሩትን የፖሊስ አባላትን ወደ ቤቴ ለመሄድ እንዲለቁኝ ብጠይቅም ምላሻቸው እንደጠበቅሁት አልነበረም። ቃል መስጠት እንዳለብኝ ነግረው ወደ ጣቢያው መለሱኝ። ፍራሽ የተነጠፈባት አንዲት ቢሮ መሰል ክፍል ውስጥ አስገቡኝ።
ደጅ ላይ ወንድ እና ሴት ጥበቃዎች በተደረገበት በዚያ ክፍል ውስጥ ለአራት ቀናት ቆየሁ። ከክፍሉ መውጣት አልችልም ነበር። መጸዳጃ ቤት የምሄደው በፖሊሶች ታጅቤ ነው። ወደ ክፍሉ የሚገቡ ሰዎችን የሚፈቅዱ እና የሚከለክሉት ፖሊሶች ናቸው።
በራሴ ፍቃድ እዚያ ክፍል ውስጥ ያደርኩት በአራተኛው ዕለት ብቻ ነበር። በዕለቱም ያደርኩት ከቀኑ አስር ሰዓት እንድወጣ ሲነገረኝ ወደ ቤተሰቦቼ ቤት የምመለስበት ትራንስፖርት ባለማግኘቴ ብቻ ነበር።
ጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር የፈጸመብኝ ዋና ሳጅን የኋላመብራት ወልደማርያም በቁጥጥር ስር የዋለው እኔ ከተለቀቅኩ ከአምስት ቀናት በኋላ ነበር። ከሰባት ወራት በኋላ ደግሞ የሐዋሳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሴቶች እና ሕጻናት ችሎት በ16 ዓመት  ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ።
የፎቶው ባለመብት, Sidaama Bureau of Justice
ቅጣቱ ከተላለፈ ከሦስት ወራት በኋላ የፍርድ ቤት ሰነዶችን ለማግኘት በምጠይቅበት ጊዜ ግን በማላውቀው ሁኔታ የተሰጠው ፍርድ መሻሻሉን ሰማሁ። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው የ16 ዓመት ፍርድ፤ በይግባኝ ወደ አስር ዓመት ተቀንሷል። ይህ ውሳኔ መቼ እና እንዴት እንደተሻሻለ አላወቅኩም። ይህ ውሳኔ ሲተላለፍ ያሳወቀኝ ዐቃቤ ሕግም አልነበረም።
የመጀመሪያውን ውሳኔ የተቀበልኩት “የሕግ ባለሙያዎች መሄድ ያለባቸውን ርቀት ተጉዘዋል” ብዬ በማሰብ ነበር። በሕግ ቋንቋ “ተመጣጣኝ ቅጣት” የሚል አገላለጽ ቢኖርም፤ በየትኛውም ሁኔታ ለተጠቂዋ ተመጣጣኝ የሚሆን ቅጣት ይኖራል ብዬ አላስብም።
ብዙ ሰው የሚያስተውለው በዚያች ደቂቃ በመደፈር ውስጥ ያለውን ስቃይ ብቻ ነው። ከዚያ በኋላ ያለውን ሥነ ልቦናዊ ጉዳት የማያስተውሉ ብዙዎች ናቸው። መደፈር የዚያች ደቂቃ ጉዳይ ብቻ የሚሆነው ምናልባት ለአጥቂው ነው። ለተጠቂዋ ግን እድሜ ልኳን የሚከተላት ህመም ነው።
በሥነ ልቦናዊ ጉዳት በጣም ተሰቃይቻለሁ። እስካሁን ድረስ ህክምና እከታተላለሁ።
የተጋፈጥኩት የእነዚያ የዘጠኝ ቀናት ስቃይ ብቻ አይደለም። እነዚያ ቀናት ምናልባትም ወደፊትም ጭምር ሕይወቴን የሚጎዳ ጠባሳ ትተውብኛል። የደረሰብኝ ጥቃት ማኅበራዊ ግንኙነቴን፣ መንፈሳዊ ሕይወቴን፣ ለራሴ ያለኝን አመለካከት ጭምር ጎድቶብኛል።
ነጻ እንደወጣሁ ቀጥታ ወደ ሥነ ልቦና ህክምና ነበር ያመራሁት። በዚያ ፍጥነት ህክምና አግኝቼ እንኳ እስከ አሁን የምሰቃይባቸው፣ በጣም ብዙ ቀኖቼን በለቅሶ እንዳሳልፍ ያስገደዱኝ ህመሞች አሉኝ።
ቤተሰቦቼ በእኔ ጉዳይ ከመጠን በላይ ተጨንቀው ስለነበር እነሱ ላይ ሌላ ጭንቀት እንዳልሆን፤ ተደብቄ ብዙ ከባድ ቀናትን አሳልፌያለሁ። ከጥቃቱ በፊት የነበረችውን ፀጋ መልሶ ማግኘት ቀርቶ፤ ትንሽ ጠንከር ያለችውን ፀጋ ለማግኘት ታግያለሁ።
ይህንን ሁሉ እያሳለፍኩ ባለሁበት ምንም ሳይነገረኝ የመጀመሪያው ውሳኔ በመቀየሩ እርዳታ ፍለጋ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ወጣሁ። ፍትህ መዛባቱን እንዲሁም ከዚያም በፊት ታስሬ እንደነበር ጠቅሼ ቲክ ቶክ ላይ ቪድዮ ለቀቅኩ። የእኔ ጉዳይ በድጋሚ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት ሳበ።
የለቀቅኩት ቪድዮ ግን በሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ዘንድ በመልካም አልታየም። የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ “የከተማውን ስም እያጠፋሽ ነው። ከድርጊትሽ ተቆጠቢ” የሚል መግለጫ አወጣ።
የተናገርኩት የደረሰብኝን ነው። የጠየቅሁት ስለ ተዛባብኝ ፍትህ ነው። ከዚህ ንግግሬ በኋላ ተጨማሪ ነገር ብናገር . . . ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል። በመጠበቅ፣ ቃል በመቀበል ሰበብ መልሰው ወደ እስር ሊያስገቡኝ ይችላሉ ብዬ ሰጋሁ ።
ይብዛም ይነስ በተደረገልኝ ህክምና፣ እግዚአብሔርም ረድቶኝ በተወሰነ ጥንካሬ ላይ ነኝ። ከዚህ በኋላ እንደ እኔ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ድምፅ መሆን፣ ክፍተቶችን መናገር አለብኝ።
ይህንን ሳደርግ ግን የሚከተለኝ ነገር አስቀድሞ በማስጠንቀቂያ ከተነገረኝ፣ ከዚያ በላይ ሀገር ውስጥ መቆየት አልችም ነበር። ያገኘሁትን አጋጣሚ ተጠቅሜ ከሀገር ለመውጣት ተገደድኩ።
ከሀገር ከወጣሁ ግንኙነት የፈጠርኩት ከዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋር ነበር። በእነርሱም አማካኝነት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከለላ ፕሮግራም ውስጥ ታቅፌ ሥልጠናዎችን እየወሰድኩ እና ድጋፍ እያገኘሁ ነው።
ከባዱን ጊዜ አልፌያለሁ። ጉዳቴ ጨርሶ ባይሽርም በተደረገልኝ እገዛ ቢያንስ አሁን እዚህ ቆሜያለሁ። ከዚህ በኋላ ግን ለብዙ ሺህዎች ድምፅ እሆናለሁ። የመሰበር ምልክት መሆን አልፈልግም። አልፌ አሳያለሁ። እጠነክራለሁ። በጥቃት ውስጥ ላለፉ እና ለሚያልፉ ሴቶች የጥንካሬ ምሳሌ እሆናለሁ።
ሴት ልጅ ከተደፈረች በኋላ “ዋጋዋ እንደበፊቱ አይደለም” ተብሎ ይታሰባል። ተፈትኖ የወጣ ወርቅ ግን ምን ያህል ውድ እንደሆነ ማሳየት አለብን።
በሌላ አቅጣጫ ሳይሆን በራሱ በሰበረኝ ነገር ላይ እጠነክራለሁ። እኔን የሰበረኝ መደፈር ነው። እኔን የሰበረኝ ፆታዊ ጥቃት ነው። በዚሁ እኔን በመታኝ ነገር ላይ ለብዙዎች መፍትሔ እሆናለሁ።
ለየትኛውም ፆታዊ ጥቃት “እምቢ” በማለት ውስጥ ያለው ማሸነፍ የሚታይበት ሕይወት እቀጥላለሁ ብዬ አስባለሁ። የደረሰብኝን ነገር፣ ያለፉኩበትን ሁኔታ የሚያሳይም መፅሀፍ እያዘጋጀን ነው።
ከዚህ በፊት በነበሩ ጠለፋዎች፣ ፆታዊ ጥቃቶች ላይ ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእኔ ላይ የደረሰው አይፈጸምም ነበር። እነዚህ የሕግ ክፍተቶች ለእኔ ጥቃት ምክንያት ሆነዋል።
ከዚህ በኋላ እነዚህን ክፍተቶች ለመቅረፍ ለሴቶች መብት እሟገታለሁ። በአሁኑ ሰዓት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ለመሆን የሚያስችሉኝን ሥልጠናዎች እየወሰድኩ ነው።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋችነትን ለራሴ በመቆም ጀምሬያለሁ። ከዚህ በኋላ ፍላጎቴ፤ በእኔ የደረሰው ነገር በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሴት እህቶቼ ላይ እንዳይደርስ መሟገት ነው።
* ፀጋ በላቸው ከጠለፋ የወጣችበትን መንገድ በተመለከተ ከቢቢሲ ጥያቄ የቀረበለት የሲዳማ ክልል ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል። የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ፤ በወቅቱ ድርጊቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎች መስጠታቸውን አስታውሰው፤ “በድጋሚ የምንሰጠው ማብራሪያ የለም” ብለዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የ20 ደቂቃ ዜናና ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ፕሮግራም
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የዛሬ 100 ዓመት የኢትዮጵያ ሕዝብ 12 ሚሊዮን ግድም ነበር።
አስኳላ አልነበረውም፣ ጠመኔ አልነበረውም፣ ጥቁር ሰሌዳ አልነበረውም። አንድ አርቆ አሳቢ 'ንጉሥ' ግን ነበረው።
በእርግጥ ንጉሡ ያኔ ገና ንጉሥ አልነበሩም። አልጋ ወራሽ ነበሩ።
አልጋ ወራሽ ኾነው በአውሮጳ ጉብኝት አደረጉ። ይሄ ጉብኝት ኢትዮጵያ ''የምትነዳበትን ማርሽ" ቀየረ።
'ጃንሆይ' በዚያ ጉብኝት ደንግጠዋል። በእርግጥ ከዚያ በፊት በምኒልክ ጊዜ አባታቸውም እንዲሁ አውሮጳን ጎብኝተው ደንግጠዋል።
አውሮጳ መጥቋል፤ ዘምኗል፣ ተመንድጓል። ሕዝባችን ግን ኋላ ቀርቷል።
እኛ ከተቀረው ዓለም በመንፈስም በግብርም ሩቅ ነን። ተዘግተናል። ትንሽ ጠቅሞን ይኾናል፤ ብዙ ግን ጎድቶናል።
ዓለም በዝማኔ ጥሎን ገስግሷል። ለካንስ ምን ያህል ድሆች እንደነበርን ለማወቅ ራሱ ወጣ ማለት ያስፈልግ ነበር።
"እንዴት ነው ከዚህ በኋላ አውሮጳ የደረሰበት የምንደርስ?" እያሉ አልጋ ወራሽ  በሐሳብ ነጎዱ።
ሚያዝያ 19/1917 ዓ.ም. ተፈሪ መኰንን ትምርት ቤት ተመረቀ።
የዚህ ትምህርት ቤት 'ግለ ታሪክ' የዘመናዊት ኢትዮጵያ 'አስኳል እና ቅርፊት' ነው። በሰፊው ቢዘከር፤ ቢሰነድ፣ ምናልባት ደግሞ ቢነበብ ብለን ይህን ዥረት ዘጋቢ ሐተታ ጻፍን።
ከመጀመሪያ ተማሪዎች ዛሬ በሕይወት ያለ አለ? ያ ሰው ዕድሜው 110 አልፏል ማለት ነው። ከኋለኞቹ ተማሪዎች ግን ብዙ አሉ።
በአንድ ዘመን በተፈሪ ቤት አብረው የተማሩ ድንገት ከተገናኙ ፍቅራቸው ለጉድ ነው፤ ''ትዝ ይልኻል? ትዝ ይልሻል?'' መባባል ከጀመሩ  መሽቶ ይነጋል።
ድሮ የራሳቸው 'ብሔራዊ'  መዝሙር ሁሉ ነበራቸው። ዛሬም በስተርጅና ያልረሱት መዝሙር። ሲገናኙ ይዘምሩታል። ''We are the Voice of Teferi Mokonnen'' ይሰኛል።
Tri-Tru-Tri Tra-La-la" እያለ የሚቀጥል ነው። የራሱ ብሔራዊ መዝሙር ያለው ሌላ ትምህርት ቤት አለ? እንጃ።
የመጀመሪያዎቹ አዳሪ ተማሪዎች 30 ብቻ ነበሩ። ተቀማጥለው ነው የተማሩት። በእርግጥ ጫማ አልነበራቸው ይሆናል። ግን በጊዜው መለኪያ 'እንደ ዕንቁላል' ነበር የተያዙት።
የደምብ ልብስ ነበራቸው። እራት ከአልጋ ወራሽ ግቢ ይመጣላቸው ነበር። ዘወትር ሐሙስ የአልጋ ወራሽ ሚስት ወ/ሮ መነን [የወደፊቷ እቴጌ] የማር ብርዝ እና እንጀራ ወጥ ያበሏቸዋል።
የሚገርመው የተማሪዎቹ ዕድሜ እና መደብ ለየቅል ነው መኾኑ ነው።
ከመካከላቸው የ9 ዓመት ልጆች ነበሩበት። ግን ደግሞ የ19 ዓመት ጎረምሳም አይጠፋም።
ካጣ ከነጣ የገበሬ ልጅ ተወልደው፣ ከዳር አገር የመጡ  ገራገር ባላገር ልጆች ነበሩበት።
አሽከር አጅቧቸው፣ ፈረሳቸውን እንደ 'ላምቦርጊኒ' ደጅ አቁመው ወደ ክፍል የሚገቡ የመሳፍንት ልጆችም ነበሩ።
በሕይወታቸው እስክሪብቶ አይተው የማያውቁ ልጆች ነበሩበት። ሽጉጥ ታጥቀው የሚመጡ የመሳፍንት ልጆችም እንዲሁ። ይሄ ታዲያ መናኛ የፈረንጅ ልቦለድ እንጂ እውን ይመስላል?
የንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ የልጅ ልጅ ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ በዚህ ረገድ የዋህነታቸውን ሲያሰረዱ፣ ''ያኔ ከኔ ጋር የሚኖሩ መስሎኝ ሁለት አሽከር አስከትዬ ነበር እኮ የመጣሁት'' ሲሉ ለዶ/ር ሞገስ ገብረማሪያም ነግረዋቸዋል። ምባልባት ደጃዝማች ይህን ያደረጉት ወደ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትምህርት ቤት በመጡ ጊዜ ይኾን?
ኋላማ ደጃዝማች ዘውዴ፣  ኦክስፎርድ ገብተው፣ ዶክተር ተብለው፣ አገራቸውን በአምባሳደርነትም በሚኒስትርነት አገልግለው 'ቤት አልባው ከንቲባ' እንደተባሉ አረፉ።
ከንቲባ ዘውዴ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ፣ አረብኛን አቀላጥፈው ይናገሩም ነበር። ብዙዎቹ የተፈሪ ዘመን ልጆች እንዲያ ነበሩ። 'ሳት የላሱ።
ያኔ ተማሪዎች በሁለት ይከፈሉ ነበር፤ አዳሪ እና ተመላላሽ። ከአልጋ ወራሽ ግቢ እራት የሚመጣላቸው ታዲያ ለአዳሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።
ጃንሆይ ድንገት መጥተው ይጎበኟቸዋል። ጃ ቢቀሩ ቢቀሩ በሳምንት ዐርብ አይቀሩም።
"በርቱልኝ ልጆቼ" ብለው፤ ግንባራቸውን አሻሽተው "አንተ ደግሞ የማንኛው ልጅ ነህ?'' ብለው፣ ስጦታ ሰጥተዋቸው ይሄዳሉ።
ድንገት ኩስስ- ክስት- ሙዝዝ-ፍዝዝ ያለ ተማሪ ካዩ ''ምን ኾኖ ነው ይህ ልጅ?" ብለው ይጠይቃሉ። የታመመ ከመሰላቸው አጥሚት ያዙለታል።
ነፍስ ኄር ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ድሮ እዚያ ተምሯል። ስለ ንጉሡ ፍቅር አውርቶ አይጠግብም ነበር። ስለተንከባከቡት ይሆናል። አንድ ጆግ አጥሚት አዘውለትም ይሆናል፤ ማን ያውቃል?
ስብሐት ፈረንሳይኛ እና አማርኛ ልቅም አድርጎ ይናገራል፤ ይጽፋልም። ቀድሞ ጊዜ በአማርኛ ሐሳብ መግለጽ የሚቻልም አይመስለውም ነበር አሉ። በኋላ ነው ነገሩ የተገላቢጦሽ መኾኑ የተገለጠለት።
"እንግሊዝኛ እንደ አማርኛ የልብ ያደርሳል? እስቲ አሁን 'አይዞህ' በእንግሊዝኛ እንዴት ይገለጻል ?
እንግሊዝኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል? እስቲ አሁን፣ 'እኔን' ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን ተውት ፣ 'የት አባቱ !' ማለትንስ የት አባቱ አውቆት?
ሰው እንቅፋት ሲመታው 'እኔን ' በሚለው መተሳሰብ ፋንታ፣ 'ዋች አውት ! አር ዩ ኦ ኬ?' የት ያደርሳል?
'ዋች አውት ' አጠጋግተን ስንተረጉመው እንግዲህ ፣ 'ምን አባሽ ያደናብርሻል?' አይደለም ?"
ስብሐት ብቻ ሳይሆን ተፈሪ መኰንን የተማሩ ብዙዎቹ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ ነበር የሚቀናቸው። ያለ ምክንያት አይደለም። ትምህርት የሚሰጠው በፈረንሳይና በእንግሊዝ አፍ ስለነበረ ነው።
በተፈሪ ተማሪ ቤት፣ ትምህርት በየትኛው ቋንቋ ይሰጥ የሚለው፣ ራሱን የቻለ 'ቀዝቃዛ ጦርነት' ያስነሳ ጉዳይ ነበር። ኋላ በጨረፍታ እናነሳዋለን።
አንቀጽ-43“እየተመላለሱ የሚማሩ ልጆች ምሳቸውን በትምህርት ቤቱ መብላት የፈለጉ እንደሆነ በየወሩ ሦስት- ሦስት ብር ይከፍላሉ፤ አከፋፈሉም ባመት ሦስት ጊዜ ነው።"
"እኔ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ ተፈሪ ለቤተ መንግሥትም ሥራ ቢኾን፣ ለቤተ ክህነትም ሥራ ቢኾን ወይም ለራሱ ሥራ ቢኾን ለሰው ሁሉ መጀመሪያ የሚያስፈልገው ትምህረት መኾኑን ስለተረዳሁ ይህን ትምህርት ቤት አቁሜያለሁ። ስሙም ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ተብሏል።"
ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ በፈረንጅኛ ስማቸው ዶ/ር ቻርለስ ማርቲን ይባላሉ። እንግሊዛዊ ኾነው ያደጉ፣ ግን ደግሞ የቋራ ሰው ናቸው።
የልደት ስማቸው ወርቅነህ መሆኑን ያወቁት ራሱ ከጎለመሱ በኋላ ነው።
በመቅደላ ጦርነት ሕጻን ሳሉ የናፒየር ጦር ይዟቸው ሄደ፤ ወደ ሕንድ፣ ወደ በርማ። ታሪካቸው የዐጤ ቴዎድሮስን ልጅ፣ የልዑል ዓለማየሁን ይመስላል።
ልዩነቱ እሳቸው በአጭር አልተቀጩም። ልዩነቱ እርሳቸው የንጉሥ ልጅ አልነበሩም። ልዩነቱ እሳቸው ወደ አገራቸው መጥተው ድንቁርናን ለመበቀል ዕድል ማግኘታቸው ነው።
ከዚህ 100 ዓመት ከደፈነው ትምህርት ቤት ጋር ታዲያ ምን ያያይዛቸዋል?
የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት አባት ጃንሆይ ናቸው ካልን፣ የትምህርት ቤቱ 'እናት' ያለ ጥርጥር ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ናቸው። አዋልደውታላ።
ጃንሆይ ከንግሥና በፊት ባደረጉት ጉብኝት ''በአውሮፓ ሥልጣኔ በቅናት 'ት-ክ-ን' ብለው መጡ'' አላልንም ቅድም? አልጋ ወራሽ ሳሉ።
ይሄን በመጠኑ ከፍ ያለ መንገብገብ እና ቁጭት የሚጋራቸው ሰው ግን አላገኙም ነበር። መኳንንቱ አልተረዷቸውም። ከሐኪም ወርቅነህ ጋር ግን ልብ ለልብ ተናበቡ።
ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ (ባርኔጣ ያጠለቁት) ከንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴ ጋር በፓሪስ፤ ዘመኑ 1928 ዓ/ም ነው።
ሐኪም ወርቅነህ (ባርኔጣ ያጠለቁት) ከንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ጋር በፓሪስ፤ ዘመኑ 1928 ዓ/ም ነው።
ሐኪም ወርቅነህ በዕድሜ የጃንሆይ ታላቅ ናቸው። የትና የት። የተማሩትም እንግሊዝ ነው። ያጠኑትም ሕክምና ነው።
በዚያ ዘመን ውጭ አገር የተማረ ኢትዮጵያዊ ማግኘት፣ ጣሊያን የቀበረውን ወርቅ እንደማግኘት ያለ ብርቅ ነገር ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን፣ ከአውሮፓ ጉዟቸው በፊት፣ ሐኪም ወርቅነህ ተፈሪ ዘንድ ይሄዱና "ለምን በስምዎ ትምህርት ቤት አይከፍቱም?" ይሏቸዋል።
ጃንሆይ ደስታ ተናነቃቸው። የጃንሆይ ፊት እኮ ሲከፋውም ሲደሰትም አያስታውቅም። ያን ቀን ግን ፈካ።
"ይሄማ በአእምሮዬ ሲመላለስ የነበረ ጉዳይ ነው፤ ችግሩ ማን ያስተዳድርልኛል? አንተ ካልያዝከው" አሉ።
ከዚህ ወዲያ ያለው ታሪክ በጣም ረዥም ስለሆነ እንዘለዋለን።
ብቻ በዚያን ጊዜ የ60 ዓመቱ ሐኪም ወርቅነህ ወገባቸው እስኪጎብጥ ሌት ተቀን ቆመው ትምህርት ቤቱን አስገነቡ። በዚያ ላይ ማስገንባት ይወዳሉ። አዲስ አበባ በዚያ ዘመን  አይታው የማታውቀው፣ ምናልባትም የመጀመርያው ዘመናዊ መኖርያ ቤት ጃንሜዳ ጋ አስገንብተው ነበር፤ ለዚያውም አርመኖችን፣ ሕንዶችንና ሌሎች የውጭ ዜጎችን ቀጥረው።
ሐኪም ግንባታ ይዋጣላቸዋል፤ ይህን ተማሪ ቤትም በ1915 አስጀምረው፣ በሚያዝያ 19/1917 ዓ. ም. ተመረቀ።
ሐኪም ወርቅነህ በዚያች ዕለት ይህን ታሪካዊ ንግግር አሰሙ፦
“…ጸንቶ የቆመ የፍጥረት ሕግ ነውና፣ ማናቸውም ሕዝብ ባለው አኳኋን ብዙ ጊዜ ሊቆይ አይችልም። ወይ ወደፊት ይገፋል፣ ወይ ወደ ኋላ ይቀራል። ወደ ኋላ የቀረ እንደሆነ ከርሱ በበለጡ ሕዝቦች ይሰጥማል። ይህ ሕግ በዓለም ሙሉ የጸና ነው።
...የጃፓን ሰዎች ሕይወትና ነጻነት ከጥፋት ያዳኑ ይህን ዋና የሚያሻቸውን ነገር [ትምህርት] በጊዜ ስላወቁ እኮ ነው።”"
ይህን ታላቅ ንግግር ያደረጉት ሐኪም ወርቅነህ ትምህርት ቤቱን ለአምስት ዓመታት አስተዳደሩት።
ይህን ተማሪ ቤት ማስተዳደር ግን ቀላል አልነበረም። አ!ቤ!ት! አስተማሪ ለማግኘት ያዩት ፍዳ። አ!ቤ!ት! ገንዘብ ለማግኘት የገረፋቸው ፊት ብዛት።
". . . ዕውቀት ዘላቂ ሃብት ነው። ማንም ሊቀማችሁ አይችልም። …ትምህርት ያልዘለቀበት አገር ነጻነቱን ይዞ ብዙ አይዘልቅም። በክንደ ብርቱ አገር ይወሰዳል። ጃፓኖች ነጻነታቸውን መጠበቅ የቻሉት እኮ ስለተማሩ ነው…"
“ተማሪዎች ጥፋት ባጠፉ ጊዜ አስተማሪዎቻቸው ቁም፣ ተቀመጥ፣ እጅህን ዘርጋ፣ እጅህን ሰብስብ እያሉ በቀላል ቅጣት ይቀጧቸዋል እንጂ፤ በአለንጋ፣ በጥፊ፣ በበትር፣ በክርን፣ ይህን በመሰለ በልጆች ላይ በሽታ የሚያመጣ በብርቱ ቅጣት እንዳይቀጡ ተከልክሏል። ነገር ግን በትምህርት ቤቱ አጥር ግቢ የአትክልትና የአበባ ሥራ በማሠራት ቢቀጧቸው አይከለከሉም። ”
አልጋ ወራሽ ተፈሪ አንድ መካነ እንሰሳት ሲጎበኙ ይታያል (ሎንዶን)። ለአራት ወራት በዘለቀው ጉብኝት ግሪክ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝና ጣሊያንን አዳርሰዋል። በቫቲካን የያኔውን የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒየስ 11ኛን አግኝተዋል። ለአጭር ደቂቃ ሙሶሎኒን ሳያገኙት አልቀሩም። የወደፊት አሳዳጃቸው መኾኑን ሳያውቁ።
አልጋ ወራሽ ተፈሪ አንድ መካነ እንሰሳት ሲጎበኙ ይታያል (ሎንዶን)። ለአራት ወራት በዘለቀው ጉብኝት ግሪክ፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝና ጣሊያንን አዳርሰዋል። በቫቲካን የያኔውን የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒየስ 11ኛን አግኝተዋል። ለአጭር ደቂቃ ሙሶሎኒን ሳያገኙት አልቀሩም። የወደፊት አሳዳጃቸው መኾኑን ሳያውቁ።
በንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት፣ አልጋ ወራሽ ተፈሪ ወደ አውሮጳ ያደረጉት ጉብኝት በትምህርት ላይ ጽኑ እምነት እንዲያሳድሩ ምክንያት ሳይኾን አልቀረም።
በንግሥት ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት፣ አልጋ ወራሽ ተፈሪ ወደ አውሮጳ ያደረጉት ጉብኝት በትምህርት ላይ ጽኑ እምነት እንዲያሳድሩ ምክንያት ሳይኾን አልቀረም።
ፈረንሳዮች የዚህ ትምህርት ቤት ማስተማሪያ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ካልሆነ ሞተን እንገኛለን አሉ።
ጃንሆይ ፈረንሳይኛ ስለሚችሉ ለፈረንሳይ ስስ ልብ አላቸውና "ይሁን" አሉ።ሐኪም ወርቅነህ ደግሞ ግማሽ አካላቸው እንግሊዛዊ ስለሆነ "ሞቼ ነው ቆሜ!" ሳይሉ አልቀሩም።
ጃንሆይ ገና ሐረር ልጅ እያሉ በካቶሊክ ሚሽነሪዎች ነው የፈረንሳይ ፊደል የቆጠሩ።
አባ ዣሩሶ እና አባ ሳሙኤል ወልደ ካህን ከፈረንሳይኛ ሌላ ጂኦግራፊን አስተምረዋቸዋል። ትንሽ ታሪክ፣ ትንሽ ፍልስፍናም አቅምሰዋቸዋል።  ስለዚህ ጃንሆይ ለፈረንሳይኛ ቅርብ ቢኾኑ አይገርምም።
ሐረር ሳሉ፣ ከጓደሉፕ የካሪቢያን ደሴት ተወላጅ የነበሩት ፈረንሳዊው ዶ/ር ጆሴፍ ቪታሊየንንም አግኝተዋል። የአባታቸው የራስ መኰንን የግል ሐኪም ነበሩ። ተፈሪ በልጅነታቸው እኚህን ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም ማየታቸው አስተሳሰባቸውን ጠግኖታል፤ ዐይናቸውን ገልጦታል። ገና ድሮ።
አባ ሳሙኤል ኋላ በክፉ አጋጣሚ ዓለማያ ሐይቅ ሰምጠው ሲሞቱ ተፈሪ በተአምር ተረፉ። እንኳንም ተረፉ። ኢትዮጵያን ማን የዕውቀት ጠበል ይረጭ ነበር?
እንደው ነገሩን አበክረን ካሰብነው'ኮ ባለፉት መቶ ዓመታት ዘመናዊ ትምህርት የቀመሰ ዜጋ የተፈሪ ውለታ የለበትምን? አለበት እንጂ። እንዴት ማለት ጥሩ ነው።
ወይ እርሳቸው በገነቡት ተማሪ ቤት ነው የተማረ፤ ወይ እርሳቸው ባስተማሩት  ዜጋ ነው የተማረ።  በቀጥታም ባይኾን በተዘዋዋሪ፤ በአንድም ኾነ በሌላ።
1998 ዓ/ም በሐረር የተነሱት ፎቶ ነው።ተፈሪ (የወደፊቱ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ) እና ልጅ ኢያሱ በዚህ ምስል ከፊት ቆመው ይታያሉ። ተፈሪ ፈረንሳይኛን ከካቶሊክ ካህናት የተማሩትበት ዘመን ሳይኾን አይቀርም።
1998 ዓ/ም በሐረር የተነሱት ፎቶ ነው።ተፈሪ (የወደፊቱ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ) እና ልጅ ኢያሱ በዚህ ምስል ከፊት ቆመው ይታያሉ። ተፈሪ ፈረንሳይኛን ከካቶሊክ ካህናት የተማሩትበት ዘመን ሳይኾን አይቀርም።
ሐኪም ወርቅነህ ገና የሦስት ዓመት ሕጻን ሳሉ ከመቅደላ በእንግሊዞች ስለተወሰዱ ልሳናቸው እንግሊዛዊ ነው። ልባቸው ነው ኢትዮጵያዊ። አማርኛ መናገርም መጻፍም የቻሉት በጎልማሳ ዕድሜያቸው ነው።
ለዚህ ነው የትምህርት ቤቱ ይፋዊ ማስተማሪያ ቋንቋ ምን ይሁን በሚለው አለመግባባቱ ያየለው።
ያንን ዘመን ያጠናው የታሪክ ፀሐፊ ፒተር ጋሬትሰን ይህን ቀዝቃዛ ጦርነት 'የሥነ ልሳን ጦርነት' ወይም 'The linguistic war' እያለ ይጠራዋል።
በመጨረሻ ጦርነቱ ተፋፋመና አስታራቂ ሐሳብ መጣ። ትምህርት በሁለቱም ቋንቋ ይሰጥ ተባለ። ሐኪም ወርቅነህ የትምህርት ቤቱ ሹም ኾኑ። ፈረንሳያዊው ሙሴ ዣን ጊየን ዳይሬክተር ኾነ።
ከፈረንሳይ አገር የፈረንሳይኛ መጻሕፍት መጡ። ከእንግሊዝ አገር የእንግሊዝኛ መጻሕፍት ገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ግን ከየት ይምጣ? በብዙ አማርኛ በሚናገር ሕዝብ መሀል አማርኛ መጽሐፍ ጠፋ።
ከንቲባ ገብሩ ከጻፏት አንዲት መጽሐፍ ውጪ ወላ ሃንቲ። አፈወርቅ ገብረየሱስ ከጻፏት አንዲት ልቦለድ ውጪ ወላ ሃንቲ። ይሄኔ ነበር ብላታ መርስዔሐዘን ወልደቂርቆስ የደረሱት።
ዝነኛው መርስዔሐዘን በዚያው አማርኛ መምህር ኾኑ። ግዕዝም ያስተምሩ ነበር።
እሳቸው ያኔ በጭንቅ ያዘጋጇት የሰዋሰው መጽሐፍ ለቀጣይ ግማሽ ምዕተ ዓመት የአገሪቱ ብቸኛ ማስተማሪያ ኾና ዘለቀች።
ሐኪም ወርቅነህ አካዳሚክስ 'ልሙጥ' መሆን የለበትም በሚለው ጽኑ አቋማቸው ይታወቃሉ።
"የሰው ልጅ ሙያ መማር አለበት፤ ሙያ የሌለው ሰው ምን ይፈይዳል?" ይሉ ነበር። አገር የምትለወጠው በሙያ ጭምር ነው የሚል አቋም ነበራቸው።
ሐኪም ወርቅነህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ አገር ሲመጡ ያስተዋሉት ነገር - ያበሳጫቸውም ነገር- ይኸው ነው። ሕዝቡ ሙያ የለውም። ለመማርም ግድ የለውም። አለማወቁም ብዙ አያውከውም።
ለመጀመርያ ጊዜ እናት አገራቸው ገብተው ዞር ዞር ሲሉ፣ የአዲሳ ሕዝብ ቆሞ ወሬ ያያል፤ ሐኪም ወርቅነህ በገኑ። ተንጨረጨሩ። ኋላ የጨርጨር ገዥ ሳሉም ሕዝቡን ሙያ ተማር እያሉ ጨቅጭቀው ገደሉት።
እዚያ ጨርጨርም ተማሪ ቤት፣ ሙያ መማሪያ ቤት ከፍተው ነበር። ይሄ በኋለኛው ዘመን ነው የኾነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባሪያ ነጻ ይሁን ሲባል የመጀመሪያውን አገር በቀል 'ኤንጂኦ' የከፈቱ እና የባሪያ ልጆችን ሙያ ያስተማሩ እሳቸው ናቸው።
እና ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ልሙጥ የቀለም ትምህርት ብቻ እንዳይሰጥ የፈለጉትም ለዚሁ ይመስላል። ከዚያ በፊት ሽመና፣ ብየዳ፣ አናጢነት ለአገሬው ዝቅ ያሉ ሙያዎች ነበሩ። ሐኪም ወርቅነህ አስከበሩት።
በእርሳቸው ጉትቶታ የእጅ ሙያ ተካተተ። ሙዚቃ እና ሥዕል ሁሉ አልቀረም። እነ ሙሴ ፓፓዚያን ሥዕል፣ ሙሴ ናልባንዲያን ደግሞ ሙዚቃ ማስተማር ጀመሩ።
ቆይቶ ሙሴ ዲትሪሽ የሚባል የጂምናስቲክ አስተማሪም ተቀጠረ። ሩሲያው ሳይሆን አይቀርም።
እንዲህ ያለ ነገር በጊዜው ለአገሪቱ ፍጹም እንግዳ ነበር።
ተፈሪ መኰንን በዘመኑ 'የአፍሪካ ሃርቫርድ' እየተባለ ይጠራ ነበር። እንዲያ ያስባለው ጥራቱ ብቻ ሳይሆን ወጪው ከባድ ስለነበረ ነው።
የአንድ ተመላላሽ ተማሪ የምሳ ወጪ ብቻ በወር 3 ብር ደረሰ። ኑሮ እሳት ሆነ።
የአንድ ተማሪ የእርሳስ፣ የእስክሪብቶ የደብተር ጠቅላላ የትምህርት መሣሪያ ወጪ በወር 1 ብር ደረሰ። ጉድ ተባለ።
የትምህርት ቤቱ ጠቅላላ ዓመታዊ በጀት ወደ 80 ሺህ ተጠጋ። የቸሩ 'ንጉሥ' ኪስ ተሟጠጠ።
አልጋ ወራሽ ለትምህርት እና ለተማሪ አይሰስቱም። ትምህርት ቤቱ ራሱ የተገነባው በገዛ ርስታቸው ላይ አይደለምን?
ልዑላኑን፣ መሳፍቱን እና መኳንንቱን ማስቸገር ጀመሩ። ለግንባታ ያዋጡት ሰዎች ዝም ዝረዝር ሐኪም ወርቅነህ መዝግበው ይዘዋል።
የዘመኑ ቢሊየነር የነበሩት ('ሺሊየነር' የሚል ቃል የተሻለ ይስማማል)የጎጃሙ ራስ ኃይሉ 5 ሺህ ብር ለገሱ። አገር ጉድ አለ።
ራስ ጉግሳ አርአያ 300 ብር ሰጡ። አገር ጉድ አለ። ''እንዲያው የመሳፍንቱ አዱኛ ማለቂያም የለው'' እያለ ባላገር ተንሾኳሾከ። የጣፈው የለም እንጂ አዝማሪ ብዙ ብሎ ሊኾን ይችላል።
በነገራችን ላይ ጃንሆይ በዚህ ትምህርት ቤት በጣም ነበር የሚኮሩት።
የውጭ እንግዳ ሲመጣ ቶሎ ብለው ወደዚህ ትምህርት ቤት ወስደው ያስጎበኛሉ። የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዳ ሲመጣባቸው ወደ ፓርኮች እንደሚወስዱት ዓይነት መኾኑ ነው።
ጃንሆይ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ርዕይ የሚያሳይላቸው ይኸው ትምህርት ቤት ስለነበረ ነው ያን ያደርጉ የነበረው።
በዚህ የተነሳ የሮዝቻይልድ ቤተሰብ አልቀረም፤ የጃፓን፣ የሆላንድ፣ የጣሊያን መሳፍንት አልቀሩም፤ ማንኛውም መሪ አዲሳ'ባን ከረገጠ ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት  ይወሰድ ነበር።
እዚህ ጋ የተፈሪ መኰንን ታላቅ ወንድም የኾነውን ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤትን እናንሳ።
ምኒልክ ፈር ቀዳጅ ነው፤ ይሄ አንድና ሁለት የለውም። ግን እንደ ተፈሪ መኰንን ገናና አልነበረም። ዝ'ም'ን አላላም። እንዲያውም ሐኪም ወርቅነህ በምኒልክ ትምህርት ቤት ጭራሽ ደስተኛ አልነበሩም።
እርግጥ ነው ሐኪም ወርቅነህ መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ንጉሥ ምኒልክ ይህን የመጀመሪያ ትምህርት ቤት እንዲመሠርቱ አበረታተዋል። እጃቸው አለበት።
ሐኪም ወርቅነህ የንጉሥ ምኒልክ የግል ሐኪም መኾናቸው ሳይዘነጋ።
ንጉሡን ብቻ ሳይሆን እቴጌ ጣይቱን፣ፓትሪያርኩን አቡነ ማቴዎስን ጭምር "ዘመናዊ ትምህርት እንደምታስቡት የሰይጣን አይደለም" እያሉ በማሳመን ብዙ ጉልበት ጨርሰዋል። ከእቴጌይቱ ጋር ብዙም ኮከባቸው ባይገጥምም እንደነገሩ አብረው ሠርተዋል።
ምኒልክ ተከፈተ። ሐኪም ግን በውጤቱ ደስተኛ አልነበሩም። ለምን?
ምክንያቱም ሐኪም ወርቅነህ ከግብፅ የመጡትን 'አስተማሪዎች' አልወደዷቸውም። ካህናት ነበሩ።
ከግብፅ እንዲመጡ የኾነው ደግሞ የኢትዮጵያ አንዳንድ ካህናት በዘመናዊ ትምህርት ላይ ጥርጣሬ ስለነበራቸው ነበር። በአጋጣሚ የኾ ነገር አይደለም። ነገሩ ከባድ የሕዝብ ዲፕሎማሲ ነው።
ንጉሡ ጥበበኛ ስለነበሩ መምህራኑን ሆን ብለው ከግብፅ ኮፕቲክ አስመጡ።  እነዚህ መነኮሳት ናቸው በምኒልክ ተማሪ ቤት አስተማሪ የኾኑት።
እነዚህን መምህራን ሐኪም ወርቅነህ ባገኙት አጋጣሚ ይወርፏቸዋል። "ብዙም የዘመናዊ ትምህርት ዕውቀት አልነበራቸው" ሲሉ ይወቅሷቸዋል።
ባልታተመው የግል ማኅደራቸው እንዲህ ጽፈዋል፤ ". . .18 ዓመት ሙሉ አንድ እንኳ የረባ ሰው አላፈሩም!"
ሐኪም እንዲያ ይበሉ እንጂ ኋላ የኢትየጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መኾን የቻሉትን እነ አክሉሉ ሃብተወልድን እነ ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸውን ያፈራ' ኮ ምኒልክ ትምህርት ቤት ነው። ንጉሡስ ቢኾኑ የት ተማሩና።
ምናልባት የቁጭታቸው ምንጭ እርሳቸው በተማሩበት የምዕራቡ የጥራት ከፍታ ልክ አለመኾኑ ይኾን? ለነገሩ እንኳንም ተቆጩ። ይሄ ቁጭት እኮ ነው ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤትን ከምኒልክ  የላቀ ለማድረግ ያነሳሳቸው።
ደግነቱ ሐኪም ወርቅነህ እና አልጋ ወራሹ ሽርክ ነበሩ፤ በትምህርት ፍልስፍናቸው ስምም ናቸው።
የሁለቱ መቀናጀት ተፈሪ መኰንን ከፈር ቀዳጁ ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት ይልቅ ብዙ የተማረ እንዲያፈራ፤ ብዙ ርቀት እንዲሄድ አስችሎታል።
ለዘመናዊት ኢትዮጵያ እንደዚህ ትምህርት ቤት አስተዋጽኦ አለው የሚባል አንዳችም ተቋም የለም፤ ኋላ ከመጣው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በስተቀር። እሱንም ቢኾን ያዋለዱት የተፈሪ ትምህርት ቤት ካናዳዊ መምህራን መኾናቸውን ልብ ይሏል።
ካናዳዊያኑ መምህራን ለኢትዮጵያ ካስተዋወቁት ‘ባዕድ' ስፖርት አንዱ ቤዝቦል ነበር። እንደ እግር ኳስ ከግቢው ወጥቶ ሊወደድ አልቻለም እንጂ።
ካናዳዊያኑ መምህራን ለኢትዮጵያ ካስተዋወቁት ‘ባዕድ' ስፖርት አንዱ ቤዝቦል ነበር። እንደ እግር ኳስ ከግቢው ወጥቶ ሊወደድ አልቻለም እንጂ።
አሜሪካዊው ዳግላስ ኤዲ በተፈሪ ትምህርት ቤት ከተማሪዎቹ ጋር በ1950ዎቹ መጨረሻ
አሜሪካዊው ዳግላስ ኤዲ በተፈሪ ትምህርት ቤት ከተማሪዎቹ ጋር በ1950ዎቹ መጨረሻ
"ለእያንዳንዱ ተማሪ የሚያስፈልግ የበዓል ወይም ከሰው መገናኛ ልብስ የሚከተለው ይሁን፦ “አንድ ኮት፣ አንድ ሱሪ፣ ሁለት የገላ የውስጥ ሹራብ ጥጥ፣ ሁለት መሐረም፣ አንድ የአውሮጳ ጫማ”
"ጃንሆይ ድንገት ክስት-ሙዝዝ-ፍዝዝ ያለ ተማሪ ካዩ ''ምን ኾኖ ነው ይህ ልጅ?" ብለው ይጠይቃሉ። የታመመ ከመሰላቸው አጥሚት ያዙለታል። "
በዚያ ዘመን ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት የኬሚስትሪ ቤተ ሙከራ ክፍል ነበረው። ከመቶ ዓመት በኋላ ይህ ያልተሟላላቸው ዩኒቨርስቲዎች መኖራቸው ሲታሰብ የታሪክ ምጸት ይመስላል።
የተፈሪ የቀድሞ ተማሪዎች በ1973 ዓ/ም የተነሳ ፎቶ
ይህ ንዑስ ርዕስ እንዳይረዝም ስንል በዝነኞች ላይ ብቻ እናተኩራለን።
ተማሪ ቤቱ ክፍለ ዘመን በደፈነ ዕድሜው ፣ በውትድርና፣ በፖለቲካ፣ በሳይንስ፣ በፍልስፍና፣ በሕክምና ታላላቅ ሰዎችን አፍርቷል። ሚኒስትሮች እና ርዕሳነ ብሔራት አልቀሩትም። የኪነ ጥበብ ሰዎችም አያንሱትም።
በታሪክ ከመፈንቅለ መንግሥት ጋር ስማቸው የሚነሱ ብዙዎቹ ከዚህ ትምህርት ቤት የወጡ መኾናቸው የሚነግረን ነገር ይኖር ይኾን? ወይስ አጋጣሚ ነው?
ለምሳሌ ከድሮዎቹ እነ ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ሌ/ጄኔራል ዐቢይ አበበ፣ መንግሥቱ ነዋይ . . . ወዘተረፈ።
ለነገሩ በጣም ብዙ የጦር መሪዎች እና ሚኒስትሮች ከዚህ ተማሪ ቤት መውጣታቸውን ልብ ይሏል። ጀጋማ ኬሎም ተፈሪ ተምረዋል። ጠላት በመጣ ጊዜ ሆለታ ገነት የጦር አካዳሚ ገብተው፣ የውጊያ ትበብ  ተምረው፤ ጣሊያንን የተፋሉ የተማሩ ወታደሮች ከዚህ ነው የወጡት።
በጦር ሳይንስ ገናና ከነበሩትና ከወለጋ ወደ ተፈሪ ቤት ከመጡ የመጀመሪያ አዳሪ ተማሪዎች መካከል ሜ/ጄኔራል ዋቅጅራ ሰርዳ ይጠቀሳሉ።
ተፈሪ ከተማሩ በኋላ የፈረንሳዩን ፕሬዝዳንት እና ጦር አዋቂ ቻርለስ ደጎልን ያፈራው የዓለም ስመ ጥሩ ሳን ሲር (Saint-Cyr) የጦር አካዳሚ ተልከው የተማሩ ናቸው። ምባልባት ከደጎል ጋር የፈረንሳይ ጢቢኛ  ዳቦ (ባጌት) ቆርሰው ይኾናል። ማን ያውቃል?
አብረዋቸው ከወለጋ ወደ ተፈሪ ከመጡት ቀደምት ተማሪዎች መካከል ታላቁ አምባሳደር፣ ሚኒስትር እና ዲፕሎማት አማኑኤል አብረሃም ይጠቀሳሉ። ኹሉም ተፈሪ ነው የተማሩት።
ዶ/ር ሞገስ ገብረማሪያም በ8 ዓመታቸው በ1948 ተፈሪ መኰንን ተመዘገቡ። እርግጥ የአባታቸው ሕልም ዲያቆን እንዲሆኑላቸው ነበር። በድምጻቸው አለማማር ምክንያት አባታቸው ተስፋ ቆርጠው ‘በቃ እንግዲህ የፈረንጅ ትምህርት ይሞከር’ ብለው አስመዘገቧቸው። ዶ/ር ሞገስ በሕክምና ተመርቀው ከንጉሡ ዲግሪያቸውን ሲቀበሉ ይታያሉ። ፊት ለፊት ቆመው የሚታዩት ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ናቸው። 1965 ዓ/ም ነው።
ዶ/ር ሞገስ ገብረማሪያም በ8 ዓመታቸው በ1948 ተፈሪ መኰንን ተመዘገቡ። እርግጥ የአባታቸው ሕልም ዲያቆን እንዲሆኑላቸው ነበር። በድምጻቸው አለማማር ምክንያት አባታቸው ተስፋ ቆርጠው ‘በቃ እንግዲህ የፈረንጅ ትምህርት ይሞከር’ ብለው አስመዘገቧቸው። ዶ/ር ሞገስ በሕክምና ተመርቀው ከንጉሡ ዲግሪያቸውን ሲቀበሉ ይታያሉ። ፊት ለፊት ቆመው የሚታዩት ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ናቸው። 1965 ዓ/ም ነው።
ኳስ ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ የተገዛው በ1925 ለተፈሪ መኰንን ተማሪዎች ሳይሆን አይቀርም። ይድነቃቸው ተሰማ በቡድኑ ውስጥ ተሰልፏል። መሐል ላይ ጥቁር የለበሱት ንጉሤ ሮባ ናቸው። ከሜክሲኮ እስከ ሞስኮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ነበሩ። ይድነቃቸው የተመረቁት በ1935 ዓ/ም ሲሆን ከተፈሪ እንደጨረሱ ወደ ፈረንሳይ ለከፍተኛ ትምህርት ተላኩ።
ኳስ ምናልባትም ለመጀመርያ ጊዜ የተገዛው በ1925 ለተፈሪ መኰንን ተማሪዎች ሳይሆን አይቀርም። ይድነቃቸው ተሰማ በቡድኑ ውስጥ ተሰልፏል። መሐል ላይ ጥቁር የለበሱት ንጉሤ ሮባ ናቸው። ከሜክሲኮ እስከ ሞስኮ ኦሎምፒክ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ነበሩ። ይድነቃቸው የተመረቁት በ1935 ዓ/ም ሲሆን ከተፈሪ እንደጨረሱ ወደ ፈረንሳይ ለከፍተኛ ትምህርት ተላኩ።
ወደ ኋለኛው ዘመን ከመጣን ተፈሪ መኰንን ያፈራው ቁጥር ስፍር የለውም። ሕዝብ የሚያውቀው ግን ሚዲያ የዘመረላቸውን ብቻ ነው።
በፖለቲካ ንቁ ከነበሩት ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም እና ታላቁ ሐኪም ፕ/ር አስራት ወልደየስ ይነሳሉ።
ርዕሰ ብሔር ከኾኑት ደግሞ መቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ይጠቀሳሉ። በነገራችሁ ላይ የቀድሞዋ ርዕሰ ብሔር የሳሕለ ወርቅ ዘውዴ አባት፣ ኮ/ል ዘውዴ ዘረፋ እዚሁ ነበር የተማሩት።
ከጥበብ ሰዎች ደበበ እሸቱ፣ ወጋየሁ ንጋቱ ፣ሃይማኖት ዓለሙ (ቴአትር)፣ ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር፣ ተስፋዬ ገሰሰ፣ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ ሰለሞን ደሬሳ፣ ልዑልሰገድ ረታ ይጠቀሳሉ።
ከቅርቦቹ የኪነ ሕንጻ ነዳፊው ፋሲል ጊዮርጊስ እና ታላቁ የሕግ ሰው አቶ ተሾመ ገብረማሪያምን ማንሳት ይቻላል።
የአፍሪካ የእግር ኳስ አባት  ይድነቃቸው ተሰማም የተፈሪ ልጅ ናቸው። ልጃቸው ታደለ ይድነቃቸውም እንዲሁ።
የጅማው አባጅፋር የልጅ ልጅ አምባሳደር አባቢያ አባጆቢር አባጂፋርም የተፈሪ ፍሬ ናቸው። ዛሬም በሕይወት አሉ።
በነገራችሁ ላይ ብዙ ሰዎች ይህ ትምህርት ቤት የመሳፍንቱና መኳንንቱ ልጆች ብቻ የተርመሰመሱበት ይመስለዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቀድሞ ተማሪዎች ግን ይህ እውነት እንዳልሆነ መስክረዋል።
ከየጠቅላይ ግዛቱ፣ ከጠረፍ ሳይቀር ተማሪ ላኩ እየተባሉ ብዙ የገበሬ ልጆች በዕድሉ ተጠቅመዋል።
እንዲያውም ችግሩ የነበረው ሕዝቡ ልጁን እንዲልክ ማሳመኑ ላይ ነበር።
ብዙ ወላጅ ዘመናዊ ትምህርትን ከሰይጣን በላይ ይፈራ ነበር - ከእምነት ጋር በተያያዘ ነው ነገሩ።
ትምህርት እየተስፋፋ ሲመጣም ይህ ችግር በብዙ ተንጸባርቋል።
ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ (ከግራ 2ኛ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2ኛው ኢትዮጵያዊ ፕሬዝዳንት ነበሩ። በቀኝ በኩል ያየህይራድ ፍቅሬና ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ይታያሉ።
ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ (ከግራ 2ኛ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2ኛው ኢትዮጵያዊ ፕሬዝዳንት ነበሩ። በቀኝ በኩል ያየህይራድ ፍቅሬና ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ይታያሉ።
ዶ/ር ጴጥሮስ አክሊሉ ወደ ማሳቹሴትስ ከማምራታቸው በፊት ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። ወንድማቸው ኮ/ል ጳውሎስም ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። አባታቸው በ1917 ከተመዘገቡ የመጀመርያዎቹ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።
ዶ/ር ጴጥሮስ አክሊሉ ወደ ማሳቹሴትስ ከማምራታቸው በፊት ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። ወንድማቸው ኮ/ል ጳውሎስም ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። አባታቸው በ1917 ከተመዘገቡ የመጀመርያዎቹ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።
ሐኪም ወርቅነህ በጃንሆይ እርዳታ ምርጥ ተማሪዎችን ስኮላርሺፕ እንዲያገኙ ይጥሩ ነበር። ያኔ ገና ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በአገሪቱ የለማ።
ተማሪዎቹ 2ኛ ደረጃ ጨርሰው ቁጭ ይበሉ? ጭንቅ ሆነ።
ሐኪም ወርቅነህ ይህን ለማሳካት ያልረገጡት ምድር አልነበረም። መጀመሪያ ከተፈሪ የተመረቁ 12 ተማሪዎች ውጭ አገር ተላኩ።
6 ፈረንሳይ፣ 6 ሊባኖስ። በሊባኖስ የአሜሪካን ዩኒቨርስቲ የሚባል ድንቅ ኮሌጅ አለ።
የሚገርመው እነዚህ ተማሪዎች የኪስ ገንዘባቸውን የሚያገኙት ከጃንሆይ ኪስ ነበር። በኋላ ነው ወጪው ከትምህርት ሚኒስቴር የሆነው።
በእንሰሳት ሕክምና ምናልባትም የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ዮሐንስ እንግዳ ኒውዮርክ ነው የተማሩት።
ጃንሆይ ከኪሳቸው ከፍለው አሜሪካ ልከው ካስተማሯቸው መካከል ታላቁ የጥቁር መብት አቀንቃኝ መላኩ በያን ይገኝበታል።
መላኩ በያን ማለት እኮ የማርከስ ጋርቬይ ወዳጅና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሐኪም ነበር። (ሐኪም ወርቅነህን እንግሊዛዊ አድርገን ከቆጠርን ማለት ነው።) እሱ ግን ተፈሪ አልተማረም። መጀመርያ ሐረር፣ ከዚያ ሕንድ፣ ከዚያ አሜሪካ ሐዋርድ ነው የተማረው።
ይልቅ መኮንን ደስታ፣ ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። መኮንን ደስታ ምናልባትም ሃርቫርድ ገብቶ ለመማር የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሳይኾኑ አይቀሩም።
ሕክምና ጀምረው በኋላ ወደ ሰው ዘር ጥናት ክፍል ዞሩ። ጃንሆይ ከስደት ከተመለሱ በኋላ ካቤኒያቸውን ሲያዋቅሩ መኮንን ደስታ የመጀመሪያው የትምህርት ሚኒስትር ነበሩ።
ከእርሳቸው በኋላ ለ20 ዓመት አካባቢ የትምህርት ሚኒስትር ራሳቸው ንጉሡ ነበሩ። ንጉሡ የትምህርት ጉዳይ የግል ጉዳያቸው አድርገው ነበር የሚወስዱት። ለዚያ ነው ለትምህርት ገንዘብ የማይሰስቱት። ለዚያ ነው ሚኒስትር እንኳ ለመሾም የሚሳሱት።
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ንጉሡ እንዲያ እንዳያደርጉ የመከሩ ነበሩ። ያስተማሯቸው ተማሪዎች ኋላ ለዙፋናቸው አደጋ እንደሚኾኑ ያስጠነቀቁ ባለሟሎችም  ነበሩ።
የነዚህ ሰዎች ትንቢት መድረሱ ባይቀርም የንጉሡ የትምህርት ፍቅር ግን ጥልቅ ስለነበር በጄ አላሉም።
በርሳቸውና በሐኪም ወርቅነህ እርዳታ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ስመ ጥር ዩኒቨርስቲዎች ገብተው የተማሩ የተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት 'ፍሬዎች' ቁጥር ሥፍር የለውም።
ሐርቫርድ ከገቡት የተፈሪ ልጆች አንዱ ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ናቸው።
ከሐርቫርድ በኋላ በዝነኛው ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተምረዋል። እሳቸው ከሐርቫርድ የተመረቁት በአውሮፓውያኑ 1957 ነበር።
"የኔም ሆነ የእኩዮቼ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ የተሸፈነልን በጃንሆይ ነበር" ሲሉ ለልጃቸው ለዶ/ር ፈላስፋ ወዳጆ ነግረውታል።
በሜሪላንድ ሥመ ጥር የአጥንት ካንሰር ልዩ ሐኪም የኾነው ዶ/ር ፈላስፋ ሙሉጌታ የአባቱን የዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆን የተፈሪ ትምህርት ቤት ትዝታ ዘለግ ላለ ጊዜ ቃለ መጠይቅ በማድረግ በድምጽ ቀርጾ አስቀምጦታል።
በዚያ ቃለ ምልልስ አባቱ ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ አስገራሚ ትዝታቸውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተርከውለታል።
ለምሳሌ ጃንሆይ ትምህርት ቤት ሲመጡ ብርቱካን፣ እንጆሬ እና ዓሣ ያመጡላቸው እንደነበር ተናግረዋል። ስለጃንሆይ የሚገርም የማስታወስ ችሎታም ለለጃቸው ተርከውለታል።
"...ጃንሆይ ነገር አይዘነጉም። ከወር በፊት እንደቀልድ የነገርናቸውን ነገር እኛ ተማሪዎች ጭራሽ ረስተነው ሳለ፣ እሳቸው ግን በወሩ አስታውሰው ይጠይቁን ነበር።"
ስፔሻሊስት ዶክተር ፈላስፋ ሙሉጌታ ከአባታቸው ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ጋር
ስፔሻሊስት ዶክተር ፈላስፋ ሙሉጌታ ከአባታቸው ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ጋር
ወንድማማቾቹ ሙሉጌታ ወዳጆ (ቀኝ) እና ክፍሌ ወዳጆ ተፈሪ መኰንን ያፈራቸው ናቸው።
ወንድማማቾቹ ሙሉጌታ ወዳጆ (ቀኝ) እና ክፍሌ ወዳጆ ተፈሪ መኰንን ያፈራቸው ናቸው።
ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ የሐርቫርድ ምሩቅ ሲሆኑ በድኅረ ጣሊያን ዘመን ተፈሪ ካፈራቸው ታላላቅ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። በበተወለዱ በ89 ዓመታቸው በቅርቡ በቤቴስዳ፣ ሜሪላንድ አርፈዋል።
ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ የሐርቫርድ ምሩቅ ሲሆኑ በድኅረ ጣሊያን ዘመን ተፈሪ ካፈራቸው ታላላቅ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። በበተወለዱ በ89 ዓመታቸው በቅርቡ በቤቴስዳ፣ ሜሪላንድ አርፈዋል።
ከዶ/ር ሙሉጌታ ውብ ትዝታዎች አንዱ የድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ይመለከታል።
ያኔ በ50ዎቹ የ12ኛ ክፍል ማትሪኩሌሽን ፈተና የሚዘጋጀው በኢትዮጵያ አልነበረም። ከዩናይትድ ኪንግደም ነበር በቀጥታ የሚመጣው።
ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ከ70 ዓመት በኋላም ያልረሱት ፈተና ላይ የተጠየቁት ጥያቄ እንዲህ ይል ነበር፦
Write an Essay on the following:
B: Busy day at the London post office
"እኛ የባሕር ዳርቸውንም ፖስታ ቤቱንም የት አይተነው እናውቅና..." ብለው ይስቃሉ።
የሐርቫርዱ ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ይህን ትዝታቸውን ለልጃቸው አውርሰው፣ የተማሩበት ተፈሪ መኰንን 100ኛ ዓመቱን ሊያከብር መሰናዶ በጀመረበት ዓመት በተወለዱ በ89 ዓመታቸው በሜሪላንድ ቤተሰዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የእርሳቸው ወንድም ታዋቂው ክፍሌ ወዳጆም የተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ካፈራቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነበሩ።
ክፍሌ ወዳጆ  ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በዊስኮንሰን ዩኒቨርሰቲ ነው። ታሪካቸው ደማቅ ነው።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በተጠባባቂ ዋና ፀሐፊነት መርተዋል።
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በተባበሩት መንግሥትታ ቋሚ መልዕክተኛ እንዲሁም ለአጭር ጊዜ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ።
ይበልጥ የሚታወቁት ግን አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው ሕገ መንግሥት ሲጻፍ በአርቃቂ ኮሚሽን መሪነታቸው ነበር።
የ1950 ተመራቂ ከኾኑት ውስጥ አክሊሉ ሃብቴ፣ተሾመ ገ/ማሪያም፣እና አስመሮም ለገሰ ይታያሉ። ሦስቱም ስኬታማ ኾነዋል። ዶ/ር አክሊሉ በኋላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2ኛው ኢትዮጵያዊ ፕሬዝዳንት፣የባሕል ሚኒስትር፣ የዓለም ባንክ የትምህርት ክፍል ዋና ኃላፊ ኾነዋል። ፕ/ር አስመሮም ደግሞ በይበልጥ በገዳ ጥናት ሥራቸው ይታወቃሉ። ተሾመ ገብረማሪያም ታላቅ የሕግ አዋቂ ነበሩ።
የ1950 ተመራቂ ከኾኑት ውስጥ አክሊሉ ሃብቴ፣ተሾመ ገ/ማሪያም፣እና አስመሮም ለገሰ ይታያሉ። ሦስቱም ስኬታማ ኾነዋል። ዶ/ር አክሊሉ በኋላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2ኛው ኢትዮጵያዊ ፕሬዝዳንት፣የባሕል ሚኒስትር፣ የዓለም ባንክ የትምህርት ክፍል ዋና ኃላፊ ኾነዋል። ፕ/ር አስመሮም ደግሞ በይበልጥ በገዳ ጥናት ሥራቸው ይታወቃሉ። ተሾመ ገብረማሪያም ታላቅ የሕግ አዋቂ ነበሩ።
ምናልባት የተማሪ ቤት መዝሙር የተጀመረው በተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ሳይኾን አይቀርም። መዝሙሩን የጻፉት እንግሊዝኛ አዋቂው ኤፍሬም ተወልደ መድኅን ነበሩ። መዝሙሩ ውስጥ እነዚህ ስንኞች ይገኙበታል፦“የተፈሪ መ. ተማሪዎች፣ ለነጻነት ብሎ መሞት፣ ይህ ነው የኛ ዋናው ምኞት”
ታላቁ የቀዶ ጥገና ሐኪም እንዲሁም ፖለቲካኛ፣ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከተፈሪ ተማሪ ቤት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልከ ብዙ ይመስላል።
አንደኛ የተማሩት እዚያ ነው። ያስተማሯቸው ደግሞ ጃንሆይ ናቸው።
ከተፈሪ መኰንን በከፍተኛ ውጤት ጨርሰው፣ ግብፅ፣ ቪክቶሪያ ኮሌጅ ተልከው፣ ከዚያም ዩናይትድ ኪንግደም፣ ስኮትላንድ፣ ኤደንብራ ዩኒቨርስቲ ለሕክምና ትምህርት ሄደው-በማዕረግ ተመርቀው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ፋከልቲን መሥርተው፤ የመጀመርያው ዲን ኾነው...፤
ዞረው ዞረው ዞረው፣ ደርግ ጃንሆይን ሊገድላቸው ዋዜማ የንጉሡ የግል ሐኪም ኾኑ።
አሳድገው፣ ላስተማሯቸውን ንጉሥ ተምረው ደረሱላቸው። የሕይወት ክብነት።
ፕሮፌሰር አስራት በኤደንብራ በሕክምና ዘርፍ ለመመረቅ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ናቸው።
በ1920 አዲስ አበባ ተወልደው፣ ድሬዳዋ አድገው፣ ተፈሪ ፊደል ቆጥረው፣ ስኮትላንድ ተመርቀው፣ ሕዝባቸውን አገልግለው፣ ለ2 ዓመት ታስረው ከቆዩ በኋላ ታመሙ።
መንግሥት ላይ በደረሰ ዓለም አቀፍ ጫና ከእስር ተፈቱ። ለሕክምና ወደ ሎንዶን፣ ከዚያም  ሂውስተን፣ ቴክሳስ ተላኩ።
በመጨረሻ ፔንሴልቬኒያ ግዛት፣ ፊላደልፊያ ከተማ፣ በፔን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው አለፉ።
ንጉሡ ከግል ርስታቸው ቆርሰው የሰጡት የተማሪ ቤቱ ካርታ
ንጉሡ ከግል ርስታቸው ቆርሰው የሰጡት የተማሪ ቤቱ ካርታ
የሐረሩ መስፍን ልዑል መኰንን ኃይለሥላሴ እና ልዕልት ሰብለ ደስታ። ሥፍራው አልተገለፀም። ዘመኑ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት 13፣ 1947 ነው።
የሐረሩ መስፍን ልዑል መኰንን ኃይለሥላሴ እና ልዕልት ሰብለ ደስታ። ሥፍራው አልተገለፀም። ዘመኑ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥቅምት 13፣ 1947 ነው።
ፕሮፌሰር ጊልበርት ሙራይ ከአልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ጋር በዓለም መንግሥት ማኅበር ዩንየን በተዘጋጀ ግብዣ ላይ፤ ግንቦት 3፣ 1936
ፕሮፌሰር ጊልበርት ሙራይ ከአልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ጋር በዓለም መንግሥት ማኅበር ዩንየን በተዘጋጀ ግብዣ ላይ፤ ግንቦት 3፣ 1936
አልጋ ወራሽ ተፈሪ በፈረንሳይ ይፋዊ ጉብኝት ላይ ሳሉ። ዘመኑ 1916 ዓ/ም ነው። በትምህርት ረገድ ከፈረንሳይ ብዙ እገዛን ጠብቀው ነበር።
አልጋ ወራሽ ተፈሪ በፈረንሳይ ይፋዊ ጉብኝት ላይ ሳሉ። ዘመኑ 1916 ዓ/ም ነው። በትምህርት ረገድ ከፈረንሳይ ብዙ እገዛን ጠብቀው ነበር።
አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ፣ ከባለቤታቸው ልዕልት መድፈሪያሽወርቅ አበበ ጋር በሎንደን አውሮፕላን ጣቢያ። ዘመኑ 1952 ዓ/ም ነው።
አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ፣ ከባለቤታቸው ልዕልት መድፈሪያሽወርቅ አበበ ጋር በሎንደን አውሮፕላን ጣቢያ። ዘመኑ 1952 ዓ/ም ነው።
የሐረሩ መስፍን ልዑል መኰንን ኃይለሥላሴና እህቱ ልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ በምዕራብ ሎንደን ኬንሲንግተን የሚኖሩበት ግቢ ከመጡ እንግዳ ጋር ሲያወጉ ይታያሉ። ዘመኑ ግንቦት፣ 1928 ነው።
የሐረሩ መስፍን ልዑል መኰንን ኃይለሥላሴና እህቱ ልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ በምዕራብ ሎንደን ኬንሲንግተን የሚኖሩበት ግቢ ከመጡ እንግዳ ጋር ሲያወጉ ይታያሉ። ዘመኑ ግንቦት፣ 1928 ነው።
የጃንሆይ የመጨረሻ ልጅ ልዑል ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ፣ ወደ ኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ከማምራታቸው በፊት እንደ ታላቅ ወንድማቸው ሁሉ በተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ገብተው ተምረዋል።
የጃንሆይ የመጨረሻ ልጅ ልዑል ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ፣ ወደ ኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ከማምራታቸው በፊት እንደ ታላቅ ወንድማቸው ሁሉ በተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ገብተው ተምረዋል።
ሐረር ተወልደው፣ መርእድ አዝማች ተብለው፣ የወሎ ገዥ ኾነው፣ ሎንዶን ኖረው፣ ፌየርፋክስ፣ ቨርጂኒያ ያለፉት የጃንሆይ ልጅ አልጋ ወራሽ አስፋወሰን ኃይለ ሥላሴ ለአጭር ጊዜ ተፈሪ ተማሪ ቤት ገብተዋል። ከዚያ በኋላ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
ሐረር ተወልደው፣ መርእድ አዝማች ተብለው፣ የወሎ ገዥ ኾነው፣ ሎንዶን ኖረው፣ ፌየርፋክስ፣ ቨርጂኒያ ያለፉት የጃንሆይ ልጅ አልጋ ወራሽ አስፋወሰን ኃይለ ሥላሴ ለአጭር ጊዜ ተፈሪ ተማሪ ቤት ገብተዋል። ከዚያ በኋላ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከሊቨርፑል ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
ልዑል መኰንን ኃይለ ሥላሴ፣ እጅግ ተወዳጁና ተመራጩ የጃንሆይ ልጅ ነበሩ። አዲስ አበባ ተወልደው ሳራ ግዛውን አግብተው፣ በዚች ምድር 32 ዓመት ብቻ ኖረው፣ በመኪና አደጋ ነበር ያረፉት። ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ለአጭር ጊዜ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ልዑል መኰንን ኃይለ ሥላሴ፣ እጅግ ተወዳጁና ተመራጩ የጃንሆይ ልጅ ነበሩ። አዲስ አበባ ተወልደው ሳራ ግዛውን አግብተው፣ በዚች ምድር 32 ዓመት ብቻ ኖረው፣ በመኪና አደጋ ነበር ያረፉት። ተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት ለአጭር ጊዜ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ፣ ኅዳር 12/ 1928 ዓ/ም የተነሳ ፎቶ፤ ቦታው አልተገለፀም።
አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ፣ ኅዳር 12/ 1928 ዓ/ም የተነሳ ፎቶ፤ ቦታው አልተገለፀም።
ልዑላኑ አስፋ ወሰን እና መኰንን ከእህታቸው ልዕልት ፀሐይ ጋር ቆመው ይታያሉ። ቦታው ዊምብልደን ነው። ሰኔ 1/1928 ዓ/ም የተነሱት ፎቶ።
ልዑላኑ አስፋ ወሰን እና መኰንን ከእህታቸው ልዕልት ፀሐይ ጋር ቆመው ይታያሉ። ቦታው ዊምብልደን ነው። ሰኔ 1/1928 ዓ/ም የተነሱት ፎቶ።
የጣሊያኑ ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሣልሳዊ ከአልጋ ወረሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ጋር፣ ሮም፤በዕለት እሑድ ፣ጥር 22፣ 1924 ዓ/ም።
የጣሊያኑ ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሣልሳዊ ከአልጋ ወረሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ጋር፣ ሮም፤በዕለት እሑድ ፣ጥር 22፣ 1924 ዓ/ም።
ሊዮ ዚፌል (ከተቀመጡት 3ኛው) በጣም የሚፈሩና የሚከበሩ የትምህርት ቤቱ የዲሲፕሊን አለቃ ነበሩ።
ሊዮ ዚፌል (ከተቀመጡት 3ኛው) በጣም የሚፈሩና የሚከበሩ የትምህርት ቤቱ የዲሲፕሊን አለቃ ነበሩ።
ከካናዳዊያን ጄስዊት መምህራን አንዱ የነበሩት ክላውድ ሰምነር ተፈሪ መኮንን ካስተማሩ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጀመርያዎቹ መምህራን አንዱ ነበሩ።
ከካናዳዊያን ጄስዊት መምህራን አንዱ የነበሩት ክላውድ ሰምነር ተፈሪ መኮንን ካስተማሩ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጀመርያዎቹ መምህራን አንዱ ነበሩ።
ሉሲየን ማት እና ዜፌል ከተማሪዎቻቸው ጋር ይታያሉ። ዘመኑ አልተገለጸም።
ሉሲየን ማት እና ዜፌል ከተማሪዎቻቸው ጋር ይታያሉ። ዘመኑ አልተገለጸም።
የሥነ ሕይወት መምህር የነበሩት አራጃንድራት ራጃ ከተማሪዎቻቸው ጋር 1973 ዓ/ም
የሥነ ሕይወት መምህር የነበሩት አራጃንድራት ራጃ ከተማሪዎቻቸው ጋር 1973 ዓ/ም
በስኮላርሺፕ ውጭ የሄዱ የተፈሪ መኰንን ተማሪዎች "ኧረ ጥራኝ ዱሩ" ብለው ከፓሪስ ወደ ቡልጋ እንዲሁም ወደ ወለጋ ጫካ ገቡ። ጥቁር አንበሳን መሠረቱ።
አንዳንዶቹ ነጭ ለባሽ፤ የውስጥ አርበኛ ኾኑ። ብዙዎቹ የተፈሪ ተማሪዎች ግን አለቁ። ያ ሁሉ የተደከመባቸው፣ አገሪቱን ከድንቁርና ያወጣሉ የተባሉ ወጣቶች ጣሊያን ቀረጣጥፎ በላቸው።
ሞገስ አስገዶም እና አብረሃ ደቦጭ ተፈሪ መኰንን ነው የተማሩት። እዚያ የተማሩ ደግሞ፣ ምን እንደሚያስነኳቸው እንጃ፣ በአገር ፍቅድ የነደዱ ኾነው ነው የሚወጡት።
እነ ሞገስ አውቀው ለጣሊያን አደሩ። ዋናውን 'ሸይጣን' ለመግደል እያሴሩ ነበር፤ ግራዚያኒን።
አብረሃ ደቦጭ ጣሊያንኛ መቻሉ ከነ ግራዚያኒ ጋር አቀራረበው። እሱን ለመግደል አመቺ ጊዜ ጠበቀ። ከወዳጁ ሞገስ ጋር ተማከረ።
አብረሃና ሞገስ በእረፍት ቀን ከጣሊያን አለቆቻቸው እየተሰወሩ፣ ከአዲስ አበባ ወጣ እያሉ፣ ገለጣ ሜዳ ላይ ቦምብ አጣጣል ሁሉ ተለማመዱ።
ለወራት ያቀዱትን የካቲት 12 ተገበሩት። እነሱ የሠሩት ጀብዱ ግራዚያኒን ቢያቆስልም፣ ብዙ ጣጣ አስከተለ።
ጣሊያን ጨከነ። ቤተሰብ ከልጆቹ ጋር ቤት ውስጥ እሳት እየሞቀ ከውጭ እሳት ተለቀቀበት።
የአዲስ አበባ ወጣት በትሬንታኳትሮ አስፋልት ላይ ተጨፈለቀ። በከተማዋ ደም እንደ ቀበና ወንዝ ፈሰሰ።አንዳንድ የጣሊያን ወታደሮች ሕዝብ መግደል ደክሟቸው የፋሺስት መንግሥትን የሥራ እረፍት ጠየቁ።
ደም አስክሯቸው፣ ክንዳቸው ቃታ በመሳብ ዝሎ ነበር። 30ሺህ ሰው መጨረስ ቀላል አልነበረም።
የሚገርመው የተፈሪ ተማሪ የነበሩት ፕ/ር አስራት አባታቸው አቶ ወልደየስ አልታዬ የተገደሉት በዚሁ ቀን ነበር፤ ከዚሁ ከተፈሪ መኰንን ተማሪ ቤት በወጡት በነ አብረሃ ደቦጭ በተቆሰቆሰ እሳት።
የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳት አርበኛ ታስጠልላላችሁ ተብለው ተረሸኑ። ሁለቱ ጓደኛሞች፣ አብረሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም፣ ተሳደው ሱዳን ድንበር ሲደርሱ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሉ።
በዚህ ክፉ ዕለት ጃንሆይ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ልከው ካስተማሯቸው የመጀመርያዎቹ ውድ ተማሪዎች መሀል አያና ብሩ፣ ዮሐንስ ቦሩ፣ በሻ ወርድ ሀብተወልድ፣ ክፍሌ ነሲቡ ተገድለዋል። የሐኪም ወርቅነህ ውድ ልጆች ዮሴፍና ቤንጃሚንም አልቀሩም። ጆሴፍ አውሮፕላን አብራሪ ነበር። ጣሊያንን ለመዋጋት ነበር ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ የገባው።
ብቻ ታሪኩ እንደ የ5 ዓመቱ የስቃይ ዘመን ረዥም ነው።
ጣሊያን ሲገባ እነሱን ያፈራው ተፈሪ መኰንን ተዘጋና ብዙም ሳይቆይ ተከፈተ።
ሲከፈት ግን የቅኝ ገዢ ልጆች ብቻ መማሪያ ኾነ። ጥቁር ወደዚያ ዝር እንዳይል ተባለ። ስሙም ‘ቪክተር ኢማኑኤል' ይሉት ኾነ።
ከአምስት ዓመት በኋላ ጣሊያን ሲወጣ እንግሊዝ ገባ። እንግሊዞች ተማሪ ቤቱን ማስተዳደር ጀመሩ።
እንግሊዞች ሲወጡ ጃንሆይ ደስ አላቸው። ልዝብ ቅኝ ገዥ ኾነው አስቸግረዋቸው ነበር። ግን ወዲያው ሐሳብ ገባቸው። ተማሪ ቤቱን ማን ያስተዳድረው?
ጃንሆይ በዚያ ወቅት ቅኝ ገዢ የሚባል ጥልት አድርገው ጠልተዋል።
ገለልተኛ አገር ፈለጉ። ካናዳን ወደዱ። በቫቲካንን ሊቃነ ጳጳሳትን አነጋግረው ከካናዳ ኢየሱሳውያን መነኮሳትን (Jesuits) በአስተማሪነት አስመጡ።
''አደራችሁን፣ ሃይማኖት መስበክ ብሎ ነገር የለም። 'አባ' ተብሎ መጠራት የለም። የሃይማኖት ካባ መልበስም የለም። ልጆቼን ቀለም ብቻ አጠጡልኝ'' አሉ።
ካናዳውያኑ ጨዋ ነበሩ፤ እንደተባሉት አደረጉ። ለረዥም ዘመን ካስተማሩ በኋላ በኢትዮጵያ ፍቅር ወደቁ። አንዳንዶቹ  ኢትዮጵያ ኖረው ሞቱ።
ተወዳጁ መምህር ግን በኢትዮጵያ መቀበር እንደተመኘ ሳይሳካለት ቀረ። ማነው ይህ መምህር?
ሉሲያ ማት ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ አዲስ አበባን (የአሁኑን አአዩ) በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የመጀመርያው ነው። በፕሬዝዳንትነት 12 ዓመታት ከዘለቀ በኋላ ወደ ካናዳ ተመለሰ። በኦንታሪዮ ካናዳ ሰድቤሪ ዩኒቨርስቲ ሥራ ጀመረ። ጃንሆይ በሉሲያ ማት የኢትዮጵያ ቆይታ ደስተኛ ስለነበሩ ለዚህ የካናዳ ዩኒቨርስቲ እርዳታ እንደሰጡ ይነገራል። ሉሲያ ማት ኢትዮጵያ ሲመጣ 35 ዓመቱ ነበር።
ማርሴል ሻኽፖንቺዬ ከካናዳ ኪዩቤክ ግዛት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በ1939 ዓ/ም ነበር። ወደ አገሩ የተመለሰው በ1967 ዓ/ም ነበር። ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን አገልግሏል። በተፈሪ ተማሪ ቤት የዕደ ጥበብ ዎርክሾፕ የጀመረው እርሱ ነው።
ከካናዳ ኩቤክ ግዛት የመጣው ሉሲያ ማት በአስተዳደር ችሎታው ከተፈሪ መኰንን አልፎ የመጀመርያውን ዩኒቨርቲ ኮሌጅ በመመሥረቱ የኢትዮጵያ ባለውለታ ኾኖ ይዘከራል።
ክላውድ ሰምነር የሞንትሪያል ሰው ነበር። ፍልስፍናና ሥነ ጽሑፍ ነው ያጠናው። በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ (የአሁን አአዩ) ፍልስፍናን ለማስተማር ምናልባትም ቀዳሚው ሰው ነበር። በግዕዝና በአማርኛ የተጻፉ የፍልስፍና ጽሑፎችን ለዓለም አስተዋውቋል።
ሉሲየን ማት ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ አዲስ አበባ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ የኾነውን) ያደራጀ ካናዳዊ ባለውለታ ነው። እውቅ የተፈሪ መኰንን ዳይሬክተር ነበር።
ሉሲየን ማት ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ አዲስ አበባ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ የኾነውን) ያደራጀ ካናዳዊ ባለውለታ ነው። እውቅ የተፈሪ መኰንን ዳይሬክተር ነበር።
በግራ በኩል ብዙ የቀድሞ ተማሪዎች የሚያስታውሱት ረዳት ዳይሬክተሩ ጌራርድ ጋኞን ከማርሴል ጋሪዮ ጋር ይታያል። ዓ/ም አልተጠቀሰም።
በግራ በኩል ብዙ የቀድሞ ተማሪዎች የሚያስታውሱት ረዳት ዳይሬክተሩ ጌራርድ ጋኞን ከማርሴል ጋሪዮ ጋር ይታያል። ዓ/ም አልተጠቀሰም።
"ጃንሆይ እኛን ከጎበኙ በኋላ ከሉሲዬ ማት ጋር 'ፍስስ' በሚል ፈረንሳይኛ ሲያወሩ ትዝ ይለኛል። "ሲሉ የሐርቫርዱ ምሩቅ ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ለልጃቸው ዶ/ር ፈላስፋ ሙሉጌታ ተርከውለታል።
"ጃንሆይ እኛን ከጎበኙ በኋላ ከሉሲዬ ማት ጋር 'ፍስስ' በሚል ፈረንሳይኛ ሲያወሩ ትዝ ይለኛል። "ሲሉ የሐርቫርዱ ምሩቅ ዶ/ር ሙሉጌታ ወዳጆ ለልጃቸው ዶ/ር ፈላስፋ ሙሉጌታ ተርከውለታል።
ከዚህ ተማሪ ቤት የወጡ ብዙዎቹ በተለያየ ጊዜ በሰጡት ቃለ መጠይቅ በሕይወታቸው እጅግ ሥነ ሥርዓት አክባሪ እና ሥራ ወዳድ ያደረጋቸው በተፈሪ የነበረው ጥብቅ ግብረ ገብነት እንደሆነ ሲናገሩ ይሰማል።
እውነተቸውን ነው። ይህ ትምህርት ቤት ጥብቅ ደንቦች ነበሩት። ሰዓት አለማክበር 'የጦር ወንጀል' ነበር። መኝታ ክፍል አያያዝ፣ የግል ንጽህና አጠባበቅ ላይ ቀልድ አልነበረም።
አበራ የማነ አብ የተባሉ የቀድሞ ተማሪ ይህን ምስክርነታቸውን በጻፉት መጽሐፍ ገልጠዋል።
ለምሳሌ በየሳምንቱ የቆሸሸ ልብስ ተወስዶ ታጥቦ እና ተተኩሶ በተማሪዎች አልጋ ላይ ይቀመጣል።
ዐርብ በ5 ሰዓት ሙስሊሞች ትምህርት አቁመው መስጊድ ይሄዳሉ።
ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እሑድ ጠዋት የቅዳሴ እና የፀሎት ሥርዓት እስኪጠናቀቅ ለክርስቲያኖች ቁርስ አይቀርብም።
አበራ የማነ አብ "ለውጥ ናፋቂው ሕይወቴ" በተሰኘ መጽሐፋቸው፣ ገጽ-14 ላይ ደግሞ፣ አንድ አስገራሚ ትዝታ ስለ ተፈሪ ተማሪ ቤት አጋርተዋል።
ንጉሡ ለዚህ ትምህርት ቤት የነበራቸውን ቦታ የሚያሳይ ነው።
" ...በዐቢይ ጾም ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ ትምህርት ቤቱን ይጎበኛሉ። በራት ሰዓት ምግብ ቤት ገብተው የምንመገበውን እየቀመሱ ያያሉ። ብዙ ጊዜ ምሳና ራት ላይ የሚቀርበው ፋጆሊ ሾርባ፣ ሚኒስትሮኒ ምናምን ነው። አንድ ቀን ሾርባው ውስጥ ትል ተገኘና ትምህርት አቆምን። ከሁለት ነው ከሦስት ቀን በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድንገት መጥተው አዳራሽ ውስጥ ሰበሰቡንና ባደረጉት ንግግር 'የሠራችሁት ሥራ በነጭ ሸማ ላይ ጥቁር ቀለም እንደማፍሰስ ነው፤ አሁኑኑ ትምህርታችሁን ጀምሩ' ብለው ገሰጹን። እኛም ጉዳዩ ንጉሠ ነገሥቱ ጋር በመድረሱ ተደናግጠን በማግሥቱ ትምህርት ቀጠልን። ''
''...ወደ ኋላ መለስ ብዬ ያኔ የሆነውን ባሰብኩ ቁጥር፣ ንጉሠ ነገሥቱ ሥራዬ ብለው አድመን ትምህርት ያቆምነውን የአንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለመምከርና ለመገሰጽ መምጣታቸው ሁሌም ይደንቀኛል። "
በ60ዎቹ ከተመረቁት መሀል አቶ ኤርሚያስ አማረ ይገኙበታል። ''የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ትዝታ'' የሚል መጽሐፍ ጽፈዋል።
በዚህ መጽሐፍ ዙርያ ከቀድሞው አሜሪካዊ መምህራቸው ዳግ ኤዲ ጋር በአንድ ቆየት ያለ የሚስተር ዳግ ፖድካስት ላይ ሲጨዋወቱ  አስቂኝ ትዝታ አጋርተዋል። አጠር ተደርጎ ሲተረክ ይህን ይመስላል።
"በዘመኑ ከተፈሪ መመረቅ ኮሌጅ የመበጠስ ያህል ከባድ ነበር። 42 ብቻ ነበርን። ሁላችንም አለፍን። ደስታችንን በተለየ ማክበር ፈለግን። ለምን የተማሪ ፓርቲ አናሰናዳም ተባለ። እንዲህ ዓይነት ጉድ ተሰምቶ አይታወቅም፥ ከዚያ በፊት። አንዳንዶቻችን ሴቶች በፓርቲው እንዲገኙልን በጥብቅ ፈለግን።
ዳይሬክተራችንን ሚስተር ጋኞን 'እባክህን ፍቀድልን' አልነው። 'ይኼ ምን ችግር አለው? አሪፍ ሐሳብ ነው!' አለን።
'ግን እኮ እንግሊዝኛ ሙዚቃ እና ሴቶች በፓርቲው እንዲገኙ እንፈልጋለን' አልነው። 'ምን!' ብሎ ተቆጣ።
በቃ ከትምህርት ቤቱ ውጭ አንድ ክለብ ተከራይተን ፓርቲውን በምሥጢር እናዘጋጅ ተባለ።
ከእቴጌ መነን ሴት ተማሪዎችን ጋበዝን። ደግነቱ የመነን ሴቶች ስለተፈሪ መኰንን ተማሪዎች ጥሩ አመለካከት ስለነበራቸው በርከት ብለው፣ ዝንጥ ብለው መጡ።
ምን ዋጋ አለው! ብዙዎቻችን ከሴቶች ጋር ቅርርብ አናውቅም። በአንድ ክለብ ለመቀመጥ ነፍሳችን ተጨነቀች። ማን ተነስቶ ይደነስ?
ፓርቲው እንደጠበቅነው አልሆን አለን። [ለቅሶ ቤት መሰለ]። እጆቻችንን አጣምረን መፋጠጥ ሆነ።
ድንገት ሦስት ወይም አራት ደፋር ተማሪዎች ከመሀላችን እምር ብለው ተነሱ። ሴት ሊያስደንሱ። ክው አልን። እንደተፈራው ከሴት ጋር ደነሱ።
እየቀናንባቸውም፤ እያሳፈረንም ፓርቲው አለቀ። ይህን አልረሳውም።
ምናልባት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው 'ዴይ ፓርቲ' ይህ ሳይሆን አይቀርም።"
ተፈሪ መኰንን ወደ 2ኛ ደረጃነት ያደገው በ1948 አካባቢ ነበር። ከዚያ ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አሁን ኮተቤ) እና ጄኔራል ዊንጌት ተከፍተዋል። ተፈሪ መኰንን 3ኛው መኾኑ ነው።
ተፈሪ መኰንን ወደ 2ኛ ደረጃነት ያደገው በ1948 አካባቢ ነበር። ከዚያ ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አሁን ኮተቤ) እና ጄኔራል ዊንጌት ተከፍተዋል። ተፈሪ መኰንን 3ኛው መኾኑ ነው።
''አደራ ኢትዮጵያ ቅበሩኝ" ይሉ ከነበሩት የድሮ ካናዳዊ መምህራን መካከል ሚስተር ጋኞ ይገኝበታል።
የቀድሞ ተማሪዎች ሁሉ መቼም የማይረሱት ዝነኛው ሚስተር ጋኞ ለረዥም ጊዜ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ነበር። ድንገት ታመመና ለሕክምና ኬንያ ተወሰደ። በሳምንቱ ሞተ።
በጄስዊቶች ሕግ አንድ 'አባት' አስክሬኑ ወደተናዘዘበት አገር የሚመለሰው በሞተበት አገር ጄስዊቶች ከሌሉ ብቻ ነው።
ለክፋቱ ኬንያ ጄስዊቶች አሉ። ጋኞ ኑዛዜው አልተፈጸመም። እዚህ ኬንያ ተቀበረ።
የሚስተር ጋኞ ወዳጅ በዚህ ባልደረባቸው ወጥቶ መቅረትና ኬንያ መቀበር ተንገበገበ። ''ጋⶉ ሕይወቱን ሙሉ ኢትዮጵያ ኖሮ እንዴት በኬንያ ይቀረበራል?'' ሲል አዘነ።
ይህ ሰው ሮናልድ ጄ ቱሬን (R. J Turenne) ይባላል። አደገኛ የጂኦግራፊ አስተማሪ ነበር።
ታላቁን የጂኦግራፊ ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያምን እጃቸውን ይዞ፣ ማስመሪያ ሰጥቶ ያስተማረ እሱ ነው።
ይህ ሰው 60 ዓመት በኢትዮጵያ ኖረ። ከዕለታት አንድ ቀን ዕድሜውን ሲቆጥር 99 ዓመት ሞልቶታል።
ከዚያ በፊት ግን ከአገሬ ኢትዯጵያ ወዴትም ንቅንቅ አልልም ብሎ አምርሯል።
የኾነ ቀን ግን በጣም ታመመ። ለተሻለ ሕክምና ኬንያ ሂድ ሲባል የጓደኛው የሚስተር ጋኞ ዕጣ ፈንታ ትዝ ብሎት አሻፈረኝ አለ።
በስንትና ስንት ጉትጎታ ለሕክምና ወደ እናት አገሩ ካናዳ ተወሰደ። እሱ እንኳ እናት አገሬ የሚላት ኢትዮጵያን ነበር።
ብቻ ታሪኩ ረዥም ነው። በመጨረሻ በካናዳ 'መቄዶንያ' ገባ። የአረጋዊያን እንክብካቤ ማዕከል እንደማለት። የድሮ ተማሪዎቹ በየዓመቱ እየሄዱ ይጠይቁት ነበር። ምክንያቱም ይወዱታላ።
ከ2 ዓመት በፊት ሊጠይቁት ሲሄዱ 99 ዓመት አልፎታል። መቶ ሊደፍን 4 ወር ገደማ ብቻ ነበር የቀረው።
''ጋሽ ቱሬን፤ ልደትህን ከተፈሪ መኰንን 100 ዓመት ጋር እናከብርልሃለን" አሉት፣ የቀድሞ የተፈሪ  ተማሪዎች ኅብረት የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ብሥራትና ጓደኞቹ።
ቱሬ ግን በሚንቀጠቀጥ ድምጽ "አይመስለኝም፤ እኔ ቀድሜ እሞታለሁ" አላቸው።
Your browser does not support this video
የፕ/ር መስፍን የቀለም አባት የነበሩት የሚስተር ቱሬ የመጨረሻ ቃል
የፕ/ር መስፍን የቀለም አባት የነበሩት የሚስተር ቱሬ የመጨረሻ ቃል
ድሮ የተፈሪ ተማሪዎች 11ኛ ክፍል ሲጨርሱ አሜሪካ ይላኩ ነበር - ተወዳድረው።
12ኛ ክፍልን ብቻ እዚያ ተምረው እንዲመለሱ ነው - ሐሳቡ። ልምድ አንዲኾናቸው።
በፎተው ላይ በውብ ፈገግታ ዋንጫ ይዞ የሚታየው የያኔው ወጣት - የነብር ጣት፣ ብሥራት አክሊሉ፣ ሜኔሶታ ግዛት ተላከ። አንድ ከከተማ ወጣ ያለ ቦታ የሚገኝ የሃብታሞች ትምህርት ቤት ተመደበ።
የተቀበሉት አሜሪካውያን ቤተሰቦች ግን ፈሩ። በተለይ የቤቱ አባወራ ፈረንጅ ሐኪም ናቸው።
"This kid from Africa . . . I don't know what to do with him'' ብለው ተጨነቁ።
''አሁን እንዴት ኾኖ ነው እሳት ከላሱ አሜሪካውያን ልጆች ጋር እኩል የሚማረው?'' ብለው ሐሳብ ገብቷቸዋል።
"አንተ ልጅ፣ ፈራሁ እኮ። 12ኛ ክፍል ይከብድህ ይኾን? ትምህርቱን ትችለዋለህ? አሜሪካ እኮ እንደ አፍሪካ አይደለም። እንዲያው ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ሄደን ከአስተማሪዎቹ ጋር ብንማከር?'' ብለው ወሰዱት።
ፈረንጅ መምህራን ጥቁሩን ብሥራትን በጥያቄ አጣደፉት።
''ለመሆኑ ሒሳብ ታውቃለህ? የፊዚክስ ሕግስ ተምረሃል? ለመሆኑ ጂኦግራፊ ታውቃለህ? ታሪክስ? ያንን ታውቃለህ? ይህንንስ?'' እያሉ አስጨነቁት።
የያኔው ብሥራት ገርሞት ያያቸዋል። እየቀለዱ ነው ወይስ የምራቸውን?
"ውይ ይሄንን እኮ እኛ 9ኛ ክፍል ተምረነዋል፤ ያንን እኮ እኛ ድሮ ነው የተማርነው" ሲል መለሰ።
ፈረንጅ አስተማሪዎች ባያምኑትም ትምህርቱ ተጀመረ። በዚህ ሜኔታንንታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመግባት ብሥራት የመጀመሪያው ጥቁር ነበር።
የሁሉም ጭንቀት 'ይሄ አፍሪካዊ ትምህርቱን እንዴት ሊወጣው ነው?' የሚል ነበር።
የክፍሉ 1ኛ ሆኖ ጨረሰ። ለዚያውም በማዕረግ። ፈረንጆቹ አሁንም አልተዋጠላቸውም።
"Did you go to a private school?"
ብቻ ታሪኩ ረዥም ነው። ለማሳጠር ወደፊት እንስፈንጠር።
ብሥራት፣ ከዚያ በኋላ ተምሮ ተምሮ፣ በኢኮኖሚክስ ዶክትሬቱን ሠርቶ፣ ቦስተን ዩኒቨርስቲ በፕሮፌሰርነት ተቀጥሮ፣ ለዓመታት ፈረንጅ ፊደል አስቆጥሮ፣ 32 ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርቶ፣ አሁን ደግሞ ለዚህ ወግ ማዕረግ ያበቃውን ተማሪ ቤት ውለታ እየመለሰ ነው።
አሁን ዶ/ር ብሥራት የቀድሞ የተፈሪ መኰንን ተማሪዎች ኅብረት ሊቀመንበር ናቸው።
"ያኔ አሜሪካ ከላኩኝ በኋላ የገባኝ ነገር፣ በተፈሪ መኰንን በጣም የላቀ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ይሰጥ እንደነበረ ነው።"
ተፈሪ የሚለውን የትምህርት ቤቱን ስም ደርግ መጣና "እንጦጦ" ብሎ ቀየረው።
በዓለም የተዘሩት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ከፋቸው። በስሙ መቀየር ትዝታቸው ደበዘዘባቸው።
ግንባር ፈጠሩ፣ ትግል ጀመሩ። ሰላማዊ ትግል፤ ስም የማስመለስ ትግል።
ይህን መራራ ትግል በፊታውራሪነት ከመሩት ውስጥ ዶ/ር ብሥራት አንዱ ናቸው። ለቢቢሲ ያጋሩትን ታሪክ ጨምቀን ስናቀርበው ይህን ይመስላል።
ኢህአዴግ ሲገባ ተፈሪ የሚለው ስም ሊመለስ የሚችልበት ዕድል ተፈጠረ።
ነገር ግን ዋናውን ሰው መለስ ዜናዊን ማን ያግኝ?
ብዙውን ጊዜ ለተፈሪ ተማሪዎች ባለሥልጣን ማግኘት ከባድ አይደለም። ለምን? በየሄዱበት ቢሮ የቀድሞ ተማሪዎች አይጠፉማ። መለስ ደግሞ ተፈሪ አልተማረም። ዊንጌት ነው የተማረው።
በስንት መከራ አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሐንስ ተገኙ። ለካንስ እሳቸውም የተፈሪ ተማሪ ነበሩ።
አፈ ጉባኤ ዳዊት እና መለስ ዜናዊ ደግሞ ከባድ ወዳጅ ነበሩ። ዳዊት ለመለስ ነገሩን ነገሩት። ''እንጦጦ የሚለው ስም ወደ ተፈሪ ይመለስ፤ ፍቀድልን?'' አሉት።
"ይሄ ምን ችግር አለው ታዲያ? መቀለ ያለው ትምህርት ቤት ዐፄ ዮሐንስ እኮ ነው የሚባለው፤ ሕጉን ተከትሎ ስሙ መቀየር ይችላል" አለ።
ሂደቱ ግን መለስ ዜናዊ እንዳቀለለው ቀላል አልሆነም።
"ብቻ ምን አለፋህ ስሙን ለማስመለስ፣ 6 ከንቲባዎችና 25 ዓመታት ፈጅቶብናል" ይላሉ ዶክተር ብሥራት።
"ስድስቱም ከንቲባዎች ታዲያ አንዳቸውም 'አይኾንም!' ብለውን አያውቁም።"
ዶ/ር ብሥራት የሚመሩት ማኅበር ጠንካራ ነው። በካሊፎርኒያ፣ በዋሺንግተን፣ በኒውዮርክ፣ በቴክሳስ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ በድምሩ 12 ቻፕተሮች አሉት።
የቀድሞ ተማሪዎች እኮ አሁን 250 ሺህ አልፈዋል። እንጦጦ የሚለውን የሚወድ ግን የለም። የተራራ እንጂ የትምህርት ቤት ስም አይደለም። ትዝታ ያደበዝዛል።
ብቻ ስም የማስመለሱ ትግል ለዓመታት ቀጠለ። በመጨረሻ ትግሉ ፍሬ አፈራ። ከወራት በፊት እንጦጦ ቴክኒክና ሞያ ወደ 'ተፈሪ መኰንን' ተመለሰ።
"ይህ እንዲሳካ ደበበ እሸቱን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ረድተውናል። የአዲስ አበባ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከንቲባ አዳነች አበቤ ሊመሰገኑ ይገባል" ይላሉ፣ ዶ/ር ብሥራት።
ትምህርት ቤቱን በአንድ ዓመት የሚበልጡት  የዕድሜ ባለጸጋው ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረወልድ ከሌሎች የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጋር በቀኝ በኩል ቆመው ይታያሉ። እሳቸውም ድሮ ተፈሪ ነው የተማሩት ፤ በቤይሩት የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ አስተዳደርና ፖለቲካ ሳይንስ ተመርቀዋል። የቀድሞዋ ርዕሰ ብሔር ክብርት ሳሕለወርቅ፣ ተፈሪ ባይማሩም አባታቸው እዚያ ተምረዋል።
ትምህርት ቤቱን በአንድ ዓመት የሚበልጡት  የዕድሜ ባለጸጋው ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረወልድ ከሌሎች የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጋር በቀኝ በኩል ቆመው ይታያሉ። እሳቸውም ድሮ ተፈሪ ነው የተማሩት ፤ በቤይሩት የአሜሪካ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ አስተዳደርና ፖለቲካ ሳይንስ ተመርቀዋል። የቀድሞዋ ርዕሰ ብሔር ክብርት ሳሕለወርቅ፣ ተፈሪ ባይማሩም አባታቸው እዚያ ተምረዋል።
የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር 100 ዓመት ለደፈነው የቀድሞ ትምህርት ቤታቸው ሕንጻ ሠርተው ሊያስረክቡ ተፍ ተፍ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
ደግነቱ የሚደግፋቸው ብዙ ነው። በየሄዱበት ተፈሪ የተማረ አያጡም።
ለምሳሌ የሚያስገነቡትን ሁለገብ ሕንጻ ዲዛይን ማሠራት ሲፈልጉ የደረሰላቸው ጎምቱው ነዳፊ ፋሲል ጊዮርጊስ ነው። እሱ ራሱ የተፈሪ ፍሬ ነው።
ገነዘብ ሲፈልጉም እንዲሁ የድሮ የተፈሪ ተማሪ ፈለጉ። አለመታደል ሆኖ ተፈሪ ብዙ ነጋዴ አላፈራም። ቢሊየነሩ ብዙአየሁ ተገኙ። እሳቸው ብዙ ረዷቸው።
ነገር ግን 60 ሚሊዮን ነው የሚፈልጉት። ተጨማሪ ገንዘብ ከየት ይምጣ?
መቼስ ቴሌቶን ያለ ሼክ አላሙዲ ተሳትፎ ግቡን አይመታምና ይጠየቁ ተባለ። ችግሩ እሳቸው ተፈሪ አልተማሩም።
ከሚወዷቸው ሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ ግን ተፈሪ ተምረዋል። የደርባ ሥራ አስፈጻሚ ኃይሌ አሰግዴ።
እነ ዶ/ር ብሥራት ደብዳቤ አረቀቁ፤ ደብዳቤው ወደ ሳዑዲ ተላከ። ቢጠበቅ ቢጠበቅ ምላሽ የለም።
ኮሚቴው ኃይሌ አሰግዴ ጋር ደወለ። "ሼኹ ዝም አሉን እኮ ምን ይሻላል?"
ከዕለታት አንድ ቀን ሼኽ መሐመድ ወደ ኃይሌ ደወሉና "እንዴት ያሉ አገር ወዳድ ናቸው ባክህ! ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ድሮ የተማሩበትን ትምህርት ቤት አስታውሰው…ማሻላህ!'' አሉ።
"በል አንድ 5 ሚሊዮን ስጣቸው- ባክህ! ኢትዮጵያን የሚወድ 'ወዳለሁ። "
"እሺ እሺ፤ በነገርዎ ላይ እኔም እዚያ ነው እኮ የተማርኩት?"
"እውነትህ ነው? ለምን አልነገርከኝም ታዲያ? በል ሌላ 5 ሚሊዮን ጨምርበት።"  ምናባዊው የስልክ ንግግራቸው ይህን ይመስላል።
እነ ዶክተር ብሥራት አንድ ሁለገብ ሕንጻና የግቢውን ዋና በር ውብ አድርገው ለማሠራት ወጥነዋል። በሩ ላይ የሚጻፈው ነገር በጭራሽ አላከራከረም።
ድሮ ጃንሆይ ትምህርት ቤት መጥተው የመከሯቸው ምክር ለሁሉም ተማሪዎች የኑዛዜ ቃል ማለት ነው። እስከዛሬ ከልባቸው አልወጣም።
እሱ ራሱ ጥቅስ ነው በሩ ላይ የሚጻፈው። መልእክቱ ጥልቅ ነው።
"ይህችንም የዕውቀት ምግብ ሰጥታ የምታሳድጋችሁን ተማሪ ቤት፣ (ወደፊት) በጥበብ አድጋችሁ፣ በአእምሮ በምትጐለምሱበት ጊዜ እግዚአብሔር እንደየዕድላችሁ በሚሰጣችሁ ዕውቀት፣ (ትምህርት ቤቷ) የሀገራችን መሣሪያ ናትና እንዳትጠብ እንድትሰፋ፣ እንዳትወድቅ እንድትበረታ እንድትረዷት እለምናችኋለሁ።"
የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር አባላት 100ኛ ዓመት ባከበሩበት ወቅት፤ የቀድሞ ተማሪ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረወልድ በ101 ዓመታቸው መሀል ላይ ይታያሉ።
የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር አባላት 100ኛ ዓመት ባከበሩበት ወቅት፤ የቀድሞ ተማሪ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረወልድ በ101 ዓመታቸው መሀል ላይ ይታያሉ።
ተጨማሪ ምሥሎችና ግብዓቶች፡ ጌቲ ኢሜጅስ፣ ኤዲ ዳግ (አሜሪካዊ የቀድሞ የተፈሪ መኰንን መምህር ፖድካስት)፣ ተፈሪ መኰንን አሉሙናይ፣ ዶ/ር ፈላስፋ ሙሉጌታ ድረ-ገጽ፣ የካናዳ ጄስዊቶች ማኅበር ድረ ገጽ፣ ፕሮፌሰር ፒተር ጋሬትሰን
ምስጋና፡ ወ/ሮ ቆንጂት ተድላ፣ ስለሺ ይልማ ረታ፣ ሚስተር ቻ፣ ዮሐንስ ገብረተክሌ
የዶናልድ ትራምፕ ሁነኛ ሰው፣ ወግ አጥባቂ ተሟጋች እንዲሁም የሚዲያ ሰው የሆነው አሜሪካዊው ቻርሊ ከርክ ረቡዕ ዕለት በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።
የ31 ዓመቱ ወጣት በአሜሪካ ኮሌጅ ውስጥ ባዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ዒላማ ተደርጎ በተተኮሰበት ጥይት መገደሉን ፖሊስ ገልጿል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም በወጣቱ አክቲቪስት የተሰማቸውን ድንጋጤ ገልፀዋል።
በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ "ታላቁ እናም ተዓምረኛው፣ ቻርሊ ከርክ ሞቷል። በአሜሪካ ከቻርሊ በስተቀር የወጣቶችን ልብ በተሻለ የሚረዳ የለም" ብለዋል።
የሊብራል መንፈስ ባረበበባቸው የአሜሪካ ኮሌጆች የኮንሰርቫቲቭ ሃሳቦችን ለማስፋፋት በማሰብ ተርኒንግ ፖይንት (Turning Point) የተሰኘውን ተቋም የጀመረው በ18 ዓመቱ ነው።
ረቡዕ ዕለት በዩታ ቫሊ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅቶት በነበረው መርሃ ግብር ላይ በጥይት ተመትቶ ሲገደል በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመሳሳይ ዝግጀቶችን አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፣ ተማሪዎች በመረሃ ግብሩ ላይ በመገኘት በተመሳሳይ ሀሳቦች ከእርሱ ጋር አንዲወያዩ እና እንዲከራከሩ የተመቻቸ ነበር።
የእሱ ማኅበራዊ ሚዲያ እና ታዋቂው ዕለታዊ ፖድካስት እንደ የልውጥ ፆታ ማንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ እምነት እና የቤተሰብ ዕሴቶች ባሉ ጉዳዮች ላይ ከተማሪዎች ጋር ሲከራከሩ የሚያሳይ ቪዲዮዎች ተቆርጠው ይጋሩበታል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የትራምፕ ቪዲዮም በከርክ ፖድካስት መጀመሪያ ላይ ይታያል።
"ቻርሊን ማመስገን እፈልጋለሁ፤ እሱ ምርጥ ሰው ነው፣ መንፈሱ፣ ለአገሩ ያለው ፍቅር፣ እስካሁን ከተመሠረቱት የወጣቶች ድርጅቶች ሁሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ አቅም ያለው የእርሱ ተቋም አስደናቂ ሥራ ሠርቷል።"
ከርክ መንግሥታዊ ያልሆነውን ድርጅት የመሠረተው ባራክ ኦባማ በአውሮፓውያኑ 2012 ዳግም ከተመረጡ በኋላ ነው።
የተቋሙ ተልዕኮ ወጣቶች ላይ ሲሆን፣ ተማሪዎችን በማደራጀት "ኃላፊነት የተሞላበት ወጪን፣ የነጻ ገበያ እና አነስተኛ መንግሥትን" ያስተዋውቃል።
ባለፈው ዓመት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች ሪፐብሊካኖች ሲመረጡ ወጣቶች ወጥተው ድምጻቸውን እንዲሰጡ በመቀስቀስ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል።
ወጣቱ ቻርሊ ከርክ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ አዲስ መራጭ ወጣቶች ወጥተው እንዲመዘገቡ በማድረግ እና በአሪዞና ግዛት ትራምፕ አሸናፊነትን እንዲያገኙ ከፍተኛ ወሳኝ ሥራዎችን በመሥራቱ ስሙ በበጎ ይናሳል።
የከርክ እና የዶናልድ ትራምፕ ወዳጅነት እየጠነከረ የመጣው አሸንፈው ዋይት ሐውስ ከገቡ በኋላ ነው። ከርክ የትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ የተገኘ ሲሆን፣ የዋይት ሐውስም ቤተኛ ሆኗል።
በጥር ወር ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ልጅ ትራምፕ ጁኒየር ጋር በመሆን ትራምፕ በአርክቲክ አካባቢ የምትገኘው እና የአሜሪካ ግዛት መሆን አለባት ሲሉ ወደ ተናገሯት ግሪንላንድ ተጉዟል።
ከቱጃር ቤተሰቦች የተገኘው ከርክ የተማረው በቺካጎ አቅራቢያ በሚገኝ የማኅበረሰብ ኮሌጅ ውስጥ ነው።
ቢሆንም ትምህርቱን የፖለቲካ አክቲቪዝም ላይ ለማሳለፍ በመፈለጉ አቋርጦ ወጥቷል።
በጣም ታዋቂ ለሆነው ዌስት ፖይንት ለተባለው የአሜሪካ ወታደራዊ አካዳሚ አመልክቶ የነበረው ከርክ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ከተማሪዎች ጋር እንደ ድኅረ ዘመናዊነት (ፖስት ሞደርኒዝም) ያሉ ሃሳቦችን አንስቶ በሚከራከርበትም ወቅት ኮሌጅ ገብቶ አለመመረቁን በማንሳት ይቀልዳል።
በመላው አሜሪካ በመዟዟር ሪፐብሊካኖች በሚያዘጋጇቸው መድረኮች ላይ ንግግር የሚያደርገው ከርክ ከበርካታ ታዋቂ ሪፐብሊካን ጋር በሚያዘጋጇቸው ግብዣዎች ላይ ይጋበዛል።
ወግ አጥባቂ የሆነው የሬዲዮ ፕሮግራሙም በማኅበራዊ መድረክ ላይ ሚሊዮኖች ይከተሉታል።
ከርክ በ2020 እና በዚህ ባለንበት 2025 የኦክስፎርድ ኅብረት ላይ ተገኝቶ ንግግር ያደረገ ሲሆን፣ ዘ ማጋ ዶክትሪን (The Maga Doctrine) የተሰኘ በሚሊዮን ቅጂዎች የተሸጠ መጽሐፍ ደራሲም ነው።
የሁለት ልጆች አባት የሆነው ከርክ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከፊት በመሆን ይታወቃል።
በፖድካስቶቹ ላይ ከሚያነሳቸው ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ባሻገር ስለ ጦር መሣሪያ ቁጥጥር ይወያያል።
ከጥቂት ወራት በፊት ከርክ "እንዳለመታደል ሆኖ ሕገ መንግሥቱ የሰጠንን መብት ለመጠበቅ በየዓመቱ የተወሰኑ ሰዎችን በጦር መሳሪያ ግድያ መገበራችን ነው" ብሎ ነበር።
ከርክ ፆታ ልውጥ ለሆኑ ሰዎች ባለው የመረረ ተቃውሞ በኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ ላይ በነበረው ጥርጣሬ፣ እንዲሁም በ2020 ትራምፕ በምርጫ ተጭበርብረዋል በሚሉት አቋሞቹ ይታወቃል።
በተተኮሰበት ጥይት ከተገደለ በኋላ ግን ከርክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በነጻነት መወያየትን ያስቀድም ነበር የሚሉ ድምጾች ተሰምተዋል።
ዊሊያም ዎልፍ የባብቲስት ሊደርሺፕ ማዕከል ዳይሬክተር "አጠቃላይ ሥራው የተመሠረተው በተከፋፈሉ ቡድኖች መካከል ያሉ ጉዳዮችን ለመፍታት ንግግርን በመስበክ ነው። ጠብን አይደግፍም ነበር" ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ዝናባማው የክረምት ወቅት አብቅቶ፣ ቅዝቃዜው እየተገፈፈ፣ ብርሃን መታየት ሲጀምር፣ ምድር በልምላሜ እና በአደይ አበባ ስትፈካ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመታቸውን አንድ ብለው ይጀምራሉ።
አሮጌው ዓመት አብቅቶ በአዲስ መተካቱን በሚያበስረው በአደይ አበባ ምድር ትዋባለች።
የክረምቱን ማብቃት እና የአዲስ ዘመን መግባትን የምታበስረው የመስቀል ወፍም በአዲስ ላባዋ ደምቃ ብቅ ትላለች።
ኢትዮጵያውያን ከሌላው ዓለም ሕዝቦች ልዩ የሚያደርጋቸውን 13 ወራት አጠናቅቀው መስከረም አንድ ላይ አዲስ ዓመታቸውን ያከብራሉ።
አዲሱን ዓመትም በልጃረዶች የአበባዮሽ ጭፈራ፣ በወንድ ታዳጊዎች የመልካም ምኞት መግለጫ ሥዕል ማጀብ የተለመደ ነው።
ከዚህ ባሻገርም እንደ ቤተሰቡ አቅም ዶሮ ወይንም በግ ማረድ፣ ጠላ መጥመቅ፣ ድፎ ዳቦ መቁረስ የዕለቱ ማድመቂያዎች ናቸው።
ቤትን በተለያየ ነገር ማሰዋብ ቄጤማ ከአደይ አበባ ጋር አድርጎ ጎዝጉዞ አዲሱን ዓመት መቀበል የበርካታ ኢትዮጵያውያን ልማድ ነው።
ምሽት ላይም ችቦ ለኩሶ "እሰይ መስከረም ጠባ" እያሉ እየዘመሩ አዲስ ዓመትን መቀበል የባሕሉ አካል ነው።
ከምድር ልምላሜ እና የአደይ አበባ ፍካት ጋር ተደማምሮ የሚከበረው አዲስ ዓመት እንደ የአካባቢው እንደየ ባህሉ የተለያየ የአከባበር መልክ ሊኖረው ይችላል።
በተለያዩ አካባቢዎች የአዲስ ዓመት መቃረብን የሚያመለክቱ የተለያዩ ክብረ በዓሎች አሏቸው።
ወንዶች ሆያ ሆዬን በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ በመጨፈር ክረምቱ እያበቃ መምጣቱን ያበስራሉ። 'ዶሮ ከጮኸ የለም ለሊት ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት' ሲሉም በተረት ያጅቡታል።
በትግራይ አሸንዳ፣ በሰቆጣ አካበቢ ሻደይ፣ በላሊበላ ደግሞ አሸንድዬ፣ እንዲሁም በቆቦ አካባቢ ሶለል በመባል የሚታወቁትም በዓላት የአዲስ ዓመት መምጣትን መጠቆሚያ ናቸው።
ከዚህ በኋላ ይኸው የልጃገረዶች ጭፈራ በአበባዮሽ በሚል የልጃገረዶች ጭፈራ ይተካል።
አበባዮሽ ልጃገረዶች በየሠፈራቸው በቡድን በቡድን ተከፋፍለው ቤት ለቤት እየዞሩ በጭፈራ ሰውን እያወደሱ ገንዘብ በመሰብሰብ የሚቦርቁበት ባህል ነው።
ለቀሪው ማኅበረሰብ ደግሞ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ፣ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ዜማ ነው።
ኢትዮጵያዊያን የአዲስ ዓመት ጅማሯቸውን ተሰባስበው፣ በደስታ እና በፍቅር "እንኳን አደረሰህ፣ አደረሰሽ"፤ "መልካም አዲስ ዓመት" እየተባባሉ ከፊታቸው ያሉት 13 ወራት በጎ እንዲሆኑ እርስ በእርሳቸው መልካም ምኞታቸውን ይገላለጻሉ።
ሌሎች አገራትስ አዲስ ዓመታቸውን እንዴት ያከብሩታል?
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው።
በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው።
ኢራን በዓለም ላይ የራሳቸው የቀን አቆጣጠር ሥርዓት ካላት አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፣ አዲስ ዓመቷንም ከሌሎች የዓለም አገራት በተለየ መልኩ የምታከብር ናት።
ኢራን ፀሐይን ወይም የሂጅራ ዘመን አቆጣጠርን መሠረት ያደረገ ሥርዓት ሲኖራት፣ አዲስ ዓመትን ሁሌ መጋቢት ወር ላይ ታከብራለች።
ቻይናም አንዲሁ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጣር ያላት ሲሆን ሉናር የተሰኘ ዘመን አቆጣጠር ሥርዓትን ትከተላለች።
የቻይና አዲስ ዓመት የሚከበርበት ወር በየአራት ዓመቱ የሚቀያየር ቢሆንም አዲስ ዓመቱ የካቲት ወር ላይ ይከበራል።
የካቲት ላይ አዲስ ዓመቷን የምታከብረው ሌላኛዋ አገር ሰሜን ኮሪያ ናት። ይህች ከምዕራባውያኑ ጋር የተኳረፈች አገር ሶላል የተሰኘ የራሷን የዘመን አቆጣጠር ትከተላለች።
ሌላኛዋ የእስያ አገር ሕንድ ደግሞ ሚያዝያ ወር ላይ አዲስ ዓመቷን ታከብራለች።
በየዓመቱ ጥቅምት ወር ላይ አዲስ ዓመቷን አንድ ብላ የምትጀምረው ደግሞ እስራኤል ስትሆን የሂብሩ የዘመን አቆጣጠርን ትከተላለች።
በመላው ዓለም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ አዲስ ዓመት ሲከበር ርችት መተኮስ የተለመደ ሆኗል።
ትልልቅ የርችት ትርዒቶች የሚከናወኑት በአብዛኛው እኩለ ሌሊት ላይ ነው።
በኒው ዚላንድ፣ ኦክላንድ ስካይ ታወር ብዙውን ጊዜ አስደናቂ የሆነ የርችት ትርዒት ማሳያ ስፍራ ነው።
በአውስትራሊያ እንዲሁ በሲድኒ የባሕር ዳርቻ ላይ በተመሳሳይ ግዙፍ የርችት ትርዒት ይታያል።
በካናዳ ቶሮንቶ፣ በናታን ፊሊፕስ አደባባይ፣ በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ፣ በከተማዋ ታዋቂ በሆነው የኮፓካባና የባሕር ዳርቻ ከዕኩለ ሌሊት ጀምሮ ሰማዩ በርችት በርቶ ያመሻል።
በዴንማርክ አዲስ ዓመት በሚከበርበት ወቅት ሳህን መስበር የተለመደ ነው።
ዴንማርካውያን ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በቤታቸው በራፍ ላይ ሳህን በመስበር አዲሱን ዓመት ብሩህ እንዲሆን ይመኛሉ።
ይህ ሳህን የመስበር ባሕል ግን በራስ ቤት በር ደጃፍ ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም።
ወዳጅ፣ ዘመድ እና ጓደኛ ቤት በር ላይ ሄዶ ሳህን በመስበር መጪዎቹ 12 ወራት የስኬት እንዲሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫ ማድረስም ይቻላል።
በብራዚል በአዲስ ዓመት ምስር መብላት የመልካም ዕድል መግለጫ፣ አዲሱ ዓመት በገንዘብ የሚንበሸበሹበት እንደሚሆን መተንበያ ተደርጎ ይቆረጣል።
በአሜሪካን ኒውዮርክ ደግሞ የአዲስ ዓመት አከባበር ፍጹም የተለየና ደማቅ ነው።
11ፓውንድ ክብደት ያለው ኳስ ከፍተኛ የብረት ማማ ላይ በማንጠልጠል አሮጌው ዓመት ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀረው በየእያንዳንዱ ሴኮንድ ዝቅ እያለ መውረድ ይጀምራል።
በስፍራው የሚገኝ ታዳሚ የአዲሱን ዓመት መግባት በእያንዳንዱ ሰከንድ አብሮ እየቆጠረ ያከብራል።
ልክ ዕኩለ ሌሊት ሲሆን፣ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ የአዲሱ ዓመት መግባት ማብሰሪያ የሆነው ርችት ይተኮሳል።
ይህ ግዙፍ ኳስ የመጣል (ball drop) ሥነ ሥርዓት የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።
በአውሮፓዊቷ ስፔን ደግሞ ልክ ዕኩለ ሌሊት ሲሆን ሰዎች የወይን ፍሬ መብላት ይጀምራሉ።
ይህም ዕኩለ ሌሊት ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ ሰዓት ልዩነት አንዳንድ የወይን ፍሬ መመገብ የባህላቸው አካል ነው።
በየሰዓቱ ልዩነት የሚበሏቸው ፍሬዎች በአዲሱ ዓመት መልካም ነገር ይዘው ይመጣሉ ተብሎ ይታመናል።
በሮማኒያ በድብ አምሳል የተሠራ ልብስ ለብሶ መደነስ እና ክፉ መንፈስን ማባረር በአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ወቅት የሚዘወተር ተግባር ነው።
ይህም በሮማኒያ ጥንታዊ ባህል መሠረት ድቦች ሰዎችን ከክፉ መንፈስ የመጠበቅ እና የመፈወስ ኃይል አላቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው።
እንደ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ያሉ አገራት አዲስ ዓመትን ለመጀመር ደወል ይደውላሉ።
በጃፓን 108 ጊዜ የሚደወል ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ በአዲስ ዓመት በየአካባቢው የደወል ድምጽ ጎልቶ ሊሰማ ይችላል።
በደቡብ አፍሪካ የማይፈለጉ ዕቃዎችን አውጥቶ በመጣል አዲስ ዓመትን በአዲስ ዕቃ መቀበል የተለመደ ሲሆን፣ በአንዳንድ የደቡብ አሜሪካ አገራት ደግሞ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ባዶ ሻንጣ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ይታያሉ።
አንዳንዶች "ሻንጣዎችን ተሸክሞ በጎዳና ላይ መንቀሰቀቀስ" በአዲሱ ዓመት በተለያዩ ጀብዱዎች የተሞላ እንደሚሆን ያምናሉ።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በምግብ ውስጥ በቂ ቫይታሚን ሳይኖር ሲቀር ተጨማሪ ቫይታሚን መውሰድ ይመከራል። ሆኖም ሁሉንም ችግር ይቀርፋል ማለት አይደለም።
የተጨማሪ ቫይታሚን እና ሚኒራል ገበያ 32.7 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። 74 በመቶ ተጠቃሚዎች አሜሪካውያን ናቸው።
የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎች ሁለት ሦስተኛውን ድርሻ ይይዛሉ።
አንዳንድ ጥናቶች እነዚህ ተጨማሪ ቫይታሚኖች እና ሚኒራሎች እምብዛም ጥቅም የላቸውም ሲሉ፣ እንዲያውም ይጎዳሉ ብለው የሚከራከሩም አልታጡም።
ለመሆኑ ሁሉም ሰው ተጨማሪ ቫይታሚን መውሰድ አለበት? ጥቅሙስ ምንድን ነው?
ተጨማሪ ቫይታሚን እና ሚኒራል ወይም በእንግሊዝኛው 'vitamin and mineral supplements' የሚወስዱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም።
ሁለቱን ንጥረ ነገሮች ሰውነታችን አያመርትም። ሆኖም ለጤና ጠቃሚ ናቸው።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ሰውነታችን የማያመርታቸውን ንጥረ ነገሮች ከምግቦች እናገኛለን። ቫይታሚን ኤ፣ ቫይታሚን ሲ እና ቫይታሚን ኬ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው።
ቫይታሚን ኤ ለዕይታ እና ለጤናማ ቆዳ ይረዳል። ቫይታሚን ሲ በሽታ የመከላከል አቅምን ያጠነክራል። ቫይታሚን ኬ ደም እንዳይረጋ ያግዛል።
ካልሽየም፣ ማግኒዢየም፣ ፖታሽየም የምናገኘውም ከምግብ ነው።
ቫይታሚን እና ሚኒራል ለሰውነታችን የሚያስፈልገው ከካርቦሃይድሬት፣ ከፕሮቲን እና ከስብ ባነሰ መጠን ነው።
ማንኛውም ተጨማሪ ቫይታሚንም ይሁን ሚኒራል ጤናማ አመጋገብን አይተካም።
ሰውነት የሚያስፈልገውን ለማሟላት አትክልት እና ፍራፍሬ፣ ለውዝ፣ ዓሣ፣ ሥጋ እና ሌሎችም ምግቦች የግድ ያስፈልጋሉ።
ፈጣን ምግቦች እና የተብላሉ ምግቦች መበራከት ጤናማ የቤት ምግብ እንዳይዘወተር ምክንያት ሆነዋል።
ፕሮፌሰር ቤስ ዳወሰን-ሀግስ በአሜሪካ በተፍስ ዩኒቨርስቲ የግብርና እና ሥነ ምግብ ተመራማሪ ናቸው።
አብዛኞቹ አሜሪካውያን በሳይንስ ከሚመከረው አትክልት እና ፍራፍሬ ግማሹን እንደሚመገቡ ይናገራሉ።
ለሰውነት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ከምግብ ያላገኙ ሰዎች በተጨማሪ ቫይታሚን እና ሚኒራል ለማካካስ ይሞክራሉ።
ምን ያህል ክፍተቱን ይሞላል? ለሚለው ቀጥተኛ መልስ የለውም።
በ1970ዎቹ የኖቤል ተሸላሚው ላይነስ ፓውሊንግ ቫይታሚን ሲ አብዝቶ መውሰድ ጉንፋንን ጨምሮ የመተንፈሻ አካላት ሕመም፣ የልብ ሕመም እና ካንሰርንም ሳይቀር ያድናል ብለው ይከራከሩ ነበር።
ከጉንፋን ውጪ ያሉ ሕመሞች ቫይታሚን ሲን በማብዛት እንደማይድኑ ሳይንስ ቢያረጋግጥም ብዙዎች አሁንም ድረስ በመላ ምቱ ያምናሉ።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ከ500 በመቶ እስከ 1,000 በመቶ እጥፍ ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች መውሰድን ያስተዋውቃሉ።
ቫይታሚን እና ሚኒራል እጅግ በተጋነነ ሁኔታ መጠቀም አደጋ ሊያስከትል ይችላል።
ቫይታሚን ዲ በብዛት ወስደው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ለዚህ ማሳያ ናቸው።
ውሃ ጥማት እና ቶሎ ቶሎ መሽናት የቫይታሚን ዲ መብዛት ምልክት ሲሆኑ ኮማ ውስጥ እስከመግባት እና እስከ ሞትም ያደርሳል።
የአሜሪካ ብሔራዊ ጤና ተቋም ቫይታሚን ኤ ማብዛት ራስ ምታት፣ የዕይታ መዛባት፣ ማቅለሽለሽ፣ የጡንቻ ሕመም እንደሚያስከትል ይገልጻል።
ቫይታሚን እና ሚኒራል ላይ የተሠሩ ጥናቶች የሚቃረኑ ውጤቶች አስገኝተዋል።
ይህ ማለት ደግሞ ተጨማሪ ቫይታሚን እና ሚኒራል በመውሰድ የሚገኘው ጥቅም እንደየሰዉ ይለያያል ማለት ነው።
'ፍሪ ራዲካልስ' የሚባሉ ጎጂ ኬሚካሎችን የሚያከስሙ አንቲኦክሲደንትስ ላይ ጥናቶች ተደርገዋል።
ፍሪ ራዲካልስ ሕዋስን የሚበጣጥሱ እና ዘረ መልን የሚጎዱ ናቸው።
ይሄንን ጉዳት ለመቀነስ አንቲኦክሲደንትስ መውሰድ ይጠቅማል ተብሎ ቢታመንም የተሳሳተ ምልከታ መሆኑ በጥናት ተደርሶበታል።
በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕብረተሰብ ጤና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጆአን ማንሰን የመሩት ጥናት አንቲኦክሲደንት የሆኑት ቫይታሚን ሲ እና ቫይታሚን ካንሰር እና የልብ ሕመምን እንደማይገቱ ያሳያል።
'አንቲኦክሲደንትስ' አብዝቶ መውሰድ ጤና እንደሚጎዳ ያሳዩ ጥናቶችም ይጠቀሳሉ።
በተለይም ሲጋራ አጫሾች ለሳምባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድላቸው እንዲጨምር ያደርጋሉ።
ቫይታሚን ኢ ማብዛት ስትሮክ ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።
ፕሮፌሰር ጆአን "ቫይታሚን ኢ ደም ያቀጥናል። የደም መርጋትን ስለሚያስቆም ደም ወደ አንጎል እንዲፈስ ሊያደርግ ይችላል። አንቲኦክሲደንት አብዝቶ መውሰድ የኦክስዴሽን መጠንን ሊጨምርም ይችላል" ይላሉ።
አንድ ንጥረ ነገር ብቻ አብዝቶ መውሰድ ሌሎች ንጥረ ነገሮች የመውሰድ አቅምንም ያዳክማል።
በቀን ከሚመከረው በላይ አንቲኦክሲደንት መውሰድ ጤናማ አይደለም።
ጤናማ አጥንት እንዲኖረን የሚያግዘው ቫይታሚን ዲ እንደ ሌሎቹ ቫይታሚኖች አይደለም።
በቂ ፀሐይ እስካገኘን ድረስ ሰውነታችን ቫይታሚን ዲ ያመርታል። ከምግብ ሊገኝም ይችላል።
የፀሐይ ብርሃን በብዛት በማይገኝባቸው በምዕራባውያን አገራት ቀዝቃዛ ወቅቶች ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ መውሰድ ይመከራል።
25 ሺህ አሜሪካውያን በተሳተፉበት ጥናት እንደታየው፤ ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ ወይም ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ መውሰድ የካንሰር፣ የልብ ሕመም እና ስትሮክ ተጋላጭነትን ይቀንሳል።
ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ መውሰድ ሕመሞቹን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል ማለት አይደለም።
እንዲያውም ቫይታሚኖችን ብቻ ለሁለት ዓመታት የወሰዱ ሰዎች በካንሰር የመሞት ተጋላጭነት ወደ 25 በመቶ እንዲሁም ለተባባሰ የካንሰር ደረጃ የመጋለጥ ዕድል ወደ 17 በመቶ ወርዶ ታይቷል።
ፕሮፌሰር ጆአን "ቫይታሚን ዲ የዕጢ ሕዋስ ብዙም እንዳይጎዳ ሊያደርግ ይችላል። ሆኖም ካንሰርን ለመዋጋት አይረዳም" ይላሉ።
ሰውነት ጤናማ ሕዋሳት አደገኛ ናቸው ብሎ ተሳስቶ ሲዋጋቸው የሚፈጠሩ ሕመሞችን (autoimmune disease) ለመከላከል ቫይታሚን ዲ ሚናው ቀላል አይደለም።
ተጨማሪ የቫይታሚን ዲ እንክብል መውሰድ በተለይም ለአዛውንቶች የአጥንት መሰንጠቅን ይከላከላል።
በ2000 በፈረንሳይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው በአዛውንቶች መንከባከቢያ ውስጥ የሚኖሩ አረጋውያን ሴቶች በቫይታሚን ዲ ተጠቃሚ ሆነዋል።
ከዚህ በተቃራኒው ቫይታሚን ዲ መውሰድ የአጥንት መሰንጠቅን የመከላከል ዕድሉ አነስተኛ ነው የሚሉ የጥናት ውጤቶችም ይፋ ሆነዋል።
ፕሮፌሰር ቤስ "ጥናቶቹ አነስተኛ ቫይታሚን ዲ ያላቸው አዛውንቶች ላይ አልተሠሩም። የተሠሩትም የቫይታሚን ዲ ጠቀሜታ ተጋኖ በሚነገርበት ወቅት ነው" ሲሉ ያስረዳሉ።
ቫይታሚን እና ሚኒራልን ጨምሮ ሌሎችም ንጥረ ነገሮች በማዋሃድ የሚሠራው ተጨማሪ እንክብል (multivitamin) በአዛውንቶች ላይ አወንታዊ ለውጥ አሳይቷል።
ፕሮፌሰር ጆአን ጥናት መሥራት የጀመሩት ከ20 ዓመት በፊት ነው።
በጥናታቸው እንዳገኙት ለ11 ዓመታት እነዚህን እንክብሎች የወሰዱ ሰዎች ላይ እንደታየው ከሆነ በካንሰር የመያዝ ዕድልን 8 በመቶ ይቀንሳሉ።
ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች የካንሰር ተጋላጭነት በ18 በመቶ ቀንሷል።
"አዛውንቶች አመጋገባቸው ውስን ስለሆነ ይሆናል ይሄ ውጤት የተገኘው" ይላሉ ፕሮፌሰር ጆአን።
ፕሮፌሰር ቤስ በ2023 በሠሩት ጥናት በየቀኑ መልቲቫይታሚን የወሰዱ ሰዎች በሦስት ዓመታት ውስጥ የአእምሮ ክህሎት መዳከም ችግርን 60 በመቶ መቀነስ ችለዋል።
ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ካንሰር እና መዘንጋት ያሉ ችግሮችን በመቀነስ ረገድም ውጤት አግኘተዋል።
ፕሮፌሰር ቤስ እና ፕሮፌሰር ጆአን እንደሚሉት፣ በርካቶች ተጨማሪ ቫይታሚን መውሰድ የለባቸውም። ጤናማ እና የተመጣጠነ አመጋገብ የተሻለው አማራጭ ነው።
የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና ተቋማት ነፍሰ ጡሮች መልቲቫይታሚን እና ፎሊክ አሲድ እንዲወስዱ ይመክራሉ።
እነዚህን ንጥረ ነገሮች ማግኘት ለጨቅላ ሕጻናት ጤናማ ዕድገት ይረዳል።
አትክልት ተመጋቢዎች እና ዓሣ የማይበሉ ሰዎች ኦሜጋ-3 ያለው የዓሣ ዘይት መውሰድ አለባቸው።
ሰውነት ቫይታሚንን በአግባቡ እንዳያብላላ የሚያግዱ ሕመሞች (Crohn's disease እና ulcerative colitis) ያሉባቸው ሰዎች ተጨማሪ ቫይታሚን ቢወስዱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንት የካንሰር እና የአእምሮ ክህሎት መዳከም ተጋላጭነትን ለመቀነስ በየቀኑ መልቲቫይታሚን እንዲወስዱ ይመከራል።
ሆኖም ግን ከሚፈለገው በላይ ቫይታሚን መውሰድ (mega-dosing) ተገቢ እንዳልሆነ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ።
ፕሮፌሰር ጆአን "መልቲቫይታሚን መውሰድ አይጎዳም። የተመጣጠነ ምግብ ከመውሰድ ጋር በተያያዘ ክፍተት ያለባቸው ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ቫይታሚን እና ሚኒራል ለማግኘት መልቲቫይታሚን እንክብል መውሰድ ይችላሉ" ይላሉ።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
እስራኤል በዓለም ላይ ውጤታማነታቸው የተፈተኑ ናቸው ተብለው የሚታመኑ የሚሳዔል ጥቃት የመከላከያ ሥርዓት ያላት አገር ናት።
ነገር ግን ከኢራን ጋር በጋባቸው ግጭት ውስጥ በሚካሄዱ የሚሳዔል ጥቃት ልውውጦች ውስጥ እነዚህን የጥቃት መከላከያዎች ጥሰው በማለፍ በሰዎች እና በሕንጻዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው።
ከዚህ ቀደም እስራኤል ሐማስ ከጋዛ፣ ሔዝቦላህ ከሊባኖስ እንዲሁም ሁቲዎች ከየመን በኩል የሚሳዔል ጥቃት ሲፈጽሙባት ቆይተዋል። በእነዚህ ወቅቶች ጥቃቶች ለመመከት ሁሉንም የሚሳዔል መከላከያ ዘዴዎችን ተጠቅማለች።
እነዚህ የእስራኤል የሚሳዔል መከላከያ ሥርዓቶች የአጭር ርቀት ሮኬቶችን ከሚመክተው አይረን ዶም እስከ ባለስቲክ ሚሳዔል ድረስ የሚከላከለውን አሮው የተሰኘ ፀረ ሚሳዔል መሣሪያዎችን ያካትታሉ።
በእስራኤል የሚሳኤል መከላከያ ሥርዓት ውስጥ ያሉት የተለያዩ ፀረ ሚሳዔል መከላከያዎች የትኞቹ ናቸው? እንዴትስ ይሠራሉ?
እስራኤል በርካታ የአየር መከላከያ ዘዴዎች አሏት። እንደየአቅማቸው በተለያየ ከፍታ እና ርቀት ላይ የሚመጡ ሚሳዔል ጥቃቶችን ለማክሸፍ የሚውሉ ናቸው።
ከእስራኤል የሚሳኤል ጋሻዎች መካከል በጣም የሚታወቀው “አይረን ዶም” ሲሆን፣ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን ለመከላከል የሚያስችል ነው። ይህ መሳሪያ ሞርታሮችን እና ከሚሳዔል ማስወንጨፊያ የሚተኮሱ ከአራት እስከ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙትን ያከሽፋል።
የ“ዳዊት ወንጭፍ” (ዴቪድስ ስሊንግ) የተሰኘው ደግሞ እስከ 300 ኪ.ሜ ርቀት ርቀት የሚጓዙትን የረዥም ርቀት ሮኬቶችን፣ ክሩዝ ሚሳዔሎችን እና የመካከለኛ ወይም የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ለመከላከል ያስችላል።
“አሮው 2” እና “አሮው 3” የሚባሉት ደግሞ እስከ 2400 ኪ.ሜ ርቀት የሚጓዙ መካከለኛ እና ረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን ይከላከላሉ።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
አይረን ዶም በጦርነት ውስጥ ተደጋግሞ የተሞከረ የዓለማችን የአየር መከላከያ ሥርዓት መሆኑ ይነገርለታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሐማስ እና ሌሎች የጋዛ ታጣቂ ቡድኖች እንዲሁም ደግሞ ሄዝቦላህ ከሊባኖስ ሆኖ ወደ እስራኤል በተኮሷቸው የሚሳዔሎች ብዛት ነው መሳሪያው ተደጋግሞ የመሞከር ዕድል ያገኘው።
በመላው እስራኤል የሚገኙ የአይረን ዶም ማስወንጨፊያዎች (ባትሪዎች) አሉ። እያንዳንዱ ባትሪ ሦስት ወይም አራት ማስወንጨፊያዎችን ይዘዋል። እያንዳንዳቸው 20 ሚሳኤሎች የማክሸፍ ብቃት አላቸው።
አይረን ዶም ለጥቃት የሚመጡ ሮኬቶችን በራዳር ፈልጎ ይከታተላል። የትኞቹ ሮኬቶች ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ ያሰላል። ባዶ ቦታ ላይ የሚወድቁትን በመተው አይረን ዶሙ ሚሳዔሎቹን ወደ እነዚህ ሮኬቶች በመተኮስ ያጨናግፋቸዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (አይዲኤፍ) እንደሚለው ከሆነ አይረን ዶም ካነጣጠረባቸው ሮኬቶች 90 በመቶ  ያህሉን ያመክናቸዋል። “ታሚር” የሚሰኙት እያንዳንዳንዳቸው ሚሳዔሎቹ 50 ሺህ ዶላር ገደማ ያስወጣሉ።
እአአ በ2006 በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል ከነበረው ጦርነት በኋላ የተሠራ መሣሪያ ነው። በወቅቱ ሄዝቦላህ ወደ እስራኤል 4 ሺህ የሚጠጉ ሮኬቶችን በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ በደርዘን የሚቆጠሩ ዜጎቿን ገድሏል።
ፀረ ሚሳዔል መሳሪያው የእስራኤል ኩባንያ በሆኑት ራፋኤል አድቫንስድ ዲፌንስ ሲስተም እና የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ የተነደፈ ሲሆን፣ የአሜሪካን መጠነኛ ድጋፍ በመጠቀም በ2011 ነበር የተመረተው።
አይረን ዶም ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመቻዎች ላይ ጥቅም የዋለው በዚያው ዓመት ሲሆን፣ ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶችን ማክሸፍ ችሏል።
የአይረን ዶም ሚሳኤሎች ከጥቅምት 2023 ወዲህ ብቻ ሐማስ እና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከጋዛ እንዲሁም ደግሞ ሄዝቦላህ ከደቡብ ሊባኖስ የተኮሷቸውን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን አክሽፏል።
በዕብራይስጥ  “ተዓምረኛው ዘንግ” በመባል የሚጠራው የዳዊት ወንጭፍ (ዴቪድስ ስሊንግ) እስከ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሚሳዔሎችን መከላከል ይችላል።
መስከረም 2024 ላይ ሄዝቦላህ ከሊባኖስ የተተኮሰውን የባለስቲክ ሚሳዔሎች ለመከላከል ጥቅም ላይ ውሏል። እንደ እስራኤል ጦር ገለጻ ከሆነ ኢራን የተሠራው ይህ ቃድር-1 የተሰኘ ባለስቲክ ሚሳኤል ከ700 እስከ አንድ ሺህ ኪሎ ግራም ክብደት ያለው የመካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል ነው።
ሄዝቦላህ ሚሳዔሉ ዒላማ አድርጎት የነበረው በቴል አቪቭ የሚገኘውን የሞሳድ ዋና መሥሪያ ቤትን እንደነበር ገልጿል። የእስራኤል ጦር ግን ሚሳኤሉ ወደ መኖሪያ መንደሮች እያመራ ነበር ብሏል።
የዳዊት ወንጭፍ በእስራኤሉ ራፋኤል አድቫንስድ ድፌንስ ሲስተምስ እና በአሜሪካው ሬይተን የጋራ ጥምረት የተሠራ ነው። በአውሮፓውያኑ 2017 ነው አገለግሎት ላይ መዋል የጀመረው።
“ስተነር” የተሰኙት ሚሳዔሎቹ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ለመምታት የተሠሩ ናቸው። እንደ አይረን ዶም ሁሉ የዳዊት ወንጭፍ ሚሳዔሎች የሚያነጣጥሩት መኖሪያ አካባቢዎች አደጋ ላይ የሚወድቁ ከሆነ ብቻ ነው።
እንደ አይረን ዶም ሁሉ የዳዊት ወንጭፍም አውሮፕላኖችን፣ ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን ይከላከላሉ።
እያንዳንዱ የዳዊት ወንጭፍ ሚሳኤል 1 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ዋጋ ወጥቶለታል።
በግንቦት 2023 በጋዛ የሚገኘውን የፍልስጤሙ እስላማዊ ጂሃድ ቡድንን ጥቃት ለመከላከል የዳዊት ወንጭፍ ጥቅም ላይ ውሏል። ቡድኑ ከአንድ ሺህ 100 በላይ ሚሳዔሎችን የተኮሰ ሲሆን፣ እስራኤል ስጋት ፈጥረዋል ካለቻቸው ውስጥ 96 በመቶውን ሮኬቶች ማምከኗን ተናግራለች።
“አሮው 2” (ቀስት) የተነደፈው ከመሬት 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በመምዘግዘግ የአጭር እና የመካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ለመከላከል ነው።
ይህ የፀረ ሚሳዔል መከላከያው የተሠራው በ1991 ከመጀመሪያው የባሕረ ሰላጤው ጦርነት ማብቂያ በኋላ ነበር። በወቅቱ ኢራቅ በደርዘን የሚቆጠሩ የሶቪየት ሠራሽ ስከድ ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል ተኩሳለች። ይህንንም ተከትሎ አሮው 2 በአውሮፓውያኑ 2000 ላይ በእስራኤል ሠራዊት ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ።
አሮው 2 ሚሳዔሎችን ከ500 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መለየት ይችላል። ሚሳዔሎቹን የሚያጨናግፈው ግን ከማስወንጨፊያዎቹ 100 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ ነው።
ሚሳዔሎቹ ከድምጽ ፍጥነት ከዘጠኝ እጥፍ በላይ ይጓዛሉ። በአንድ ጊዜም እስከ 14 ዒላማዎች ላይ ሊተኩስ ይችላል።
አሮው 2 በአውሮፓውያኑ 2017 የሶሪያን ሚሳዔልን ለመምታት ለመጀመሪያ ጊዜ በውጊያ ወቅት ጥቅም ላይ ውሏል ተብሏል።
የዚሁ ፀረ ሚሳዔል ዝርያ የሆነው አሮው 3 ደግሞ በዚያው ዓመት ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው። ይህ መሳሪያ ከከባቢ አየር ውጪ የሚጓዙ የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ለመጥለፍ የተነደፈ ነው። 2400 ኪ.ሜ የመጓዝ አቅምም አለው።
በአውሮፓውያኑ 2017 አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በውጊያ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው ደግሞ በ2023 ነው። በዚህም የመን ውስጥ ያሉት የሁቲ አማጺያን በደቡብ እስራኤል በሚገኘው በኤላት የባሕር ዳርቻ ከተማ ላይ የተኮሱትን ባለስቲክ ሚሳዔል ለማክሸፍ አገልግሏል።
አሮው 3 የተመረተው በመንግሥታዊው የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንደስትሪ ሲሆን፣ በአሜሪካ ቦይንግ ኩባንያ ድጋፍ ተደርጎለታል።
ሁሉም የእስራኤል የሚሳዔል መከላከያ ሥርዓቶች የኢራንን ግዙፍ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳዔሎችን ለመመከት ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ጥቅም ላይ ውለዋል።
የሚሳዔል መከላከያዎቹን ጨምሮ የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬስ ተዋጊ ጄቶችም 300 የሚጠጉትን የኢራን ሚሳዔሎች መትተው ማክሸፋቸው መዘገቡ ይታወሳል።
ታድ የተባለው ፀረ ሚሳዔል ከሌሎቹ አዲሱ የሚሳዔል መከላከያ ሲሆን፣ የተሠራውም በእስራኤል የቅርብ ወዳጅ አሜሪካ ነው።
ይህን የሚሳዔል መከላከያን አሜሪካ ለእስራኤል የሰጠችው ባለፈው ጥቅምት ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነው።
ይህ ታድ የተባለው ሚሳዔል እንደ ዴቪድስ ስሊንግ ፀረ ሚሳዔል ሥርዓት የጠላት ሚሳዔል ከ150 አስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደ ዒላማው በተቃረበበት በመጨረሻው ደረጃ ላይ ነው መትቶ የሚጥለው።
ይህ የሚሳዔል ማምከኛ መሳሪያ በጠላት የተተኮሱ ሚሳዔሎችን በመሬት ከባቢ አየር ውስጥ እና ከዚያም ውጪ መትቶ ማክሸፍ ይችላል።
ይህ መሳሪያ ስድስት ፀረ ሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ያሉት ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው ስምንት ሚሳዔሎችን ስለሚይዙ በአንድ ጊዜ 48 ሚሳዔሎችን ይታጠቃል።
ታድ የተባለውን ፀረ ሚሳዔል ለማንቀሳቀስ አሜሪካ ወታደሮቿን እስራኤል ውስጥ አሰማርታለች።
የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ይህንን ታድ የተባለ ፀረ ሚሳዔል ሥርዓት ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ እየተጠቀመበት ሲሆን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ገዝተው ታጥቀውታል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሲነሳ በረሃ ባጠየመው ፊታቸው ላይ ጺማቸው የጎፈረ አንድ ጎልማሳ አይዘነጉም።
የእኚህ ሰው ስም እንዲሁ አይጠራም። ብዙ ቅጽሎች ይቀድሙታል። የጉባው መናኝ፣ ህልመኛው፣ ታታሪው፣ ትሁቱ፣ ባህታዊው. . . ሌላም ሌላም።
ጉባ እና የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት መኖሪያቸውም መለያቸውም የሆነ፤ እርሳቸውም ለግድቡ "ፊት" የነበሩ ሰው።
ስማቸው ከግድቡ ጋር ከተጣበቀ ባለታሪኮች መካከልም አንዱ ናቸው - ኢንጂነር ስመኘው በቀለ።
ኢንጂነሩ የመሠረተ ድንጋይ ከተጣለበት መጋቢት 24/2003 ዓ.ም. አንስቶ የግድቡን ፕሮጀክት ለሰባት ዓመታት መርተዋል።
ባልደረቦቻቸው፣ የሚያውቋቸው፣ የቤተሰብ አባሎቻቸው ስለ እርሳቸው ሲጠየቁ ሳይጠቅሱ የማያልፉት ሙሉ ጊዜያቸውን ለግድቡ መስጠታቸውን ነው። ይህ ግብራቸው ከሊቅ እስከ ደቂቅ የተመሰከረለት ነው።
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን በአንድ ቃለ ምልልሳቸው ላይ "ስመኘው ልጆቹን፣ ሚስቱን እና ቤተሰቡን ትቶ ያገባው ሕዳሴን ነበር" ብለዋል።
የቤተሰብ አባሎቻቸውም የሚያስረግጡት ይህንኑ ነው።
የኢንጂነሩን ሕልፈት ተከትሎ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የቤተሰብ አባል "እሱ አገሬን ሥራዬን እያለ ሁሉም ሰው ረስቶታል። እሱ ሁሉ ነገሩ ሥራው ላይ ነበር። ዘመድ አይልም . . ." ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እኚህ የቤተሰብ አባል እንዳሉት ኢንጂነሩ ማኅበራዊ ሕይወት የሚባል ነገር እንኳን አልነበራቸውም።
ኢንጂነሩ ለሕጻናት ልጆቻቸው፣ ለደካማ ቤተሰቦቻቸው፣ ለራሳቸው እንዲሁም ለማኅበራዊ ሕይወታቸው መስጠት ያለባቸውን ጊዜ ሁሉ ለግድቡ ገብረዋል።
እርሳቸው የግድቡን ሥራ እየመሩ በነበረበት ወቅት ባልደረባቸው የነበረችው ኢንጂነር ብሩክታዊት እሸቱ፣ "ኢንጂነሩ እረፍት አልበራቸውም" ስትል ለቢቢሲ እማኝነቷን ሰጥታለች።
የግድቡ ግንባታ 24 ሰዓት የሚከናወን ስለነበር ሌሊት ሳይቀር ወደ ግንባታው ሥፍራ በድንገት የመጡበት ቀን ጥቂት እንዳልነበር ትናገራለች።
በዚህ ሁሉ ውስጥ እያለፉ "ትህትናቸው ያስገርመኝ ነበር" የምትለው ብሩክታዊት፣ እውቀታቸው እና አክብሮታቸው የሠራተኛውን ቀልብ የገዛ እንደነበርም ታወሳለች።
የሙቀት መጠኑ 43 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርሰውን የጉባን በረሃ ተቋቁመን እንድንሠራ የሚያበረቱን እርሳቸው ነበሩም ትላለች።
"እንኳን በእርሳቸው የኃላፊነት ደረጃ በእኛ ደረጃም ከባድ መስዋዕትነት ነው የከፈልነው" ስትልም ኢንጂነሩ ታሪክ እና ሕልም ተሸክመው ያሳለፏቸው ጊዜያት ቀላል እንዳልነበሩ ትዘክራለች።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የዎል ስትሪት ጆርናል የአፍሪካ ዘጋቢ ማቲና ስቴቪስ ግሪድኒፍ የኢንጂነሩን ሕልፈት ተከትሎ ለቢቢሲ ስትናገር፣ "እርሳቸው የመጡት ይህንን አገራዊ ህልም ለመወከል ነው" ብላለች።
ኢንጂነሩን በቅርበት እንደምታውቃቸው የተናገረችው ጋዜጠኛዋ፣ "ኢንጂነር ስመኘው የበዛ የአገር ፍቅር ያላቸው ለአገራቸው መለወጥ ሕይወታቸውን የሰጡ ነበሩ" በማለት ነበር የገለጸቻቸው።
"ለወደፊቷ ኢትዮጵያ የሚችሉትን ለማበርከት ሙሉ ሕይወታቸውን የሰጡ ይመስሉ ነበር" ስትልም አክላለች።
ኢንጂነሩም ቢሆኑ ህልማቸውን አብዝተው ይናገሩ ነበር።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠ ከአንድ ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 'ሚት ኢቲቪ' ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ አንድ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
"አሁን የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንድ ዓመት ሆነው። ደስተኛ ነዎት ወይ?" የሚል።
ኢንጂነር ስመኘው ወደ ጥያቄው የተንደረደሩት የወሰዱት ኃላፊነት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ለመግለጽ በሚመስል አኳኋን ቁጥሮችን በመጥቀስ ነበር።
ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምን ያህል ስፋት፣ ከፍታ እና ይዘት እንዳለው፣ ስንት ሠራተኞች እንደተሳተፉበት፣ ግድቡ ስለሚገኝበት ቦታ እና የአየር ጠባይ እንዲሁም ቤተሰባቸው ከሚኖርበት አዲስ አበባ ምን ያህል እንደሚርቅ አብራሩ።
". . . የአገራችን ዕድገት ጥሩ ሆኖ ማየት እንፈልጋለን። ለዘላቂ ልማት ደግሞ 'ሃይድሮ ፓዎር' የጀርባ አጥንት ነው። ሁሉም በግድቡ ላይ የሚሳተፈው የግድቡ ማኅበረሰብ ሙቀቱን እና ርቀቱን አያስበውም። ምክንያቱም ህልም አለን" ነበር ያሉት።
አገራቸው ከፍ ብላ፣ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተሰልፋ ፣ ትውልዱ ካለፈው የተሻለ የሚኖርባት እንድትሆን ይመኙ ነበር።
ህልም ያነገቡት የግድብ ግንባታን እንደሚመራ እንደ አንድ ኢንጂነር ብቻ ሳይሆን ለአገር እና ለትውልድ እንደሚቆረቆር የአገር መሪም ጭምር ነበር።
"ሲመጡ እንደ ፕሮጀክት መሪ ሳይሆን እንደ አገር መሪ ነበር የምንቀበላቸው" የምትለው ብሩክታዊት፣ ይህን እንድናደርግ የሚያስገድደን እውቀታቸው እና ትህትናቸው ነበር ብላለች።
"ቦታው በጣም ከባድ ነው። በተራራ የተከበበ ቦታ ነው። እንደዚህ የሚገለጽ አይደለም። የበረሃው ነበልባል ይታይ ነበር" ስትልም ኢንጂነሩ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ሆነው የተጫወቱት ሚና በቃላት የሚገለጽ እንዳልሆነ ትናገራለች።
"ግድቡ ሲመረቅ ቢያዩት ትልቅ ኩራት ነበር። አሁንም ቢሆን ግድቡ ላይ ሐውልት ቢቀመጥላቸው እና በዚያ መልኩ ትውልድ ቢያስታውሳቸው ደስ ይለኛል።"
በግልገል ግቤ አንድ ከዚያም በሕዳሴ ግድብ ለሁለት ዓመት ገደማ አብረዋቸው የሠሩት እና የእርሳቸውን ሕልፈት ተከትሎ የግድቡን ግንባታ እንዲመሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮም፣ "ለሙያው ቦታ የሚሰጥ መሃንዲስ ነው። ለያዘው ሥራ እና ዓላማ ቁርጠኛ የሆነ፤ ብዙ ጊዜውን ለሥራው የሚሰጥ ጥሩ ሠራተኛ" ሲሉ ነበር የተናገሩት ከኢንጂነሩ ሞት በኋላ ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ።
"የለፋበትን ውጤት ሳያይ ማለፉም አሳዝኖኛል።" ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት, Grand Ethiopian Renaissance Dam
ግድቡ የዓለምን ትኩረት የሳበው እና ጂኦፖለቲካዊ ውዝግብ የተፈጠረው ወዲያውኑ ነበር።
የግድቡ ግንባታ በተጀመረ በአንድ ወር ውስጥ ነበር ስጋት የገባቸው ግብፅ እና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በግድቡ ግንባታ ዙሪያ የቴክኒክ ኮሚቴ አዋቅረው ጥናት ማካሄድ የጀመሩት።
የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚቆጠሩት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ኃላፊነቱን የተረከቡት ዓለም ትኩረቱን ኢትዮጵያ ላይ ባደረገበት፣ የገንዘብ አቅም ባልጎለበተበት፣ "አባይን በአገሩ እናሳድረው በሚል ትልቅ ህልም እና ተስፋ" ብቻ ነበር።
ግንባታው ሲጀመርም ". . . አገራችንን ወደ ላቀ ደረጃ እናደርሳለን። ይህን ቃል ኪዳን ነው እየገባን ያለነው" ብለዋል።
ለግድቡ ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን እንደ ቃል አቀባይ እና የዘመቻ መሪ ሆነው እንዳገለገሉም ይነገርላቸዋል።
ኢንጂነር ስመኘው በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ድጋፍ እና ተሳትፎ የተጀመረው ታላቁ ሕዳሴ ግድብን ለሚጎበኙ የአገር ውስጥ እና የውጭ ዜጎች እዚያው ጉባ በረሃ ላይ ቆመው እልፍ ጊዜ አስረድተዋል።
በንግግሮቻቸው ውስጥም ለአገር ያላቸው ፍቅር፣ ለሥራ ያላቸው ቁርጠኝነት እና ህልም ፍንትው ብሎ ይታይ ነበር።
ከማለፋቸው ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት ከአገር ውጭ ለሚገኝ 'ሰላም' ለተሰኘ ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የተናገሩትም ለዚህ ማሳያ ይሆናል።
ኢንጂነሩ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን እንዴት እንደሚገልጹት ተጠይቀው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ምላሻቸውን በአንድ ጠንካራ ዓረፍተ ነገር ነበር ያሰሩት።
ግድቡን "እንደ ተጨማሪ የስሜት ህዋስ አድርገን ነው የምንቆጥረው" በሚል።
ሕዳሴ ግድብን ልክ እንደ ዓይን፣ እንደ አፍንጫ፣  እንደ ጆሮ፣  እንደ እጅ . . .።
ኢንጂነር ስመኘው የሕዳሴ ግድብን ሥራ ለመምራት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኃላፊነቱን ከተረከቡ በኋላ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት እዚያው ደፋ ቀና ሲሉ ነበር።
". . . የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸውን ከፍ ማድረግ፣ መካከለኛ ገቢ ያላትን አገር ማየት፣ መጪው ትውልድ ከእኛ በተሻለ ሁኔታ የሚኖርባትን አገር መፍጠር ነው ህልማችን። ለዚህም ነው እራሳችንን እረስተን ተቋማዊ አስተሳሰብ እና አገራዊ አስተሳሳብ ይዘን ለውጥ እያየን ያለነው" ብለው ነበር በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ላይ።
አንዳንዶችም 'የበረሃው ባህታዊ' የሚሏቸው ወደው አይደለም - "ራሳቸውን ረስተው" ለሕዳሴው ግድብ ማደራቸውን፤ ጉባ መመነናቸውን ልብ ቢሉ እንጂ።
ምንም እንኳን ወደ ኋላ ላይ የግድቡ የግንባታ ሒደት ተጓትቷል የሚሉ ቅሬታዎች ሲቀርቡ የነበረ ቢሆንም፤ ኢንጂነሩ የግድቡን ግንባታ ከመሠረት ድንጋይ ወደ ከ60 በመቶ በላይ ማድረሳቸው ተገልጿል።
የኢንጂነሩን ሕልፈት ተከትሎ ፕሮጀክቱን እንዲመሩ ሥልጣን የተሰጣቸው ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ፣ ኃላፊነቱን ከተረከቡ ከአንድ ዓመት በኋላ የግድቡ ግንባታ ሒደት የደረሰበትን ደረጃ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
"የግድቡ ሲቪል ሥራ ወደ 84 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 28 በመቶ ደርሷል። በአጠቃላይ ግድቡ ወደ 68 በመቶ ደርሷል።"
ኢንጂነር ስመኘው የውሃ ኃይል ማመንጫ ግንባታን ሲመሩ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያቸው አልነበረም።
በግልገል ግቤ አንድ እና በግልገል ግቤ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫ ግንባታን መርተዋል።
ከአፍሪካ በግዝፈቱ ቀዳሚ የሆነው ግድብ ግንባታ የመጀመሪያ መሪ የነበሩት ኢንጂነር ስመኘው ጎንደር፣ ማክሰኝት በተባለች አነስተኛ ከተማ ነው የተወለዱት። የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም በእንፍራንዝ፣ በደሴ እና በወልዲያ ከተሞች ተከታትለዋል።
ከዚያም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሥልጣን ኮተቤ መብራት ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል፣ በኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ በዲፕሎማ ተመርቀዋል። በመቀጠልም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል በሲቪል ምህንድስና ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
በአገር ውስጥ እና በውጭ ከሚገኙ የተለያዩ የሃይድሮ ፓወር ኦፕሬሽን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ሥልጣናዎችንም ወስደዋል።
በሥራቸውም ከመምህርነት ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የአገሪቱን ግዙፍ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታን እስከ መምራት ደርሰዋል።
የሕዝብ ዕይታ ውስጥ የገቡት እና ትኩረት የሳቡት ግን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን መምራት ከጀመሩ በኋላ ነበር።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በሥራ አስኪያጅነት ለሰባት ዓመታት ከመሩ በኋላ ነበር በጨፍጋጋማው የሐምሌ ወር የኢንጂነሩ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማው።
ሐሙስ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም. ጠዋት ሕይወታቸው አልፎ የተገኘው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ አደባባይ ቆማ በነበረችው ላንድክሩዘር ቪ8 መኪናቸው ውስጥ ነበር።
ዜናው በርካቶችን ያስደነገጠ፣ ያሳዘነ፣ ያስቆጣም ጭምር ነበር።
ኢንጂነሩ እንዴት እንደ ዓይን ብሌናቸው ከሚያዩት ግድብ በዚህ መልኩ ተለዩ የሚለው እስካሁንም ድረስ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።
ፖሊስ በወቅቱ ኢንጂነሩ የራሳቸውን ሕይወት ቀጥፈዋል ሲል ነው መግለጫ የሰጠው።
ከሆነስ ለምን ራሳቸውን አጠፉ? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ግን እስካሁን አልተገኘም።
ሞታቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰው ነበር።
"ጀግና አይሞትም"፣ "ኢንጂነር ህያው ነው"፣ "ፍትህ ለኢንጅነር"፣ " የሚሉ መፈክሮች ተነበዋል፤ ተሰምተዋል። በርካታ ወጣቶችም "የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድ" የሚል ካናቴራ ለብሰው "ለኢንጂነሩ ፍትሕ" ጠይቀዋል።
የሁለት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት በነበሩት ኢንጂነሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወቅትም ልጆቻቸው ለአባታቸው ፍትሕን ሲጠይቁ ተደምጠዋል።
ከዚያን ጊዜ በኋላ ግን ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ የሚያውቋቸው በእርሳቸው ሕይወት እና አሟሟት ላይ ዝምታን መርጠዋል።
ሕልፈታቸው የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግድቡ ግንባታ እየሄደ በነበረበት ፍጥነት በአስር ዓመት ውስጥም አይጠናቀቅም ብለዋል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት ከተንሸራሸረ በኋላ ነበር።
ይህንን ተከትሎም የግድቡን ግንባታ ሒደት ለመጠየቅ ከቢቢሲ ለኢንጂነሩ ስልክ ተደውሎ ነበር።
ኢንጅነሩ ከመሞታቸው ከአንድ ቀን በፊት ለቢቢሲ በሰጡት በዚህ አጭር ቃለ ምልልስ ላይ እንዲህ ነበር ያሉት።
"የተባለውን ጉዳይ አልሰማሁትም። 'ኦርጋናይዝድ' ሁኑና በመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኩል ኮሚዩኒኬት አድርጉኝ አግባብ ያለው ምላሽ እሰጣለሁ። . . .
"[ግድቡ] የአንቺም ፕሮጀክት ነው። መግለጫ ለመስጠት ዝግጁ ነን። አካሄድ ደግሞ ጠብቄ ብሄድ መልካም ስለሚሆን ነው። ፕሮጀክቱ እየተሠራ ነው።"
በንግግራቸው ውስጥ በብዙዎች ልብ ውስጥ የቀረው ትህትናቸው አልተለያቸውም ነበር - "ከአክብሮት ጋር!"።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
የኢትዮጵያ መንግሥት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ግንባታን አጠናቅቆ በዚህ ዓመት የመጨረሻ ቀናት በይፋ ለማስመረቅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰምቷል።
በተለይ አብዛኛውን የናይል ውሃ በብቸኝነት ስትጠቀም የነበረችው ግብፅ በግድቡ ግንባታ እና ውሃ ሙሌት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታ መቆየቷ ይታወቃል።
ባለፉት ዓመታትም ሱዳንን ጨምሮ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ድርድር ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ ግድቡ አምስት ጊዜ በውሃ ተሞልቶ ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ እየተዘጋጀ ነው።
ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጵያ አሳሪ ስምምነት እንድትፈርም በተደጋጋሚ ብትጠይቅም ኢትዮጵያ ግን ሳትቀበለው ቀርታ የደረጉተ ድርድሮች ያለ ውጤት ቀርተዋል።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ብታጠናቅቅም አሁንም ለንግግር እና ለድርድር በሯ ክፍት መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከቢቢሲ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ይህ ግዙፍ ግድብ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፣ ይህም ለበርካታ የአገሪቱ ዜጎች የኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲያዩ ዕድል እንደሚፈጥር ሚኒስትሩ አመልክተዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ መንግሥት 46 በመቶ የሚሆነው የኤሌትሪክ የማያገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የጀመረውን ጥረት እንደሚያግዝ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገለፀዋል።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት 54 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።
"46 በመቶ ያህሉ አሁንም የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተጠቃሚ አይደለም። በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህንን ቁጥር ለመቀነስ ነው እየሠራን ያለነው።"
ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት ዕቅድ ከአምስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2030 ቢያንስ 90 በመቶ የአገሪቱ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በአፍሪካ ግዙመሆኑ እየተነገረለት ያለው የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታው በአምሰት ዓመት ይጠናቀቃል ቢባልም 14 ዓመታትን ፈጅቷል።
ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ይህ ግድብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የተገነባው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ለመገንባት ከአሜሪካ ድጋፍ ማግኘቷን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው" ቢሉም አገራቸው መቼ እና በምን መልኩ ገንዘቡን እንደሰጠች ያሉት ነገር ግን የለም።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ "ይህ የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ገንዘብ ነው የተገነባው" በማለት አገሪቱ ከየትኘውም ወገን የገንዘብ ድጋፍ ሳታገኝ በሕዝቧ እና በራሷ አቅም መገንባቷን በተመለከተ ሲነገር የቆየውን አረጋግጠዋል።
ከተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ግድቡን ለመገንባት ስለተገኘ ገንዘብ የሚሰጡ አስተያየቶችን በተመለከተ ሲናገሩም "ይህ ውሸት ነው" በማለት "በኢትዮጵያውያን ንፁህ ገንዘብ ገንብተን፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ለምረቃ የሚበቃው" ብለዋል።
አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጪን የጠየቀው ይህ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ የተገነባው ሕዝቡ ባወጣው ገንዘብ እና አገር ውስጥ ባለ ሃብት መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለግድቡ ግንባታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብቱን ያፈሰሰበት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ለግድቡ ድጋፍ አድርገናል የሚለው አስተያየትን ትክክል ያልሆነ በማለት ውድቅ አድርገዋል።
የሕዳሴ ግድብ ምረቃ መቃረቡን ግብፅ "የዓለም አቀፍ ሕግን በጣሰ መልኩ በምሥራቃዊ ናይል ተፋሰስ የሚደረግ የተናጠል እርምጃን" እንደማትቀበል ለበርካታ አፍሪካ አገራት አሳውቃለች።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የናይል ተፋሰስ አገራት ከሆኑት ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኡጋንዳ፣ ከኬንያ እንዲሁም ከተፋሰሱ ውጪ ካሉት ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በተናጠል በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ግብፅ፣ ኢትዮጵያ የግድቡ ውሃ ሙሌት እንዲሁም አስተዳደርን በተመለከተ አስገዳጅ ስምምነት እንድትፈርም ያደረገችው ጥረት ሳይሳካ ምረቃው የሳምንታት ጊዜ በቀረበት ወቅት ነበር።
የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት በጀመረችበት ወቅት ግብፅ እና ሱዳን "የንግግሩ አካል ስለነበሩ ያውቁታል። እንዲያውቁት እስከተደረገ ድረስ ኢትዮጵያ  ግድቡ ጉዳት እንደማያደርስ ለማስረዳት እና ለመነጋገር ዝግጁ ነች" ብለዋል።
በተደጋጋሚ የተደረጉ ውይይቶችን እና ድርድሮችን ያስታወሱት ሚኒስትሩ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድንም የግድቡን ግንባታ ገምግሞ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት እንደሌለ መናገሩን ገልጸዋል።
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከላይኛው የናይል ተፋሰስ አገራት አንዷ ከሆነችው የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር ከሳምንታት በፊት በሰጡት መግለጫ "105 ሚሊዮን ዜጎቻችን እና 10 ሚሊዮን የሚሆኑ በአገራችን ያሉ እንግዶቻችን በሕይወት የሚያቆየው ውሃ እንዲነካ ፈጽሞ እንደማንፈቅድ ነው" ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር አድርገው ነበር።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ከጅምሩ እንዲሁም የውሃ ሙሌቶችን በጽኑ ያወገዙት አልሲሲ፤ አገራቸው በግድቡ የሥራ ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራት እና በተናጠል በናይል ውሃ ላይ የሚካሄድ የትኛውንም ዓይነት ሥራ ግብፅ እንደማትቀበለው በተደጋጋሚ አስታውቀዋል።
"ግብፅ በውሃ ደኅንነቷ ላይ የተደቀነን የኅልውና ስጋት ችላ ትለዋለች ብሎ የሚያስብ ማንኛውም አካል ተሳስቷል። የዓለም አቀፍ ሕጎችን መሠረት በማድረግ የሕዝቦቻችንን የኅልውና ሃብቶች ለማስጠበቅ ማንኛውንም እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ አል ሲሲ አስጠንቅቀዋል።
የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ምስክርነት ብቻ ሳይሆን የመርኅ ስምምነት በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብፅ መካከል መፈረሙን አስታውሰዋል።
"ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ ግድቡን እየገነባች ከታችኛው የተፋሰሱ አገራት ጋር ትነጋገራለች ይላል። ይህ በግልጽ ተጽፎ ይገኛል። ስለዚህ ግድቡን መገንባት እንድናቆም ሳይሆን እየገነባን እንድንደራደር፣ እየገነባን መረጃ እንድንለዋወጥ፣ እየገነባን ሃሳቦችን እንድንለዋወጥ፣ እየገነባን ስጋት የሚኖር ከሆነ በጠረጴዛ ዙሪያ እንድንወያይ ነው።"
ግድቡን በሚመለከት በተከታታይ ሲካሄዱ የነበሩ የግብፅ፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ሦስትዮሽ ድርድሮች አንዱ ወገን ሌላኛውን ለድርድሩ አለመሳካት ተጠያቂ በማድረግ ምንም ዓይነት ውጤት ሳያስገኙ የውሃ ሙሌቱ እና የግድቡ ግንባታ ወደ ፍጻሜው ደርሷል።
ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ ላይ ያላት ድርሻዋን ባረጋገጠ መልኩ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ ስምምነት እንዲደረስ እና ግንባታው የግብፅ የውሃ ደኅንነት ላይ አደጋ እንደማይጋርጥ ስታስታውቅ ቆይታለች።
ድርድር ሁለቱም ወገኖች የሚያሸንፉበት ማለት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ "አንዱ ወገን ድርድር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ ከሆነ ለመቀጠል አስቸጋሪ ይሆናል" ያሉት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ጥቅሟን እና መብቷን በሚያስከበር ሁኔታ በድርድሩ ውስጥ ስትሳተፍ መቆያቷን አስታውሰዋል።
"እስካሁን ድረስ የሕዳሴውን ግድብ በሚመለከት የተደረጉ ድርድሮች ላይ ሁሉ ኢትዮጵያ ተሳትፋለች" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "ወደፊትም በዚሁ አንቀጥላለን። አሁንም ለመደራደር ፈቃደኛ የሚሆን አካል ካለ እኛ ዝግጁ ነን" ብለዋል።
አክለውም "እንደ አለመታደል ሆኖ ግብፃውያን ናቸው ከድርድሩ የወጡት ወይም ከሁለት ዓመት በፊት ድርድር አንፈልግም ያሉት እነሱ ናቸው።"
ለዚህም ምክንያት ነው ያሉትን ሲጠቅሱ፣ "ኢትዮጵያ እነርሱ የሚፈልጉትን የውሃ መጠን እንድትለቅ አስገድደው ለማስፈረም ነው። እኛ የአባይ ውሃ ለተፋሰሱ አገራት በሙሉ መሆኑን እናምናለን። እነርሱ ግን አሁንም በቅኝ ግዛት ውል ላይ የሙጥኝ ብለዋል። እርሱ ደግሞ የላይኛውን የተፋሰስ አገራት ከጨዋታ ውጪ አድርጎ መብቱን ለሱዳን እና ለግብፅ ጠቅልሎ የሚሰጥ ነው። ያ ደግሞ ኢ ፍትሐዊ ነው። ያንን ማንም ሊቀበል አይችልም።"
ግብፅ በአውሮፓውያኑ 1959 የተፈረመውና የአብዛኛውን የወንዙን ውሃ ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት መሠረት አድርጋ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርኅ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት በመጥቀስ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ትቃወማለች።
ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብፅ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃ እንድታገኝ እና 86 በመቶ የናይልን ውሃ የምታመነጨውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይ እና ኢፍትሐዊ እንደሆነም ይጠቀሳል።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
በተለመደው አካሄድ በሳምንት አምስት ቀን ሠርተን ሁለት ቀን እናርፋለን። ሰኞ ሲመጣ ወደ ሥራ እንመለሳለን። ይሄ አሠራር ምን ያህል ውጤታማ ይሆን?
'ኔቸር ሂውማን ቢሄቪየር' በተባለው የሳይንስ መጽሔት ላይ የታተመው ጥናት ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል።
እስካሁን በዘርፉ ከተሠሩ ጥናቶች ሰፊው ነው። በሳምንት አራት ቀን ብቻ መሥራት የሰዎችን ጤና እንደሚያሻሽል ጥናቱ ያትታል።
ጥናቱን የሠሩት የቦስተን ኮሌጅ ባለሙያዎች ናቸው። ከሥራ ጋር በተያያዘ መታከት፣ በሥራ ደስተኛ መሆን እንዲሁም አካላዊ እና አእምሯዊ ጤናን መዝነዋል።
በአሜሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአውስትራሊያ፣ በካናዳ፣ በአየርላንድ እና በኒው ዚላንድ በሚገኙ 141 ተቋማት ውስጥ ነው ምርምሩ የተካሄደው።
የጥናቱ መሪ ፕሮፌሰር ዌን ፋን "በሠራተኞች ጤና ላይ ትልቅ ለውጥ አይተናል" ብለዋል።
እንዲሁም አራት ቀናት ብቻ በመሥራት የተቋማት ውጤታማነት እና ትርፋማነትም ጨምሯል።
በተቋሙ ውስጥ አጥኚዎቹ ያደረጉት ሙከራ ከተጠናቀቀ በኋላ 90 በመቶ የሚሆኑት በሳምንት አራት ቀናት ብቻ ለመሥራት ወስነዋል።
በሳምንት አራት ቀን መሥራት የጤና ጥቅም እንዳለው ከተረጋገጠ ለምን ይሄንን አሠራር መተግበር አልተቻለም?
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ቻይናውያን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት እስከ ምሽቱ ሦስት ሰዓት ድረስ በሳምንት ስድስት ቀናት በመሥራት ይታወቃሉ።
በሕንድ እያደረገ በመጣው የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሠራተኞች ረዥም ሰዓት እንዲያገለግሉ ጫና ይደረግባቸዋል። ከሥራ ሰዓት ውጪ በመሥራት የዓለም አቀፍ ገበያውን ፍላጎት ለማሟላት ይሞከራል።
ፕሮፌሰር ዌን እንደሚሉት እንደ ቻይና፣ ሕንድ፣ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ባሉት አገራት ረዥም ሰዓት መሥራት የሚያስከብር ነው።
በጃፓን ከሥራ ሰዓት ውጪ አብዝቶ መሥራት የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ በሥራ ብዛት የሚከሰት ሞት 'ካሮሺ' የሚል ስም ተሰጥቶታል።
በጃፓን የሥራ ገበያ ባለሙያ ሂሮሺ ኦኖ "በጃፓን ሥራ ከሥራነትም በላይ ነው። እንደ ማኅበራዊ ክንውን ነው የሚታየው" ይላሉ።
ሥራ ባይኖርም እንኳን ማልዶ መግባት እና ዘግይቶ መውጣት የተለመደ ነው።
"ይህም የሚደረገው ቁርጠኛነትን ለማሳየት ነው። እንደ ማርሻል አርትስ ለዕይታ የሚደረግ ነው" ይላሉ ባለሙያው።
ሳይሠሩ የሚበሉ ሰዎች በጣም ስለሚጠሉ ሁሉም ሰው ታታሪነቱን ለማሳየት ይሞክራል። አንድ ሰው አርብ እረፍት ቢወጣ 'እንዴት የሥራ ቀን ይዘላል?' ተብሎ ይታማል።
በጃፓን የአባቶች የእረፍት ፈቃድ ሳይቀር ይታጠፋል።
"አንድ ዓመት ያህል የአባትነት እረፍት መውጣት ቢቻልም የሚጠቀሙበት ጥቂት ወንዶች ናቸው። በርካቶች እረፍት በመውሰድ የሥራ ባልደረቦቻቸውን ማስቸገር አይፈልጉም" ሲሉ ሂሮሺ ያስረዳሉ።
ፕሮፌሰር ዌን እንደሚገልጹት ቡድናቸው የሠራው ጥናት ስለ ሥራ ባህል ያለውን አመለካከለት ሊቀይር ይችላል።
በአይስላንድ 90 በመቶ የሚሆኑት ነዋሪዎች የሥራ ሰዓታቸውን አሳጥረዋል። የሥራ ሰዓትን ማሳጠርም በሕግ ይፈቀዳል።
የሥራ ሰዓት ወይም ቀናት ለማሳጠር በሚል በደቡብ አፍሪካ፣ በብራዚል፣ በፈረንሳይ፣ በስፔን፣ በዶሚኒካን ሪፐብሊክ እና በቦትስዋና ሙከራዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
ቶኪዮ ለመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ቀናትን አራት ለማድረግ ጅማሮ ላይ ናት። ዱባይም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች።
ደቡብ ኮሪያ በ67 ተቋማት ውስጥ አራት ቀን ከግማሽ መሥራትን በቅርቡ ትተገብራለች።
'4 ዴይ ግሎባል' የተባለው ተቋም ኃላፊ ካረን ሎዌ "ከኮቪድ ወረርሽኝ ወዲህ ሕይወት እና ሥራ ተጣጥመው እየሄዱ አለመሆኑ ታውቋል" ይላሉ።
በብራዚል፣ በናሚቢያ፣ በጀርመን እና በሌሎችም አገራት ተቋማቸው አራት ቀን እንዴት መሥራት እንደሚቻል መንገድ ያመላክታል።
ኮሎራዶ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በ250 ሠራተኞች በሳምንት አራት ቀን ብቻ መሥራትን ተግብረዋል። ትልቁ ስኬታችን የሚሉት ተሞክሮም ይሄ ነው።
ፖሊስ ጣቢያው ለተጨማሪ ሰዓት ክፍያ የሚያወጣውን ወጪ በ80 በመቶ ቀንሷል።
"ድንገተኛ ጥሪ በሚያስተናግድ ፖሊስ ጣቢያ አሠራሩ ውጤታማ ከሆነ በየትኛውም ተቋም ሊተገበር ይችላል ማለት ነው" ይላሉ።
በአውሮፓውያኑ 2019 ሥራውን ሲጀምሩ በጣት የሚቆጠሩ ተቋማት ብቻ ነበሩ ሐሳቡን የተቀበሉት። አሁን ግን በሺዎች የሚቆጠሩ መሥሪያ ቤቶች አሠራራቸውን ለመለወጥ ቆርጠው ተነስተዋል።
"አሠራሩ ውጤታማ እንደሆነ ማስረጃዎች አሉ። ነገሩን መረዳት ብቻ ነው የሚጠይቀው" በማለት ያስረዳሉ።
ውስን የሥራ ቀናት ሲባል ውጤታማነት የሚቀንስ የሚመስላቸው ብዙ ቢሆኑም እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው።
በ2019 የማይክሮሶፍት የጃፓን ቅርንጫፍ በሳምንት አራት ቀናት በመሥራት ውጤታማነቱ በእያንዳንዱ ሠራተኛ 40 በመቶ ጨምሯል።
ካረን እንደሚገልጹት፣ ግዙፍ ተቋማት በተለያዩ አገራት ቅርንጫፍ ስላላቸው እና የሥራ ሰዓት ልዩነት ስለሚገጥማቸው አሠራሩን ለመተግበር ሊቸገሩ ይችላሉ።
ፕሮፌሰር ዌን እንደሚሉት፣ የሥራ ቀናት ሲቀነሱ አላስፈላጊ ስብሰባዎች ወደ ስልክ ጥሪ ወይም አጭር የጽሑፍ መልዕክት ተለውጠዋል።
የሥራ ቀናት ሲቀነሱ ሥራን ለማካካስ ሠራተኞች በበለጠ ይሠራሉ የሚለው አመለካከት የተዛባ መሆኑን ያስረዳሉ።
"አምስት የሥራ ቀናትን ወደ አራት ለማውረድ መጨነቅ አይደለም ነጥቡ። ብክነትን መቀነስ ነው ግቡ" ይላሉ።
በኬፕ ታውን በስቴልቦሽ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ሼሪል ዴቪስ እንደሚሉት፣ አራት ቀናት ብቻ መሥራት ጤናማ ሕይወትን ለመምራት ይረዳል።
ሼሪል የሚመሩት ቡድን ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች የሥራ ቀናት ወደ አራት ከመቀነሳቸው በፊት በከፍተኛ ድካም ይንገላቱ ለነበሩ 30 ሺሀ ተማሪዎች የሥነ ልቦና ድጋፍ ይሰጡ ነበር።
"ብዙዎቹ ሠራተኞች እየታመሙ ይቀሩ ነበር። ሰነፍ ሁነው ሳይሆን ከፍተኛ ሥራ ስለሚያደክማቸው ነበር። ሥራው እንጥፍጣፊ አቅም እንዳይቀራቸው ነበር የሚያደርጋቸው" ይላሉ።
ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የአእምሮ ጭንቀት ከሚስተዋልባቸው አገራት መካከል ትጠቀሳለች።
ሼሪል ከበላይ ያሉ አለቆች ፈቃደኛ ባይሆኑም አራት ቀን ብቻ መሥራትን ተግባራዊ ለማድረግ ታግለዋል።
"ስኬታማ አይሆንም ብለው ነበር። ግን ውጤታማ ሆንን" ይላሉ።
አሠራሩ ከመተግበሩ በፊት በስድስት ወራት ውስጥ 51 ጊዜ በሕመም ምክንያት ፈቃድ ተጠይቋል። አራት ቀናት ብቻ መሥራት ሲጀምር ግን ወደ አራት ቀን ፈቃድ ብቻ ወርዷል።
የተሻለ እንቅልፍ እንደሚተኙ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ እና አዳዲስ ጊዜ ማሳለፊያዎች መጀመራቸውን የተናገሩ ብዙዎች ናቸው።
በትርፍ ቀናቸው በመሥራት ገንዘብ ለማግኘት ይሞክራሉ ተብሎ ቢታሰብም ከአንድ ሰው በስተቀር የተቀሩት እረፍታቸውን በአግባቡ መጠቀም ነው የመረጡት።
"ትኩረታቸው ጨምሯል። የሥነ ልቦና ድጋፍ ለሚሰጧቸው ተማሪዎች የበለጠ ሐዘኔታም ያሳያሉ" ሲሉ ለውጡን ይገልጻሉ።
የሥራ ቀናትን የመቀነስ አሠራር ሁሉንም ተቋም ውጤታማ ያደርጋል ማለት አይደለም።
ፕሮፌሰር ዌን እንደሚሉት፣ የአንድ አገር የምጣኔ ሃብት አወቃቀር ከግምት ውስጥ መግባት አለበት።
"አብዛኞቹ አፍሪካውያን በግብርና ወይም በማዕድን ማውጣት ሥራ የተሰማሩ ናቸው። ሥራዎቹ ኢ-መደበኛ ስለሆኑ በቀላሉ የሥራ ቀንን መቀነስ አይቻልም" ይላሉ።
አነስተኛ ገቢ በሚያስገኙ የጉልበት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሥራ ቀናቸውን ከመቀነስ ይልቅ ጨምረው ደመወዛቸውን ማሳደግ ነው የሚመርጡት።
ፕሮፌሰር ዌን የግንባታ፣ አገልግሎት ሰጪ እና የፋብሪካ አምራች ተቋማትን በጥናታቸው አካትተዋል።
"በየትኛውም ዘርፍ አራት ቀን በሳምንት መሥራት ሊተገር ይችላል። ሆኖም ለሁሉም በውጤታማነት ይሠራል ማለት አልፈልግም" ይላሉ።
የሥራ ባህል እየተለወጠ የመጣው ወጣቶች በሚያሳድሩት ጫና መሆኑን ባለሙያዎች ይስማሙበታል።
በቅርቡ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው ወጣቶች ከደመወዝ ይልቅ በሥራ እና በግል ሕይወታቸው መካከል ያለውን ሚዛን ማመጣጠንን ይመርጣሉ።
በደቡብ ኮሪያ ደመወዛቸው ተቀንሶ የሥራ ቀናትም ቢቀነሱላቸው የሚመርጡ ወጣቶች ተበራክተዋል።
"ወጣቶች የተለመደውን አሠራር አይፈልጉትም። የሥራ ዓላማ እና ሕይወት ምን መምሰል አለበት በሚለው ላይ የተለየ ዕይታ አላቸው" ይላሉ ፕ/ር ዌን።
ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ በርካቶች ከሥራ መልቀቃቸው (ግሬት ሬዚግኔሽን በመባል የሚታወቀው) እንዲሁም አዳዲስ የሥራ ማቆም ልማዶች መምጣታቸውን እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ።
በሥራ ቦታ ላይ አስፈላጊ የሆነውን ብቻ ማከናወን (ኳየት ኩዊቲንግ) የሚባለው እና በቻይና የሥራ ጫናን አለመቀበት (ላይንግ ፍላት የሚባለው) ከዚህ ጋር በተያያዥ ይጠቀሳሉ።
ሂሮሺ "አሁን 30 በመቶ የጃፓን ወንዶች የአባትነት እረፍት ይወጣሉ። እነዚህ በአብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው። ኮቪድ ለውጥ አምጥቷል። አራት ቀናት ብቻ በሳምንት መሥራት ይለመዳል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ" ይላሉ።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ፓላንዳዊት ናት። አማርኛን ከ40 ዓመት በፊት ነው የተማረችው።
እሷ አማርኛ ስትማር ጓድ መንግሥቱ ምናልባት የእድገት በኅብረት ዘመቻን እያሰናዱ ነበር። እንደው የጊዜውን ርዝማኔ ለማስታወስ ነው እንጂ ነገሩ ምንም ግንኙነት የለውም።
እና ያኔ ድሮ አማርኛን በዲግሪ ተመርቃ እስከዛሬ ታስተምራለች።
ላለፉት 23 ዓመታት በርካታ ፈረንጅ በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች።
ዶ/ር ኤቫን 'አንቺ' እንበላት እንጂ በሥራዋ አንቱታን የተጎናጸፈች ሴት ናት። የአማርኛ የቁልምጫ ስሟ ሔዋን ይባላል።
ብታምኑም ባታምኑም፣እሷ የምታስተምርበት ዋርሶ ዩኒቨርስቲ አማርኛን ማስተማር ከጀመረ 75 ዓመት አልፎታል።
የፎቶው ባለመብት, Warsaw University- Ethiopian studies
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
ኔፕልስ፣ ፓሪስ እና ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲዎች አማርኛ ማስተማር ከጀመሩ 100 ዓመት አልፏቸዋል።
በኔፕልስ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት አፈወርቅ ገብረየሱስ ናቸው። ይህ ማለት በ1890ዎቹ መሆኑ ነው። ጥንት በዓድዋ ዘመን።
አማርኛ በጀርመን፣ ሐምቡርግም ዩኒቨርስቲም ይሰጣል። እዚያም ድሮ ነው የተጀመረው። ዛሬም ድረስ አለ፤ ለዚያውም ሳይቋረጥ።
የመጀመሪያው መምህር ወልደማሪያም ደስታ የሚባሉ ሰው ናቸው። በ1909 ከአንኮበር-ሐምቡርግ ሄደው አምስት ዓመት አስተምረዋል።
በዶክተር ኤቫ አገር፣ ፖላንድ አማርኛን ማስተማር የጀመሩት ፕሮፌሰር ስቴፋን ስትሬልሲን ናቸው።የዛሬ 75 ዓመት ገደማ።
እሳቸው አማርኛን ያጠኑት በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ነው። ቋንቋውን የተማሩት ደግሞ በፈረንሳይ ነው። እኚህ ሰው ከባድ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ ይባላል።
በዚህም ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የወርቅ ኒሻን ተበርክቶላቸዋል።
1950ዎቹ የአፍሪካ ጥናትን ከመሠረቱ ወዲህ ብዙ ለፉ። አማርኛን በአውሮፓ አስፋፉ።
እርሳቸው የመሠረቱት ተቋም ሰፍቶ፣ አድጎ እና ተመንድጎ በ1977 የአፍሪካ ቋንቋዎች እና ባሕል ትምህርት ክፍል ተባለ።
ከአማርኛ እና ከግዕዝ ሌላ ሐውሳ እና ስዋሂሊ ቋንቋዎችን ማስተማር ጀመረ።
ዶ/ር ኤቫ በዚህ ዘመን ባስቆጠረ ተቋም ነው አማርኛን የምታስተምረው።
እሷ ፕሮፌሰር ስቴፈንን አልደረሰችባቸውም። በዝና ነው የምታውቃቸው።
የዋርሶ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ትምህርት ክፍል ብዙ ተማሪ አይቀበልም።
አንዱ ምክንያት ብዙ ተማሪዎች አማርኛ ከባድ ነው ብለው ስለሚፈሩ ነው። ከጀመሩት ውስጥ ሲሶዎቹ አይጨርሱትም።
በየዓመቱ በአማካይ 10 ተማሪዎችን ይቀበላል። ግዕዝን ደግሞ እንደ ኮርስ ለማንኛውም ለፈለገ ተማሪ ይሰጣል።
በ75 ዓመታት ውስጥ  ቁጥራቸው ከመቶ ትንሽ ከፍ ያሉ ተማሪዎች በማስተርስ አስመርቋል። 12 የሚሆኑት ፒኤችዲ ይዘዋል።
የሆነስ ሆኖ፣ የዛሬ 40 ዓመት ኤቫ አማርኛ ለመማር እንዴት ወሰነች?
የፎቶው ባለመብት, African studies, University of Warsaw
"ሒሳብ፣ ሕግ፣ ፊዚክስ እንደዚህ ዓይነት ትምህርት ብዙም አይማርከኝም ነበር። ከዚያ ይልቅ ሥነ ጥበብ፣  ኪነ ጥበብ፣ ቋንቋ እና የሩቅ አገር ባሕል ይማርከኝ ነበር።"
ዋርሶ ዩኒቨርስቲ ያኔ ድሮ የኦሪየንታል ጥናት ክፍል ነበረው። ዶ/ር ኤቫ እዚያ ስለሚሰጠው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሰማች። ተሳበች። ተመዘገበች፣ ተማረች። ተመረቀች።
አማርኛን ለአምስት ዓመታት ነው የተማረችው። አራት ዓመት በፖላንድ ከተማረች በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኮላርሺፕ አግኝታ 1 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ አቅንታ ከአገሬው ጋር ተምራለች።
ኢትዮጵያ የመሄድ አጋጣሚን መጀመሪያ ስታገኝ እንዴት እንደፈነደቀች።
"እኔ ወጣት በነበርኩበት በዚያ ዘመን እኛ ስለ ኢትዮጵያ ምንም አናውቅም፤ ፖላንድ ውስጥ በትምህርት ቤት ጭራሽ ስለ ኢትዮጵያ ምንም ተምረን አናውቅም. . ."  ትላለች።
አምስት ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገረው ዶክተር ኤቫ 'ከቋንቋዎች ሁሉ አማርኛ ለምን ማረከሽ?' ስትባል 'ድምጹ ነዋ!' ትላለች።
ብዙዎች ጀርመንኛ ኮስተር ያለ ነው። ፈረንሳይኛ ፍቅር ነው። አረብኛ ሉስሉስ ነው ይላሉ። ለመሆኑ አማርኛ ለባዕድ ጆሮ እንዴት ያለ ነው?
"የፏፏቴ ድምጽ ነው ያለው. . ." ትላለች ዶክተር ኤቫ።
"ሰዎች ሲያወሩት መስማት በቃ ፏፏቴ ሲፈስ እንደመስማት ያለ ነው።"
ጥበብ ስለምትወድ አማርኛ ድምጹ ብቻ ሳይሆን አጻጻፉ ማረካት። ፊደል ትወዳለች። እያንዳንዱ ቅርጽ ውብ የጥለት ጥልፍ ሆኖ ነው የሚታያት።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትሄድ ደግሞ የምግቡን ዓይነት እና ብዛት የባሕሉን ጉራማሌነት ወደደችው። ያልወደደችው ግን አንድ ነገር ብቻ ነበር።
"ባሌ ጉራጌ ነው" የምትለው ዶ/ር ኤቫ ክትፎ ግን የምትሞትለት ምግብ አይደለም።
"ያሳዝናል፣ ክትፎ ለኔ ጨጓራ አልተሠራም" ትላለች።
ቢሆንም ራሷ ስትበላው ነው እንጂ ሲያጎርሷት አትወድም።
ዶክተር ኤቫ እናት አገሯን ፖላንድን እና ኢትዮጵያን አነጻጽሪ ስትባል ሁለቱን ሕዝቦች እንግዳ ተቀባይነት ብቻ ያመሳስላቸዋል ትላለች። ከዚያ በተረፈ የጋራ ነገር አላገኘችም።
በፖላንድ "እንጀራችን ድንች ነው" የምትለው ኤቫ ከኢትዮጵያ ባሕል ጉርሻ እጅግ ያስገርማታል።
". . . ጉርሻ ለእኔ በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው። አንደኛ ትልቅ ነው፤ ለመዋጥ ያስቸግራል። ሁለተኛ በአንድ አያበቃም" ትላለች።
'የእናት ጡት ሁለት ነው' ተብሎ ጉርሻ የሚደገመው ነገር ይስቃታል። የሚወዱትን ሰው ሁለት ጊዜ ለማጉረስ የተፈጠረ አባባል ሆኖ ነው የሚሰማት።
በአፍሪቃ ቋንቋዎች እና ባሕሎች ተቋም በሥነ-ልሳን ክፍል አማርኛ የሚያስተምሩት እሷ እና ባልደረባዋ ፕሮፌሰር ማርቲን ናቸው።
ፕሮፌሰር ማርቲን ከአማርኛ በተጨማሪ ግዕዝም ያስተምራሉ።
ዶ/ር ኤቫ ድሮ አማርኛ ስትማር 7 ፈረንጆች አብረዋት ነበሩ፤ የክፍሏ ልጆች። አሁን በተለያየ ዓለም በተለያየ ዘርፍ ይሠራሉ።
አንዳንዶቹ በኤምባሲ፣ አንዳንዶቹ ምናልባትም አማርኛውን ጨርሶ ረስተውት ይሆናል።
እርሷ ግን ያኔ በዲግሪ እንደተመረቀች ወዲያውኑ ለእረፍት ለንደን ሄደች።
በዚያው በለንደን ስኩል ኦፍ ኦሪየንታል እና የአፍሪካ ጥናት ገባች። እዚያው ደግሞ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ወሰደች።
ፍቅር እስከ መቃብር እና ሌሎች የአማርኛ ልቦለድ ታሪኮችን መተርጎም የጀመረችው ያኔ ነው። እስከዛሬ ግን አልጨረሰችውም።
'ፍቅር እስከ መቃብር' ወደ ፈረንሳይኛ እና ወደ ኖርዌይ ቋንቋ ተመልሷል። የእሷ ህልም ወደ ፖሊሽ መተርጎም ነው።
አሁን ስለእሱ ብዙ ማውራት አትፈልግም። "ህልሜን ካሳካሁት በኋላ ብናወራ አይሻልም?" ትላለች።
በሥነ ጽሑፍ ባለሙያ ሆና ከለንዶን ወደ ፖላንድ ከተመለሰች በኋላ ዶክትሬቷን ሠራች።
ከዚያ የበቃች የነቃች የአማርኛ ቋንቋ አስተማሪ ሆነች።
እርሷ ግን አሁንም "የአማርኛ ቋንቋ ተማሪ ነኝ" ትላለች። ከጎኗ መዝገበ ቃላት አይለያትም።
የሚገርመው በ23 ዓመታት ውስጥ አንድም ሐበሻ ተማሪ ገጥሟት አያውቅም።
በፖላንድ የተወለዱ ሁለተኛ ትውልድ ሐበሾችን ግን አስተምራለች።
ዶክተር ኤቫ ከማስተማሩ ሌላ  የአማርኛ አስተርጓሚ ናት።
ለምሳሌ በስደት ወደ ፖላንድ የመጡ አማርኛ ተናጋሪዎች ለጥገኝነት ቃለ መጠይቅ ሲደረጉ 'ዶክተር ኤቫን ጥሩ' ነው የሚባለው። እሷ ትጠራለች፤ ታስተረጉማለች።
በፖላንድ ፍርድ ቤትም እንዲሁ የአማርኛ አስተርጓሚ ናት።
የቆዳዋ ቅላት አሳስቷቸው ፈረንጅ ሲያሙ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሐበሾች አሉ፤ በዶክተር ኤቫ።
አማርኛ የማትችል መስሏቸው ሰዎች በአዲስ አበባ ከአንዴም፣ ሁለት ሦስቴ ሲያሟት ይዛቸዋለች፤ ታዝባቸዋለች። ከመሳቅ ሌላ ግን ልታስደነግጣቸው አልፈለገችም።
ዶ/ር ኤቫ ቀጭን ናት። 'ቀጮ' የምትባል ዓይነት ቀጭን።
አንድ ጊዜ ካፌ ቁጭ ብላ ሳለ ከጎን የተቀመጡ ጎረምሶች 'ሲቦጭቋት' ሰማቻቸው።
"ሹፋትማ ይቺን የጫት እንጨት የመሰለች ፈረንጅ" ብለው።
ሲያሙኝ 'ከጆሮዬ ዘለቀ'። ቀጭን ስለሆንኩ እኮ ነው" ብላ ያን ዘለግ ያለ ሳቋን ትስቃለች።
ዶ/ር ኤቫ "አዎ አማርኛ ከባድ ነው። ቀላል ቋንቋ አይደለም። ቢሆንም ግን ከማንደሪን [የቻይና ቋንቋ] ይሻላል" ትላለች።
ከአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ፖሊሽኛ ሌላ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ሩሲያኛ አቀላጥፋ ትናገራለች።
"አማርኛ ከባድ ብቻ ሳይሆን አያልቅም፤ አሁንም እየተማርኩ ነው፣ ገና አያልቅም።"
ዶክተር ኤቫ የአማርኛ አንዳንድ ቃላት የኮረኮሯት ያህል ያስቋታል።
እግር ላይ ያለች ትንሽ ነገር ለምን 'ቁርጭምጭሚት' ተባለች? እያለች ዝም ብሎ ግርም ይላታል። በዚህ ነገር ቁርጭምጭሚቷን ወለም እስኪላት ድረስ ነው የምትስቀው።
"አያስቅም ግን? እስኪ በለውማ 'ቁ-ር-ጭ-ም-ጭ-ሚ-ት"  (ሌላ ረዥም ሳቅ). . .
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ
ከአፍንጫችን የሚወጣ ፈሳሽ ወይንም 'ንፍጥ' ራሳችንን ከበሽታ በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ያውቃሉ? ከዚህም በተጨማሪ ቀለሙ ብቻ በሰውነታችን ውስጥ ስላለው ነገር ለመረዳት እንደሚጠቅምስ?
በጥንታዊቷ ግሪክ ንፍጥ የሰውን ጤና እና ሰብዕና ለማመጣጠን ድርሻ ካላቸው አራት የሰውነት ፈሳሾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታሰብ ነበር።
ሐኪሙ ሂፖክራቲስ አክታ፣ ደም፣ ቢጫ ሐሞት እና ጥቁር ሐሞት አራቱ "ሂውመረስ" የሚል ንድፈ ሃሳብ ፈጠረ።
አንድ ሰው እነዚህ ሂውመረስ ሚዛናቸውን ጠብቀው መገኘታቸው የስሜታችንን ሁኔታ ሊወስኑ ይችላሉ።
ከእነርሱ ውስጥ የአንዱ ከመጠን በላይ መጨመር በሽታን ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ አክታ በአንጎል እና በሳንባ ውስጥ እንደሚፈጠር ይታሰብ ነበር። እና ቅዝቃዜ እና እርጥበት አዘል አየር ባለበት ወቅት ከመጠን በላይ ሊበዛ አልፎ ተርፎም የሚጥል በሽታ ሊያስከትል ይችላል።
እርግጥ ነው አሁን ከአፍንጫችን የሚወጣው ፈሳሽ የሰዎችን ሰብዕና እንደማይጎዳ ወይም በሽታን እንደማያመጣ እናውቃለን፤ይልቁንም እኛን ከበሽታ ለመከላከል ይጠቅመናል።
ማንም ሰው በማስነጠስ ወቅት በንፍጥ መዝረክረክን ወይም በአጠቃላይ ንፍጥን አይወድም።
በአፍንጫችን ውስጥ ያለው ንፍጥ ከሰው አካል ድንቅ ነገሮች መካከል አንዱ ነው ሊባል ይችላል።
የበሽታ መከላከል አቅማችንን አልፈው በመግባት ጤናችንን ከሚያቃውሱ ወራሪዎች ይጠብቀናል።
እና በውስጣችን ስላለው ነገር ጥልቅ ግንዛቤን የሚገልጽ ልዩ ውህድ አለው።
አሁን ሳይንቲስቶች ከኮቪድ-19 እስከ ሥር የሰደደ የሳንባ ሕመም ድረስ ያለውን ነገር በተሻለ ሁኔታ ለመመርመር እና ለማከም ንፍጥን በአግባቡ ለመመርመር ይሞክራሉ።
ይህ ለስላሳው እና በቀላሉ የሚጣበቀው ፈሳሽ የአፍንጫችን የውስጥ ክፍልን ከባክቴሪያ ይከላከላል። የአፍንጫችንን የውስጥ ክፍል ያጸዳል፤ ማንኛውንም ባክቴሪያ፣ ቫይረስ፣ የአበባ ብናኝ፣ ቆሻሻ፣አቧራ እና ሌሎች በሽታ አምጪዎች ወደ ሰውነታችን በመተንፈሻ አካሎቻችን በኩል ሊገቡ ይችላሉ።
ንፍጥ በመቶዎች በሚቆጠሩ ጥቃቅን በአፍንጫችን ውስጥ ባሉ ፀጉሮች በመታገዝ በውጪው ዓለም እና በውስጣችን መካከል መከላከያ ግንብ ሆኖ ያገለግላል።
በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን እና ክትባት ፕሮፌሰር የሆኑት ዳንዬላ ፌሬራ እንዳሉት የአዋቂ ሰው አካል በቀን ውስጥ ከ100 ሚሊ ሜትር በላይ ፈሳሽ ያመርታል። ነገር ግን ሕጻናት ከአዋቂዎች በበለጠ አፍንጫቸው ፈሻሽ ያመርታል።
የእኛ የንፍጥ ቀለም እና የፈሳሹ ወጥነት በሰውነታችን ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ በቀላሉ እንድናውቅ ሊረዳን ይችላል።
ከአፍንጫችን ጥርት ያለ ፈሻሽ የሚወጣ ከሆነ እንደ የአበባ ዱቄት ወይም አቧራ የመሳሰሉ ረብሸውናል ማለት ነው።
ነጭ ንፍጥ ደግሞ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ውስጥ ገብቷል ማለት ነው። ምክንያቱም ነጩ ፈሻሽ የሚፈጠረው ሰርጎ ገቦችን ለመዋጋት በተጠሩት ነጭ የደም ሴሎች አማካኝነት ነው። ንፋጥ ወደ ቢጫነት ሲቀየር ደግሞ የሞቱ ነጭ የደም ሴሎች በብዛት ተከማችተው እየወጡ ነው ማለት ነው።
የእርስዎ ንፍጥ ቀይ ወይም ሮዝ ከሆነ ደግሞ፣ ምናልባት አፍንጫዎትን በሚያጸዱበት ወቅት ውስጡን ጎድተውት ተቆጥቶ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ከአፍንጫ የሚወጣን ፈሻሽ ወይንም ንፍጥን መመልከት የመጀመሪያው እርምጃ ብቻ ነው።
ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት
አንጀታችን የተለያዩ ረቂቅ ተህዋሲያንን ይይዛል።ሰውነታችን የባክቴሪያዎች፣ የቫይረሶች፣ የፈንገሶች እና ሌሎች ረቂቅ ተሕዋስያን ሥነ ምኅዳር ነው ማለት እንችላለን።
በተመሳሳይም በንፍጣችን ውስጥ የሚገኙት የተለያዩ ረቂቅ ተህዋሲያን አስፈላጊ መሆናቸውን ሳይንቲስቶች ያምናሉ።
በእርግጥ ሳይንቲስቶች እነዚህ ረቂቅ ተህዋሲያን ከሰው ልጅ ጤና እና ከትክክለኛው የሰውነት በሽታ የመከላከል ሥርዓት ጋር የተቆራኘ ነው ብለው ያምናሉ።
ሁሉም ሰው ንፍጥ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሲያን የተለያዩ ናቸው። በፆታችን፣ በዕድሜያችን፣ በምንኖርበት ቦታ፣ በአመጋገባችን እና የምናጨስ ከሆነ የተለያየ ይሆናል።
የረቂቅ ተህዋሲያኑ ስሪት ወደ ሰውነታችን በመተንፈሻ አካላችን በኩል የሚገቡ ወራሪዎችን ለመከላከል የሚረዳ ነው።
እነዚህ መስተጋብሮች ውስጥ አንዳንዶቹ ደግሞ ስውር ናቸው። እንደ አውሮፓውያኑ በ2024 የተደረገ ጥናት ለአብነት ያህል ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ስቴፕሎኮከስ  (Staphylococcus ) የተሰኘ ባክቴሪያ በአፍንጫ ውስጥ በሕይወት የተገኘ ሲሆን ሰውን በመረረዝ፣ ትኩሳት እና መግል የተሞላ እብጠቶችን አስከትሏል።
ይህ ንፍጥ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሲ እና ባክቴሪያ ምን ያህል አይረን አለው በሚለው ላይ የተመሠረተ ነው።
ፌሬራ የጤናማ ንፍጥ ረቂቅ ተህዋሲያን ምን እንደሚመስሉ በትክክል ለማወቅ እየተመራመሩ ሲሆን፣ ይህንንም በየቀኑ በአፍንጫ ውስጥ የሚረጭ መድኃኒት ውስጥ በማካተት የንፍጥን ጤናን ለማጎልበት ያገለግላል።
ፌሬራ "አስቡት በአፍንጫችን ያለውን ነገር እዚያው የሚቆዩ እና የሚቆጣጠሩ ብዙ ጥሩ መልካም ዝርያዎችን ይዘን፣ መጥፎ ተህዋሲያን ገብተው እንድንታመም ብናደርግ" ሲሉ የሚያስቡትን ያስረዳሉ።
የፌሬራ ባልደረቦች በአፍንጫ ውስጥ የሚገኝ ትክክለኛው የረቂቅ ተህዋሲያን ዓይነቶች ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ለይተዋል።
እና እነዚህ ባክቴሪያዎች የሰዎችን የአየር መተላለፊያዎችን ተቆጣጥረው ለረዥም ጊዜ የሚቆዩ እና ጤንነታቸውን ለማሻሻል ይችሉ እንደሆነ ለማየት እየሞከሩ ነው።
ፌሬራ እንደሚሉት ንፍጥ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሲያን ከበሽታ መከላከል ሥርዓት ጋር በጣም የተቆራኙ ስለሆኑ፣ በሽታ የመከላከል ሥርዓቱን እንዴት እንደሚያሳድጉ እና ክትባቶችን የበለጠ እንዲቀበሉ ለማድረግም እያጠኑት ነው።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አንድ ሰው ለክትባት የሚሰጠው ምላሽ የሚወሰነው ባለው የረቂቅ ተህዋሲያን ዓይነት ነው።
ለምሳሌ በኮቪድ-19 ክትባት ላይ የተደረጉ ጥናቶች የንፍጥ ረቂቅ ተህዋሲያን ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረ ይጠቁማሉ። እና በምላሹ ረቂቅ ተህዋሲያኑ ክትባቱ ውጤታማነት ላይ የራሳቸውን ተጽዕኖ አሳድረዋል።
ፌሬራ "የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዳንታመም ለመከላከል ጥሩ ነበሩ። ነገር ግን ቫይረሱን ማስተላለፋችንን ቀጠልን" ብለዋል።
"በእውነቱ በጣም የተሻሉ ክትባቶችን ቀጣዩ ትውልድ በኮቪድ-19ም ሆነ በጉንፋን ወይም ሌላ የመተንፈሻ አካል ቫይረስ እንዳይታመም የሚያደርግ መሥራት እንችል ነበር። ሁሉም ነገር በንፍጥ የበሽታ መከላከል ውስጥ ነው ያለው።"
የፌሬራ ምርምር ትክክለኛውን የንፍጥ ረቂቅ ተህዋሲያን ቀመር ለመጠቆም ሁለት ዓመታትን ሊወስድ ቢችልም በስዊድን ውስጥ ሳይንቲስቶች የጤናማ ሰዎችን ንፍጥ በራይኖሲነሲቲስ (rhinosinusitis) ምክንያት ለረጅም ጊዜ በተዘጋ አፍንጫ እና በአለርጂ ምክንያት የሚፈጠር ትኩሳት የሚታመሙ ሰዎች አፍንጫ ውስጥ በማስቀመጥ መፍትሄ ለማግኘት ቀደም ብለው ምርምር ጀምረዋል።
ተመራማሪዎቹ 22 ጎልማሶች በየቀኑ ከጤናማ ጓደኞቻቸው ወይም አጋሮቻቸው የተሰበሰቡ ንፍጦችን በሲሪንጅ ለአምስት ቀናት አፍንጫቸው ውስጥ እንዲጨምሩ ጠይቀዋል።
ቢያንስ በ16 ሕሙማን ላይ እንደ ሳል እና የፊት ሕመም ያሉ ምልክቶች እስከ ሦስት ወር ድረስ በ40 በመቶ ቀንሷል።
ጥናቱን የመሩት በስዊድን ሄልሲንግቦርግ ሆስፒታል የጭንቅላት እና የአንገት ቀዶ ጥገና አማካሪ አንደር ማርተንሰን "ይህ ለእኛ ታላቅ ዜና ነበር፣ ማንም አሉታዊ የጎንዮሽ ጉዳቶችን አላሳየም" ብለዋል።
እነዚህ ሙከራዎች በሌሎች ላቦራቶሪዎች ውስጥ በአንጀት ረቂቅ ተህዋሲያን እና የዓይነ ምድር ንቅለ ተከላ ላይ የተሠራ ጥናትን እንደመነሻ መጠቀማቸውን ተናግረዋል።
ያ የመጀመሪያው የሙከራ ምርምር የእነዚህ ሰዎች ንፍጥ ረቂቅ ተህዋሲያን እንዴት እንደተቀየሩ እና በአፍንጫቸው ውስጥ ባሉ ተህዋሲያን ላይ ምን እንደተፈጠረ፣ እንደጨመሩ ወይም እንደሚቀነሱ የሚያሳዩ መረጃዎች አልሰበሰበም።
ስለዚህ ሌላ ትልቅ እና ትኩረት ያደረገ ሙከራ በመካሄድ ላይ ነው።
በእርግጥ ንፍጥ ሥር ለሰደደ የአፍንጫ እና የሳንባ በሽታዎች ትልቅ እንቅፋት ሊሆን ይችላል።
በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ የአንገት በላይ ስፔሻሊስት የሆኑት ጄኔፈር ሙሊጋን የዓለምን ሕዝብ ከ5 እስከ 12 በመቶ የሚያጠቃው ሥር የሰደደ የራይኖሲኑሲቲስ (rhinosinusitis) እና የአፍንጫ ውስጥ እብጠት (nasal polyps) ያለባቸውን ሰዎች ለማጥናት ንፍጥን ይጠቀማሉ።
በሥራዋ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የአፍንጫ ኅብረ ሕዋሳት ከራይኖሲኑሲቲስ  ሕሙማን በቀዶ ሕክምና ታስወግድ ነበር።
ነገር ግን ይህ የሕክምና ዓይነት ዘላቂ መፍትሄ ሆኖ አላገኘችውም። የእርሷ ጥናት እንደሚያሳየው ንፍጥ አንድ ሰው በራይኖሲኑሲቲስ ሲያዝ በሰውነቱ ውስጥ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ በቅርበት ለመመርመር ትክክለኛ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
"እኛ እዚህ ያሉ ወንጀለኞች እነማን እንደሆኑ ለማቃለል እየተጠቀምን ነው፣ ይህን ሁኔታ ማን እየነዳው ነው?" ይላል ሙሊጋን እያንዳንዱ በሽተኛ ለራይኖሲኑሲቲስ መንስኤው ትንሽ የተለየ መገለጫ አለው ሲል ተናግሯል።
በተመሳሳይ፣ ከዚህ በፊት የሚደረግ ሕክምና በአብዛኛው እንደ ሙከራ ነበር፤ ከታካሚ ታካሚ በጣም የተለያየ እና አንዳንዴም በአስር ሺዎች የሚቆጠር  ዶላር የሚፈጅ እና ወራትን ይወስድ ነበር።
ሙሊጋን ንፍጥን በመመርመር በፍጥነት አስፈላጊውን ሕክምና ወይም ቀዶ ሕክምና ለመለየት ይረዳል ትላለች።
በስታንፈርድ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ምሁራን የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ንፍጥን በመመርመር የረቂቅ ተህዋሲያንን ናሙና ለመለየት የሚያገለግል መሳሪያ ሠርተው የፈጠራ ባለቤትነት ለማግኘት እየጠበቁ ነው።
በ2025 የምግብ እና መድኃኒቶች ቁጥጥር ባለሥልጣን ከአፍንጫ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሲያንን ለመመርመር የሚያገለግለውን መሳሪያ አጽድቋል።
መሳሪያው ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ ናሙናዎችን በመሰብሰብ በውስጡ የሚገኙ ረቂቅ ተህዋሲያንን ይለያል፤ ይህም ናሙና አወሳሰድ ወጥነት እንዲኖረው ማድረግ ብቻ ሳይሆን የምርምሮች መለያየትን ይቀንሳል።
ሙሊጋን ሰዎች የማሽተት ስሜታቸውን እንዲያጡ የሚያደርጋቸውን ነገር ለማጥናት ተመሳሳይ መሳሪያዎችን ተጠቅማለች።
ቡድኗ ቀድሞውንም ቢሆን አፍንጫ ላይ የሚረጭ ቫይታሚን ዲ በሲጋራ ምክንያት በተከሰተ እብጠት ምክንያት የማሽተት አቅማቸውን ያጡ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ መድኃኒት አግኝቷል።
ስለዚህ እነዚህ የመመርመሪያ መሳሪያዎች እና ሕክምናዎች ለሳንባ በሽታዎችም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
አዳዲስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አይኤል-26 ፕሮቲን በሕሙማን ንፍጥ ውስጥ የሚገኙበትን መጠን በቀላሉ በመመርመር አንድ ሰው ለከባድ የሳንባ ምች በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ማወቅ ይችላሉ።
ይህ በአጫሽ ሰዎች ዘንድ የሚከሰት በሽታ ሲሆን፣ በዓለም ላይ አራተኛው በጣም የተስፋፋ የሞት መንስኤ ነው። ንፍጥን በመመርመር እና ያለውን ረቂቅ ተህዋሲያን በማየት ሕመሙን ቀድሞ ማወቅ እና በፍጥነት ማከም ይቻላል።
በተመሳሳይ ዘዴ በዓለም ዙሪያ ያሉ ተመራማሪዎች በተመሳሳይ ዘዴ አስምን፣ የሳንባ ካንሰርን፣ አልዛይመርን እና ፓርኪንሰንን ለመለየት እየሞከሩ ነው።
ሙሊጋን "ንፍጥ በግል የተዘጋጀ የወደፊቱ መድኃኒት ነው ብዬ እኔ በሙሉ ልቤ አምናለሁ" ብላለች።
© 2025 BBC. ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም. ስለ ውጪ ሊንኮች ያለን አቀራረብ